December 20, 2021
11 mins read

ሰሜን ወሎን ወደ“ደቡብ ትግራይ” ደቡብ ወሎን ደግሞ ወደ “ሰሜን ኦርምያ” የማጠቃለሉ ቅዠት (እውነቱ ቢሆን)

Fanoፋኖ ብዙ ጠላት እንዳለው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ለዚህም ነው በደሴ የተፈጸመን የወሎ ህብረትን ዘረፋ ወደ ፋኖ ላማላከክ የተሞከረው፡፡ ፍኖ የ46 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ አለው፡፤ ጠላቶቹ አማራን መክተው በፊቱ ሊቆሙ አይችሉም፡፤ ዳሩ ግን ምን ያደርጋል አማራው በሚፈለገውና በሚገባው ልክ፣ ፍጥነትና ደረጃ በሁሉም ዘርፎች ገና በበቂ አልተደራጀም፡፡ ለ30ና ለ40 አመታት በወያኔ ከፍተኛ ደባና ተንኮል ተሰርቶበታል፡፡ የዘር ማጥፋት ተፈጽሞበታል፡፤ ደህይቶና ኋላቀር ሆኖ ተቀብሮ ኖሯል፡፡ አሁን ደግሞ በተረኛውና ምናልባትም ከወያኔ በበለጠ አማራን በሚያሰጋው በኦሮሙማ የረቀቀ ሴራና አማራን አጠላልፎና ከፋፍሎ የመጣል አደገኛ ቁማር እየተሰራበት ይገኛል፡፡፡የሆድ አደሮቹ አማራወች የብልጽግና ፓርቲ መሪወች የሆኑት እነደመቀ መኮንንም በሁለት እግሩ መቆም ያልቻለውን ባለ አንድ እግሩን የኦሮሙማ መንግስት ያንኑ አንድ እግሩን በትከሻቸው ተሽክመው አንዳልጦት እስክሚከሰከስ ድረስ እሹሩሩ እያሉት ይገኛሉ፡፡በተጓዳኝም እነዚሁ ሆዳሞች የአማራ አለኝታ የሆነውን ፋኖን እንዳይደራጅ የቻሉትን አፈና፣ እቀባና ክልከላ <እስካስኬዳቸው ድረስ> ማድረጋቸውን ቀጥለውበታል፡፡

አማራው በትክክልና በሀቅ ቢቆጠር ብዛቱ ከ46 ሚሊዮንም ይበልጣል፡፤ይህንን እውነታ ወያኔና ኦነግ ዱሮ ገና ሳይጣሉ በፊት በጋራ በአማራ ላይ ቆምረው የሰሩት ቁማር መሆኑን የወደቀው የወያኔ መንግስትም ተረኛው የኦሮሙማ መንግስትም ሁለቱም ያውቁታል፡፤ ዘግይቶም ቢሆን መላው የአማራ ህዝብም ይህንን የተሰራበትን ሸፍጥና ደባ ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፤ወደፊት ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ በሀቅ ሲደረግ ሁሉም ህዝብ ልኩንና አቅሙን ብዛቱንና ማንነቱን ለይቶ ያውቃል፡፤ ያኔ እውነቱ ፈጥጦና አግጥጦ ሲወጣ አማራው ለአመታት በሸፍጥ የተሰራበት የበጀት ድልድልና የድምጽ አሰጣጥ ቁማሮች እንዴት ይቆመርባቸው እንደነበረ ገሀድ ይወጣሉ፡፡

የአሜሪካ ዜግንቱን ስለመመለሱ በቂ ማረጋገጫ ያላቀረበውና ወደር የለሹ እብሪተኛ ጃዋር መሀመድ “ግማሽ መንግስት እኔ ነኝ” ብሎ በይፋ ከማወጅ አልፎ ሁሉንም አይነት ግፍና ሰቆቃ በድፍን ኦሮሚያ ባለው ከ7 እስከ 8 ሚሊዮን በሚቆጠረው የአማራ ህዝብ ላይ ፈጽሟልም አስፈጽሟልም፡፡ በተረኝነትና የኬኛ ፖለቲካ ያበጠው የኦሮሙማ ቡድን እንደሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ሁሉ አገሬ ናት ብሎ በኦሮሞያ ክልል ለዘመናት የኖረውን አማራን “ነፍጠኛ ውጣ”፣ ይህ የኦሮሚያ መሬት ለአማራ አገሩ አይደለምና እዚህ መኖር አትችሉም…ወዘተ እያስባለና በተለይም አማራዎች በሆኑ እናቶች ላይ፣ እርጉዞች ላይ፣ ገበሬወች ላይ፣ በሴት ዩኒቨርሲቲ ተማሪወች ላይ …ወዘተ እጅግ ሰቅጣጭና ዘግናኝ ግፎችን፣ ጭካኔወችንና እንሰሳዊ ድርጊቶችን ፈጽሟል፤ አስፈጽሟል፡፡የኦሮሞ ክልል መሪ ተብየወቹና አንድ ጊዜ “ነፍጠኛን ሰብረነዋል” ሌላ ጊዜ ደግሞ “በማፍዘዝም በማዘዝም” እያሉ የሚመጻደቁት ባለውቅቶቹ እነሽመልስ አብዲሳም ታሪክ ይቅር የማይለው ደባ በአማራው ላይ ከመፈጸም ዛሬም፣ አልታቀቡም፡፡ ማንን ፈርተው? ምንንስ ፈርተው?? መንግስትና ህግ አለ በሚባልበት አገር ይህ መሰሉ ዘግናኝ ድርጊት በአሁኑ ዘመን በአማራው ላይ መፈጸሙን ማንም ምንጊዜም ሊረሳው የማይችል ጉዳይ ነው፡፤ ድርጊቶቹ በሙሉ ለአማራው የአእምሮ ቁስልና፣ የስብእናው ርክሰቶች ሆነው ለዘለአለም ይኖራሉ፤፡ ጃዋር ይህንን ሁሉ ሲያደርግ አብይ እያወቀ ተባባሪ በሚመስል መልኩ ምንም ሳያደርገው ቆይቶ ሳለ በስተመጨረሻው ላይ ግን ጃዋር አብይ አህመድ የተቀመጠበትን ወንበር መነቅነቅ ሲጀምር እስር ቤት ሊወረውረው በቅቷል፡፡

ወሎን ሰሜን ኦሮሚያ የማድረግ የኦሮሙማ ጥረት የተጀመረው ቀደም ብሎ ነው፡፤ ለዚሁም ይረዳ ዘንድ “የወሎ ህብረት’ የሚል ለኦሮሚያ መስፋፋትና ታላቅነት የሚሰራ ድርጅት በደሴ ተፈጠረ፡፡ አብይ አህመድ አሁንም የኢትዮጵያ መሪ ነኝ እያለና ለኦሮሙማ የበላይነትና መስፋፋት በድብቅም በገሀድም እየሰራ ባለበት ወቅት ወሎን ሰሜን ኦሮሚያ የማስደረግ የሴራ ፖለቲካውን ቀጥሎበታል፡፡ አብይም ይህንኑ አስቀጥሎ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

እዚህ ላይ ጃዋር በሉት ዳውድ ኢብሳ፤ አብይ አህመድ በሉት መራራ ጉዲና የኦሮሙማን አመለካከትና እምነት እንደዚሁም ኦሮምያን በሌሎች ላይ በማስፋፋትና የበላይ በማድረግ አንድ ናቸው፡፡ ወያኔ እንደ ቅማንት ነጻ አውጭና አገው ነጻ አውጭ… ወዘተ እያለ እንደጠፈጠፋቸው ጸረ አማራ ስብስቦች ሁሉ ኦርሙማም በወሎ የራሱን አሻንጉሊት ለመጠፍጠፍ አልቦዘነም፡፡ይህ ስሌትም ሁሉንም የኦሮሙማ አንጃወች አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዚሁ ቅዠት አንጻር ሰሜን ወሎ ወደ “ደቡብ ትግራይ” እንደዚሁም ደቡብ ወሎ ወደ “ሰሜን ኦሮሚያ” ይጠቃለላሉ ማለት ነው፡፡በዚህም የቅዠት አካሄድ የሚያስፈራው ሁለቱም ቅዠታሞች የሰሜን – ደቡብ ድንበራችን ነው ብለው በሚያስቡት ቦታ ላይ ሲገናኙ እንዳይዋጉ ነው፡፤ መቼስ ቅዠት አይደል??

ከወያኔና ኦሮሙማ ቅዠት አንጻር ሌላው ገራሚ ነገር ባለሰፊ ታሪኩ የንጉስ ሚካኤል አገር “ወሎ” አይኖርም ማለት ነው፡፤ ለነገሩኮ ፍርጃ ሆነና ወሎ ከደርግ ስርአት በስተቀር በሶስቱም ስርአቶች ጥርስ ውስጥ የገባ ህዝብ ነው፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት ንጉሱ ወደ ውጭ ሲሸሹ አትሸሹም ብሎ መንገድ በመዝጋቱ በንጉሱ ጥርስ ተያዘበት፡፡ “ከወያኔ ጋርም የተባበረ ጥቅር ዉሻ ይውለድ’ ብሎ ህዝቡ ላለመተባበር በመማማሉ የደረሰበትን ሁሉ ታሪክ መዝግቦታል፡፤ አብይ አህመድም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ወሎ ሄዶ ስብሰባ ሲመራ በህዝቡ በተለይም በአንዲት አይነ ስውር ነገር ግን እጅግ ልባም ሴትዮ ለኦሮሞ ስለሚያደርገው አድሏዊነቱና በአማራ ልዩ ሀይል ትጥቅና ስልጠና ላይ ስለተናገረው ማጣጣልና ማጥላላትን አስመልክቶ ለቀረበለት ግልጽ ጥያቄ በተለይ ጉዳዩ እንዲያ ይፋ ሆኖ በመጠየቁ አብይ ቀንድ አውጥቶ ምን እንደተናገረ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ቪድዮው አሁንም አለ፡፡

ወደ ጉዳያችን ስንመለስ ይህንን የኦሮሙማ ቅዠት ተሸክሞ መሳሪያ በመሆን የአማራ አንዲነት እንዲላላ አጥብቆ በመስራት ያለው ‘የወሎ ህብረት” ከወያኔ ቀጥሎ በደሴ ከተማ ዘረፋን ያካሄደ ስብስብ ነው፡፡ ስብስቡ ዘረፋውን ያካሄደው እራሱ ሆኖ እያለ ይባስ ብሎ ዘረፋውን ያካሄደው የአማራ ፋኖ ነው እያስባለ የሀሰት ዜና በመንዛት ላይ ይገኛል፡፡ የደሴ ህዝብማ ፋኖን እንዴት እንደተቀበለው፣ እንዴትስ ብሎ ፋኖን በስስት አይኑ እንደሚያየው ህዝቡ እውነታውን በአደባባይ አስመስክሯል፡፤ የደሴን ህዝብ ከወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝና ግፍ ነጻ ያወጣውን የፋኖን አቀባበልም ታሪክ በሰነዱ የደሴ ህዝብም በልቡ መዝግበውት ይኖራሉ፡፡ እነ አብይ አህመድ በወሎ ህዝብ ላይ ጭነው እየጋለቡት ያለው “የወሎ ህብረት” የተሰኘው የውርደት ፈረሳቸውም የትም ሳያደርሳቸው በወሎ ህዝብ “ንቁ” ንቀትና አማራዊ አንዲነት ፉርሽ ሆኖ ውርደቱን ይከናነባል፡፡ ሞት ለከፋፋዮች!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop