ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለመታደግ ከተፈለገ……..ፊልጶስ

በማንኛውም ዘመን ቢሆን ጦርነት አስፈላጊ የሆነበት ግዜ የለም፤ ግን ድግሞ ዓለማችን በተለይም እኛ ብዙው ታሪካችን እና ኑሯችን  የጦርነት ነው።  ለዘመናት ያደረግነውና እይደረግነው ያለው የ’ርስ በርስ ጦርነት  የዓለም ጭራ ብቻ ሳይሆን ግዛታችን እና እንድነታችን እየፈረስ ጠረፍ አልባ ለመሆን በቅተናል።  ትልቅ ከመሆን ትንሽ መሆንን መርጠናል::

አሁን ያለው ጦርነት  የአገርና የህዝብ የህልውና ጦርነት በመሆኑ በድል መወጣት የግድ ይለናል። ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ህዝብና መንግስት ተናቦ፣ በሰከነ መንፈስ ከሴራ ፓለቲካና ከመንደርተኛ አስተሳሰብ ወ’ተን፤ የሁላችን መዳኛ ኢትዮጳያን ኢትዮጵያ መሆኖን ከተቀበልን ብቻ ነው።

በዚህ ወቅት የጦርነቱ ሁኔታና የመንግሥትን አቋም ካየነው ወያኔ ወደ መቀሌ በመመለሱ አትሪፊ ነው። ከበቂ በላይ ዘርፋል፣ ገሏል፣ የቻለውን ጭኖ ያልቻለውን አውድሞ ሄዷል። በተቃራኒው በወሎ፣ በጎንደር፣ በሸዋና በአፋር ሰው ሰርቶ ሊተካው የማይችል ለዘምናት የሚቆይ አዕምሯዊና ቁሳዊ ውድመት ደርሶል።

ኢትዮጵያ  ተጎሳቁላለች1 አልቅሳለች! ደምታለች!

በ’ርግጥ ”ዱቄት” ሆኗል ያለው መንግሥት ከዚህ ደረጃ እስኪደርስ፤

1/ እንዴት ተፈቀደለት?

2/ ተጥያቂውስ ማነው?

3/ በጦርነቱ ወቅት አመራር እየሰጡ ያሉታ ወያኔን ከተንቤን በርሃ አውጥተው ሸዋ  እንዲገባ ያደርጉት ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጀምሮ ለፍርድ ይቀርባሉ ወይ? ሌላው ቢቀር ለሰሩት ስህተት ወይም አሻጥር  የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ይጠይቃሉ ወይ?

4/ ህዝብስ የደረስበት ግፍ ምንም ዓይነት ምድራዊ ካሳ የማይክሰው ቢሆንም እውነቱን እንኳን የማወቅ መብት የለውም ወይ?

5/ ጦርነቱስ እስከምን ድረስ  ነው?

በመንግሥት፣ በአንዳንድ ወገኖችና ካድሪዎች (መስሎ አዳሪዋች) በኩል ያለው ስሜታዊ የድል ጭፈራና ፋከራ ጦርነቱ  ያለቀ አስምስሎታል። ትግራይን ተቆጣጥሮ ፤ወያኔን እስከ አመለካከቱ ወደ ማይመለስበት መቅበር ካልቻለ፤ ምዕራቡን ዓለም ከጎኑ ያሰለፈው ወያኔ እንደገና እንደሚያንሰራራ ሳይታለም የተፈታ ነው።

እናም ህዝብም ሆነ በእውነት ለኢትዮጵያ እንድነት ቁመናል የምንል ፤ በአሁኑ ወያኔን ወደ መቀሌ የመመለስ ድል አንዘናጋ፤ ከፊት ለፊታችን ትልቁ ጦርነት ይጠብቀናልና። መንግሥት ግልጽ ሆኑ ከኦነጋዊ ብልጽግና ድብቅ ዓላማና አሻጥር ራሱን አጽድቶ ፤ ህዝብን አስተባብሮ ከታገል ወያኔ እስከ አመለካከቱ እስከመጨረሻው እንደሚሸኝ ጥርጥር የለውም።

ወያኔ ትግራይ ውስጥ እንዲመሽግ ከተፈቀደለት ግን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ምንግዜም ዕረፍት አይኖረንም፤ ተረኛዎቹ ገዥዎች ኦነጋዊ ብልጽግናም የወያኔን መኖርና እነሱ እንገነባታለን ለሚሏት ”ኦሮሚያ” ማረጋገጫ ይሆናል።

ጥያቄው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ይፈቅዳል ወይ ነው።  መልሴ መፍቅድ አይደለም መታሰብም የለበትም ነው። ከአሁን በኋላ ህዝብ ከትላንቱ ስህተቱ መማር የግድ ይለዋል ብቻ ሳይሆን መንግስትንም ሆነ ሌሎቹን ምክንያት በማድረግ  ወያኔና አመለካከቱ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖር ከፈቅድን ለምከፍለው ዋጋ ተጠያቂ  እኛ እንጂ ማንም ሊሆን አይችልም።

 

ጦርነቱን በድል ለማጠናቀቅና ኢትዮጵያን ለመታደግ ከተፈለገ መንግሥት  ከጦርነቱ ጎን ለጎን  ከወያኔ የወርሳቼንና አሁን እየተጠቀመባቸው ያሉ የጸረ-ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቅና አስፈላጊም ከሆነ ማስገደድ የወቅቱ ትግል ነው። ስለዚህ ፤

 

1/ህገ-መንግሥቱ=> ስለ ወያኔና ኦነግ ህገ-መንግሥት ( ነፍሳቼውን ይማረውና ፕ/መ መስፍን ”ህገ-አራዊት” ይሉት ነበር።) አሁን ላለንብት የሰቆቃ ዘመን አድርሶናል። ይሁን እንጂ  ብልጽግናዎች በደማችን ያገኘነው ”አይነኬ” መሆኑን አስረግጠው ነግረውናል። የኢትዮጵያዊያን ”ተራጀዲ” ተውኔት የሚያስመስለው ደግሞ፤ ትላንት ህገ-መንግሥቱ እስከ አለ ድረስ ኢትዮጵያ አገር አትሆንም ሲሉን የነበሩትና ህገ-መንግሥቱ አይውክለንም ያሉት፤ አሁን  ህገ- መንግሥቱን ተቀብለው ብቻ አይደለም ጠባቂና አስጠባቂ  መሆናቸው ነው።አሁን አገራችን የምትተዳደረው በአስቼኳያ ግዜ አዋጅ ነው። ስለዚህም አስቼኳይ አውጁን መሰረት አድርጎ ህገ-መንገሥቱንም በተመሳሳይ መንገድ ማገድ ይቻላል።   እውነት በእውነት የብልጽግና መንግሥት በተለይም ጠቅላይ ሚኒስተሩ  በተግባር የሚፈትኑበት በመሆኑ እና  በእውንት ኢትዮጵያ ! ኢትዮጵያ የምንልም ይህ እንዲተገበር ፊለፊት መናገርና መጋፈጥ የግድ ይለናል።

2/ክልል=>  አሁን ያለው ጎሳንና ቋንቋን መሰረት ያደረገ ክልል ወያኔ የቀበረው ቦምብ፤ ኦነጋዊያን የሚመጻደቁበት ጸረ-ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ጸረ-ተፈጥሮ ነው። ይህ የክልል እስተዳደር እስከአለ ድረስ መቸውንም ቢሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ‘ረፍት ማግኘት አይደለም ከጦርነት አዙሪት አይወጣም። ስለዚህም  የክልል አስተዳደር መልካ ምድርንና ምጣኔ ሃብትን መሰረት ያደረገ አውቃቀር እንዲኖረው  ገዥዎቻችንን ማስገደድና  የኢትዮጵያ ህዝብ ታግሎ ማስፈጸም ያለበት ለነገ የሚባል ጉዳይ ነው ፤ ምክንያቱም መከረውና ግፋ የተረፈው ለህዝብ እንጅ ለገዥዎቻችን አይደልምና። ገዥዎቻችንማ የስልጣናቸው ማራዘሚያና ለሚሰሩት ወንጀል  መደበቂያ  የጎሳ ክልላቸው ነው።

3/ሰንደቅ ዓላማችን =>   አረንጓዴ፣  ቢጫና ቀይ የኢትዮጵያዊን ሰንደቅ ዓላማ ነው።ይህ ሰንደቅ ዓላማችን ሚሊዮኖች የተሰውለት ፤ አሁንም እየተሰውለት ያለና ወደፊትም ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ መሰዋአት የሚከፍልበት የማንነቱና የአንድነቱ  አርማው ነው።  ይሁን እንጂ እንደምታዮት አሁንም በጦርነትም ላይ ይሁን በማንኛውም ቦታ  መንግስትም  የሚጠቀመው ወያኔ ሰፍቶ የሰጠውን  ባለ ”አምባሻው”  ነው ። ክልሎችም የሚያውለበልቦት ወያኔ የሰራላቸን ምንም ዕይነት ታሪክ የሌለው ነው። ‘ርግጥ ነው በአፋር፣ በጎንደር፣ በጎጃምና በወሎ የሚገኙ ተዋጊዎች የሚይዙት ነባሩን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ነው።   ለአንድ አገር እንደነት ለሚደረግ ጦርነት ሁለት ዓይነት ሰንደቅ ዓላማ ይዛ ያለች አገር እስከማውቀ ደረስ የእኛዋ ብቻ ነች። ያወም ጠላታችን ሆኖ እየወጋን ያለው ኃይል  የጫነብንን ሰንደቅ ዓላማ።

ስለዚህ መንግሥት  ነባሩ   አረንጓዴ፣  ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማችን እንዲጠቅም መጠየቅና  መታገል   ከህዝብ ይጠበቃል።

ትላንት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አንደራደርም ሲሉን የነበሩት ዛሬ የስልጣን ወንበሩን ሲፈናጠጡ የወያኔን ሰንደቅ ዓላማ ከጀርባቸው ሰቅለው “እዩኝ ! እዩኝ! “ ሲሉ ማየት የሚያስተዛዝብ ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ለሰንደቅ ዓላማው ከዚህ በኋላ መክፈል ያለበትን መስዋእትነት መክፈል አለበት።

4/የፓለቲካ እስረኞችን ማስፈታት=> የፓለቲካ እስረኞች በተለይም  የባልደራስ  አመራር አባላት እነ አቶ እስክንድር ነጋ እና በአመለካከታቸው ብቻ የተሰሩ ጋዜጠኞችን ሳይውል ሳያድሩ እንዲፈቱ ማደረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይና ኃላፊነት ነው። መንግሥት ለኦነጋዊ ብልጽግ ዓላማ እንቅፋት ይሆናሉ ተብለው ያለፍርድ የታሰሩ ዜጎችን አሳሰረን አንድነታችን እና ኢትዮጵያዊነታችንን ልናስከብር አንችልም።

5/ አዲስ አበባ=> አዲስ አባባ በኦነጋዊን ብልጽግና ”ኬኛ” ተብላ መዲናነቷ ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለኦነጋዊያን እንድትሆን  መስራት ከተጀምረ ዓመታት አስቆጠርን።  የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነትን አሻራ   ነው የተባለ  ሁሉ  እንዲጠፋና እንዲወድም ተፈርዶብታል።  በዚህ ከቀጠልን ነገ ከነገ ወዲያ ከአዲስ አበባ ውጡ መባላችን እንደማይቀር ተገንዝበን፤ ኦነጋዊ ብልጽግና ከዚህ እኩይ ድርጊቱ እንዲታገድ ማድረግና አዲስ አበባ የሁላችን የኢትዮጵያው  መሆኗን ማረጋገጥ  መቻል አለብን። በተለይ በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥት የኦነጋዊነትን የበላይነት በከተማዋ ውስጥ ለማረጋገጥ ሌት-ተቀን እየሰራ ስለሆነ መራራ ትግል ያስፈልገናል።

6/ ግድያው ይቁም => በተለይም በወለጋና በቢሻንጉል እንዲሁም በተለያዮ እካባቢዎች  በተለይም በአማራ  ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ግድይ ማስቆም  አለብን። ግድያውን ማሽሞንሞን አያስፈልግም፤ በኦሮሚያ ብልጽግና መዋቅር ተዘርግቶለት የሚካሄድ የዘር ማጥፋት ወንጅል ነው። ስለዚህ ይህን  የዘር ፍጅት በልመና እና በልቅሶ የሚቀር ሳይሆን በትግል ነውና  ከላፈው ተምረን ይህን መንግስታዊ ግድያ ማስቆም መቻል አለብን።

7/ የአገራችን የውጭ ግንኙነት=> ምዕራቡ ዓለምም ሆነ ሱዳን እና ግብጽ እንዲህ እንዲፈነጩብን ያደራጋቸው የመንግሥት ድክመት መሆኑ መዘንጋት የለበትም። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ  በመንግሥት ደካማነት የተፈጠረውን ክፍተት መሙላትና አገራችንን በምንም መስፈርት ቢሆን የውጩ ዓለም  የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት መታገልና መቋቋም  የህልውናችን ጉዳይ መሆን አለበት፥፥አንዳንድ ወገኖች ገዥው  ኦነጋዊ ብልጽግና ከወያኔ የሚለይበት በስልጣን እንጅ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ናቸው፤ ስለዚህ ጣልቃ ግብነቱን በገዥው ኃይል እስከሆነ ድረስ መቃዎም የለብንም የሚሉ አሉ።  ነገር ግን ምዕራቡ ዓለም  እንደተለመደው የራሳቸውን ጥቅምና ፍላጎት  በእኛ ላይ ለመጫን እንጂ፤ በምንም ዓይነት መስፈርት ቢሆን ኢትዮጵያን ሊታደግ ጣልቃ የሚገባ  የውጭ አገር የለም። ችግሩ ከወያኔ ጋር ብቻ ሳይሆን ከህዳሴው ግድብ ጋር የተያያዘና የምዕራቡ ዓለም የዘመናት ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና የማዳከም ሴራ መሆኑን መገንዘብ ይገባናል። ሊያንግሱልን የፈለጉት እኮ ወያኔን እና የቤተ-መንግሥቱ ግማሽ አካል የሆነውን ኦነግ ሸኔ ነው። እናም ለአገራችን እኛው በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ከተደራጀንና ኃይል ከፈጠርን፤ የአገራችን እጣ በእኛው እጅ ነው።

 

ማሳሰቢያ፤

ይድራስ  በኢትዮጵያ ጠ/ሚ  አብይ አህመድ ጥሪ ተደርጎላችሁ ወደ አገር ቤት ለምትገቡ ኢትዮጵያዊያን ፤

ከላይ ላነሰዋቸው ጉዳዮች  እናንተንም ይመለከታለና በቆይታችሁ  ለጋበዛችሁ መንግሥት አቅርባችሁ ለተፈጻሚነቱ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ቁማችሁ እንደምትታገሉና የድርሻችሁን እንደምትወጡ ተስፋ አደርጋልሁ። መቼም  ለዛ  በጦርነት የምድርን ፍዳ ሁሉ ላየ  ምጻተኛ ህዝብ ጮማ ቆረጣና  በውስኪ  መራጨትን ልታሳዮት እንዳልተጋብዛችሁ እምነቴ ነው። በእርግጥ ውጤቱን አብረን የምናየው ይሆናል።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!

ፊልጶስ

ኅዳር 2014

E-mail: [email protected]

1 Comment

 1. የቀረቡት ሃሳቦች መልካም ናቸው ። ይሁንድ እንጅ ለዘመናት የመጣንበት ህወሃት መራሹ እና አሁን ደግሞ በተረኛው ኦህዴዴ/ኦነግ የበላይነት የቀጠለው የበሰበሰና የከረፋ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት እንደ ሥርዓት ካልተወገደ በስተቀር ከአጠቃላይና አስከፊ ቀውስ ጨርሶ መውጫ የለንም ።
  ቀውስ (crisis) እንደ ግለሰብ ወይም እንደ ማህበረሰብ ወይም እንደ ትውልድ ወይም እንደ አገር በመደበኛነት ለምናከናውናቸው ፣ ለምናስባቸውና ለምቀድናቸው ሥራዎች (ጉዳዮች) በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሊያጋጥሙን ከሚችሉ ተግዳሮቶች (challenges) በላይ ሁሉንም ትኩረታችንንና አቅማችንን በሚጠይቅ ፣ ጊዜ በማይሰጥ እና አደገኛ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መሆናችንን የሚገልፅ ሰፊና ጥልቅ ፅንሰ ሃሳብ ነው። በሌላ አገላለፅ ቀውስ በፅዕኑ መርህ፣ ዓላማና የግብ መዳረሻ ላይ ሳንቆም ለምንደርተው የትርክትና የትንታኔ ድሪቶ ማሳመሪያነት ወይም ማድመቂያነት የምንጠቀምበት ሳይሆን ፈጣንና ውጤታማ የሆነ የአእምሮ እና የተግባር ቅንጅትን በሚጠይቅና እጅግ ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መሆናችንን የሚነግረን ቃል (term) ነው።
  የቀውስ ምክንያት የተፈጥሮ ወይም ሰው ሠራሽ ሊሆን ይችላል። ይህን ከሁለቱ በአንደኛው ወይም በሁለቱም ሊያጋጥም የሚችል ቀውስ አስፈላጊ ፣ ወቅታዊና ውጤታማ የሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ ለመቋቋምና ብሎም ወደ መደበኛውና ሁለገብ (ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ) የሥራ እንቅስቃሴ ለመመለስ ይቻል ዘንድ ቢያንስ መሠረታዊ የሃላፊነትና የተጠያቂነት ስሜት ወይም ህሊና ባላቸው ፖለቲከኞች የሚመራ ሥርዓተ ፖለቲካ መኖርን የግድ ይላል። ይህ በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ብቸኛ ምርጫ የሚሆነው የቁም ሙት ከመሆን ይልቅ የመቃብር ሙት መሆንን በሚያስመኝ አስከፊ አዙሪት ውስጥ ለመኖር (መኖር ከተባለ) መዘጋጀት ነው የሚሆነው። አለመታደል ወይም የፈጣሪ ቁጣ ሆኖብን ሳይሆን በገንዛ ራሳችን ተደጋጋሚና አስከፊ ውድቀት ምክንያት የዚህ አይነት እጅግ አሳፋሪና አስከፊ ምርጫ ሰለባዎች ብንሆን ያሳዝን እንደሆነ እንጅ ከቶ አያስገርምም።ለዘመናት የመጣንበትና አሁንም የምንገኝበት የእኛነታችን ቀውስ ይህንን ያህል ግዙፍና መሪር ነው።
  የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ቀውስ በየትኛውም ጊዜና ማህበረሰብ ውስጥ ሊያጋጥም (ሊፈጠር) የሚችል ክስተት ነው። የሚከሰትበት ተጨባጭ ሁኔታና የሚስተናግድበት መንገድ በዋናነት የሚወሰነው ግን መንበረ ሥልጣን ላይ የተቀመጡ ወይም የሚቀመጡ ፖለቲከኞች ከምር በሆነ የሃላፊነትና የተጠያቂነት ስሜት ወቅታዊና ውጤታማ እርምጃ ይወስዳሉ ወይንስ ቀውስን ለርካሽ ፖለቲካ ቁማራቸው ይጠቀሙበታል? የሚለውውን ጥያቄ በትክክል ለመመለስ በመቻል ወይም ባለመቻል ነው ።
  ይበጀናል የምንለው የእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለውጥ እውን ይሆን ዘንድ ያካሄድናቸውና የምናካሄዳቸው እንቅስቃሴዎቻችን እጅግ ተደጋጋሚና አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ እየከሸፉ የመከራውና የውርደቱ ቀውስ በቀላሉ ፍፃሜ እንደማይኖረው ግልፅ የሆነው ከመሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ ተጋድሎ እየተንሸራተትን ሸፍጠኛ፣ ሴረኛ፣ ፈሪና ጨካኝ ገዥዎቻችን ከሚሰብኩን ባዶ ስብከት እና ከሚወረውሩልን (ከሚጥሉልን) እጅግ አዋራጅ ፍርፋሪ ጋር መለማመድ የጀመርን እለት ነው።
  እኩይ ገዥዎቻችን ያስታቀፉን አጠቃላይ ማለትም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ፣ ሞራላዊ፣ ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ ቀውስ ህዝብን አስቆጥቶ ልክ ለሌለው መንበረ ሥልጣናቸው አደጋ እንዳያስከትል ለማድረግ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የማይፈፅሙት ሸፍጥና ሴራ የለም። ለዚህም ነው ለሥልጣናቸው መቀጠል ጠቃሚ ሆኖ እስካገኙት ድረስ በቁጥጥራቸው ወይም በተፅዕኗቸው ሥር ያላደረጉትና የማያደርጉት መንግሥታዊ ተቋም ፈልጎ ማግኘት የማይታሰበው። በእውነት ስለእውነት ከተነጋገርን ከዚህ እኩይ የገዥዎች አስቀያሚ ተፅግኖ ነፃ የሆነ መንግሥታዊ ያልሆነ በተለይ አገር በቀል ድርጅትም (NGO) ፈልጎ ማግኘትም በእጅጉ አስቸጋሪ ነው።
  አንድን አገር አገር የሚያሰኙት ጉዳዮች ጅኦግራፊያዊ ግዛት፣ ሥርዓተ መንግሥት እና ህዝብ (delimited and demarcated territory፣ organized and functional government ፣ and population) ናቸው ። ከእነዚህ መካከል ደግሞ ዶ/ር በእድሉ ዋቅጀራ (አሁን ያለውን እምነትና አቋም አላውቅም) “አገር ማለት ሰው” እንዳለው ሁሉ ዋነኛው አካል (part) ሰው (ህዝብ) ነው። የወሳኙ አካል (የህዝቡ) ልኡላዊ የሥልጣን ባለቤትነት እና የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሚጨፈለቅበት ግዙፍና መሪር እውነታ ውስጥ የገንዛ እራስን ልክ የሌለው ቀውስ (ውድቀት) ምክንያትነትን ጠቅልሎ በውጭ ሃይሎች ላይ በመደፍደፍ በየአደባባዩና በየመሥሪያ ቤቱ እየዞሩ “እጃችሁን አንሱ (hands off!)” እያሉ መፎከር ከቶ የትም አያደርስም። የእራስን አስቀያሚና አዋራጅ የፖለቲካ አስተሳሰብና አካሄድ በቅጡ እያደረጉ የውጭ ሃይሎች የሚያካሂዱትን አላስፈላጊ ወይም ጤናማ ያልሆነ ጣልቃ ገብነት በሰለጠነና ውጤት ማምጣት በሚቻልበት አኳኋን መሞገትና መቃወም ትክክል ነው።
  “አገራችን በገንዛ እራሳችን እኩያን ገዥዎች ምስቅልቅሏ ቢወጣ፣ ለአካባቢው ሥጋት ብትሆን እና የእኛም መከራና ውርደት ቢራዘም ምን አገባችሁ” የሚል አይነት እጅግ የወረደና አዋራጅ የፖለቲካ አስተሳሰብና አካሄድ ግን ፈፅሞ ትክክል ሊሆን አይችልም። መነሻው ከእኛውና ከእኛው ጓዳ የሆነውን የእኛነታችን ቀውስ ተገቢና ወቅታዊ በሆነ እርምጃ ለማቃለልና ብሎም ለማስወገድ የሚያስችል እልህ አስጨራሽ የጋራ ትግል ከማድረግ ጎን ለጎን የውጭ ሃይሎችን አላስፈላጊ ወይም ጤናማ ያልሆነ ጫና (ጣልቃ ገብነት) ከመቋቋም ይልቅ የአገር ልኡላዊነትን ከገር አፍራሽ ገዥ ቡድኖችና ከአድርባይ ፖለቲከኞች ጋር እያቀላቀሉ በየአደባባዩ እግዚኦ ማለት የትም አያደርስም።
  አዎ! የግዛትና ልኡላዊነት እና የህዝብ የስብአዊና የዴሞክራሲዊ መብቶች (ልኡላዊነት) በአስተማማኝ ሁኔታ እውን እንዲሆን የሚያስችል ጉልህ ሥራ ባልሠራንበት መሪር ሃቅ ውስጥ የየረሳቸውን ብሔራዊ ጥቅም እያሰሉ የሚንቀሳቀሱ የውጭ መንግሥታትና ድርጅቶች በር ላይ እየቆምን እግዚኦ የማለቱ ፖለቲካ የት ያደርሰናል? ብለን ለመጠይቅ ጊዜው አልፏል አይባልምና አሁንም ይህን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ይኖርብናል።
  ከባዱንና እጅግ ጨርሶ ጊዜ የማይሰጠውን የገንዛ እራሳችንን (የአገራችንን) የቤት ሥራ አጥብቀን እየሸሸን ገዥዎች የሚሰጡንን የቤት ሥራ እንደወረደ በመቀበል በየአገራቱ አደባባዮችና በየመንግሥታቱ መሥሪያ ቤቶች የማስተጋባቱ የፖለቲካ ልማድ ለሩብ ምእተ ዓመት በህወሃተ የበላይነት ሥር ከቆየው እና አሁን ደግሞ በተረኛ የኦህዴድ/አሮሙማ የበላይነት ሥር ከሚገኘው የበሰበሰና የከረፋ ኢህአዴጋዊ ሥርዓት ፈፅሞ ነፃ አያወጣንም።
  አዎ! የውጭ መንግሥታትና ሌሎች ድርጅቶች ከአላስፈላጊ ወይም ገንቢነት ከሌለው ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠቡ ማሳሰብና መቃወም እንደ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ነገሮችን ከምር እንደሚከታተልና ሚዛናዊ ህሊና እንዳለው ማነኛውም ሰው ትክክል ነው። ሸፍጠኛ፣ ሴረኛ ፣ ፈሪና ጨካኝ ገዥ ቡድኖችን በጋራ ትግል አስገድዶ ወደ እውነተኛው ዴሞክራሲያዊ ፍኖት ከማስገባት ይልቅ የእነርሱው ሰላባ በመሆን የሚደረግ ተቃውሞና ውግዘት ግን ከፖለቲካም ይሁን ከሞራል አንፃር ጨርሶ ትርጉም አይሰጥም።
  ጣልቃ ገቡ የምንላቸው አካላት “ያገኛችሁትን መልካም የለውጥ አጋጣሚ በአግባቡ ባለጠቀማችሁ በአስከፊ የመገዳደልና የሰብአዊ ቀውስ ፖለቲካ ውስጥ የዘፈቋችሁን ገዥ ቡድኖችና ሌሎች የፖለቲካ ሃይሎችን አደብ ማስገዛት አልተቻላችሁም። ከህዝባችሁ ሰብአዊ ቀውስ አልፋችሁ ለቀጠናው ያለመረጋጋት አደጋ ስትሆኑና ብሔራዊ ጥቅማችን ሥጋት ላይ ስትጥሉ እንዴት ዝም እንበል? ብለው ቢጠይቁን “የጠላነውና የተቃወምነው ህወሃትን እንጅ ህወሃት ሠራሹን ሥርዓት ያስቀጠለውን አብይ አህመድንና ብልፅግና አይደለም” ልንል ነው እንዴ? ይህ እጅና እግሩ የማይለይ የፖለቲካ አስተሳሰብና አካሄድ የእኛነታችን ቀውስ በግልፅ ካላሳየን እና ተገቢና ወቅታዊ የእርምት እርምጃ እንድንወስድ ካላስገደደን መቸና እና እንዴት ከተዘፈቅንበት የእኛነት ቀውስ እንደምንወጣ ለማሰብ ወይም ለመተንበይ በእጅጉ ያስቸግራል።
  ይህ እጅግ ወደ ኋላ የቀረና ጎጅ የፖለቲካ አስተሰብና አካሄድ እኩያን ገዥዎቻችን በሃይማኖታዊ ተቋማት እና በፖለቲካ ወይም በመንግሥት መካከል መኖር ያለበትን የግንኙነት መስመር ጥሰው ሃይማኖታዊ እምነትን ሳይቀር የግፍ ፖለቲካ ጨዋታቸው አካል ሲያደርጉት ለምንና እንዴት ብለን በግልፅና በቀጥታ ከመሞገት (ከመቃወም) ይልቅ ከሁኔታዎች ጋር ልክ በሌለው የስሜታዊነት ፈረስ የመክነክፉ ልማድ መታረም ይኖርበታል።
  አዎ! የጭቆና (የግፍ) አገዛዝን እና ልክ የሌለው የኑሮ ጉስቁልናን ሰንካላ ምድራዊ (ዓለማዊ) ሰበብ ከመደርደር አልፈን በዚሁ ክፉ የቀውስ አዙሪት ውስጥ እንድንኖር የእውነተኛው አምላክ (ፈጣሪ) ፈቃድ የሆነ ይመስል የተግባር አልባ እግዚኦታን እግዚኦ ከማለት ክፉ ልማድ ለመላቀቅ እልህ አስጨራሽ ሥራ ሠርቶ መገኘትን የግድ ይለናል።
  ቀጥተኛና ግልፅ አስተያየት በተሰነዘረ ቁጥር በአግባቡ ከመረዳትና በሰለጠነ አስተሳሰብ በመጋፈጥ ዘመናትን ካስቆጠረው እና አሁንም የስያሜ፣ የቅርፅና የሥልጣን ሽሚያ ተረኝነት እንጅ ዴሞክራሲያዊ ይዘት ጨርሶ የሌለውን የሸፍጥና የሴራ ፖለቲካ ያስቀጠለውን የኦህዴድ/ብልፅግና ገዥ ቡድን “ጥሩ ሲሠራ መደገፍ እና ጥሩ ሳይሠራ ደግሞ መቃወም” በሚል እጅግ እንጭጭና ሰንካላ የትንታኔ ድሪቶ በመደረት እውነተኛ ለውጥ እውን ይሆናል ብሎ መጠበቅ የፖለቲካ እኛነታችንን ቀውስ ከማባባስ ያለፈ ፋይዳ የለውም። የቀድሞ አለቃቸውን ከቤተ መንግሥት አስወጥተው አስከፊ የጎሳ/የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓቱን ግን ያስቀጠሉ ኦህዴድ/ብልፅግናዊያንን “መደገፍና መቃወም” በሚል የአድርባይነት (የልክስክስነት) የፖለቲካ አስተሳሰብ ከገባንበት አጠቃላይና አስከፊ ቀውስ አንወጣም።
  ዘመናትን ያስቆጠረውና አሁንም በተረኛ ገዥ ቡድኖች የቀጠለው ሥርዓተ ኢህአዴግ ያስከተለውና እያስከተለ ያለው መከራና ውርደት ያሳዝናል እንጅ ከቶ አያስገርምም ። የእኩያን ህዋሃት ፖለቲከኞች ፍፁም እብደት የተሞላበት የፖለቲካ አስተሳሰብና የሞራል ዝቅጠትም እንዲሁ ። “ለምን አይገርምም?” የሚል ጥያቄ ቢነሳ መልሱ ምርምር የሚጠይቅ አይደለም። እኩያን ገዥዎቻችንና ፖለቲከኞቻችን ሲፈልጉ በባዶ ዲስኩራቸው እያዘናጉ (እያታለሉ)፣ ሲያስፈልጋቸው ድንቁርናን (ignorance) እንደ መሣሪያ እየተጠቀሙ ፣ ሲያሻቸው ደግሞ እርስ በርስ እያጋጩና እያጋደሉ ፣ ሲሳካላቸው ደግሞ እንደ ደመ ነፍስ እንስሳ ከሆዱ መሙላት በላይ የማያስበውን በተለይ ምሁር ተብየውን በሆዱ እየገዙ ፣ እና ይህ ሁሉ በቂ ሆኖ አልታያቸው ሲል ደግሞ “የእኔን ያየህ ተቀጣ” ሰይፋቸውን እየመዘዙ የመከራና የውርደት ሥርዓታቸውን እንድንለማመደው ካደረጉን አያሌ ዘመን አስቆጥረናልና።
  ከሦስት አሥርተ ዓመታት በላይ ተዘፍቀን የኖርንበትንና አሁንም እጅግ በሚያሳዝን አኳኋን የተዘፈቅንበትን አጠቃላይ ማለትም ፖለሊካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ፣ ሞራላዊ እና መንፈሳዊ (spiritual) ቀውስ ፈፅሞ ባናስወግደውም በአንፃራዊነት በመግታት ወደ እውነተኛ የነፃነትና የፍትህ ሥርዓት ለመሸጋገር እንዳንችል ካደረጉን ምክንያቶች አንዱ ስለ ቀውስ መሠረታዊ ምክንያት እና ስለመፍትሄው ያለን አስተሳሰብ እራሱ በቀውስ የተሞላ በመሆኑ ነው ።
  በገደብ የለሽ ሥልጣንና የአገር (የህዝብ) ሃብት ዝርፊያ ህሊናቸው ጨርሶ የደነቆረ ገዥ ቡድኖች በእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አግባብ ከቀውስ እንዲያወጡን መለማመን (መማፀን) እራሱ በእጅጉ የተቃወሰ የፖለቲካ አስተሰብ ነውና ጨርሶ ሳይጨልም ወደ ትክክለኛው ፍኖተ ዴሞክራሲና ፍኖተ ሰላም መሰባሰብ የግድ ነው።
  ስለ አስከፊው የእኛነት ቀውስ አምርረንና አብዝተን እየተረክን ወደ መፍትሄው ስንመጣ ግን የቀውሱ መሠረታዊ ምክንያት (root cause) የሆነውን የፖለቲካ አስተሳሰብና ሥርዓተ መንግሥት ትተን ባስከተለው፣ እያስከተለ ባለውና ሊያስከትል በሚችለው የህመም ስቃይ (painful symptom) ላይ ተቸክለን ጊዜን፣ እውቀትንና ሃብትን ማባከን በእጅጉ ሊያሳስበን ይገባል ።
  ከሦስት ዓመታት በላይ ንፁሃን በገንዛ አገራቸውና ቀያቸው የቁም ስቃይና የአሰቃቂ ግድያ ሰለባዎች ሲሆኑ እንኳን ተገቢውን የመከላከልና ፈጥኖ የመድረስ እርምጃ ሊወስድ የገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ለሦስት ቀናት ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ለማድረግ እና በተሊቪዚዮን መስኮት ቀርቦ ሃዘኑን ለመግለፅ ቢያንስ የሞራል ግዴታውን ያልተወጣውን ጠቅላይ ሚኒስትር አሁን ከሰሞኑ ወደ ጦር ግንባር በመዝለቅ የተነሳውን ፍቶ ግራፍና የተቀረፀውን ቪዲዮ በየሚዲያው ቦግና ብልጭ እያደረጉ ያዙንና ልቀቁን የማለቱ የፖለቲካ ጨዋታ ከኖርንበትና ካለንበት የእኛነት ቀውስ ፈፅሞ አያወጣንም ።
  ትግራይን ለእኩያን ህወሃቶች ማስረከብ ብቻ ሳይሆን ከኦነግ ጋር ጥምረት ፈጥረው ሰሜን ሸዋ ድረስ በመዝለቅ መግለፅ የሚያስቸግር ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት እንዲደርሱ ካስደረገ በኋላ ቤተ መንግሥቱ ሥጋት ላይ መውደቁ ሲሰማው ጦር ግንባር አካባቢ በመዝለቅ በርከት ያሉ ቀናትን አሳልፎ ሲመለስ በተለመደው የሰላ አንደበቱ “ድል በድል ሆነናልና ደስ ይበላችሁ” ሲል ለምንና እዴት? ብለን ሳንጠይቅ ጮቤ የመርገጣችን ነገር የሚነግረን ከመሪሩ ተሞክሯችን እንዳልተማርንና ከገባንበት ቀውስ ለመውጣትም በእጅጉ ፈታኝ እንደሆነብንና እንደሚሆንብን ነው።
  ይህ ክፉ የእኛነት ቀውስ ግልፅና ግልፅ የሆነው ደግሞ “ሸፍጠኛና ሴረኛ ህወሃት/ኢህአዴግ ወለድ ፖለቲከኞች ህወሃት ሠራሹንና ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉበትን የጎሳ/የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት እውን ይለውጡታል ወይንስ ለማታለያነት ባሰለጠኑት አንደበታቸው እያታለሉን ያስቀጥሉታል?” ብሎ ለመጠየቅ የሚያስችል ጊዜ ሳንወስድ “የዘመናችን ሙሴዎች፣ የኢትዮጵያ ትንሳኤ መልእክተኞች፣ ከሰማየ ሰማያት የተላኩልን ነፃ አውጭዎች፣ ወዘተ” እያልን እራሳችንን አዋርደን ለአዋራጆቻችን አሳልፈነ የሰጠን እለት ነው።
  ለዚህ ነው በአስከፊው ቀውስ የተመታነው እንደ ግለሰብ ወይም እንደ የፖለተካ ቡድን ወይም እንደ አንድና ሁለት ተቋም ፣ ወዘተ ሳይሆን እንደ ማህበረሰብ ወይም እንደ ህዝብ ወይም እንደ ትውልድ ነው ብሎ በግልፅና በቀጥታ መናገር ትክክል የሚሆነው።
  ለሩብ መቶ ክፍለ ዘመን አስከፊ የጎሳ/የቋንቋ አጥንት ስሌት የፖለቲካ ሥርዓታቸውን ህገ መንግሥታዊ በማድረግ መከረኛውን ህዝብ የመከራና የውርደት ህይወት (ህይወት ከተባለ) ሲያስቆጥሩት የኖሩት ኢህአዴጋዊያን ከሦስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ “ተራው የእኛ ነው እና የለም ተራ የሚባል ነገር የለም” በሚሉ ሁለት እኩያን አንጃዎች ተከፍለው እና የየራሳቸውን ግብረበላዎች አሰልፈው የቀውሱን ስፋትና ጥልቀት ይበልጥ አስከፊ አድርገውት ቀጥለዋል ።
  በቁጥር ቀላል ያልሆነውና ህዝብን አንቅቶና አደራጅቶ ለእውአተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማብቃት የሚጠበቅበት የተማረው የህብረተሰብ ክፍልም ከመሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለውጥ መርህ ፣ዓላማና ግብ በአስከፊ አኳኋን በመንሸራተት ሸፍጠኛና ሴረኛ ኢህአዴጋዊያንን (ብልፅግናዊያንን) “አገር ይፈርሳል” በሚል የፍርሃት ቆፈን ተቀፍድዶ ከሸፍጥ፣ ከሴራ፣ ከግልና ከቡድን የሥልጣን ጥማት ልክፍተኛ ገዥዎች ጋር የፖለቲካ አመንዛራነት መደነሱን ተያይዞታል።
  አዎ! ለዘመናት የመጣንበትና አሁንም የምንገኝበት እጅግ አስከፊ የእኛነታችን ቀውስ ጠልፎ ያበላሸው ወገኔ ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ብቻ አይደለም በእጅጉ የሚያሳስበው። ያልደረሰበትና ያላበላሸው የሙያና ሌላም መስክ አለመኖሩም ነው በእጅጉ የሚያስደነግጠው።
  ከእኔ ወዲያ ለዴሞክራሲና ለሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ላሳር ነው ሲለን የነበረው ምሁር፣ አርቲስት፣ አክቲቪስት ፣ ባለሃብት፣ የሃይማኖት መሪና ሰባኪ ፣ ጋዜጠኛ ፣ ወዘተ ሁሉ ምን? ለምን? እንዴት? ከየት ወደ የት? መቼ? በነማንና ለነማን? ከዚያስ? ብሎ ሳይጠይቅ በሸፈጠኛና ሴረኛ ገዥ ቡድኖች ወጥመድ እየተጠለፈ ሲወድቅ መስማትና ማየት የሚነግረን የውድቀታችን አስከፊነት እንጅ ከውድቀት መውጣታችን አይደለም።
  ሁለቱንም (ህወሃትን እና ኦህዴድ/ብልፅግናን) አደብ እንዲገዙ እና ወደ ሰለጠነና ሁሉን አሳታፊ ወደ ሆነ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲመለሱ የሚያስገድድ የጋራ ርብርብ ከማድረግ ይልቅ “አብይንና አስተዳሩን መተቸት ከነውርነት አልፎ አገር ያፈርሳል” የሚለው ወገን በበዛበት የፖለቲካ እውነታ ውስጥ እንኳን ዴሞክራሲያዊት ህልውናዋ ቀጣይ የሚሆን አገር መጠበቅ በእጅጉ ያስቸግራል። ይህ በፖለቲካ አስተሳሰብ ድህነት ወይም በአድርባይነት ክፉ ልክፍት ወይም በተለጣፊነት ወራዳነት ወይም በሞራል ጎስቋላነት የተበከለ እኛነታችን ነገ ሳይሆን ዛሬውኑ ተገቢው እርማት ካልተደረገበት በስተቀር የሚያስከትለው ውጤት አገር የመፈራረስ ብቻ ሳይሆን በመንደር መንግሥታት መካከል በሚደረግ ሽኩቻ ወደ ባሰ ፍርስራሽነት መለወጥ ነው የሚሆነው።
  እርግጥ ነው ዘመናትን ላስቆጠረውና አሁንም እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ የዚህ ትውልድ ዋነኛ መታወቂያ ሆኖ ለቀጠለው የመግደልና የመገዳደል ፣ የርሃብ ፣ የጥማት ፣ የበሽታ እና የድንቁርና ቀውስ ዋነኛው ምክንያትና ተጠያቂ የፖለቲካ ሥርዓት መበስበስና መከርፋት እንጅ ህዝብ ወይም ማህበረሰብ አይደለም። ሆኖ አያውቅም ። ሳይማር ያስተማራቸው ልጆቹ የአድርባይነት ወይም በፍርሃት ልክፍት ሰለባዎች የሆኑበት ህዝብ የባለጌና ጨካኝ ገዥዎች ቀንበርን ሰብሮ ነፃነትንና ፍትህን ለመጎናፀፍ ከቶ አይቻለውም
  በአንድ በኩል “ከቤተ መንግሥት ፖለቲካ ለምን ተወገድን” በሚሉ (ህወሃቶች) እና በሌላ በኩል ደግሞ “ተራው የእኛ ነውና አትረብሹን” በሚሉ ተረኛ የኦሮሙማ ፖለቲከኞች መካከል በተነሳ የሥልጣን ሽኩ ቻ የተለኮሰውና አገርን (ህዝብን) መግለፅ በሚያስቸግር አስከፊ ሁኔታ ውስጥ የዘፈቀው የእርስ በርስ ጦርነት ጥንተ መነሻው ጨርሶ ያልተለወጠው የኢህአዴጋዊያን ሥርዓተ ፖለቲካ መሆኑን የሚጠራጠር ነፃነትና ፍትህ ፈላጊ የአገሬ ሰው የሚኖር አይመስለኝም ።
  የገንዛ ራችንን ግዙፍና መሪር እውነታ በመሸሽ እዚህ ግባ የማይባል የሰበብ ድሪቶ የመደረት ክፉ አባዜ ሰለባዎች በመሆናችን ለመቀበል እየተቸገርን ነው እንጅ ለዘመናት የመጣንበትና አሁንም ይበልጥ አስከፊ በሆነ ሁኔታ የቀጠለው ግዙፉና መሪሩ የቀውስ አዙሪታችን መሠረታዊ ምክንያት ሊያጋጥም ይችላል የሚባል አስተዳደራዊ ድክመት (ስህተት) ወይም ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ክስተት ሳይሆን የለየለት የፖለቲካ ሥርዓት መበስበስና መከርፋት ነው።
  ዴሞክራሲያዊ በሆኑ እና ዴሞክራሲያዊ ባይሆኑም በአንፃራዊነት እይታ የሃላፊነትና የተጠያቂነት ስሜት ባለባቸው የፖለቲካ ሥርዓቶች ውስጥ የሚከሰት ቀውስ ለጊዜውም ቢሆን ከፍተኛ አሉታዊ ጉዳት ሊያስከትል ቢችልም ከቁጥጥር ውጭ በመሆን አገርን (ህዝብን) በመኖርና ባለመኖር ሁኔታ ውስጥ አይጥልም ። በሁሉም የህይወት ዘርፎች ላይ የእራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው ቢችልም እጅግ አስከፊ የሆነ አጠቃላይ ማለትም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊ፣ ሥነ ምግባራዊ ፣ ሞራላዊ እና መንፈሳዊ ቀውስን ግን አያስከትልም።
  በአገራችን መሬት ላይ የሆነውና እየሆነ ያለው ግን ከዚህ ፍፁም ተቃራኒው ነው። ለዘመናት የመጣንበት አስከፊ የጎሳ/የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት ወላጆችና ውላጆች (ህወሃት/ ኦህዴድ/ ብልፅግና) “በበላይነት የመግዛቱ ተራ ይገባናል እና የለም የእኛ የበላይነት አይደፈርም” በሚል የሥልጣን ሽሚያ ምክንያት የመግደል፣ የመጋደልና የማገዳደል ፖለቲካውን እጅግ ፈጣንና አስከፊ በሆነ ሁኔታ ተያይዘውታል።
  ግልፅና ቀጥተኛ አስተያየቶች በተሰነዘሩ ቁጥር የድንጋጤ ወይም የፍርሃት ስሜታቸውን ለመቆጣጠር የሚሳናቸው ወገኖች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ በሚገባ እገነዘባለሁ።
  የዚህ ክፉ ልማድ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ የገንዛ ራስን ግዙፉና መሪር እውነት በአግባቡ ከመጋፈጥ ይልቅ የሰበብ ድሪቶ እየደረቱ ራስንን የመሸንገል (የማታለል) ክፉ ልማድ (አባዜ) ነው ። እየተፈራረቁ መንበረ ሥልጣኑን ለሚቆጣጠሩ ባለጌና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የመከራውና የውርደቱ ዘመን እንዲራዘም ካደረጉት ዋነኛ ምክንያቶችም አንዱ ይኸው የፖለቲካ አስተሳሰብ ድህነት እና የሞራል ጉስቁልና መሆኑን ለመረዳት ከቶ የተለየ ምርምር ወይም እውቀት አይጠይቅም። በእያንዳንዱ መከረኛ ወገን ጓዳ ውስጥ በግልፅና በቀጥታ የሚታይ መሪር ሃቅ ነውና።
  በእውን ለመማርና አገሩን ለተሻለ ሥርዓተ ፖለቲካ ለማብቃት ከምር ለሚፈልግ ፖለቲከኛ ወይም ገዥ ቡድን የአገራችን የፖለቲካ ታሪክ ትልቅና ወደር የሌለው የተሞክሮ ትምህርት ቤት በሆነው ነበር ።
  የአገሬ ህዝብ አለመታደል ወይም የፈጣሪ ቁጣ ሆኖበት ሳይሆን እነዚህን ሸፍጠኛ፣ ሴረኛና ጨካኝ የጎሳ/የጎጥ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞችን በፅኑ መርህና የተግባር ውሎ ድል ነስቶ እውነተኛ የነፃነትና የፍትህ ሥርዓትን እውን ለማድረግ የሚያግዘው የፖለቲካ ሃይል አምጦ መውለድና ማጎልበት ባለመቻሉ እያደር አስከፊ እየሆነ ከሚሄድ የመከራና የውርደት ቀውስ አዙሪት ሰብሮ ለመውጣት አልሆነለትም።
  ከመከላከያ ሃይሉና ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት ሃይሎች አልፎ ሲቪል ዜጎችን እጅግ ስሜታዊ በሆነ የአገር አድን ጥሪ ስም በጅምላ እያጋደሉና የቂም በቀል መርዝ እየጋቱ “ስለ እምዬ ኢትዮጵያ ሲባል እንሰዋለን” የሚሉንን ገዥዎቻችንንና ፖለቲከኞቻችንን ለምን? እንዴት? እስከየትና እስከመቼ? መሠረታዊው ግቡስ ምድነው? በቤኒሻንጉል ፣ በኦሮሚያ እና በቤተ መንግሥቱ አቅራቢያ (አዲስ አበባና አካባቢዋ) ምን ተደረገ? ምንስ እየተደረገ ነው? ብሎ ለመጠየቅ የሚያስችል ቢያንስ የሞራል አቅም ከማጣት የባሰ የእኛነት ቀውስ የለም።
  ከእራስ መከራና ውርደት ተምሮ የተሻለ ሥራ ሠርቶ ያለመገኘት እጅግ አሳፋሪ የፖለቲካ አስተሳሰባብና አካሄድ በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም ይበልጥ አስከፊ በሆነ ሁኔታ የመቀጠሉ ግዙፍና መሪር ሃቅ ህሊናችንን ከምር ከማሳስብ ይልቅ ይበልጥ እየተለማመድነው የመምጣታችን አደጋ የእኛነታችን ቀውስ ማሳያ መሆኑን ከምር የተረዳን አይመስልም።
  እራሱን ወደ የህገ መንግሥታዊ የዘውድ ሥርዓት ተሃድሶ (reform of constitutional monarchy) ለማሸጋገር ፈፅሞ ፈቃደኛና ዝግጁ ባልነበረው ፍፁማዊ የዘውድ አገዛዝ (absolute monarchy) ምክንያት በወቅቱ ከነበሩት ሁለት የዓለም ርእዮተ ዓለም ካምፖች አንዱን (ሶሻሊዝምን/ኮምኒዝምን) መታገያና ማታገያ በማድረግ ከአምባገነንና እጅግ ጨካኝ ወታደራዊ አገዛዝ ጋር ሲተናነቅ ካለቀው እና ከተላለቀው ትውልድ ታሪክ በጤናማ ህሊና ለሚመራ የገዥ ቡድንና የተቃውሞ ፖለቲካ አራማጅ ሁሉ ከበቂ በላይ ትምህርት ሰጭ በሆነ ነበር።
  በ1983 ሥልጣነ መንበሩ ላይ የተሰየሙት ገዥ ቡድኖች ካለፈው ከተሞክሮ ተምረው የተሻለ ሥርዓተ ፖለቲካ እውን ከማድረግ ይልቅ ኋላ ቀሩንና አደገኛውን የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካን ይበልጥ ከፋፍሎና አደንቁሮ ለመግዛትና ለመዝረፍ ያመቻቸው ዘንድ ህገ መንግሥታዊ አደርገውት አረፉ ። ለዚህ ያግዛቸው ዘንድ ያንን ትውልድ ብቻ ሳይሆን ከእነ ችግሮቻቸውም ቢሆን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያዊነት እሴቶችን በዋጋ ሊተመን በማይችል መስዋእትነት ያቆዩትን ትውልዶች ሁሉ ፣ በተለይም ደግሞ ነፍጠኛ በሚል እጅግ ደምሳሳና አደገኛ ስያሜ የሚጠሩትን የአማራ ማህበረሰብ ዋነኛና ብቸኛ ተጠያቂ አደረጉት።
  ታዳጊ ትውልዱንም በፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን በሥርዓተ ትምህርት ቀርፀው ይህንኑ መርዛቸውን ጋቱት ። በየመድረኩና በየትምህርት ተቋሙ” እኛና እነርሱ ወይም እኛና እናንተ” በሚል እስከ መጋደል እንዲደርስ አደረጉት። ንፁሃን ወገኖቹ በሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች እና ዓላማቸውን በሚጋሩ እኩያን ቡድኖች የቁም ሰቆቃ ፣ የግድያ እና የመፈናቀል ሰለባዎች ሲሆኑ እንደ አንድ የአገር ዜጋ ወይም ሰው ለምንና እንዴት ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ የየትኛው ጎሳና መንደር ሰዎች ናቸው በሚል እራሱን ከደመ ነፍስ እንስሳት በታች ዝቅ እንዲያደርግ አደረጉት ። በዚያው ሥርዓት ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉት የዛሬዎቹ ተረኛ ገዥ ቡድኖችም ከአስከፊው ተሞክሯችው ተምረው የተሻለ ሥራ አለመሥራታቸው አልበቃ ብሎ አገሪቱን የበለጠ ምድረ ሲኦል አድርገዋት አረፉ። የቀድሞ ጌቶቻቸውን ከበላያቸው ላይ በማስወገድ ሥርዓቱን ግን ይበልጥ አስከፊ በሆነ ሁኔታ እያስቀጠሉ “ከእኛ ወዲያ የለውጥ ሐዋርያነት ላሳር ነው” በሚል በመከረኛው ህዝብ የማገናዘብ አቅም ላይ ተሳለቁ ።
  የእራሳችንን አሳፋሪ ድክመት (ውድቀት) በአሸናፊነት መንፈስና የተግባር ተጋድሎ ማሸነፍና በድል አድራጊነት ወደ ፊት መራመድ ሲያቅተን ከረቂቅ አእምሮና ከሙሉ አካል ጋር ለትልቅ ዓላማ የፈጠረንን ፈጣሪ ሳይቀር በምክንያትነት እየጠቅስን ከገባንበት አስከፊ የእኛነት ቀውስ ለመውጣት ከቶ የሚቻለን አይሆነም።
  ለዚህ ነው አስከፊው የግፍ አገዛዝ ሥርዓት ታሪካችን መለወጥ አለበት በሚል ፀንተው በመቆማቸው የግፍ እሥር ሰለባ የሆኑትን የዴሞክራሲ አርበኞች ከመታደግ ይልቅ “በአገር ይፈርሳል” ስም ከባለጌና ጨካኝ ተረኛ ገዥዎቻቻችን እግሮች ሥር በመንደፋደፍ እራሳችንን ያዋረድነው ። ታዲያ ይህ አይነት እጅግ አስከፊና አሳፋሪ የፖልቲካ አስተሳሰብና አካሄድ ለእኛነት ቀውስ (ውድቀት) አይነተኛ ምክንያቶች አንዱ የመሆኑ እውነታ ምን ያስገርማል?
  እናም ለዘመናት የዘለቀውና አሁን ደግሞ እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ የቀጠለው የጎሳ/የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች ሥርዓት ሁሉን አሳታፊና እውነተኛ በሆነ የዴሞክራሲያዊ ሽግግር እንደ ሥርዓት እስካልተወገደ ድረስ እንኳን ዴሞክራሲያዊት የሆነች የድህነትንና የጭቆናን አስከፊ ህመም እየታመሙ የሚኖሩባት አገርን ማስቀጠል የሚቻል አይሆንም ።
  ከገንዛ እራስ መሪር እውነት መሸሽ ከቶ አይቻልምና ብቸኛው ምርጫ የአጠቃላይና የአስከፊ ቀውስ ዋነኛ ምክንያት (root cause) የሆነውን ህወሃት ሠራሽ የፖለቲካ አስተሳሰብና መዋቅራዊ ሥርዓት እንደ ሥርዓት አስወግዶ ሁሉን አሳታፊ በሆነ ዴሞክራሲያዊ የሽግግር አግባብ ለዜጎቿ ሁሉ የምትመች ዴሞክራሲያዊት አገር እውን ማድረግ ነው። ይህ ካልሆነ ወይ ለዘመናት የመጣንበትንና አሁንም የምንገኝበትን የመከራና የውርደት አገዛዝ ቀንበር ተሸክሞ መቀጠል ፣ ወይም ደግሞ በጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች የጭካኔና የዘረፋ አገዛዝ ሥር የሚወድቁ ትንንሽ የመንደር መንግሥታትን መሥርቶ በማያቋርጥ የመግደልና የመገዳደል የፖለቲካ አዙሪት ውስጥ መኖር ነው (መኖር ከተባለ) ።
  ከዘመን ጠገቡና ልክ ከሌለው የእኛነት ቀውስ በመማር ክፉውን አሸንፈን በጎውን (እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን) እውን እንድናደርግ እየተመኘሁ አበቃሁ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.