December 30, 2021
14 mins read

በአሁኑ ሁኔታ የአማራንና የአፋርን ነዋሪ ደህንነት መከላከል የሚቻለው በዋናነት በትግራይ ውስጥ የመከላከያ ዞን ሲኖር ነው

Abiy uniform 1ከ ዚዜው ደረስ [email protected]

የሰሞኑ ጭውውት የህወሀትን ተስፋፊ ሀይል ከአማራና አፋር ክልል ጠራርገን አወጣነው በብዙ ሽወች የሚቆጠሩትንም ደመሰስን ማረክን ሰለዚህም ሰራዊቱ የመጀመሪያ ዙር ተልእኮህን አጠናቋል እና ባለበት ይቁም ተብሏል የሚለው ነው፡፡

የመንግስት ባለህበት ቁም የሚለው ትእዛዝ እጅግ ያልተጠበቀና ግራ የሚያጋባ እርምጃ ስለመሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ በተለይም ደግሞ የትግራይ ህዝብ የጥሞና ግዜ እንዲያገኝና እንዲሁም ገበሬውም የእርሻ ጊዜው ሳያልፍ ወድ እርሻው እንዲሚለስ እድል ለመሰጠት አንድ ጎን ተኩስ ማቆም ብቻ ሳይሆን ከመላው ትግራይ በፈቃዳችን ለቀን ወጥተናል ብሎ በተናቀረ በቀናት ውስጥ እግር በእግር እየተከታተለ ህወሀት የከሰተውን ሰፊ ወረራ የሚያስታውስ ሁሉ የአሁሁን የምንግስት እርምጃ በጥራሬ ቢሚለከትው የሚገርም አይደለም፡፡

ሀዚህ ጋር ተያይዞም የሚነሱትን ጥይቄውች ውስጥ ጥቂቱ የሚከተለውን ይመስላሉ፡፡

የተፈናቀሉት፣ የአስገድዶ መደፈር ሰላባ የሆኑት ምክንያቱ ሳይገባቸው ሀብት ንብረታቸውን አንዲሁም ቤተስቦቻቸውን ያጡ የአፈርና አማራ ተወላጆች ገና ለደረስባቸው ግፍ ጊዜ አግኝተው በአግባቡ ማስብ ሳይችሉ ሀዘናቸውን በቅጡ ሳይወጡ እጅግ ብዙወቹም ተሰደው ከሚገኙበት የስደት ጣቢያም ይሁን ዘመድ ተመልሰው የደረስውን ጉዳት በአግባቡ ሳይመለከቱ በቃ በ እናነት ላይ የተካሄደው ወረራን ያካሄደው አካል ላይ የሚካሄደው እንቅሰቃሴ በዚሁ ይቆማል መባሉ ጊዜውን የጠበቀ ነውን? የሚለው የመጀመሪያ ጥያቄ ነው፡፡

ለዚህ ተጎጂ ህዝብ የሰላም ማረጋገጫው እንዲህ በ ሀዝብ ግንኙነት ሹም በኩል በሚነገር የ10 ደቂቃ መግለጫ መሆኑ ከስቃዩ ጥልቀትና ካስከተለውም ጠባሳ አንጻር ሲታይ የሚመጥነው ነውን? ይህ ህዝብ ከደረስበት ግፍ አንጻር የሚገባው የማስተማመኛ ንግግር የመንግስት መገናኛ ፐረስ ኮንፍረንስ የሁለት ጥያቄዎች ምላሽ የሚመጥነው ነውን? ለመሆኑ ለተጎጂው የስነልቦና ስብራትና ሀዘን መንግስታዊ ማበረታቻው ይህ መሆን ይኖርበታልን? ይህስ መተማመንን ሊገነባ የሚችል ለየት ያለ ማህበራዊ ይዘት ያለው ወይይት አያስፈልግም ነበር ? ፍራቻቸውን ተስፋቸውንና ምን ቢሆን ምን ቢደረግ መረጋጋት እንደሚሰማቸው፣ ማማከር በየጊዜ ሊከሰት ለሚችለውን የስሜት መዘበራረቅ ምን መደረግ እንደሚገባው ወዘተ ከተጎጂው ህብረተ ስብ ጋር መመካከህ፣ መነጋገር ተገቢ አይሆንም ነበርን?

እንዴት ነው ከአማራና አፋር ክልል ተጠራርጎ ወጥቷል የተባለው ሀይል አሁንም ሰሜን ጎንደርና ወሎ ውስጥ ቢይንስ ሶስት ወረዳ ውስጥ የሚገኘው ? እንዴት ተጠራርጎ ወጡ የተባለው ህወሀቶች በሁሉቱም ክልል በአራት አቅጣጫ ሶስት ቀን ባልሞላ ጊዜ መልሶ ለማጥቃት ብቃት ያገኙው ፣ ይህስ ከሆነ መልሶ ለማጥቃት ከምንገምተው በላይ እምቅ ሀይል ይኖረው ይሆን?

በአፋርና አማራ ክልል የተማረኩት የህወሀት ተዋጊዎች በአብዛኛው ብዙም ስልጠና ያልወስዱ ህጻናትና ከየቦታው የተለቀሙ የትግራይ ተወላጆች እንጂ ለአመታት የሰለጠነው የትግራይ ልዩ ሀይል አባላት አልነበሩም፡፡ ታዲያ ያ በሰሜ እዝ ላይ ታላቅ ጥፋትን የፈጸመ እጅግ የሰለጠነ ጦር የት ነው ያልው? ለመቼና ምንን ለመውጋት አድፍጦ ይሆን የሚሉ እጅግ ረባሽ ጥያቄዎችን እስነስቷል፡፡

ታዲያ ይህ ጉዳይ አሁን የተወሰደው ውሳኔ የአማራና የአፋር ህዝብ ለሌላ ዙር ጥቃትና ወረራ ተጋላጭ ያደርገው ይሆን? ይህ በያንዳንዱ ዜጋ መጠየቅ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

ቀድም ሲል የኢትዮጵያ ሰራዊት ከትግራይ ሲወጣ “እንደጉም ተበትኗል፣ የተባለው ጦር አማራና አፋር በመዝለቅ እጅግ ስፊ ግፍና ውድመት ያደረሰ መሆኑን ሁላችንም አንረሳም፡፡ ይህ አሁን እንዳይደገም የሚከተሉትን እሰነዝራለሁ፡፡

ሰለታገስን ወይም እኛ የሞራል ከፍታ ባለው መንገድ ትግሉን ለመምራት ብንፈልግም ሀወሀት በተመሳሳይ ደረጃ ይመጣል ማለት አይደለም፡፡በሩጫ ላይ የነበረው ህወሀት የመንግስትን ተኩስ ማቆም የሚጠቀምበት፣ትንፋሹን ስብስቦ በሁሉም መልክ ራሱን ለማጠናከር ነው፡፡ይህም ሰለሆነ በምንግስት በኩል ከዚህ ቦታ አናልፍም ሰለተባለ ጦርነቱ ይቆማል ማለት እንዳልሆነ ግልጰ ሊሆን ይገባል፡፡

ህወሀት ቂመኛ ድርጅት ነው፡፡ በተለይም አማራ የሚባለውን ህብረተስብ አንገት ካላስደፋ አርፎ አይተኛም፣ ይህንንም ፣ ከጦርነቱ በፌት ለ 27 አመታት የአሁኑ ጦርነት እንደታወጀም ከነ ጌታቸው ረዳና ደብረጽዮን አንደበት በተደጋጋሚ የሰማነው ነው፡፡ ይህም ህወሀት አቅም እስካገኘ ድረስ የጦርነቱን ቀጣይነት አይቀሬ መሆነን ያሳያል፡፡

ህወሀት ወልቃይት ጠገዴን አጥቶ መኖር አይፈልግም ምናልባትም አይችልም፡፡ ለዚህ ሲል የትግራይን ህዝብ እንዲከፍል የማይጠይቀው ዋጋ የለም፡፡ ሰለዚህም አሁንም እነዚህን ቦታዎች መልሶ እስካልያዘ ድረስ ጦርነቱ አይቀሬ ነው፡ይህ ደግሞ በወያኔ የሚቀነቀን ብቻ ሳይሆን ባእዳን ሀገራትም የአማራ ሰራዊት ከወልቃይት ጠገዴና ራያ ይውጡ እያሉ ደጋግመው በመናገራቸው ሀወሀትን ያልተጨበጠ ተስፋ ይዞ እንዲጓዝ መሆኑን መዘንጋት አያሻም

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ህወሀት አሁንም በግድም ይሁን በውድ ሰራዊት እየመለመለና እያሰለጠነም ነው፣ ይህ ታዲያ ለጦርነት የሚደረገውን ዝግጅት እና የዚህም የመጀመሪያው ተጠቂ ተጎራባች ክልሎች እንደሚሆኑ ግልጽ ነው፡፡

ታዲያ ነባራዊው ሁኔታ በህወሀት ተንኳሽነት የጦርነቱን አይቀሬነት ካመላከት ፣ በዚህ በኩልስ ምን ይደርግ የሚለው እጅግ ወሳኝ ይሆናል፡፡ ለወታደራዊ ባለሙያውች ጥልቅ እስትራተጂውን ተቼ እንደ አንድ ዜጋ በኔ እይታ የሚከሉትን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ይታየኛል፡፡

የጦር እዋቂወች እንደሚሉት፣ ስላምን ከፈለግክ ለጦርነት በበቂ ተዘጋጅ ፡፡ The original Latin of the expression “if you want peace, prepare for war” የአማራም ሆነ የአፋር ህዝብ ራሱን ለመከላከል መደራጅት ለጦርነት ብቃት ባልው ሁኔታም ዝግጁ ሆኖ ይገባል፡፡ ይህም በሰው በሰው ሀይል፣ በመሳሪያ ጥራትና ብዛት፣ በስንቅና በስላላ ተግባር ወዘት መሆን ይኖርበታል፣ ይህ የጦርነቱን

በመላው ሀገሪቱም ይህን አደጋ ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ሁሉን አቀፍ ዝግጅት አጠናክሮ መቀጠል ያሻል፣ መዘናጋት አያሻም፡፡

ከዚህ በተጭማሪ በዋናነት ህወሀትን ሀይል በሀገራችን ላይ ምንም አስጊ ጉዳት ወደማያደርስበት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ደረጃ ዝቅ እንዲል የሚደረገው ጥቃት እንዲቀጥል ማድረግ እንዳለ ሆኖ፣ የሀወሀትን ጥቃት በሌሎች ክልሎች ጉዳት ማድረሱን ለመከላከል አንዱ መፍትሄ በትግራይ ክልል የመከላከያ ቀጠና (ባፈር ዞን) መመስረት አስፈላጊ ነው ፡፡ የመከላከያ ቀጠና (ቡፈር ዞን) መመስረት አስፈላጊ ህወሀት በአጎራቻች ክልሎች ላይ የማያቋርጥ ስጋትን በመደቀን ከተረጋጋ ህይወታቸን እንዳያበላሽ፣ በተለመደ ባህሪው ድንገተኛ ወረራን ለማካሄድ ሙከራ ቢያደርግ ገና ከጅምሩ ለማምከን በሱስተኛ ደረጃም በአካባቢው ለሚገኘው የትግራይ ህዝብ ሙሉ ድጋፍን በመስጠት ለሊአላውም የትግራይ ህዝብ ከ ህወሀት ተላቆ መኖር የሚኖረውን ጠቀሜታ በማሳየት ለዚህም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርገ ተጨማሪ ድጋፍን ለመስጠት ነው፡፡

የመከላከያ ቀጠና (ባፈር ዞን) መመስረትና በዚህም መሰረት ይህዝብን ድህንነት ማረጋገጥ በአለማችን የማይታወቅ ጉዳይ ሳይሆን በተለይም እንከ አሁ ድረስ እስራሴል ብጎላን ክፍተኛ ተራሮች በኩል እንዲሁም ብዙወች ፓለስትኒያኖች በሚኖሩበት መእራባዊ ድንበሯ ( ዌስት ባንክ) በኩል የመሰረተቻቸው የመከላከያ ቀጠናዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የሁለተኛውን የአለም ጦርነት ተከትሎ እስታሊን በሀገሩ ዙሪያ በፈጠራቸው የመከላከያ ቀጠናዎች የተባበረውን የመራቡን ሀይል እንዳይወረው ከፍተኛ መከላከያ ሆኖት እንደኖረ ታሪክ ያሳየናል፡፡

ላይ የተጠቀሱት ሁለቱም ምሳሌዎች በተለያዩ ላላዊ ምንግስታት መሀል የተካሄደውን የሚያመለክቱ በመሆኑ የኢትዮጰያ አንድ አካል ከህፕነችው ትግራይ ጋር ሙሉ በሙሉ አንድ እንዳልሆነ እገነዘባለሁ፡፡ ቁም ነገሩ ግኝ የመከላከያ ቀጠና (ባፈር ዞን) በመመስረት እርፎ ከማይተኛ ጦረኛ ሀይል ሀገርና ህዝብን እንዴት መከላከል እንደሚቻል ማሳየት ሰለሆነ ሊወራረሱ የሚችሉትን ሀሳቦች መመርመርና መተግበር ነው፡፡

በመጨረሻም ለትግራይ ችግር መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው በወታደራዊ የበላይነት ብቻ ሳይሆን ከህወሀት ውጭ የሚገኘው ሌላው የትግራይ ሀይል ጋር ግልጽ ያለ ድፍረት የተሞላው ንግግር በማድረግ የወደፊት እጣ ፈንታንም እንድ ምእራፍ ላይ ማድረስ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop