በኢትዮጵያ ታሪክ ለህዝብ እና አገር ጠንቅ የሆኑ የአስተሳሰብ እና ተግባር የጥፋት መልዕክተኞች በተለያየ ዘመን እና የታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያ ለማጥፋት በዋናነት ቅድሚያ ተሰጥቶ ከሚሰራባቸዉ ዉስጥ ኢትዮጵያዊነት ህብረት እና አንድነት በሚፈልጉት ለራሳቸዉ ጥቅም ይጠቅማል ብለዉ በሚቀይሱት መንገድ ማንገዳገድ እና ማወላገድ ነዉ ፡፡
የቀደሙትም ሆነ የሚገኙት የኢትዮጵያ መንግስታትም ቢሆኑ ከነበራቸዉ እና ካላቸዉ የስልጣን ምኞት እና ፍላጎት ጊዜ የገዙ እና የሚገዙ የመሰላቸዉ ለህዝብ እና ለህዝብ ልጆች የነፃነት እና ፍትህ ጥሪ ድምፅ ጆሮ እና ትኩረት ከመስጠት በስዉር ለኢትዮጵያ የአንድነት ግዛት መዳከም እና ለህዝቦች የመከራ ጊዜ መራዘም በርትተዉ ከሚሰሩ ጠላቶች ጋር በአንድም በሌላም ሲያዉቁም ሳያዉቁም ተባብረዋል፡፡
ከቅርብ ዘመናት ሲጀመር ከኢጣሊያን ፪ኛ ወረራ 1928.ዓ.ም. የክፉ ቀን ጀግኖችን አገርን ከጥፋት ፤ህዝብን ከዕልቂት የታደጉትን ፣ በ1966 ዓ.ም. ህዝባዊ ለዉጥ ግንባር ቀደም የለዉጥ መሪ እና አስተባባሪ የነበሩትን እና አይነኬ የጠባለዉን የዘዉድ ስርዓት በቃ ያሉትን ፣ እንዲሁም ከ1983 ዓ.ም. በፊት እና በኋላ በኢትዮጵያ አንድነት እና በኢትዮጵያዉያን አንድነት እና ህብረት አጥብቀዉ ለሰሩት ኢትዮጵያዉያን “ የመከራ እና ሞት ምድር ” መኋኗን ቀጥላለች፡፡
የኢትዮጵያን ህብረት እና አንድነት መጠናከር እና መኖር የህዝብ ስልጣን መረጋገጫ እና ማላጋጫ የማድረግ አባዜ የተጠናወጣቸዉ የታሪክ እና የትዉልድ ዕንክርዳድ በግል እና በፖለቲካ ወገንተኛ ጥቅም በመስከር ዛሬም ኢትዮጵያዊነት የርኩስ መዉጊያ ሆኗል፤ ቀጥሏል፡፡
ዛሬ በኢትዮጵያዊነት ላይ የማይደራደረዉ ኢትዮጵያዊዉ በተለይም ዓማራ ለ፫ አሰርተ ዓመታት በገፍ እና በጂምላ በማንነት ላይ ጥቃት፣ ስደት እና ሞት በድፍን ኢትዮጵያ በዕቅድ እና በስልት በተከታታይ ተከናዉኗል፡፡
በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያዊነት ዓማራነት ባለበት ይሙት ይል የነበር ፀረ ኢትዮጵያዊ ዛሬ በኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያ ነፃነት እና አንድነት ላይ ስላለዉ የመከራ ዶፍ ካለፉት ፴ ዓመታት የቀጠለዉ የሞት እና የስደት መስፈሪያ ቁና ተትረፍርፎ እና ገንፍሎ እየፈሰሰ ነዉ ፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ ለዘመናት ተዘርቶ ለ፴ ዓመታት ጎምርቶ እና አፍርቶ እየተስፋፋ እና እየከረፋ ያለዉ የጥላቻ ዘመቻ የአገሪቷን አንድነት እና የህዝቦች ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል የጥፋት ማዕበል ቀጥሏል፡፡
የኢትዮጵያ ጠላቶች እና አፍራሽ ጋሻ ጃግሪዎች ትናትም ዛሬም በኢትዮጵያዉያን ሞት እና ስደት የሚፅናኑ እና የሚዝናኑ በስያሜ እንጂ በተግባር ከኢትዮጵያም ሆነ ከህዝቧ የተፋቱ አድር ባዮች እና ክፉዎች የጥፋት ትብብራቸዉን ፊት ለፊት ከሚገኙ ጠላቶች በረቀቀ እና በመጠቀ ስልት ገፍተዋል፡፡
“ግመሎች ይጓዛሉ፤ ዉሾችም ይጮሃሉ…..” እንዲሉ ሁሉም የምድራችን መከራ እና ሰቃይ ሲቀጥል የዚህ የጭንቅ ጊዜ ተጋድሎ የሚደረገዉ የሞት ሽረት ትንቅንቅ በዋናነት ትናንት እና ዛሬ በአገሩ ስደት እና ሞት ሲያስተናግድ ለነበረዉ ህዝብ ብቻ የተተወ መሆኑ እና ለዚህም መተባበር እና ሞት ህይዎት ወይም ሞት ብቸኛ ምርጫ የሆነዉ ኢትዮጵያዊ አገር እና ወገን መታደጉ የሚያቅለሸልሻቸዉ ወዳጂ መሳይ በልቶ ካጂ የህዝቡን አንድነት እና ህብረት ማደነቃቀፍ የማይነቀፍ አድርገዉ ቀጥለዋል፡፡
አገርም ሆነ ህዝብ የሚኖር እና የሚከበር በዕዉነተኛ የህዝብ ልጂ እና በዜጎች እንጂ በኢትዮጵያዊነት ስም ለኢትዮጵያ ዕዉነት ዕድገት እና ብሄራዊ ኩራት የኖሩትን እና የተዋደቁትን በማደናቀፍ እና በመጥለፍ የሚጠበቅ ሞት እንጂ ትንሳኤ ሊሆን አይችልም ፡፡
የኢትዮጵያ ትንሳኤም ሆነ ሞት መንስዔ ኢትዮጵያዊነት በዚህ ጥላ ስር ዓማራነት መደራጀት እና ህልዎት መኖር ለፖለቲካ ስልጣን መቀጠል ፤አለመቀጠል ጉዳይ ጋር አስፍቶ እና አንሰራፍቶ በማየያዝ ሆኖ ሲታይ የ፻ ዓመታት የጥፋት ድግስ አካል ነዉ ፡፡
ለዚህም ነዉ ከጥንት አስከ ዛሬ የዓማራ ህዝብ በተለያየ ሴራ ወጥመድ የማዳከም እና የማዉደም ጥረት እንደ አሜባ ተለዋዋጭ ገዳይ ጠላት የኢትዮጵያዉያን መደራጀት እና ህብረት አምርሮ ቢጠላ አይገርምም ፡፡
ከዚህ ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን እያስተጋቡ የኢትዮጵያዉያንን ራስን እና አገርን የመከላከል ተፈጥሯዊ እና ሠባዊ ብሄራዊ መብት ችሮታ ለማድረግ የሚዳዳቸዉ የዉስጥ አድር ባይ እና አዝግ አባዜ የተጠናወታቸዉ የወዳጂ አሳዳጂ ሲያጥላሉ ማየታችን የሚያስጨንቃቸዉ የግል ጥቅም እና ምቾት መሆኑን ነግቶ አስኪመሽ ማደንቆር እና ማደናገር ቀጥለዉበታል፡፡
የኢትዮጵያ ህዘብ በተለይም የዓማራ ህዝብ መደራጀት እና አንድነት መኖር አለመኖር ከኢትዮጵያዊነት እና ታላቋ ኢትዮጵያ ህልዉና ጋር በቀጥታ የማይነጣጠል መሆኑን የዘመናት የቀደመ ታሪካችን ቀርቶ ጠላቶቻችን የማይክዱት ዕዉነት ሆኖ ሳለ የዓማራ መደራጀት ለኢትዮጵያ ትንሳዔ ብቸኛ ለይኩን መሆኑን ኢትዮጵያዉያን ነን የሚሉት ሁሉ እየመረራቸዉ ሊቀበሉት እና ሊያከብሩት ይገባል፡፡
የዓማራ ህዝብ ራሱን ከጥቃት ፤አገሩን ከዉርደት እና ጥፋት ለመታደግ ብሄራዊ አንድነት መኖር እና መንበር የሚያስፈራዉ ጠላት ዲያብሎስ ብቻ ነዉ ፡፡
ከዚህ ግብር እና ተግባር ጋር የሚተባበር የዉስጥም ሆነ የዉጭ ጠላት ስለማይለይ መኃል ሰፈሪ እና መሰሪ አስመሳዮች የወዳጂ ጠላቶች ከመሆን በምንም ሊለዩ አይችሉም ፡፡
ማንም ጥቃትን እና ባርነትን ተዋርዶ እየኖረ አሜን ብሎ የሚኖር ቢኖር እርሱ ዉርደትን እና ክህደትን ልብሱ እና ጉርሱ አድርጎ ሊኖር የሚፈልግ ነዉ ፡፡
በየትኛዉም የኢትዮጵያ የጠላት ከበባ እና ወከባ ጊዜ እና ታሪክ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር የማስከበር እና የማክበር ጉዳይ በምንም የማይለዉጠዉን በኢትዮጵያዊ ማንነት በጠላትነት ፈርጆ ሲያሳድደዉ የነበረዉ ጠላት ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ሲዘምትበት ራሱን የመከላከል ጉዞዉን ለማደናቀፍ ህብረቱን እና ቁርጠኝነቱን የሚፈራ ፀረ ኢትዮጵያ መሆኑ ከዚህ የላቀ ምልክት ሊኖር አይችልም፡፡
ሁሉም ራሱን እና አገሩን ማዳን የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ጠላት ለዘመናት የመደራጀት ዕድል አገኝቶ ቀርቶ መቶም ኢትዮጵያን ለማጥፋት የኢትዮጵያዉን ሞት እና ስደት የመጀመሪያም የመጨረሻም ህልሙ መሆኑን ከሶስት አስርት ዓመታት አስካሁን የተጓዝንዉን የመከራ መንገድ መርሳት ሞት ነዉ ፡፡
“አበዉ ያቆሰልከዉን አዉሬ አትመነዉ… .”.ሲሉን እኛ ኢትዮጵያዉያን በቁም ወግቶ ያቆሰለንን የጭቃ እሾህ ለቅመን ፣ አድርቀን ሳናቃጥል …. ድል ሳይሆን ራስን ሆነ አገርን በድጋሚ በመግደል በትዉልድ እና በታሪክ የሚያስጠይቅ ለክፉ ሰሪዎች መተባበር ለተዉልድ ደም የስቃይ ዘመን ማስተላለፍ ይሆናል ፡፡
በሠላም እና ዕርቅ ያለደረቀ የጥላቻ ጅረት የሚቃረጠዉ በኃይል ብቻ ነዉ ፡፡ ጠላትም ሆነ ክፉ ሰሪ ሞቶም እንደሚገድል በጥባጭ ሳለ ጥሩ አይጠጣም የሚለዉን የአበዉ ብሂል እብሮ ማየት ሠዉ ለሆነ ኢትዮጵያዊ ደጋግሞ ግድ ይላል፡፡
“አንድነት ኃይል ነዉ ”