December 13, 2021
4 mins read

ፕሬዚዳንት ሲሲ ሆይ ከነጮች ጋር ሆነሀ ለማረድ የገዘገዝካት ኢትዮጵያ አትምርህም

2015 8 26 egyptian president abdel fattah alሲሲ ሆይ በቀደዱልህ ቦይ መፍሰስህን አቁም። ዋጋ ያስከፍላል፣ አውሮፓና አሜሪካ አብይ አህመድን ከስልጣኑ አውርደው በሌላ መተካት የፈለጉበት ምክንያት ግልፅ ነው። ባጭር አነጋጋር አብይ አሕመድ ለነጮቹ ፍላጎት አልገዛም አልታዘዝም በማለቱ ነው ።

ለዚህ ነው እነሱ በሩቅ ሁነው ከውስጥ የቅርብ ጠላት ያበጁለት። እነሱ የፈጠሯቸውን ጥላቶች ተጠቅመው አሰቡበት አልደረሱም። አንተም ከነሱ ጋር አብረህ ቢላዋኻን ስለህ ተነሳህበት። ገዝግዘህም አቆሰልከው። ግን አልሞተም ነጮቹ ከኢትዮጵያ ሩቅ ናቸው። አብይ እነሱን መጉዳት አይችልም። ግብፅና ሱዳን ግን በጣም ቅርብ ነን። ነጮቹ በኢትዮጵያ ላይ የሞከሩት መንገድ ልክ አልነበረም፣ እነሱም አምነው፣ የሄድንበት መንገድ ልክ ስላልነበረ አብይ ሆይ እንወያይ እያሉ እየለፈለፉ ነው።

ሲሲ ሆይ አንተስ ምን ሊበቃህ ነው..?

እንደነሱ አንተም እንወያይ ልትል ነው..?

ሠውየው እኮ አብይ አሕመድ ሚባል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነው። አንተ ከነጮች ጋር አብረህ አስተኝተህ በቢላዋ ጉሮሮውን ቆርጠህ ልትገድለው አስበህ ያቆሰልከው ሰው ነው። አንተ ከነሱ ጋር አብረህ ያቆሰልከውን የቁስሉን ህመም በደንብ ያውቀዋል። አሁን ትንሽ ቢቀረው እንጅ ቁስሉ እየደረቀለት ነው። ከበፊቱ በበለጠ አምሮበት በጀግንነት በክብርና በላቀ የህዝብ ፍቅር ታጅቦ ወደቦታው ተመልሷል።

ነገ ግን እሱ በምላሹ ጉሮሯችንን ሊያንቀን ነው ። አንተስ ምን ልታደርግ አሰብክ. ?

የዱሮውን ነጠላ ዜማ ልትከፍትልን ነው ..? የመለድከው ቀያይ መስመር ልታሰምርልን ይሆን ..? አንተና ሚኒስተሮችህ ሀገር ላገር እየዞራችሁ በጋዜጠኞች ፊት

የግብፅ ታሪካዊ ውሃ ……. አይነካም

ሁሉን አቀፍ ስምምነት ….. ያስፈልጋል

ከሦስተኛ ሙሌቱ በፊት ህጋዊና አስገዳጅ ……. ስምምነት ላይ መድረስ አለብን ልትሉን ይሆን .?

ከዛስ ደሞ ኢትዮጵያ ይህንን ተቀብላ እንድትስማማ አለማቀፉ ማህበረሰብ ጫና

እንዲያደርግባት መግለጫ ትሰጡ ይሆን

ከዛም የተባበሩት መንግስት ድርጅት የአውሮፓ ህብረት ያደራድረን ልትሉ ይሆን ?

ተሰታችሁኮ ያልቅም ይሄንን ብላችሁ አልበቃ

ሲላችሁ ፤ « ኢትዮጵያን በኬኒያና ኡጋንዳ በኩል ከበናታል».! ወዳጆቿን ጅቡቲና ሶማሊያን ይዘናቸዋል። ከሱዳንና ከደ/ሱዳን ጋር ውይይት እያደረግን ነው ልትሉን ይሆን .? እናተ አትሉም አይባልም። እንደለመዳችሁት ትሉናላችሁ።

የናተ ይሄ ሁሉ ማለት ለኢትዮጵያ ምኗም አደለም። እኛ ይሄንን እያልን ስንጮህ ኢትዮጵያ ግድቡን ጀምራ ገንብታ ውሃ ቆጥራበታለች። እኛ ይሄንን እያልን ስንጮህ ኢትዩጵያ የመጀመሪያና ሁለተኛውን ውሃ ሙሊት ሞልታለች።

ፕሬዚዳንት ሲሲ ሆይ በቀደዱለት ቦይ መፍሰስ ፣ ነገንና ከነገወዲያን አስቦ አለመጓዝ ትርፉ ፀፀት ነው ። ሳይረፍድ በግዜ ሌላ መላ ፈልግ ።

 

sulemanግብፃዊዩ የፖለቲካ ተንታኝ ኢማድ አልብሔይሪ ለፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ሲሲ ያስተላለፈው መልዕክት

ሱሌማን አብደላ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop