December 15, 2021
17 mins read

 የትግራይ ህዝብ ሆይ ፤ የሲዖል ጉዞ ይብቃህ !  – መኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

”  አጭር ርቀትን ብቻህን ብትጓዝ ይመረጣል ፡፡ ረጅም ርቀትን ግን ከሰው ጋር ብትጓዝ ይሻላል ፡፤ ከሞኝ ሰው ጋር ግን አንድ ኢንችም አብረኸው አትጓዝ ፡፡ ቀንህን ያደፈርስብሃል ፡፡   ጉዞህ ደስታ ቢስ   እንዲሆን ከፈለክ  ከሞኝ ጋር ተጓዝ ፡፡ ” የጠቢባን ምክር ፡፡

ትግራይ የተሰኘውን የኢትዮጵ አንድ ክፍለ ዛሬ የሚመራው የሞኝ ስብስብ ነው ፡፡ ማን ነው በዚህ በዘመነ እና በቴክኖሎጂ በተራቀቀ  ክፍለ ዘመን ፤ በዚህ ዓለም በጠበበችበት ና ለመበልፀግ ተባብሮ መስራት ብቻ በሚያስፈልግበት ወቅት ፤ የህሊናን ግዝፈት ብቻ ለተሸለ ህይወት በሚያበቃበት ጌዜ ፤ ህዝብን ለማጥፋት ቢላ ስሎ በመንጋ ይሚንቀሳቀስ ? እንዲህ ያለ ፀረ ህዝብ በዓለም ላይ ከቶ የለም ፡፡

ዛሬ በአገራችን  ጥቂት አሸባሪዎች ፣ ” በጠመንጃና በሥለት እያስፈራራሁ ሌሎችን አበርክኬ እገዛለሁ ፡፡ ” በማለት፣ በገዛ ውንድም ና እህቶቻቸው ላይ ያለአንደች በደል ፤ ቂም ና ቁርሾ ፣ በእብድነት ና  ከአውሬ በባሰ ተግባር ላይ ለጆሮ በሚከብድና ለአይን በሚዘገንን ጭካኔ ተሰማርተዋል ፡፡ በአማራ ና በአፋር ክልል ነዋሪ ህዝብ ላይ  የሞት ብትር በእየለቱ በመንጋ እየሰነዘሩ ፤ በግፍም ንጹሃኑን ሁሉ እየገደሉ ነው ፡፡ እንስሳትን ጭምር ፡፡ እንስሳን መግድል ከጅልነትም የባሰ አስነዋሪና አሳፋሪ ድርጊት ነው ፡፡ አርዶ መብላት ሲገባ እንስሳትን መረሸን የሞኝ ስራ ነው ፡፡ የአሸባሪውን ትህነግ  የተጃጃለ አስተሳሰብና አመልካከት በተጨባጭ የሚያሳይ ድርጊትም ነው ፡፡   አሸባሪው ወያኔ ይኽንን  እንከፍ እና ጅል አስተሳሰቡን ሲተገብር እንኳ ፤ ነውሩን  ለመደበቅ አልሞከረም ፡፡  አሸባሪውና ዕብዱ የወያኔ አመራር  እጅግ ሞኝ ፤ ጅላጅል ና ጨካኝ ሰዎች የሚመሩት ቡድን ነው የምልህ ይኽንን ዋቢ አድረጌ ነው  ፡፡ዛሬ አሸባሪውን ትህነግ  የሚመሩት ለተርታው ሰው ብልህና ብልጥ ይመስላሉ እንጂ የተጃጃሉ ናቸው ፡፤ እጅግ ሞኝ ፤ ጅላጅል ና ጨካኝ ሰዎች ናቸው የትግራይን ህዝብ እያወናበዱና እያስገደዱ እነደ ችቦ ወደሚንቦገቦገው የጥይት እሳት በጭካኔ እየወረወሩት ያሉት   ፡፡

አሸባሪው ትህነግ ፣ በጭካኔ  የተሞላ የነፍሰ ገዳይ ቡድን ስብስብ ነው ፡፡ ”  ለምንድነው የገዛ አገርህን የምትወጋው ? ለምንድነው  ካለህበት በህጋዊነት መጥተህ  ብትጎራበተው የማያገልኸን ፣ በዜግነትህ በአገርህ ሰርተህ የመኖር መብትህን የሚያከብርለህን ወንድምኽን የምትገለው ? ፡፡ አብሮህ ቡና ለመጠጠት ፣ የአንተን ልጅ ክርስትና ለማንሳት ፡፡ አብሮህ ለመስገድና ለመፀለይ ከቶም የማያቅማማውን  ወገንህን በጭካኔ ጋዝ አርከፍክፈህ ማቃጠልስ ሰውኛ ነውን ? ” ተብሎ ቢጠየቅ ፡፡ በንዴት ጦፎ ” ደግ አደርግሁ ! ገና ምን አይታችሁ !? ኢትዮጵያ ! ኢትዮጵ ! የምትሉትን ሁሉ አጠፋችኋለሁ ፡፡ በማለት በንዴት ጦፎ እደሚመልስላችሁ አትጠራጠሩ ፡፡ ያበዱና የተጃጃሉ  ፤ መግደል ና ማሰቃየት የደስታቸው ምንጭ የሆነ ፤ ውሸት እና ስግብግብነትን መርህ ያደረጉ ፤ ከሰውኛ አስተሳሰብ ያፈነገጠ የአውሬ ባህሪ ያላቸው ፤  በሆዳቸው የተጃጃሉ እና በግፍ የገደሏቸው ሰዎች  ዘወትር በእውን እና በህልማቸው በመምጣት እንቅለፍ የሚሳጧቸው ሰዎች ሁሉ ባህሪያቸው እንዲህ ነውና አይግረማችሁ ፡፡   ዛሬና አሁን የትግራይን  ክልል ፤ ስለህይወት ምንም ያልገባቸው በሆዳቸው የሚያስቡ ፤ ጥቂት ሞኝ ሰዎች እየመሩት እንደሆነ ግን ተገንዘቡ ፡ ፡፡ ይኸንን እውነት ነው ፡፡  በአንዲት ሉአላዊ አገር ውስጥ እንደ ማንኛውም ክልል መስተዳደር በህገ መንግስቱ መሰረት መኖር እንቢ ማለታቸውን ስታስተውሉ ፣ እውነቱን ትረዳላችሁ ፡፡

ወያኔዎች ከጅምሩ የአገሪቱን ከፍተኛውን የስልጣን በትር በአሜሪካና በምዕራብያኑ ሴራ እንደጨበጡ በኢትዮጵያ ህዝብ ቅቡልነት የሌላቸው የአገር መሪዎች ያለመሆናቸውን ተገንዝበው ነበር ፡፡  አገሪቱን አምስት አመት እንኳን ሳይመሩ የህዝቡን አንድነትና ለኢትዮፕያ ያለውን ቀናኢነት ተገንዝበው ነበር ፡፡ ለዚህም ነው ፣ የአገርን ሀብት እየሰረቁ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በአውሮፓና በአሜሪካ ያስቀመጡት ፡፡ …

ይኽም  ብቻ አይደለም ፡፡ በትግራይ የሚኖረውን ዜጋ ከሲቪል ሥራ ይልቅ በፖሊስ ፤ በልዩ ሃይል ፣ በሚሊሻ ተቀጥሮ ደሞዝ እየተከፈለው የእነሱ ሎሌ ሆኖ እንዲኖር ከማድረጋቸውም በላይ ህዝቡ የተመፅዋች አስተሳሰብ እንዲኖረውና መሪው ፓርቲ ህውሐት  ወያኔ ከስሩ ከተነቀለ ፤ በርሃብና በችግር እንደሚቆላ በአንድ ለአምስቱ ጠርንፎ አሳምኗቸዋል ፡፡ ይሁን እንጂ መሬት ላይ ያለው እውነት የሚያሳየን ፤ ብልጥና ብልህ ነኝ ባዩ ወያኔ በተጨባጭ  ሞኝና ስግብግብ በመሆን ፤  ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በምግብ ለሥራ ፕሮግራም ላይ ተሰማርቶ ለ27 ዓመት ስንዴ ከአሜሪካና አውሮፓ በውጪ የዕርዳታ ድርጅቶች አማካይነት በኢትዮጵያ መንግስት እየተገዛ በየወሩ እንዲሰፈርለት እና ታዛዥ ፣ የወያኔ  ጥገኛ እንዲሆን እንዳደረገው ነው ፡፡

ዛሬ አሸባሪው ቡድን ፤ ሁለት ጉድጎድ ያላት አይጥ አትሞትም በሚል ከንቱ ሃሳብ ፣ በገዛ አገሩ በኢትዮጵያ ላይ ለመሸፈት በሞኝነት አቀዶ መሳሪያ ሲደብቅና ሲያከማች እንደነበረ ዛሬ የገዛ አገሩን ህዝብ ሲወር ተረጋግጧል  ፡፡ ጥቂቶች እየተጃጃሉ ና እየጀዘቡ መሆኑን ባለመገንዘብ ፤ ጭራሽ ለራሳቸው የመላአክትን ቦታ ሰጥተው ፤ ሤጣን  መሆናቸውን ለማረሳሳት በምላስ ጉልበት  እጅግ ሲጥሩ እና ከበሬ ወለደ በባሰ ውሸትን በየቀኑ ውሸት ሲመርቱ እና ለየሶሻል ሚዲው ሲሸጡ ይስተዋላል ፡፡

የአማራን ክልል ወረው ፣ በህዝቡ ላይ እያደረሱ ያሉትን ሰቆቃ  ፡፡ በእውነቱ  የሚፈጽሙት ሰዋዊ ያልሆነ ድርጊት ከሞኝ እና ፈፅሞ ከተጃጃለ ና ከአእምሮ ቢስ ና ከሞኝ ሰው የሚመነጭ እንጂ ከጤነኛ ና ከብልህ ሰው ህሊና የሚመነጭ ከቶም አይደለም ፡፡ጥቂት የማይባለው  የትግራይ ህዝብ ባለማወቅ ተጠርንፎ በእነዚህ ግፈኛና ጨካኝ ሰዎች የእሳት እራት እየሆነ ነው ፡፡ እነዚህ ሞኝ ሰዎች የዛሬ 46 ዓመት የተመሰረተውን ትህነግ ወያኔን እንደ አንድ ነጻ አውጪ ቆጥረው ዛሬም በሌለ ጭቆና የሚያላዝኑ ናቸው ፡፡ ራሳቸው ኢህዴግ የሚባል ፓርቲ መስርተው ጭቆናን አሶግደናል ብለው ፣ ሥልጣንን ለ27 ዓመት የሙጥኝ ያሉ መሆናቸውን እንኳን ዘንግተዋል ፡፡   ለ27 ዓመት በብዝበዛ ላይ ተመስርተው ይኽቺን ደሃ አገር አልጋጧትም እነዴ ?! በብዝበዛ ላይ ተሰማርተው አገራችንን ሲግጡ ከከረሙ በኋላ ፣ ባልጠበቁት ፤ በብልህ መንገድ ከስልጣን ሲፈነገሉ ወደቀደመ ሞኝነታቸው  ተመልሰው ” እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀልን ፡፡ ” አውነተኛ ሃሰብ በሆዳቸው አድርገው ፣ዛሬ ና አሁን ፤ የዋሁን የትግራ ህዝብ በሀሰተኛ ትርክት አእምሮውን በማጦዝ ፣ የጥይት እራት እያደረጉት ነው ፡፡ እነዚህ ዛሬም ድረስ የሌለ ጭቆናን እንዳለ የሚያመላክት የነጻ አውጪ ሥም ለራሳቸው ሰጥተው   በትህነግ ስም በጠመንጃ  ና በጨካኝ አራጅ ሰራዊታቸው እያስፈራሩ  የትግራይ ክልል ነዋሪዎችን በማያጋባቸውና ባልገባቸው ጠርነት ውስጥ በማስገባት የገዛ አገራቸውን እንዲወጉና ፤ የገዛ ወገናቸውን እንዲገድሉና እንዲዘርፉ እያደረጓቸው ነው ፡፡  ይህ ፍፁም አሳፋሪ እና አሳዛኝ ድርጊት እስከወድያኛው የሚቆመው የትግራይ ህዝብ ከሞኝ መሪ አላማ ጋር አብሬ አልጎዝም ብሎ ፣ የሲዖል ጉዞውን ሲያቆም ብቻ ነው ፡፡

በትግራይ ክልል የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የሲዖል ጉዞ ይበቃል ማለት አለበት ፡፡ በዚህ ጦርነት የሚጎዱት በአሜሪካና በአውሮፓ ለዘመዶቻቸው ጥሪት ያስቀመጡ ፣ ቤት የገዙ ፤ በጣት የሚቆጠሩ ከሃዲ የትግራይ ክልል ተወላጅ ኢትዮጵያውያን አይደሉም ፡፡በዚህ ጦርነት የሚጎዱት ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው ከመከላከያ የከዱ ከፍተኛ መኮንኖች አይደሉም ፡፡ ተጎጂው ኑሮው ከእጅ ወደአፍ የሆነ የትግራይ ተርታ ህዝብ ነው ፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ጦርነት ተጎጂዋ ኢትዮጵያ ናት ፡፡ ይኽ ጦርነት ተገቢ ያልሆነ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለአገር ሉአላዊነት ሲል ተገዶ የገባበት በመላው የኢትዮጵያውን ዘንድ የሚደገፍ ጦርነት መሆኑ መታወቅ አለበት ፡፡ ይህ ጦርነት የአሜሪካ ፣ የአውሮፓና የግብፅ  ስግብግቦች በእጅ አዙር በቅጥረኛው ሞኙ ወያኔ አማካንነት እያካሄዱት ያለው ኢትዮጵያን ካዓለም ካርታ ላይ የማጥፋት ና ያላትን ሀብት የመቀራመት ዓላማን ያነገበ ጦርነት ነው ፡፡ እናም አንድ ሰው እና አንድ ጥይት እሰከሚቀረን ድረስ እኛ ኢትዮጵያውያን እንዋጋለን እንጂ ፤ ህይወታችን እያለ ፤ ለበዝባዢ ስግብግቦች አገራችንን አሳልፈን አንሰጥም ፡፡ በዚህ አጋጣሚም በገንዘብ የምትደለሉ ሆዳሞችንም እናስጠነቅቃችኋለን ፤ ከዚህ በኋላ በየትናውም ኻላፊነት ላይ ያለ ሲቪልም ሆነ የጦር አመራር ራሱን ከስግብግብ አመለካከት ና ከጅላጅልነት ካላጠራ የሚወሰድበት እርምጃ የማያዳግምና ለሌሎች ከሃዲዎች አስተማሪ የሚሆን እንደሆነ ማወቅ አለበት ፡፡ የኢትዮጵ ልጆች ማናችንም ክብራችንን ለሆዳችን አንሸጥም ፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን አይደለም ለሰወ ላሳደግነው  እንስሳ ከፍተኛ ፍቅር ያለን ህዝቦች ነን ፡፡…

ከእንግዲህ ከአእምሮው ጋር ያለው ወገናችን የትግራይ ህዝብ ፣ ” አንዳችም ዘላቂ ጥቅም በማያስገኝልን ፣ ትግራይን ለሚቀጥሉት 50 ዓመታት ደሃ አድርጎ በሚያስቀር ተርጉመ ቢስ ጦርነት ፤ በእነዚህ ሞኝ ልጆቻችን እየተመራን የሞት ጉዞ አንቀጥልም ፡፡ ወደሲዖል መጓዛችን  ይበቃ ! ይበቃል !!  የእኛ ፍላጎት ሠላም ፤ ፍትህ ፣ ዴሞክራሲ ፣ ልማት እና ከስንዴ ዱቄት እርጥባን መላቀቅ ነው ፡፡  ዘረፋና ስርቆትን ፣ ጭካኔን ና ነፍስ ማጥፋትን  በማስተማር ከሰውነት ተረታ አሰውጥታችሁ ፤ ከአውሬ ብሰን እንድንታይ ከወገናችን ከኢትዮጵያ ህዝብ ነጥላችሁ  በሆዳችን በመግዛት አታሰቃዩን ፡፡ ” በማለት ግልፅ የሰላም አቋሙን  ለሞኝ መሪዎቹ በማሳወቅ ፣ ሰላሙን ራሱ  ሊያውጅ ይገባዋል ፡፡ ይህንንም በቅርብ ያደርገዋል ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ  ፡፡ ቀላል ነው ፡፡ አፈሙዙ እንደሆነ በእጁ ነው ፡፡ ለትግራይ እናቶች ፤ህፃናቶች እና ለአዘውነት አባቶቹ የወደፊት መልካም ህይወት የትግራይ ወጣት በእጅጉ እንደሚያስብ አምናለሁና ይህንኑ ይተገብራል ፡፡ ራሱን አገራቸውን በዶላር ከሸጡ ከሞኝ መሪዎች ነፃ ያወጣል ፡፡ ለመልካም ነገር ቆርጠው ከተነሱና ጅልነትን ከተጠየፉ አያሌ የስኬት ጉዞዎችን ከብልሆች ጋር  መጎዝ እነደሚቻልም ይገነዘባል ፡፡  ወዳጄ ” ለመኖር ብላ እንጂ ፣ ለመብላት ብቻ አትኑር ፡፡ ” የተባለው በዋዛ እንዳይመስለህ ፡፡ እየበሉ እዳሪ መውጣትማ ለእንስሳም ብርቅ አይደለም ፡፡ ….

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop