ጥያቄ ለዶር እሌኒ ገ/መድህን – ሰለሞን ስዩም

/ር እሌኒን መጀመሪያ ያየኋት ቴድቶክ የሚባለዉ መድረክ ላይ ነበር (https://youtu.be/9ZwNaaJxw40)። እጅግ ተመስጬ በኩራት ነበር ያየሁት።  የእህል እጥረት ወይንም ድርቅ ተብሎ የሚገለጸው ችግር ትክክል አይደለም፣ በቂ እህል አለ ግን ችግሩ ገበያ ማግኘት ነው የሚለውን አሳማኝ ንድፈሀሳቧን ይዛ ኢትዮጵያ ገብታ የኢትዮጵያን ምርት ገበያ ድርጅት (ECX) ማቋቋማን እንደትልቅ የሀገር ድል አይቼ ተደስቼ ነበር። የ2000 /ምሩን ቀነኒሳ በቀለንና የ2001 ..ሩን ቡልቻ ደመቅሳን ተከትላ በሁዋላ ላይ ጂማ ታይምስ የተባለዉ የየሩ ጋዜጣ ባዘጋጀዉ ሽልማት የ2002 .. የአመቱ ሰዉ ተብላ መመረጧንም እሰየዉ ብዬ ነበር። በቂ ትምህርትና የሥራ ልምድ ቀስሞ ተመልሶ ሀገርን አገልግሎ እዉቅና ማግኘት በርግጥም አስደሳችና አራያነት ያለዉ ተግባር ነዉ።

ዉሎ አድሮ ግን አንዳንድ ጥናታዊ ጽሁፎችን አስደግፈው የቀረቡት ስራዎች ላይ የምርት ገበያዉ ድርጅት ገበበሬውን ጎድተዉታል፣ ከገበያ የጨረታ ዋጋ ባነሰ የገበሬውን ምርት ሰብስቦ ለወያኔዉ ለኤፈርት አቅርቧል፣ ክልላዊ አድልዎም ይደረግ ነበረ የሚሉ ክሶች ሰምቻለሁ። ነገር ግን ይህቺ  በአለም አቀፍ ታዋቂ ተቋማት የሰራች፣ የስመጥሩዎቹ የስታንፎርድና የኮርኔል ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ እንዲህ ያለ ነገር ውስጥ አትገባም፣ በተለመደው ተንኮሉና ስግብግብነቱ ወያኔ የገበያ ድርጅቱን ሥራ አበላሽቶባት ይሆናል እንጂ ዶ/ር እሌኒ እንደዋዛ ህልሟንና አሻራዋን የተወችበትን የህይወቷን ትልቅ ስራ አታበላሽም ብዬ ማሰቤ አልቀረም።

እውነታውን ለባለሞያዎቹ ትቼ ርዕሱ ላይ ወደተመለከቱት ጥያቄዎቼ ልሂድ።

ከሰሞኑ አምባሳደር ብርሀኔ፣ ፕሮፌሰር ይስሀቅ እና ዶር እሌኒ የተገኙበት የዙም ስብሰባ ላይ ዶ/ር እሌኒን ለማየት ችያለሁ። ብዙም ባትናገርም አንዳንድ እንደዋዛ የሰጠቻቸዉ አስተያየቶች ነበሩ። ከዚህም ጋር በተያያዘ በሀገርም ዉስጥ ሆነ በዉጪ እየቀረቡ ያሉት ዘገባዎች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያዉያኑ ሀዘን የበረታዉ ዶ/ር እሌኒ ላይ ነዉ። ከትህነግ የሽብር ቡድኑ መሪዉ ከአምባሳደር ብርሀኔም ሆነ ከሰብሳቢዉ ከፕሮፌሰር ይስሀቅ በተለየ ሁኔታ የሚመለከታትና ሀገሯንና መንግስቷን በታማኝነት አሁንም ታገለግላለች ብሎ አቅርቦ ያያት ሰዉ እንደነበረች ይገመታል።

ሌላዉ ጥያቄ በዚሁ ስብሰባ ላይ ሰምቼ በሁዋላ ያየሁት አዲስአበባ የዶ/ር እሌኒ አባቷ ያሉበት የለጋጣፎ መኖሪያ ቤቷ በመፈተሹ በእጅጉ ተቆጥታና አዝና ያስቀመጠችዉን ሰፊ የትዊተር ጽሁፍ ይመለከታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰላም ስምምነቱ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ትክክለኛው የትግበራ ስራ በቅርቡ ይጀምራል፣ ቀጥሎስ ምን ይጠበቃል? - ሰዋለ በለው

በነዚህ ሁለት ጉዳዮች ዙሪያ አንዳንድ ጥያቄዎች ላንሳ።

1) በስብሰባው ላይ ዶ/ር ኢሌኒ ፓለቲካ ውስጥ የለውም የምትለው ወኃ ያነሳል? ሞቅ ካለው የቆየ የወዳጅ ሰላምታ በሁዋላ፣ አምባሳደር ብርሀኔን የምትሰራውን አደንቃለሁ በርታ ይቅናህ አይነት ንግግር ነበር ያደረገችው። ዲሲ ላይ የአማራ ብቻ ሲቀር የማይታወቁ ሰዎችን በዘር ሰብስቦ እርሱ እንደገና በቁንጮነት የሚመራዉ ኢሕአድግ ቁጥር 2 የፌዝ ኮንፈደሬሽን በማቋቋም ለመፈንቅለ መንግስት የተንቀሳቀሰው ይሄ የትህነግ መሪ ነው የሚደነቀው፣ እንዲሳካለትስ የሚጸለይለት? ከዚህ በላይ ምን ፓለቲካ አለ? ወይንስ ሴራዉን በአግባቡ ባለመረዳት በየዋህነት የተሰጠ አስተያየት ነበር? በርግጥ ለዚህ ጥያቄ ሙሉ መልስ መሆኑን እርግጠኛ ባልሆንም ዶ/ር እሌኒ ማብራርያ ሰጥተዉበት ለህጋዊዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያላቸዉን ድጋፍ በጽሁፍ መግለጻቸዉን አይቻለሁ። ምናልባትም መልሱ በቂ ነዉ በሚባል ደረጃ ለአምባሳደሩ በሰጡት አድናቆትና የስኬት ምኞት ላይ እንደገና ማብራሪያ ማስጠት ይኖርብዎት ይሆን?

2) /ር እሌኒ ከሽግግሩ በሁዋላ ስለ መልሶ ግንባታ (ሪኮንስትራክሽን፣ ማርሻል ፕላን) ስታወራ ይህ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወግዶ ከሚመጣው አዲስ መንግስት ጋር ስለሚሰራ ሥራ የሚመስል አንድምታ አለው። ይህንን ቃል የአሜሪካ መንግሥትም ለኢትዮጵያ ሰጥቶ ነበር የሚታዘዝለት ቢሆን ኖሮ። ፓለቲካዊ ይመስላል። ግን ይህም በጦርነቱ ለደረሰው አጠቃላይ ዉድመት እንጂ ከመንግሥት ለውጥ ፍላጎት ጋር ያልተገናኘ አስተያየት ሊሆን ይችላል? አብራሪያ ቢታከልበት።

3) /ር እሌኒ አዲስ አበባ ቤቷ መፈተሹን እርሷ፣ አምባሳደር ብርሀኔና ፕሮፌሰር ይስሀቅ አንስተዉ መንግስትን ኮንነዋል። አምባሰደሩ ስሟን ተከትለዉ በዘር ላይ የተመሰረተ ፍተሻ መሆኑን አስረድቷል። ዶ/ር እሌኒም ባለ11 ክፍል ሰፊ ትዊት ጽፋ ነበር።

ግን ምንድነው ችግሩ? በዚህ አደገኛ ጊዜ፣ ቤቴ ተፈተሸ ብሎ እርስዋ ካላት ትልቅ ቦታ አኳያ በአስተዳደሩ ላይ በአደባባይ ክስ እንዴት መደርደር ይቻላል? የተገረፈ፣ ቶርቸርድ የሆነ፣ የተዘረፈ፣ የታሰረ ሰው አልነበረም። የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው የሚያገለግሉትን የኔ ነዉ የሚሉትን መንግሥት በአደባባይ በዚህ ልክ መኮነንና ማሳጣት የጤና ነው? ይህስ ከፓለቲካ ጋር ያልተገናኘ በየዋህነት የቀረበ አስተያየት ሊሆን ይችላል?

በአምባሳደር ማእረግ ሀገራቸውን ያገለገሉት የ96 አመት የዕድሜ ባለጸጋ አባቷ ይደነግጣሉ ተብሎ ጨቅላ ህጻናትን እንደ ቅጠል የሚያረግፈው ወያኔ ለአዲስ አበባ አዘጋጅቶት በነበረዉ የእልቂት ድግስ ሊደርስ የሚችለውን ሽብር በመገመት መታገስ እንዴት አቃታት? አባቴ ፈታሾቹን በማየታቸው ለአምስት ሙሉ ሰአት ተሰቃዩ ስትለን አሸባሪው ትህነግ ባደረሰው እልቂት ስንት ጨቅላ ህጻናት ከነሙሉቤተሰባቸው ለእድሜ ልክ መሰናበታቸውን ግምት ውስጥ ማስገባት እንዴት አልተቻለም? ይህስ ከጀርባዉ መንግስትን የማጣጣል ፖለቲካ ሊሆን አይችልም? ወይንስ ብዙ ችግር ሳያይ ምናልባትም አብዛናዉን እድሚዉን በዉጪ ሀገር ለኖረ አንድ ቅንጡ ሰዉ በየዋህነት ሊያቀርበዉ የሚችለዉ ቅሬታ ነዉ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለአልሙዲ “ማፅናኛ”

/ር እሌኒ እንደጠቆመችዉ ጥቆማው የሀሰት ሊሆን እንደሚችል ታዉቋል። ግን እርሷ እንኳን ንጹህ ብትሆንም ወያኔ እርስዋ ግቢ ውስጥ ደብቆ የቀበረው መሳሪያ ቢኖርስ? በየቤተክርስቲያኑ የጦር መሳሪያ ደብቆ ለሚያስቀምጥ ድርጅት ይሄ አይጠረጠርም ማለት አይቻልም። በተለይ እርስዋ የረዥም ጊዜ ትውውቅና የሥራ ቅርበት ስለነበራት የወያኔ ሹማምንት ቤቷ ይመላለሱ እንደነበር ስለሚገመት ምንም ነገር ማድረግ እንደሚችሉ መጠርጠር አይቻልም ነበር?

ከዚህ ሁሉ ሲያልፍ ኦሮሞም ትግሬም አይደለሁም ማለት ምን ማለት ነው? መንግስት ተጠርጣሪዎችን በዘር ለይቶ ይፈትሻል ብሎ የምእራባውያኑን የሀሰት ከበሮ መደለቅ አይሆንም? ለአሸባሪው ትህነግ ያደሩ ከሁሉም ዘር የመጡ ተጠርጣሪዎች አልተጠቆሙም፣ አልተፈተሹም? አሸባሪዎቹ ትህነግና ኦነግ ሸኔ ዘርን መሰረት በማድረጋቸዉ ፍተሻዉና ጥቆማዉ በአብዛኛዉ ወደነዚህ ቡድኖች ላይ ቢያተኩር ለምን ያስቆጣል። እንዲህ ያለዉን ፍተሻ እኮ በአደባባይ ቀርበዉ ተገቢነቱን የገለጹ መፈተሻቸዉም ተገቢ እንደነበረ የገለጹ በካታ ሰዎች አይተናል። ለሀገሪቱ ሰላም ሲባል ጉዳዩ እስኪጣራ ምቾታቸዉም ሆነ የተጣለባቸዉ እምነት መጉደሉ ያላስቆጣቸዉ እንዲያዉም መደረግ እንዳለበት አስምረዉ ድጋፋቸዉን ብዙዎች ገለጸዋል። ዶ/ር እሌኒ ይሄ እንዴት ከበዳት?

የዶ/ር እሌኒን አባት ስም በተመለከተ ይሄ ስም በደቡብ ህዝቦች፣ በኦሮሞም፣ በአማራም አለ። ለዚህም ነው የርስዋም አባት ስም የሆነው። በስሟ ምክንያት በዘር ተፈርጃ ነው የሚለው የነአምባሳደር ብርሀኔ ክስ ጌቶቻቸውን ያሳምን እንደሁ እንጂ ኢትዮጵያዉያን ይቀበሉታል? በዚህ ላይ ደግሞ ካስፈለገ እሌኒ ማን እንደሆነችና ከዬት እንደ መጣች በቀላሉ ማወቅ አይቻልም? ምስጢር ነበር?

/ር እሌኒ አንዲት ሴት እንደጠቆመቻት ትገልጻለች። ምንም እንኳን እርስዋ በሀገር ውስጥ በሰፊው ብትታወቅም 17ቱም ፈታሾች (ማን ኢንተርቪው እንዳደረጋቸው እግዜር ይወቅ) ስላላወቋት ተደንቃለች። ባልተለመደ ሁኔታ ከፈታሾቹ ውስጥ /”  እሌኒ ያላት ባለመኖሩና ይህንንም መጠሪያዋን ባለማወቃቸው ተከፍታለች። ነገርግን ይህንን አዙሮ በበጎው በማየት መጽናናት አይቻልም ነበር?

ተጨማሪ ያንብቡ:  የደብረጺዮን ፖለቲካ

የመጡት ሰዎች በደረሳቸዉ ጥቆማ መሰረት ሀገር የማዳን አስቸኳይ ተልዕኮ ይዘው ፈትሸው ለመውጣት ነው። ያደረጉትም ይህንን ነው። ጥቆማው ስህተት ሆኖ ምንም አለመገኘቱ ጠቋሚውን ያስጠይቀው እንደሆን እንጂ ፈታሾችን አያስኮንንም። በዚህ ላይ መንግስት በቂ ስልጠና የተቀበለ ሰፊ የሰው ሀይል ኖሮት እያንዳንዱን ተጠቋሚ አጥንቶ ወደስራ እስኪገባ ድረስ የተፈራው ችግር ቢደርስስ?

ይህንን አስቦ በአርአያነት እንዲያውም በማንኛውም ቤት ፍተሻ እንዲደረግ ማበረታታት ይቻል ነበር። ከሀገር ደህንነት የሚበልጥ ነገር የለም። በዚህ ላይ ተንኮሉ የማያልቅበት ወያኔ ከራሱ ሰው ይልቅ የማይጠረጠሩ ሰዎች ጋ ባለቤቶቹም ጭምር ሳያውቁ ብዙ ነገር መቅበር እንደሚችል አይታወቅም ነበር? ከህዝብ ጋር ተቀላቅለው ይኖር የነበሩ ለወያኔ ያደሩ ከሀዲዎች ደሴ ላይ ያደረሱት እልቂት አዲስአበባ ላይ እንዳይደርስ ሲባል ለሚከፈለው መስዋዕትነት ፍተሻ በጣም ቀላሉ ሆኖ ሊቆጠር አይችልም ነበር?

ሌላው የኮረኮረኝ አስተያየት ዶ/ር እሌኒ ኢትዮጵያን ያገለገለችበትን ህያ አመት መስዋዕትነት የከፈለችበት የቁጭት ጊዜ አድርጋ ማቅረብዋ ነው። ተከብሮ ተሸልሞ ሀገርን ማገልገል ስንቱ ዳያስፓራ የሚመኘው ትልቅ እድል ሆኖ ሳለ እንዴት የሚያስቆጭ መስዋዕትነት ተደርጎ ይቀርባል? የሚቆጨዉስ እንደወጡ ቀርቶ የባእድን ሀገር እያገለገሉ መኖሩ አልነበረም? ባእድ ሀገር ዉስጥ ሰርቼ ወደሀገሬ እመለሳለሁ ለሚለዉ ባእድ ያስኬድ ይሆናል ግን ለአንድ እትዮጵያዊ እንግዳ ነገር ነዉ። ይህስ እንዲያዉ ችግሩን ለማጉላት ያህል ይሆን? ወይንስ የአገላለጽ ስህተት?

/ር እሌኒ ቲዊቷን ስታጠቃልል ለቤተሰብዋና ለሀገሯ በማዘን ነው። ይህም ፍተሻዉን ተከትሎ የቀረበው አስተያየቷ ኢትዮጵያን የሀዘን ማቅ ያለበሰውን ወያኔን ሳይሆን የሚመለከተው ውድ የህይወት መስዋዕትነት ከፍሎ የአጋንንቱን ቡድን የሚታገለውን መንግስት የሚመለከት ይመስላል። እንዴት ሊሆን ይችላል?

/ር እሌኒ በምታገኘዉ አጋጣሚ በማንኛዉም መድረክ ላይ መልስ መስጠት ብትችል እንደኔዉ ተመሳሳይ ጥያቄ ያላቸዉ ሰዎች በቂ ግንዛቤ ሊያገኙ የሚችሉ ይመስለኛል።

ሰለሞን ስዩም

ሲያትል፣ ዋሽንግተን
ኖቬምበር 282021

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share