እንዳለመታደል ሆኖ በአስማሳይነት እና አድር ባይነት አስተሳሰብ ደዌ ቁራኛ መሆናችን መድኃኒት አልባ በሽታ ሆኗል፡፡
ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ አንድነት እና በዜጎች የዕለት ተዕለት ደህንነት እና ዉሎ ማደር ጭንቅ በሆነበት ፣ የሰዎች በአገራቸዉ በህይወት ሰርቶ የመኖር የህልዉና እና ነፃነት ጉዳይ አደጋ በሆነበት ዘመን አይቶ እንዳላየ ፤ሰምቶ እንዳልሰማ ያለፉትን ተዋቂ የሚሉን መታወቅ እና ማወቅ እየቅል መሆናቸዉን ካለማወቅ ይመስለናል ፡፡
ከዉስጥ አፍራሽ ተልዕኮ ጌኞች ፣ጥገኞች እና ሞግዚቶች ከፍጥረታቸዉ ጀምሮ ኢትዮጵያን ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነቷን ለማናጋት ጠላት በማለት የማጥላላት የኖረባቸዉ ፀረ ኢትዮጵያዊነት፣ፀረ ዓማራ፣ ፀረ ኃይማኖት ዘመቻ የጥፋት አሜኬላ የዘራዉ ከግማሽ ምዕተ ዓመት አስቀድሞ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ የዜጎች እና የግለሰብ ሠባዊ መብት እና ነፃነት በግፈኞች ይሁንታ እና ማን አለብኝነት ሲገፈፍ እና ግፍ ለሶስት አሰርተ ዓመታት እንደ ሀምሌ ጅረት ሞልቶ ሲጎርፍ አልነበርንም ባዮች ታዋቂ የምንል ከሆነ ባዮች አላዋቂዎች መሆናችንን ከአድርባይነት በላይ ስራችን አስቀድመዉ አስተዋዉቀዉናል ፡፡
መቸም መታወቅ በበጎነትም በክፋት እና ጥፋትም አለ እና ታወቂ ስንል ምን ሰርተዉ ታወቁ ማለትን መልመድ ፣መለማመድ እና ማስለመድ ይኖርብናል፡፡
ሀሰት እና ጥላቻ ፣መድሎ እና አድሎ ፣ጠበታችነት እና ምቀኝነት….. በዚህ በምንኖርባት የክፋት እና ዕብሪት ዓለም ዝነኛ ፤ታዋቂ ስለማድረጋቸዉ መቸም ቢሆን እንግባባለን፡፡
ለአብነት ጨካኞች እና ፈሪዎች በጥላቻ መጋረጃ የተደበቁ ዓለም የማይረሳቸዉ ብዙዎች ሲሆኑ በዚሁ በሀሰተኛ ዓለም በቁማቸዉ ያልሰሩትን የሚያገኑ ፣ ያልደከሙበትን የሚቀሙ ፣ ያሻቸዉን የሚሾሙ ፤የጠሉትን የሚከሱ….ብዙዎች ነበሩ አሉ ፡፡
የአፍሪካችን መሪዎች ሳይሰሩ ፣ሳይመሩ እና ሳይማሩ በህዝብ እና በአገር ጫንቃ የኖሩ ፤የሚኖሩ በህይወት እያሉ በቁም በራስ ወዳድነት እና አምልኮት የታበዩ ብዙዎች ነበሩ አሉ ፡፡
ለአስረጅነት የዛየሩ ሞቡቱ ሰሴኮ፣የሱዳን አልበሽር፣ የየመን አብዱል አዚዝ ፣የቱኒዝያዉ ቤኒ አሊ……እንዲሁም ከመካከለኛዉ ምስራቅ የሶርያዉ በሽር አላሳድ(ዶ/ር) ሲሆኑ ከአዉሮፓ የኢጣሊያዉ ሞሶሎኒ፣ የጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር…. የሜክስሲኮዉ ቀበሮ ካርሎስ፣ የአልቃይዳዉ የ40 ኪ.ግ. ክብደት የነበረዉ ዓለምን በሽብር ተግባርከታዋቂም ታወቂ ከሚባሉት ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡
ወደ ራስ ስንመለስ ባለፉት የረጅም ዓመታት በህዝብ እና አገር የጥፋት እና ሞት ዘመቻ ማንነትን እና ኢትዮጵያዊነትን መሰረት ያደረገ መጠነ ሠፊ ግፍ፣ ሰቆቃ ፣በደል እና ማግለል በዲሞክራሲ እና ልማት ሽፋን ፈላጭ ቆራጭነት እና በአገር ሀብት ላይ መጠነ ሰፊ ምዝበራ ሲካሄድ ባለየ የኖረ እና ይህን ግፍ ባይነቅፍ እንደማይደግፍ ህዝባዊ ዉግንና ያላሳየ ከግፈኞች እና ከበዳዮች አለመሆኑን ማረጋገጥ አይቻልም ፡፡
ይህ ደግሞ ህዝብ እና አገር በማስጨነቅ ከሚታወቁት የተለየ ዕዉቅና እና መታወቅ የተለየ ስብዕና እና ማንነት የሚለይ አይሆንም ፡፡
መታወቅ በዕዉቀት እና ጥበብ ማስተዋል ያለበት አገር እና ህዝብ የሚረባ ሲሆን አዋቂ ታዋቂ ሲያሰኝ ከዚህ ዉጭ መታወቅ ቢቸግር እና ቢጨንቅ ከመሆን ሌላ ትርጉም አይኖረዉም፡፡
ማወቅ ለርዕት እና ዕዉነት ዋስትና መቆም ሲሆን መታወቅ ሲሆን ይህ የሠባዊነት መገለጫ እና የሠዉ ልክ ይሆናል፡፡
አላዋቂ ታወቂ በይምሰል እና ማስመሰል ከመሸነጋገል ባለፈ ከሰሞነኛ ዉዳሴ አይራመድም ፡፡ በማወቅ መታወቅ የበጎ ምግባር ፣ተግባር እና መኖር ፍሬ ስለሚሆን ይህ ለምንጊዜም ስም እና ዓለም ይወርሳል ዝንት ዓለም በታሪክ እና በትዉልድ ሲዘከር ይኖራል ፡፡
የሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ስም ያወርሳል….የሚሉት አበዉ መታወቅ በበጎም ፤በክፉም አለ እና በጎ እና ከመቃብር በላይ የሚኖር ህያዉ ስራ በምግባር እና ተግባር ትተህ ዕለፍ ነዉ ፡፡
ይህም የታላቁን አስክንድር እና የቀደሙትን የዕኛዎች ህያዋን ወዋኞቻችን ያስታዉስ ዘንድ የታላቁን አስክንድር ኑዛዜ ልበል “ እጀን ከመቃብር በላይ ….. ” ፡፡ አስተዉሎት ወይም ዕዉቀት ማለት ሞትን እያሰቡ ህያዉነትን ተስፋ ማድረግ ነዉ ፡፡ ይህን ጊዜ የማይሻር ፤የማይቀየር መታወቅ በማወቅ ይደምቃል ፡፡
“በዚህ ዓለም ሲኖር ደስ የሚለዉ ነገር ፤
እንደ ሚሞት አዉቆ እንደማይሞት መኖር፡”(……..)
ይህም ህያዉነት በዕዉቀት እና ዕዉነት የሚገኝ በተግባር የሚገለጥ የማይደለዝ ፤ የማይበረዝ ስብዕና ነዉ፡፡
ማላጂ
አንድነት ኃይል ነዉ !!!