የዐማራ ሕዝብ ግራኝ አሕመድ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ከፈጸመበት ወረራ እስካሁን ድረስ ጨርሶ አላገገመም፡፡ ወለጋን፣ አሩሲን፣ ባሌን፣ ገሙገፋንና ሐረርጌን በመሳሰሉት የገዛ ራሱ በነበሩ ግዛቶች ውስጥ መጤ እየተባለ በኦነጋውያን የሚጨፈጨፈው፣ ከግራኝ አሕመድ ወረራ ጨርሶ ባለማገገሙ ምክኒያት ነው፣ ጨፍጫፊወቹ በነዚህ ግዛቶች ላይ የተስፋፉትና የተንሰራፉት ግራኝ በቀደደው በር ገብተው ነበርና፡፡
ከግራኝ አሕመድ ወረራ ያላገገመው የአማራ ሕዝብ፣ ከግራኝ አሕመድ ቢበስ እንጅ የማያንስ ወረራ በወያኔ ተፈጽሞበታል፡፡ ከግራኝ ወረራ በመጠኑም ቢሆን ለማገገም ምዕተ ዓመታት እንደፈጀበት፣ ከወያኔ ወረራ በመጠኑም ቢሆን ለማገገም ምዕተ ዓመታት እንደሚፈጅበት እሙን ነው፡፡
የአማራ ሕዝብ በመጠኑም ቢሆን የማገገም ዕድል የሚኖረው ግን ለመጀመርያ ጊዜ በግራኝ አሕመድ፣ ለሁለተኛ ጊዜ በወያኔ የተፈጸመበት ዓይነት ወረራ፣ ለሦስተኛ ጊዜ በወያኔም ሆነ በኦነግ ካልተፈጸመበት ብቻና ብቻ ነው፡፡ የግራኝና የወያኔ ዓይነት ወረራ ለሦስተኛ ጊዜ ከተደገመበት ግን፣ የአማራ ሕዝብ ወይ እንደ ደራሳ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ አለያም እንደ ዶርዜ ሕዳጣን መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
የሕልውናው ጦርነት ዋና ዓላማ ደግሞ ወያኔን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት፣ ትልቁን የአማራ ሕዝብ ሌላው የኢትዮጵያ ደራሳ ወይም ዶርዜ ለማድረግ ለሚያስብ ሁሉ መቀጣጫ ማድረግ ነው፡፡ በሌላ አባባል የሕልውናው ጦርነት ዓላማ በግራኝ ተጀምሮ በወያኔ ለሁለተኛ ጊዜ የተደገመው ዓይነት ወረራ፣ ለሦስተኛ ጊዜ መቸም ቢሆን እንደማይደገም ማረጋገጥ ነው፡፡
ወያኔ አራት ኪሎ ከተቀመጡት የብልጽግና ፀራማሮችና የነሱ ሎሌወች ከሆኑት ከብአዴን ሆድአደሮች ጋር ተመሳጥሮ፣ እንዲሁም ወለጋ ውስጥ ከመሸጉት ኦነጋውያን ጋር ተባብሮ ጎንደርንና ላኮመልዛን የወረረው ለማውደም፣ ለመጨፍጨፍና ለመዝረፍ እንጅ ለወታደራዊ ዓላማ አልነበረም፡፡ ባለመታደል ደግሞ ይህ አልፋና ኦሜጋው አማራን መጥላትና መጥላት ብቻ የሆነ፣ ዕድሉን ባገኘ ቁጥር ዐማራን ለማውደም፣ ለመጨፍጨፍና ለመዝረፍ ተጠንቅቆ የሚጠባበቅ ቡድን፣ ከሞላ ጎደል በሁሉም የትግራይ ሰወች ዘንድ ከመወደድ አልፎ ይመለክበታል፡፡
የትግራይን ሰው ወያኔን አትውደድ ወይም አታምልክ ማለት አይቻልም፣ መብቱ ነውና፡፡ ወያኔ ዐማራን በመጨፍጨፍና በመዝረፍ የሚያገኘውን ጥቅም ተካፋይ መሆን ግን መብቱ አይደለም፡፡ ወያኔ የአማራ ትምህርት ቤቶችን እያፈራረሰ በሚወስዳቸው ወንበሮችና ጥቁር ሰሌዳወች የትግሬ ልጆች ሊማሩ አይችሉም፡፡ ወያኔ ከየሆስፒታሎቹ እየወላለቀ በሚያግዛቸው አልጋወች፣ የትግራይ ሕሙማኖች ሊተኙ አይችሉም፡፡ ወያኔ ከአማራ ገበሬ ጣራወች እየገነጣጠለ በሚጭናቸው ቆርቆሮወች የትግራይ ገበሬ ጣራወች ሊከደኑ አይችሉም፡፡ ወያኔ ከአማራ ከተሞች የሚነቃቅላቸው ጀነሬተሮች በትግራይ ከተሞች ላይ ሊተከሉ አይችሉም፡፡ ባጭሩ ለመናገር ያማራ ቤት ፈርሶ የትግሬ ቤት ሊበጅ አይችልም፡፡ አማራን አገር አሳጥቶ ትግሬን ባላገር ማድረግ አይቻልም፡፡
ስለዚህም፣ የሕልውናው ጦርነት የመጀመርያው ዓላማ መሆን ያለበት የዘመኑን ወያኔወች እተፈጠሩበት እደደቢት ድረስ ሂዶ ድባቅ መምታትና፣ የተራረፉትን መሪወቻቸውን ደግሞ ለፍርድ ማቅረብና ተገቢውን ቅጣት መስጠት ነው፡፡ ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው ደግሞ የናዚ ወንጀለኞች ባንድነት ተሰባሰበው ለፍርድ በቀረቡበት በኑረምቤርግ ችሎት (Nuremberg trials) ዓይነት ነው፡፡ ከያሉበት ተለቃቅመው፣ ባንድነት ተሰባስበው፣ በይፋ ችሎት ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው ደግሞ፣ ትልቁን ጥፋት ባደረሱበት በላኮመልዛ ሕዝብ ዋና ከተማ ደሴ ላይ ነው፡፡
የዘመኑን ወያኔወች በጦርነትም፣ በችሎትም ማስወገድ ግን የአማራን ሕዝብ ከሌላ የወያኔ ወረራ አያድነውም፣ የወያኔ የአማራ ጥላቻ ከሞላ ጎደል በሁሉም የትግራይ ልሂቃን ልብ ላይ ተዘርቶ፣ አፍርቶ፣ ጎምርቷልና፡፡ በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት ሰወች በስተቀር የትግሬ ልሂቅ የሚባል ሁሉ በአማራ ጥላቻ ከመስከር አልፎ ጠንብዟል፡፡
ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ከሌላ የወያኔ ወረራ ሊድን የሚችለው እነዚህን በአማራ ጥላቻ የጠነበዙ የትግራይ ልሂቃኖች ራሱ የትግራይ ሕዝብ በጽኑ እንዲዋጋቸው በማድረግ ብቻ ነው፡፡ በጽኑ እንዲዋጋቸው ማድረግ የሚቻለው ደግሞ እነሱ በቀደዱለት ቦይ ከፈሰሰ መዳረሻው ቀላይ እንደሆነ በግልጽና በተግባር በመሳየት ነው፡፡
በግልጽና በተግባር ከማሳየቻ መንገዶች ውስጥ ደግሞ አንዱና ዋናው ተመጣጣኝ ካሳ ነው፡፡ ወያኔ ጎንደርንና ላኮመልዛን ወርሮ መጠነ ሰፊ ጥፋት ያጠፋው፣ በውስጥም በውጭም ያለው የትግራይ ሰው ሁሉም በሚባል ደረጃ መጠነ ሰፊ ድጋፍ ስላደረገለት ነው፡፡ ስለዚህም ወያኔ ላጠፋው ጥፋት መላው የትግራይ ሕዝብ ተገቢውን ካሳ መክፈል አለበት፣ ናዚ ላጠፋው ጥፋት ካሳ የከፈለው ናዚን በስፋት የደገፈው መላው የጀርመን ሕዝብ እንደሆነ፡፡
የትግራይ ሕዝብ ለአማራ ሕዝብ ካሳ የሚከፍለው ደግሞ ከሚከተሉት ከሁለቱ መንገዶች ባንዱ መንገድ ነው፡፡ የትግሬ ሕዝብ ከቀረው የጦቢያ ሕዝብ ጋር አብሬ ብኖር ይበጀኛል ካለ፣ ለትግራይ ክፍለ ሀገር ከሚመደበው በጀት ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ አምሳ በመቶው እየተቀነሰ፣ ለጎንደርና ለላኮመልዛ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች መሥርያ እንዲውል በማድረግ ቢያንስ ቢያንስ ለአምሳ ዓመታት ካሳ መክፈል አለበት፡፡ የትግሬ ሕዝብ ከጦበያ ተገንጥየ ደሴት በመመሥረት የጦቢያ ሌሶቶ (Lesotho) እሆናለሁ ካለ ደግሞ መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ ሊባል ይገባል፡፡ ወደ ሌሶቶ ከማቅናቱ በፊት ግን ከሱ አብራክ በተወለደውና የሱ ሙሉ ድጋፍ ባለው በወያኔ አማካኝነት በአማራ ሕዝብ ላይ ለደረሰው ጥፋትና ውድመት ሙሉ ካሳ እንደሚከፍል አስገዳጅ ፊርማ መፈረም አለበት፡፡
የአማራ ሕዝብ በትግራይ በኩል ሊመጣበት የሚችለውን የወደፊት አደጋ ማስወገድ የሚችለው በዚህ መንገድ ነው፡፡ የትግሬ ሕዝበ ለራሱ ቆዳ ሲል ወያኔንና የወያኔን ፀረማራ አስተሳሰብ በጽኑ ሲዋጋ ከተመለከተ ደግሞ፣ የኦሮሞ ሕዝብም ለራሱ ቆዳ ሲል ኦነግንና የኦነግን ፀራማራ አስተሳሰብ በጽኑ ይዋጋል፡፡
መስፍን አረጋ