በትግራይ ግዛት የተጀመረው ትሕነግ አምባገነንነት የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግ ለማስከበር የወሰደው ርምጃ አስቸጋሪ መሆኑን ሁሉም ሕዝብ የተረዳው አይደለም። ትሕነግ አንድን የጠላት ሀገር እንደመውጋትና መውረር አላማ አድርጎ የተነሳ በመሆኑ፣ አነሳሱ በሙሉ ጦርነት ነው። የመንግሥት መከላከያ የወሰድው እርምጃ ልዩ ነው። እሱም ለትግራ ሕዝብ እንዲሁም ትሕነግ ባለበበት ሕዝብ መካከል ውስጥ ሆኖ ለሚያደርገው ተኩስ አጸፌታ ለማድረግ የንጹሐኑን ህይወት አብሮ የሚያጠፋ ስለሆነ ርምጃው የተወሰነ ሆኗል። ይህ ልዩ ትርጉም ተስጥቶታል። በተጨማሪ ትሕነግ የተከለከሉ የብዙሀንን ህይዎት ማጥፊያ በእጁ የሚገኝ መሆኑ ስለታወቀ፣ ለዚያም የሕግ ማስከበር ርምጃው ልዩ ስልት አስፈላጊ ሆኖ ነበር። ይህ ግምት በስራ ውሎ የተወሰደው ሁለተኛው እርምጃ የሕግ ማስከበሩ ጉዳይ ፍጻሜ እያገኘ ነው።
ትሕነግ እንዲወድም የውጭና የውስጥ ጠላቶች ለራሳቸው ግብ ሲሉ የጀመረውን ጥርነት እስከፍጻሜው እንዲገፋበት ጧት ማታ እያበረታቱት ቆይተዋል። አላማቸው ተፈጽሟል። ወያኔዎችም (ትሕነግ) ከዚህ ዕውቅና እና ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ለመግባት በራሳቸው ጠባብ አስተሳሰብ ስለተዋጡ ሌላ የሚጠብቃቸውን ችግር አርቆ ለማየት ብዙ ይጎላቸዋል። ይህ ጉዳይ፣ በነሰየ፣ አሉላ፣ ስታሊን፣ ስለሞን ተካልኝ ወዘተ የሚቀኝ ሀሳብ አይሆንም። ትግራይ በጥሩ ሀገራዊ አቋሟ አንዱ ባላና ምሰሶ ነበረች። ይህ በመሆኑ፣ የምሐል ሀገሩ (ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃም፣ ጎንደር)፣ የወለጋው፣ የአፋሩ፣ የከፋው፣ የሱማሌው፣ የከባታው፣ ወዘተ በከንቱ ሃሳብ ተነስቶ የቀረውን ግዛትና ሕዝብ ለክፉና ለጠላት አጋልጦ እንዳይሰጥ ሌሎቹ አውታር በመሆን እያገለገሉ ኖረዋል። ኦሮሞ የተባለው ግዛት የተነደፈው በውጩ ኃይል እገሮች ሲሆን፣ አላማው የጠቅላላ የኢትዮጵያን ደቡብ ምድር ለመቆጣጠር ታስቦ ነው። አቀራረጹን የተገነዘበ ይህንን አላማ አይስትም። ኦሮሞን ለመቆጣጠር፣ የምሐል ሀገሩን (አማራ) አስቀድሞ መሰናክል እንዳይሆን መቆጣጠር አስፈልጓል። አማራን ለማድከም ትግሬን ማድከም ያስፈልጋል። ትግሬን በቀውስ አስተሳሰብ ቀስቅሶ መስዋዕት ማድረግ አስፈላጊ ነበር። ትግሬ እንደ አንድ ትልቅ ግዛት ኃይል ለመሆን አሁን ሙሉ በሙሉ መክናለች። የመሐል አገሩ ሀይል አጋዡን አጥቷል በሚለ አስተሳሰብ ወደ ኦሮምያ ምድር ጉዞው ቀጥሏል። የነ እዝቅየል ተራ ነው የኦሮሞን ሰው እንደ ወያኔው ለማምከን። እዝቅየል ከነደብረጽዮን፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ወዘተ የማይተናነስ አረመኔ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ በቂ ንቁ ሰው አለው የሚል ግምት አለ። እነ ሽመልስን፣ በቀለን፣ የቀረውን የሸኔ መንጋ መቋቋም ይችላል። የምሐሉ ሀገር ወያኔን (ትሕነግን) እንደተቋቋመ የታቀደለትን የጥፋት ሂደት አስቦ መነሳት አለበት። አለበለዚያ ከ10 ዓመት በማይበልጥ መሬቱን አጥቶ የፋክተሪ ወለል ጠራጊ ይሆናል። ወተት ገዝቶ የሚጠጣ፣ እሸት ከገባያ የሚገዝ የወዝ አደር ሰው ይሆናል ዕድል ለተረፈው ሰው።
አክሱም የብዙ መቶ አመት ምናልባት የሺህ ዘመንት ስልጣኔ ቁንጮ ነበረች። ሶስት ሺህ ሲባል ከዚያ በፊት የነበረውን የስልጣኔ ታሪክ አያመለክትም። የዘመኑ የትግራይ ሰው አመጣጡ ቅርብ ነበር። የትግራይ ታሪክ ክርስቶስ ከመወለዱ ከስድስት አመት በፊት በኢትዮጵያ አይታወቅም። የመካከለኛው ምስራቅ የሶሪያና ኢራክ ሕዝብ በወራሪ እየታወከ የሚኖር ሕዝብ ነበር። ሽሽትና መፈናቀል የበዛበት ስለነበር ወደ ደቡብ ምድር በብዛት ይጎርፍ ነበር። ይህ ስደተኛ ሕዝብ ነው ቀይ ባህርን አቋርጦ ኢትዮጵያ ምድር የሰፈረው። የኢትዮጵያ ነገሥታት በየጊዜው እየተቀበሉ መጠልያ ሰጡት። በሰፊው የታወቀው ይኼው የኢትዮጵያ ደግነት በነብዩ መሀመድ ተጠቅሷል። የግሪክ ፈላስፋዎችም በተረኩት ታሪክ ላይ ይነበባል። ስለዚህ፣ አክሱም የማራውና የአዳሉ፣ የብሌኑና የእገው ታሪክ እንጂ የትግራይ አለመሆኑን ወያኔዎች ቢያውቁ ለማይመለከታቸው ታሪክ ተቆርቋሪ ሲበዛም የተሪኩ ባለቤትነትን ባልተመኙ ነበሩ። ከዚህ ውጭ ግን ትግራይ የኢትዮጵያ ታሪክ ታሪካቸው አይደለም ማለት ፍጹም ስህተት ይሆናል።
አባ በዝብዝ ኋላ አፄ ዮሐንስ አራተኛው የተባሉት የኢትዮጵያ ንጉሠነገሥት ሲሆኑ የትግራይን ንጉሦች (መሳፍንቶች) ካወደሙ በኋላ እናም አፄ ቴዎድሮስ በእንድሊዝ ጦር እጅ ከመማረክ ራሳቸውን ማጥፋት የሀገራቸው ታሪክ እንዲጠበቅ አድርጉ። እንዳጋጣሚ፣ እንግሊዞች ራስ በዝብዝን የቅኝ ግዛት እንደራሴ አድርገው ሀገሪቱን በቁጥጥራቸው አርገው አልሄዱም። ራስ በዝብዝ ንጉሠነገሥት ሆኑ። ዳሩ ግን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያጸድቀው ሲዎርድ ሲዋረድ የመጣው የቀዳማዊ ምንሊክ ሥርዎ መንግሥት ዘርፍን ስለነበር ስርዎመንግሥቱ ወደ ዳግማዊ ምንሊክ ተላለፈ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ተቀበላቸው። ከዚያ ውጭ የነበረው ጥቂቱ የእፄ ዮሐንስ ብሰተኞች ነበሩ። የነዚህ ብሰተኞች ባህሪ የውጭ ጠላት ለሆኑ ቀዳዳ ሰጥተዋል። ይህን የብሰተኞች (የወያኔ) አቋም ያፋፋሙ አስካሪዎች ትሕነግ ተፈጠሩ። አገር መሸጥ ሳይሆን የሚታያቸው ሀገር የመቆርቆር በውጮቹ ጠላቶች የተደገፈ አላማቸው ሆነ። ጌታና አሽከር ተፈጠረ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአምላኩ ስለሚያምን በእንድነት ኃይሉ ትልቁን አላማ አከሸፈ። አንድ ሌላ ይቀረዋል።
የአለም ታላላቅና ትናንሽ ሀገሮች ባለፈው ሁለት አመት ያሳዩት ሚና አስገራሚ ነው። ትልቅ ድራማ ተሰርቷል። አክተሮቹ ድራማውን እንደማይሆን አድርገውታል። በስቴጁ በኢትዮጵያ ያልሆኑትን ሆነዋል። የሚጫወቱት ሚና ባንድ በኩል የተቃራኒ ባህሪያቸውን ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የዕውነተኛ ጥቅማቸውን ሲያራምዱ ታይተዋል። ዋናው የታየ እና ያልታየ አላማቸው በመካከላቸው ያለውን የጥቅም የፖለቲካ የበላይነት ግብግብ በኢትዮጵያ ምድር ላይ በማድረጋቸው ነው። ይህ ሲሆን፣ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ሳይሆን፣ እየሳተ አህያውን የገረፈ እየመሰለው ዳውላውን መውቃቱ ነው። ያም ከሆነ ተሰምቶታል እንበል። ግን ለዳግም ተመሳሳይ ተጻራሪ ነገር ሲፈጠር ማን በየት እንደተሰለፈ ማወቅ ይገባል። ማን ምንድነው ባህሪው ብለን የምንጠይቀው አያሌ አይደለም። ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ተንኮለኛው እስራኤል ምንድናቸው? እንግሊዝ አሜሪካ ምን እየሆኑ ነው? ማንን በምን ጥቅም ላይ እንገምግማቸው? አንድ ናቸው ወይስ በውስጥ መስመር ልዩነታቸውን ያካሂዳሉ? በመጨረሻ ለኢትዮጵያ የሰላም መንገድ አስጊ የምሆኑት እነማን ናቸው? በምንስ ምክንያት? ይህን አጥብቀን ማወቅ አለብን። ይህ ደግሞ ቀደም ብሎ የተፈለመ ስለሆነ በረጅሙ እጃቸው፣ በሚገቡበትና በሚታዩበት ሁሉ እንለያቸው። ደግሞ ካባና ጋቢ ለብሰው ቢመጡ አናሳስታቸው፣ እነሱ ግን የማምታታትና የማዘናጋት ጥበባቸው የላቁ ናቸው።
ሰላምን እየተመኘሁ
ዘውገ ፋንታ