December 13, 2021
8 mins read

በልጠን ካልተገኘን….!!! – ቹቹ አለባቸው

በአሁኑ ወቅት ሕይወት በአማራ ክልል ተጎሳቁሏል፡፡ ይህ መጎሳቆል በተለይም በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞን፤ ሰሜን ወሎ፤ደቡብ ወሎ፤ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሙሉ በሙሉ፤ እንዲሁም በሰሜን ሽዋ፤ ደቡብ ጎንደርና ሰሜን ጎንደር ዞኖች በከፊል በከፋ ሁኔታ የሕይወት መጎሳቆል ተከስቷል፡፡ ማህበራዊ ቀውሱ በእነዚህ አካባቢዎች አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል፡፡ ትምህርት የለም፤ የጤና አገልግሎት የለም፤ የግብርና ልማት የለም፤ መሰረተ ልማት የተባለ በሙሉ ወድሟል፡፡ ዓላማው ከጭፍጨፋ የሚተርፍ አማራ ካለ፣ አንድ መቶ ዓመት በድህነት ወደኋላ መመለስ ነው። ከሁሉም በላይ በህዝባችን ላይ የደረሰው የስነ ልቦና ጉዳት እጅጉን ከባድ ነው፡፡ ቀላል ግምት የማይሰጠው ሰብዓዊ ኪሳራ ደርሶብናል፡፡

አሳዛኙ እና ቁጭት ሊፈጥርብን የሚገባው ጉዳይ፤ ይህ አውዳሚና ታሪክ ይቅር የማይለው የጥፋት ተግባር የተፈፀመው ከ5 ሚሊየን በማይበልጥ ህዝብ በወጡት የትግራይ ወጣቶችና ጎልማሳዎች መሆኑ ነው፡፡ ልብ በሉ ከዚህ ከአማራ አንፃር ሲነፃፀር በቁጥር አናሳ ከሆነ ማህበረሰብ የተገኙ ወሮበላዎች ናቸው 30 ሚሊየን በሚሻገረው ህዝባችን ላይ ይሄን ሁሉ አስቃቂና በታሪክ የማይረሳ ሁለንተናዊ ውድመት ያደረሱት፡፡

በአንጻሩ ደግሞ የት*ግሬ ወ*ራሪ ይሄን ያክል ውድመት እያደረሰ፤ እንደ አማራ የተሰጠው ምላሽ በልኩ አለመሆኑ እጅግ ያበሳጫል፡፡ እኛ አማራዎች ካወቅንበት ራሳችንን እንድንመረምር የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን ፡፡እውነት ነው መጀመሪያ አካባቢ መዘናጋት ስለነበር የአማራ ህዝብ በጠላቶቹ ልክ አለመዘጋጀቱ ያን ያክ ላይገርመን ይችላል፡፡ነገር ግን የጠላት አውዳሚነት በተግባር ከተረጋገጠ በኋላም ቢሆን እንደ አማራ እየተሰጠ ያለው ምላሽ በልኩ ነው ማለት አልችልም፡፡ለምሳሌ ዛሬም ቢሆን ወጣቱ ሊከት በሚገባው ልክ ወደ መከላከያ እና ልዩ ኃይል እየከተተ አይደለም፡፡በተለይም የአማራ ወጣት መከላከያን እዲቀላቀል ብዙ ተደከመ፤ብዙ ተለፈለፈ፤ ምላሹ ግን አሁን አጥጋቢ ሁኖ አይታይም፡፡

እንዴው የእውነት እንነገጋር ከተባለ በአሁኑ ወቅት አቅሙ ለጦርነት የፈቀደለት በተለይም የአማራ ወጣት ቴክኖሎጂን መሰረት ካደረገው ከዘመናዊ ውትድርና ውጭ ሌላ የሚያስበው ነገር መኖር አለበት? አማራ እንደ አማራ በማንነቱ እየተጠቃ፤ ንብረቱ እየተዘረፈና እየወደመበት፤ እናቶቻን እና እህቶቻን እየተደፈሩ፤ …ወዘተ የአማራ ወጣት እንዴት እንቅልፍ ተኝቶ ሊያድር ተቻለው? ዛሬ ላይ የዋግ፤ ኦሮሞ ብ/ሰብ፤ የድፍን ወሎና ሸዋ ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነው እያለ፤ የጎንደር፤ አዊና ጎጃም ወጣቶች የሚማሩት ትምህርት እንዴት ሊጣፍጣቸው ይቻላቸዋል?

በአጠቃላይ ጊዜው ዛሬም ሆነ ነገ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአማራ እጅግ አሳሳቢ ነው። ይሄንን አሳሳቢ ሁኔታ መቅረፍ የሚቻለው ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ከገነባን ብቻ ነው፡፡ በተለይም ትህነግ ዛሬም ሆነ ነገ በሕይወት እስካለ ድረስ አማራን ሳያንበረክክና ፤የጀመረውን ውድመት ወደ ጎንደርና ጎጃም ሳያስፋፋ ተኝቶ ያድራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ መንታ ልብ አማራ ካለ፤ ይህን መሰሉ አማራ መቸም ቢሆን የትህነግን ባህሪና ዓላማ ከአማራ አንፃር አይረዳውም ማለት ነው፡፡

ስለዚህ የአማራ ህዝብ የት*ግሬ ወ*ራሪ ዛሬም ሆነ ነገ እያደረሰብን ካለውና ሊያደርስብን ከሚችለው ውድመትና ውርደት መትረፍ የሚችለው፤ ጠንካራ የመከላካያ ሠራዊት ኃይል ሲኖር ብቻ መሆኑን ተገንዝቦ በመከላካያ ውስጥ የአማራ ተሳትፎ በእጅጉ እንዲጨምር አልሞ መስራት አለበት፡፡ በመከላከያ ውስጥ ትርጉም ያለው ተሳትፎ ሳይኖርህ ተወረርን፤ ንብረት ወደመ፤ እህቴ ተደፈረች ብትል ጩኽት መፍትሄ አይሆንም፡፡ መፍትሄው ጠላት የሚፈራው የፀጥታ ኃይል በተለይም መከላካያ ሠራዊት እንዲገነባ አስተዋፆ ማድረግ ነው፡፡

በመጨረሻም!

የአማራ ህዝብ በተለይም ወጣቱ፣ በተደጋጋሚ የሚቀርብልህን መከላከያን ተቀላቀል ጥሪ አሁንም እንደተለመደው ችላ ብለህ ካለፍነው፤ ዛሬም ሆነ ነገ የት*ግሬ ወ*ራሪ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ላለውና ለሚያደርሰው ውድመት አሜን ብሎ እንደመቀበል ይቆጠራል፡፡

አማራ ከጠላቶቹ በልጦ ካልተገኘ በስተቀር፤ በአሁኑ ወቅት በከፊል አማራ ያየነው ሁለንተናዊ ውድመትና ውርደት፤ እንዲሁም የሥነ-ልቦና ስብራት፤ ነገ ወደ ጎንደርና ጎጃም ተስፋቶ መላ አማራን በማዳረስ የመላ አማራን ውርደትና ስብራት ሊያስከትል እንደሚችል ማመን ያስፈልጋል፡፡ ይህ ታሪካዊ እፍረት እንዳይከሰት ከፈለግን፤ የአማራ ህዝብ ልጆቹን ወደ መከላከያ ዛሬውኑ ይላክ፤ የአማራ ወጣቶችም የሁኔታዎችን አስቸጋሪነት በመገንዛብ ዛሬውን መከላከያን ተቀላቀሉ፤ የምዝገባ ጊዜው እያለቀ ነው፤ነገ ከነገ ወድያ ዕድሉ ላይገኝ ይችላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop