ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን ከስሩ ለማጥፋት የተለያዩ ደረጃዎች እና ክፍሎች ሲታይ አሁን ላይ የመጨረሻዉ የአጥፍቶ መጥፋት ትንቅንቅ ተጋድሎ ቀጥሏል ፤ ብሷል ፡፡
ለዚህም የጥፋት እና ሞት መላ ምት በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ፡-
፩ኛ. ኢትዮጵያዊነት አንድነት እና ህብረት መናድ፣
፪ኛ. ኢትዮጵያዊነት አመላካች ታሪክ መሸርሸር እና ማደናገር /ማዛባት ፣ማሳጣት ፤መቀማት ፤
፪ኛ. ማንነት ተኮር ማጥላላት፣ ማግለል፣ ማፈናቀል፣ ማታለል ፣መግደል ፤
፫ኛ. ኢትዮጵያዊ መሰረትን እና ብሄራዊ ኩራትን ማናጋት፣
፬ኛ. የራስን የጥፋት እና የዉድቀት አስተሳሰብ እና ድርጊት በመደበቅ አሁን የምንዋደቅበት አገር በደም እና አጥንት ያቆዩዓትን አገር በበጎ ምግባር እና ተግባር ባለቤት የሆኑትን የአገር ባለዉለታዎች ስም እና ስራ ማጉደፍ ፤
፭ኛ. ኢትዮጵያዉያን በትዉልድ አገር ምድር እና አፈር ባይተዋር በማድረግ የሚኖሩባት አገር ማሳጣት ለአለፉት ፴(ሠላሳ) ዓመት በዕቅድ የተሰራበት የዉስጥ ጠላቶች የረጅም ጊዜ ምኞት እንደነበር መርሳት ባልተገባ ነበር ፡፡
ይህ ሁሉ በነበረበት የኢትዮጵያ ነባራዊ የዘመናት ተግዳሮት ፫ኛዉ ብሄራዊ ክህደት ከታወጀበት ጥቅምት ፳፬ ሁለት ሽ አስራ ሶስት ዓ.ም. ጀምሮ የሚታዩ እና የሚሰሙ ለዕዉነተኛ ነጻነት ማብቃታቸዉ ሲበዛ የሚያጠራጥር ስለመሆናቸዉ የሚያጠያይቅ አይሆንም ፡፡
ለዚህም ከ ፭ ቱ ፬ቱን ወደ ዉስጥ ከመመልከት ይልቅ ወደ ወጪ ማንጠራራት እንደ ስልት መያዝ ከመደንዘዝ የማያልፍ ለመዘናጋት እና ዝገት መዳረጋችን ምድር ላይ ያለዉ እና እየደረሰ ያለዉን ማወቅ ተገቢ ነዉ ፡፡
ለዚህም ዕዉነተኛ ስም እና ተግባር በተጨባጭ ማየያዝ አለመቻል ሲሆን ይህም ፡-
የጥቅምት ወር ሁለት ሽ አስራ ሶስት የወረራ እና መስፋፋት ህልም “ብሄራዊ ክህደት” ሆኖ ሳለ “የህግ ማስከበር ” ማለት ፣
የጥፋት እና ሞት አዋጂ በአማራ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያ ሲታወጂ “ ከሀዲ እና ገዳይ” እንደማለት “ጁንታ” ፣ ማለት ፣
ጦርነት ምሽት ተጀምሮ ሳይነጋ ድል አድራጊነትን አሜን ብሎ መቀበል እና ማስተጋባት ለጦርነት እና የህዝብ መከራ ማብቃት መባቻ ማራዘም አስከትሏል፡፡ ይህን በሚመለከት ድል ሳታደርግ ድል አታብስር ፣ በጊዜያዊ ድል መዘናጋት ለሞት ነዉ በሚል ታህሳስ 2013 ዓ.ም. ስሙልን ማለታችን በወቅቱ በፅሁፍ ወጥቷል፣
በዚሁ ሶስተኛዉ የዉስጥ ችግር እና ጦርነት መቶ በመቶ መጠናቀቅ እና የጠላት እንደ ጉም መብነን በችኮላ የተበሰረ ድል አይሉት መደለል የአሳር ጉዞዉን አራዝሞታል፤ ህዝቡን በተለይም ዓማራ የፍዳ ዘመኑን እንዲራዘም አድርጎታል ፣
የትግራይ ህዝብ እንዲሰራ ፤ ትግራይ እንድትለማ ፤ ኢትዮጵያ እንድትወድም ፤ ዓማራ እንዲከስም የትግራይ መንጋ ወራሪ እና መዝባሪ ዳግም የጥፋት እና ሞት ዝግጂት ለማድረግ ዕድል አግኝቷል፣
ከዚኅም በላይ ትግራይ ስትለማ ኢትዮጵያ ትታመም ፤ ዓማራ ይክሰም ከማለት የማይለይ የጥፋት እና ሞት ዕድል በር እንዲከፈት መከላከያ ለቆ እንዲወጣ እና ጠላትም የጨረቅ መንገድ ያድርግልህ እንደተባለ ያለምንም ከልካይ ከትግራይ ዋሻ በመነሳት አስከ ጣርማ በር ዘልቆ በመግባት የያዘዉን አንጠልጥሎ ፣ የገደለዉን ገድሎ ፤የተረፈዉን አቃጥሎ እና ነቅሎ የምኞቱን ዓማራን ማዳከም ኢትዮጵያን የማጥፋት የመጨረሻዉ ግብ “ ከሳጥናኤል ትብብር ጋር አስከ ሲኦል” የሚለዉን ፬ እጁን ምኞቱን አሳክቷል ማለት ይቻላል፣
የቀደሙት መዘናጋት ያስከተሉብን የመከራ ቁስል ሳይሽር ጠላትን ፣ አስተሳሰቡን እና ዕኩይ ድርጊቱን ማሳነስ እና መድበስበስም የጦርነቱን መነሻ እና መድረሻ በዉል ካለመረዳት ወይም ችግርን ወደ ዉስጥ ከመመልከት ወደ ዉጭ የማላከክ ልምድ የለቀቀን አይመስልም ፡፡ ጠላትን ወይምጥፋትን ከማሳነስ ድልን ማሳነስ ለዕዉነተኛ እና ዘላቂ ድል ይጠቅማል ፡፡ አሁን በምንገኝበት ጦርነት ጠላት አከርካሪዉ ተመቷል የሚቀረዉ እንደ ቃርሚያ “መልቀም” መባሉ በተጠለፍንበት መጠላለፍ እና መደነቃቀፍ እንዳይሆን ዛሬም ቢሆን ከትናንት ስህተት ልንማር ይገባል፡፡
ማንም ራሱን እና አገሩን ዕወዳለሁ የሚል የኢትዮጵያ ህዝብ እና አንድነት ጠላት የዕርሱ ወዳጂ ሊሆን እንደማይችል የሚቀበል እና ለኢትዮጵያ ትንሳዔ በትጋት ከሚሰሩት እና ከሚኖሩት ጋር አሁን ህብረት እና አንድነት ሊመሰርት ይገባል፡፡
ኢትዮጵያዊ እየሞተ እና እየተገፋ በሚኖርባት አገር ዕዉነተኛ ዕድገት እና ብሄራዊ አንድነት የሚመጣዉ ዕዉነተኛ ነፃነት እና ሠባዊ መብት ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ ፡፡
ነፃነ ወይም ሞት ከሚል ሚዛናዊ እና ወቅታዊ አማራጭ ዉጭ በአድርባይነት በችሮታ የሚገኝ ባርነት እና ሆድ አደርነት ነዉ ፡፡
ብሄራዊ የኢትዮጵያን አንድነት እና የህዝቧን ጥቅም ፣ መብት እና ደህንነት ስጋት ከሚሆኑ ኃይሎች ጋር ከሆነ ተጋድሏችን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያን ጠላት ጋር አጋርነት ያላቸዉን ሁሉ ከምንጫቸዉ ለማደረቅ ከኢትዮጵያዉያን ጋር በህብረት እና አንድነት መቆም እና ከፊት መገኘት ይኖርብናል፡፡
በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ሀብት በተገኘ መሳሪያ አገራቸዉን እና ህዝባቸዉን የሚያጠቁ እና ያለበሱ እና ያገረሱ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለሚነክሱ ከኃዲ ጠላቶች አደብ ለማስገዛት ብቸኛዉ መንገድ መዘጋጀት ፣ መንቃት እና በህብረት በኃል አስከመጨረሻዉ ማክሰም ነዉ ፡፡
ማናችንም ቢሆን ዛሬ የምንኖርባትን አገር ማጣት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ዓለም ስንለይ የምናርፍበትን አፈር ለማሳጣት ሌት ከቀን ለሚሰራ የዉስጥ እና መሃል ሰፋሪ ጠላት ከ፭ ቱ ፬ቱን እጂ በመስጠት እና ወደ ዉስጥ ችግር እና የችግር ምንጭ ማተኮር የሚገባን ጊዜ አሁን ነዉ ፡፡
“ጠላትን ያስታጠቀ ራሱን እና ወገኑን ማስታጠቅ የሚሳነዉ ህዝብ አይኖርም ፡፡ ”
አበዉ“ ዕሾክን በሾክ” እንዲሉ “ዕዉነተኛ እና የሚያስተኛ ዘላቂ ሠላም የሚረጋገጠዉ …ከጦርነት ድል በኋላ ከሚገኝ ኃይል ነዉ” ፡፡
“ዕዉነተኛ ብሄራዊ ፍቅር የሚገለጠዉ ለማይቀር ትግል እና ድል ዞትር ራስን ማመዘጋጀት እና ማብቃት ነዉ ፡፡ ”
“የኢትዮጵያዉያንን አንድነት እና ህብረት የሚፈራ ከትንሳዔዋ ሞቷን የሚመኝ ነዉ” ፡፡
የጠላት የመጨረሻዉ ምኞት እና ፍላጎት እንደሚባለዉ ዓማራን አንገት ከማስደፋት(ዉርደት) ባሻገር ፪ቱንም ( ዓማራ / ኢትዮጵያ) በቅደም ተከተል ማክሰም ነዉ ፡፡
ማላጂ
“አንድነት ኃይል ነዉ ”