December 14, 2021
16 mins read

የብርሃን አካል በሆኑ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት የአንድነት፣ ነጻነትና ፍቅር ፍሬዎች ይጎመራሉ – ሚኪያስ ግዛው

- ይህ ጽሁፍ መታሰብያነቱ ከጨለማ ኃይሎች ጋር ታግለው በጀግንነት ለተሰዉት የሸዋ ሮቢት ነዋሪዎች ለሆኑት ለአቶ እሸቴ ሞገስና ልጃቸው ይታገሱ እሸቴ ይሁንልኝ –

በልዩ ልዩ ቀለማት ያበበው፣ በትላልቆቹ ኃይማኖቶች የታጀበው፣ ትዕግስትና ማስተዋል የታደለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሠማይ ላይ የሚገኘው እግዚአብሄር ንጉሥም አሸናፊም መሆኑን ያምናል። እግዚአብሄር ምድርና ሠማይን ሲፈጥር ጨለማን ገርስሶ ብርሃን አልብሷል (creation battle)፣ ዛሬም ቢሆን እርሱ አምላክ በጽዮን ተራራ ላይ ሆኖ የትርምስ ኃይሎችን ይታገላል (the Zion battle)፣ ትላንት ባህሩን ከፍሎ እስራኤሎችን ያሻገረው አምላክ (the Exodus battle)ወደፊት ከዚሁ የጨለማ ኃይል ጋር የመጨረሻውን ፍልሚያ (the battle of the day of the Lord) በማድረግ ሁሉን ይፈጽማል።

abc News የተባለው የዜና አውታር ሐምሌ 25 ቀን2008 ዓም – “የሃሪኬን ንፋስ መኖርያ ኢትዮጵያ ናትን? (The real Home of Hurricanes: Ethiopia?) የሚል ዘገባ አሰራጭቶ ነበር። ጽሁፉ መብረቃዊ ነጎድጓዶች (thunderstormes) ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ተነስተው ሲያበቁ ከሰሃራ በረሃ ሙቀትና ኃይል ዝቀው (picking up the heat and energy) ከአትላንቲንክ ውቅያኖስ ጋር ተዛምደው፣ አሜሪካንን የሚያናውጡ ሃሪኬኖች (Hurricane)ይሆናሉ የሚል ይዘት ያለው ነው። በተጨማሪሞ – The Birth of the Hurricane: Genesis and Evolution  – በሚል አንድ የቪዲዮ ገለጻ  ሃሪኬኖች ከኢትዮጵያ ተራሮች ላይ ይነሳሉ  ካለ በኋላ ከሰሃራ በረሃ ላይ ያለውን ነፋስ ይዘው ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር ተደባልቀው ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ አገሮችን አጥቅተው ነበር ሲል ያትታል።

ጥናቶቹ ብርቱ የነፋስ ኃይል ከኢትዮጵያ ሰሜን ተራሮች ላይ እንደሚነሳ ግንዛቤ ያስጨብጣል። የናሳ (NASA) ሳይንቲስቶች አሜሪካንን በብርቱ የሚመታው ሃሪኬን አውሎ ነፋስ ምንጩ ራስ ደጀን ተራራ ነው ይላሉ። ለመሆኑ ይህ ምርምር የአሜሪካ መሪዎች ኢትዮጵያን በክፉ እንዲያይዋት ጥላቻ አሳድሮባቸው ይሆን? ራስ ወዳዶቹ ትህነጎችም ሁኔታውን ተጠቅመው ይሆን ከአሜሪካ ጋር የተወዳጁት? መቼም ይህ ሁሉ እገዛ፣ ይህ ሁሉ የሎቢይስቶች ጩኸት፣ ይህ ሁሉ ማስፈራርያና ዛቻ፣ ይህ ሁሉ የዜና ሽፋን ካለ ምክንያት አይደለም። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የሚያውከው የጨለማ ኃይል አድዋ ተራራ ሥር ከተቀበሩት ቅኝ ገዥዎች የሙት መንፈስ የተነነ ቢሆንስ? በእርግጥ ከራስ ደጀን አናት የሚፍለቀለቀው ነፋስ አቅራብያው ካለው የቅኝ ገዥዎች የሙት መንፈስ ጋር ሊስማማ አይችልም። አንዳንድ የትህነግ መሪዎች ሲዖልም ቢሆን ወርደን ከዚያም ተመልሰን ኢትዮጵያን እናፈርሳለን” ሲሉ መደመጣቸው ለምን ይሆን? ያንዳንድ የተጋሩ አክቲቪስቶች እግዚአብሄርን ሳይቀር የመናቅ የትዕቢትና የድፍረት ንግግርስ ከየት መጣ? የትግራይ ሕዝብም ቢሆን አማኝ ነው። ታድያ ለምን ይሆን ከአብራኩ የወጡት ልጆች በአማራና አፋር ክልል ይህን ሁሉ ዘግናኝና አሳፋሪ ጥፋት የፈጸሙት?አሜሪካና አውሮፓ ለትህነግ መጠነ ሠፊ እርዳታ ማድረጋቸው በምላሹ ምን ለማግኘት ነው?በኢትዮጵያ አሳፋሪ ባህሎችን ለማስፋፋት ወይስ በቅኝ ግዛት ሥር አድርጎ ለማስተዳደርበእርግጥ የብርሃንና ጨለማ ትግል ሜዳ ትሆን አገራችን?

የጨለማው ኃይል ስልት በዴሞክራሲ ስም መጮህ ነው። ሠብዓዊ ፍጡራንን አፍኖ የሚገድለው ስለ ሠብዓዊ መብት የሚለፍፈው የጨለማ ኃይል ድምጹን የሚያስተጋባለት CNN ነው። CNN – የጨለማው ኃይል ውልዶች የሆኑት ጥቂት ባንዳዎች – ደጋጎቹን የትግራይ ልጆች አሰልፈው – የሴራ መተግበርያቸው፣ የዝርፊያቸው ምንጭ፣ የሥልጣናቸው መወጣጫና የቅኝ ገዥዎች ዓላማ ማስፈጸምያ ማድረጋቸውን አይዘግብም። ቢዘግብም ትህነግ አዲስ አበባን ልትይዝ አንድ ሳምንት ቀራት የሚል ውሸት ነው። እነዚህ አባቶቻቸው ለኢጣልያ ያደሩ ጥቂት የባንዳ ልጆች በትግራይ ልጆች እንዲሁም በሆዳሞች ጀርባ ባይጋልቡ ኖሮ እናት ዓለም ኢትዮጵያ ይህ ሁሉ መከራ አይደርስባትም ነበር።

ትህነግም ስትዋሽ የምዕራቡን ሜዲያ ታስከነዳለች። ህወሃት መልካም አካሄድን ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ማስቀየር ተክናለች። ትህነግ ስሙ እናንት ተጋሩዎች የዓለም አንድ ቁጥር ተዋጊዎች ናችሁ፣ ግዙፉን በአፍሪካ ውስጥ ጠንካራ መከላከያ ኃይል የነበረውን የደርግ ሠራዊት አሸንፋችኋል” በሚል ባዶ ትርክት ስሜትን አሳብጣ ወጣቱን ለጭዳ ዳርጋለች። ትህነጎች ዛሬም አማኞቹን የትግራይ ልጆች በሲዖል ትምህርት በክለው እድቅድቁ ጨለማ ገደል ወርውረዋቸዋል። ምርከኞች – በወረራ በተያዙ አካባቢዎች አውሮፕላን ማረፍያን፣ ዩኒቨርሲቲን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታሎችን ሳይመርጡ እንዲያወድሙ – በተጨማሪም – መነኮሳትን፣ እናቶችንና ልጃገረዶችን አስገድደው እንዲደፍሩ እንዲሁም በዘረፋ፣ በቃጠሎ፣ በጅምላ ጭፍጨፋ፣ ከብቶችን በመግደል፣ ሠላማዊ ሰዎችን ረሽኖ በማቃጠል፣ መስጊዶችን በማፍረስ፣ ጽላተ መንበሩን ሳይቀር በማርከስ ቀሳፊ ምግባር ላይ እንዲሰማሩ መታዘዛቸውን ተናግረዋል። የምዕራብያውያኑ የዜና ምንጮች ይህን ዘግናኝ ግፍ ለመዘገብ የሞራል አቅም እስኪያጡ ድረስ በህወሃት ፍቅር ተለክፈዋል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ባለሥልጣኖች የሃያ ሰባቱ ዓመት ዘረፋና አሸሸገዳሜ ባላረካቸው ብዔልዜቡሎች፣ አፍኒኖች፣ ይሉኝታና ፈሪሃ እግዚአብሄር በሌላቸው መያኔዎች ግፊት የሰው ነፍስ በከንቱ እንደ ቅጠል ሲረግፍ አንዳች አይሉም። በምትኩ ወያኔ በውሸት፣ በሠበካ ወሬና የድሆች ዓይኖችን በባዶ ተስፋ አስራ ወደፊት መገፍተር እንድትችል ስውር ኃይል ያስታጥቋታል።

ውድ ኢትዮጵያውያን – ኢትዮጵያ በብርሃንና ጨለማ ኃይል መካከል ፍልሚያ የሚደረግባት ምድር ነች። በትህነግ ጀርባ ላይ የሚጋልቡት የምዕራቡ መንግሥታት ኢትዮጵያን ከቶም ቢሆን አያንበረክኳትም። በእርግጥ ትግሉ መራራ ነው። ዛሬ በአማራና በአፋር ምድር የተደቆሰው የጨለማ ኃይል አርፎ ይቀመጣል ማለት አይደለም። ለሌላ ሁከት ሌላ አማራጭ ይከተላል። በሰሜን ወይም ደቡብ ሱዳን በኩል ካልሆነለት ፊቱን ወደ ፈሮዖኖቹ ያዞራል። በጅቡቲ በኩል መንገዱ ከታጠረበት ወደ ኬንያ ይጠመዝዛል። ይሄኛው ፊት ከነሳው ወደ እዛ ይሄዳል። የጨለማው ኃይል የኤኮኖሚው እገዳ አላዋጣ ካለው ኢትዮጵያን ከዓለም መድረክ ሊያገላት ይሞክራል። የእርዳታ ምግብ በማድረስ አሳቦ በሺህ የሚቆጠሩ ከባድ መኪናዎችን ለትህነግ የሸለመው የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ነገም መላ ፈጥሮ ሌላ ሻጥር ይሠራል። ምዕራቡ ዓለም ሎሌዎቹን የትህነግ መሪዎች ለመርዳት በሰማይ ባይሆንላቸው ምድር ሰርስረው ይገባሉ። እነሱ ምን ቸገራቸው – ብሄራዊ ፍላጎታቸው ይስመርላቸው እንጂ – ምድሪቱ ጨለማ ቢወርሳት እናቶች ማቅ ቢለብሱ የሚያዝኑበት አንጀት የላቸውም።

ታሪክ ሁሉንም እንደየፈርጁ ትከትባለች። በኃይለ ሥላሴ ዘመን በቀዳማይ ወያኔ ስም፣ በደርግ ዘመን በዳግማይ ወያነ ስም – ዛሬም በሣልሳዊ ወያነ ስም በየጥሻውና ጉድባው የሚወድቁትን የትግራይ ልጆችን ደመከልብ ሞትን ታያለች። የኢትዮጵያ ተራሮች፣ ሜዳና ሸንተረሩ ሁሉን ያስተውላሉ። መልክዓምድር በዚህ በኩል ባንዳዎችን ስትታዘብ በያ በኩል ደግሞ አርበኞችን ትመለከታለች። ታሪክ ሁሉን ታያለች። ለውድ አገራችው ሲሉ ከጨለማ ኃይሎች ጋር ታግለው የተሰዉት አቶ እሸቴ ሞገስና ልጃቸው ይታገሱ እሸቴ ሸዋ ሮቢት ድረስ ሠተት ብለው የመጡትን የባንዳ ሎሌዎች ወደ ሲዖል ሸኝተው እነርሱ ወደ ዘላለማዊው ብርሃን መተኮሳቸውን ታሪክ ነች ያበሰረችን። አባት እሸቴ ሞገስ ቀድሞ የተሰዋውን የልጃቸውን ይታገሱ አስከሬን ትቼ አልሄድም ብለው የቻሉትን ያህል ታግለው ተሰውተዋል። አቶ እሸቴ ፍቅርን፣ ቆራጥነትን፣ ጀግንነትን፣ መስዋዕትነትን ባንድ ላይ ያጣመሩ – ለሃገር፣ ለህዝብና ለወገን የቆሙ አርበኛ ናቸው። የአባትና ልጅ ገድል ዝንተ ዓመት ያበራል፣ የመስዋዕትነታቸው ፍሬም ይጎመራል።

ዘመኑ ምን ያላሳየን ነገር አለ። በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በአጭር ወራቶች ታላቅ አጀንዳ ሆና ተደጋጋሚ ስብሰባ የተጠራባት ብቸኛ ሃገር ኢትዮጵያ ሆናለች። ለጌታም ጌታ አለው እንዲሉ – በጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ሊደቁሷት ያሰቡት ባለ ኒውክለሮች፣ ሴራቸው ድምጽን በድምጽ በሚሽሩት ተገዳዳሪዎቻቸው ተቃውሞ አፈር ድሜ ለብሷል። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ግርማ ሞገስ እያለበሰ የጠላቶችዋን ደባ ደግሞ ደጋግሞ ውድቅ አድርጓል። ያለፉትንም ይሁን ያሁኑ ዘመን ጦርነቶች – በእግዚአብሔርና በጨለማው ኃይል ሠይጣን መካከል ፍልሚያ ከሚደረጉባቸው የዓለም ክፍሎች (battle against the powers of chos) መካከል በእሳት ቶኖች የተከበብችዋ፣ የብሉይና ያዲስ ኪዳን ምድር ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ፍንትው አድርጎ አሳይቷል። ኃይሏ እውነትና ፅናት የሆነው ኢትዮጵያ – ቅኝ ገዥዎችን ታዋክባለች፣ ባንዳዎቻቸውን ትቀጣለች፣ ወዳጆቿን ታከብራለች። ይህች በእግዚአብሄር መዳፍ ላይ ያለች ኢትዮጵያ እንድፈርስ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር የሚተባበሩ፣ ወዮ ለነሱ!

ኢትዮጵያን የነካ የለውም በረካ” ይባላል። ዛሬ ኃያላን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ የሠነዘረቱን ሠፊ ጥቃት ካልገቱ ራሳቸውን ይጎዳሉ። አንዳንድ ምዕራብያውያን ሃገሮች በእጅ አዙር አፍሪካን የማስተዳደር ዓላማቸውን ላንዴና ለመጨረሻ ሊቀብሩ ይገባል። ሁሉን አየን፣ ምንስ ቀረን?ኢትዮጵያውያን ብንኖርም ብንሞትም ለቅድስት ኢትዮጵያና ለአፍሪካ ነው። ሌላ ሶስተኛ አማራጭ የለንም። ኢትዮጵያውያን አይደላንም፣ ድላችን የሃገርን ሉዓላዊነት ሳያስደፍሩ ማቆየትና ለትውልድ ማስተላለፍ ብቻ ነው። ትልቅ ሃቅ አለ – የብርሃን አካል በሆኑ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት የአንድነት፣ ነጻነትና ፍቅር ፍሬዎች ይጎመራሉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop