ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ እና ዶክተሩ መሪዋ (ድንቄም ዶክተር) – ከፋንታ ስለሽ

ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ በበፊት አጠራሩ ኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አንጋፋ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ነበር፡፡ በተቋሙ ውስጥ የነበሩ መምህራን የአካዳሚክ ብቃታቸው ልዩ ነበር፡፡ በተቋሙ ሰልጥነው የሚመረቁት ተማሪዎችም በስራ አለም ላይ የነበራቸው ብቃት የሚያስደንቅ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር በነበር ቀረ፡፡

በቅርቡ ተቋሙ የትምህርት ዩኒቨርስቲ  መባሉን ሰማን፡፡ ይህ ውሳኔ ተቋሙን ወደ ነበረበት ከፍታ እንደሚያወጣው የታመነ ቢሆንም አሁን ባለው አመራር ተቋሙ ሊቀየር አይችልም፡፡ ምክንያቱን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

1ኛ. የተቋሙ መሪ ዶ/ር ብርሀነ መስቀል ጠና አቅም አልባ ስለሆነ፡፡ ሰውየው ትምህርት ባለፈበት ያለፈ ሰው አይመስልም፡፡ የመጨረሻ ደካማ ነው፡፡ መቸም ሁሉም ሰው ድክመት ይኖርበታል፤ የእሱ ግን የተለየ ነው፡፡ አጀብ ነው ድክመቱ፡፡

2ኛ. ዶ/ር ብርሀነ መስቀል ጠና የተቋሙ ተልዕኮ ለእርሱ ጉዳዩ አይደለም፡፡ እርሱ ሙሉ ወታደራዊ ትጥቅ በታጠቁ ሁለት ጠባቂዎች መታጀብን እና የካድሬነት ስራውን መስራት እንጅ የተቋሙ ስራ ለእርሱ ጉዳዩ አይደለም፡፡ የተቋሙ ስራ የሚገባውም አይመስለኝም፡፡ ያን ለመረዳት አቅምም ያንሰዋል፡፡ የትኛውም የዩኒቨርስቲ ፕረዘዳንት በታጣቂ ሲታጀብ ታይቶ አይታወቅም፤ እርሱ ግን እንደ ወታደራዊ ጀነራል በወታደር ነው የሚጠበቀው፡፡ አሁን እሱ ማን ይሙት ዝንብ ይወረው እንደሆነ እንጅ ሰው የሚያጠቃው ሰው ነው፡፡ ምክንያቱም በአስተሳሰቡ ልጅ ነው፤ ልጅን ደግሞ ማንም አይተናኮለውም፡፡

3ኛ. በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች በሙሉ በዘር እና በትውውቅ የተቃኑ ናቸው፡፡ ብቃት ቦታ የለውም፡፡ ተቋሙ አዲስ አበባ ከተማ በመገኘቱ ምክንያት በርካታ ምሁራንን ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መሳብ ቢችልም ምሁራኑን እየተጠቀመባቸው ግን አይደልም፡፡ አብዛኛው መምህራን በተቋሙና በመሪው አዝኖ ግቢ የሚመጣው ለማስተማር ብቻ ነው፤ ምርምር አይታሰብም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ማነቆዎች

4ኛ. ዶ/ር ብርሀነ መስቀል ጠና የወያኔን ስርዓት የሚመጥን ሰብዕና ሊኖረው ይችል ይሆናል (ያም ምናልባት)፤ በብልፅግና ስርዓት ግን ለአመራርም፣ ለአባልነትም የሚመጥን ሰብዕና የለውም፡፡ ይህን ሰው የተቋም መሪ ማድረግ ተቋሙን እና የተቋሙን ማኅበረሰብ መናቅ ነው፡፡

5ኛ.ዶ/ር ብርሀነ መስቀል ጠና በበርካት ሙስናዎች የተጨማለቀ ግለሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ በረዳት ምሩቅነት የተቀጠሩትን መምህራን(ተገቢ ባልሆነ መንገድ ዘር ተቆጥሮ የገቡ መምህራን) የሁለተኛ ድግሪ ደመወዝ እንዲከፈላቸው አድርጓል፤ አሁንም ዘርን በመቁጠር የተለያዩ መምህራንን ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በውድድር ሳይሆን በዝውውር አስመጥቷል፤ ምንም የማያውቀው ሰውየ ተመራማሪ ነኝ በማለት በተለያዩ የምርምር ስራዎች ውስጥ በመግባት ዘረፋ ያካሂዳል፤የሚስቱን የእህት ባል(ኮማንደር ዳምጤን) ጡረተኛ የሆነን ግለሰብ ያለውድድር ቀጥሯል፤ ያለ ውድድር የሚቀጠሩ በርካታ ናቸው፡፡

6ኛ. በርካታ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶች ወደ ግቢወ እንዳይመጡ አድርጓል(ከፕሮጀክቱ ውስጥ እኔን ካላስገባችሁኝ በማለት)፡፡ ብዙ የሀገር ውስጥም የውጭም ፕሮጀክቶች ወደ ተቋሙ እንዳይመጡ ያደርጋል እርሱ ጥቅም የማያገኝበት ከሆነ፡፡

7ኛ. ለተቋሙ በሚገዙ እቃዎች ላይ ከፍተኛ ስርቆት ነው የሚፈፅመው፡፡ በግዥ ሂደቱ ላይ ጥቅም የማያገኝበት ከሆነ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ይህንን ጉዳይ ለመሸፈን ዳይሬክቶሬቱን ቀይሮታል፡፡ ለስርቆት እንዲመቸው የማይፈልጋቸውን ሰዎች ከፊቱ ዘወር እንዲሉ ያደርጋል፡፡

8ኛ.ሰውየው የፈፀማቸውን ወንጀሎች በዚች አጭር ፅሁፍ መዘርዘር አይቻልም፡፡ ሰውየው በአስተሳሰቡ ልጅ ስለሆነ ብዙ ስህተቶቸን ፈፅሟል፤(መረጃዎች ከጨረታ ቢሮ፣ ከሰው ኃብት ቢሮ፤ ከምርምር ቢሮ፣ ከፋይናንስ ቢሮ በርካታ መረጃዎች ይገኛሉ)፡፡ መረጃዎች እንዳይጠፉ የሚመለከተው አካል ክትትል ያድርግ፡፡ ሰውየው ባጠፋው ጥፋት ሊጠየቅ ይገባል፤ ከቦታውም ሊነሳ ይገባል፡፡

9ኛ. ሰውየው ስብሰባ ሰብስቦ የሚያወራው ወሬ እንጨት እንጨት ይላል፤ ንግግር አይችል፤ ድክመቱን ለመሸፈን የሚያወራው ወሬ አድማጭን አይመጥንም፤ የመኝታ ቤት ወሬ ሁሉ ያወራል፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ ከትምህርት ጋር የተፋታ ሰው ነው፡፡ እንዴት ያሳዝናል፡፡ ከእውቀት ነፃ መሆን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የግል ወይም የቡድን   የፖለቲካ ትርፍን እያሰሉ አዋጅ ማወጅ የእውነተኛ ለውጥ ባህሪ አይደለም! - ጠገናው ጎሹ

ስለዚህ የሚመለከታቸው አካላት የትምህርት ሚኒስቴር(ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፤ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ) እና የተቋሙ የቦርድ አመራር አባላት የሰውየውን ሁኔታ ገምግማችሁ የእርምት እርምጃ እንደምትወስዱ ተስፋ እያደረግሁ ይህን ምክረ-ሀሳብ የማቀርበው ግን ተቋሙ እንዲያድግ ካለኝ ፍላጎት እንጅ ከግለሰቡ ጋር ምንም ግጭት የለኝም፡፡ እንዴውም ከጎኑ ካሉት ሰዎች አንዱ ነኝ፡፡ በሚያደርጋቸው ነገሮች ተጠቃሚ ነኝ፡፡ ስልጣንም ሰጦኛል ግን የሚገባኝ ሁኖ አይደለም፡፡ የሚያደርገው እና የሚናገረው ነገር ሁሉ አይጥመኝም፤ ስብሰባ ያበዛል፤ጅል ነው፡፡ በተለይ ከአሁኑ አዲስ አመራሮች ላይ ወሬው እና ጉራው በዝቷል፡፡ በዚህ ድክመቱ ደግሞ ሚኒስቴር ሊያደርጉት እንዳሰቡ አውርቶኛል፡፡ ብልፅግና ይህንን ካደረጉ የወያኔ እጣ ፈንታ ነው የሚያጋጥማቸው፡፡

ሰላም ሁኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share