ጠ/ሚ አብይ አህመድ የሚዋጉት ከኮሎኒያሊዝም ጋር ነው – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

r55c232አሜሪካ ውሥጥ ያሉ ዘረኛ ነጮችም ሆኑ አውሮፓ ውሥጥ ያሉ ፣ ጥቁርን እንደ ደነዝ ነው የሚቆጥሩት ። መቼም “ ነጭ ላም አፈቀርኩ ። ሚሥቴን መሠለችኝ ። “ ባይልም ውሻን በግልፅ ማፍቀሩ ያውም በጠያፍ መልኩ አሣምረው ያውቁታል ። ወዳጄ እብደት ነጭ እና ጥቁር አይልም ። በሁሉም የሰው ዘር ውሥጥ እብደት አለ ። ማን ነበር “ የሞት ጥላ የሚያንጃብበት ፍጡር ላይ ሁሉ እብደት አለ ። መጠኑ ይለያይ እንጂ ያለው ? ” ረሳሁት ። እርግጥ ነው በዓሉ ግርማ በልቦለድ ድርሰቶቹ መሠል ሃሳቦችን ማካፈሉ ትዝ ይለኛል ።

ወድ ወገኖቼ ፣ ሰው ሁሉ በቅርፁ ና በይዘቱ አንድ ነው ። የሚለያየው ተነጂ ና ተነጂ ባለመሆን ብቻ ነው ። ብዙው ሰው ተነጂ የሚሆነው ከህፃንነቱ ጀምሮ በሚጫንበት አሥተሣሠብ ነው ። ከተጫነበት አመለካከት እና አሥተሣሠብ ውሥጥ ተገቢውን አሥቀምጦ ጠቃሚውን ለማሶገድ የሚችል የራሱ የሆነ የህይወት ምልከታ ከሌለው በመንጋ ማሰብን ፣ በመንጋ ማመንን ፣ በመንጋ መፍረድን እንደ ትክክል ይቆጥራል ።

ለምሳሌ በእኛ አገር ሰውን በቋንቋው ፈርጆ በማቅረብ የሥህተትና የጭካኔ መንገድን የሚያሥተምር ና ተከታይ ለማፍራት የውሸት ትርክት የሚፈጥር ሞልቷል ። የእርሱን ሤጣናዊ ፍልሥፍና ትዕዛዝ የሚከተል ፤ የሚተገብር ና ሌሎች የሚያጋባ ፣ የትም ክልል ልታገኙ ትችላላችሁ ።እንደ ትግራይ ክልል ባይበዛም ።

ዛሬ ና አሁንም ጥቂት የማንባል ኢትዮጵያዊያን 30 ዓመት ሙሉ ከተቆራኘን ፣ ሰው መሆንን አሥረሺ የሴጣን ቁራኛ አልተላቀቅንም ። አውሮፓና አሜራካ እንዲሁም ኢሲያውያኑ ህዝባቸው ሰው መሆንን እንዲያምን አድርገው በማሥተዳደር ፣ ከአፍሪካ የሚፈልሱትን ጥቁሮች የራሳቸው ዜጋ በማደረግ በሰውነታቸው አቅፈው ይዘው ፣ አእምሮና ጉልበታቸውን በመበዝበዝ ሲበለፅጉ ፤ አፍሪካውያን ግን በምዕራቡ ና በአሜሪካ ቱጃሮች የብዝበዛ ሴራ ከድህነትና ከድንቁርና እንዳይላቀቁ ተደርገዋል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢህአዴግ የወደፊት ዕጣ ፈንታ | ባይሳ ዋቅ-ወያ

ምዕራባዊያኑ እና አሜሪካ የአፍሪካ ህዝብ በድህነት ማጥ እሥከወዲያኛው እንዲዳክር ለማድረግ ዛሬም አያሌ ሴራዎችን በአፍሪካ እየተገበሩ ነው ። በይበልጥም ኢትዮጵየያውያን ቅሥማቸው እንዲሰበር በበርቱ እየጣሩ ነው ። የኢትዮጵያውያን ውድቀት የአፍሪካ ውድቀት እንደሆነም በበርቱ ሥላመኑ የውክልና ጦርነቱን ገፍተውበት አሻንጉሊት የሽግግር መንግሥት እሥከማቋቋም ደርሰዋል ።

አሜሪካ በደህንነት ድርጅቷ ኦኬስትራነት ኢትዮጵያን የማፈራረሥ ሴራ ጎንጉና በአገሯ የኢትዮጵያ አሻንጉሊት የታክሲ ሹፊሮች ሥብሥብን “ እንደ መንግሥት ማደራጀቷ ቢታወቅም ፤ የኢትዮጵያዊያንን አትንኩኝ ባይነት ና ለነጭ ያለመሥገድ ና ለዘመናት ተከብረው የቆዩበትን የአእምሮ ግዝፈት በለመገንዘብዋ እንደሆነ የታወቀ ነውና በቅርቡ ውርደቷን መከናነቧ አይቀርም ።

ከውርደቷ በኋላም ፣ የአሜሪካ ዜጎች የመሪዎቹን ሂትለር ና ሞሶሎኒነት በመረዳት መሪዎቹን እንደሚያወግዛቸውና በድርጊታቸው እንደሚያፍር አምናለሁ ።

ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፣ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥነታቸው አፍሪካውያን ሁሉ ሊዋደቁለት የሚገባውን ይኽንን ጦርነት ለመምራት ወደ ግንባር የዘመቱት ድልን በአጭር ጊዜ ለማብሰር ና ይኽንኑ እውነት ለዓለም ለማሳየት ነው ።

ከዚሁ ጎንም አፍሪካ የምርጥ ፣ የእንቁ ፣የድንቅና የውብ አእምሮና ጥበብ ባለቤቶች የሚኖሩባት አገር መሆኖንን ለዓለም ለማሳወቅ ነው ።

ከዚህ የአፍሪካ ድል ከሆነው ፣ የኢትዮጵያዊያን ታላቅ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዛዝን ያለመቀበል ጦርነት መጠናቀቅ በኋላ ፣ በራሳቸው አእምሮ የሚያሥቡ ፣ መጋነትን የሚጠየፉ የበዙ አፍሪካውያን እንደሚፈጠሩ እምነቴ የፀና ነው ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.