የዕዉነት ብርኃን በክፉዎች የክህደት መጋረጃ ለጊዜዉ ቢከለልም መንጋት እና ዕዉነት ሆኖ መገለጥ አይቀሬ መሆኑን ከአለፉት ግማሽ ክ/ዘመናት የነበረብንን የህልዉና ችግር እና ስንክሳር ማስታወስ አሁን ስለሚደረገዉ የመጨረሻ ምዕራፍ የህልዉና እና ነፃነት ትግል እና ተጋድሎ ለሚኖረዉ ስምረት እና ዉጤት ፋይዳ ብዙ ነዉ ፡፡
ነገር ግን ከዕዉነት ሽሽት መዳረሻዉ ባይታወቅም ለዘመናት ከመሪር ሀቅ ጋር ያለመገፋጥ እና አድር ባይነት የመከራ ገፍት እና ቀንበር ተሸካሚ ህዝብ በደል እና ዕሮሮ ጊዜ ማራዘም ይሆናል፡፡
ይሁንና ከዕዉነተኛ ቀዳሚ ሁነኛ የታሪክ መስክ መነሳት ይገባል፡፡ የአገር እና ህዝብ ህልዉና ጥያቄ ዉስጥ ሲገባ እና የኢትዮጵያዉያን የህልዉና እና ነፃነት ስጋት እና ትግል ጥሪ ከአንድ ክ/ዘመን በላይ አስቆጥሯል፡፡
ሆኖም የኢትዮጵያ እና ህዝቧ በታሪካዊ ጠላቶች በተለይም በግናባር ቀደምትነት በጠላትነት የሚፈርጀዉ የዓማራ ህዝብ በትግራይ ህዝባዊ ነፃነት ትግል አራማጆች በመመሪያቸዉ ላይ በ1968 ዓ.ም. በማያሻማ ሁኔታ ዘርተዋል ይህንም እንክርዳድ በአሁኑ እያጨድን እንገኛለን፡፡
ለዚህም በት.ህ.ነ.ግ. የአገር ክህደት እና ኢትዮጵያዉያን ወገኖች ዉርደት ስምምነት (መመሪያ/ማኒፌስቶ) አስቀድሞ የነበር ነዉ ፡፡ የኢትዮጵያ እና ዜጎች ህልዉና እና ነጻነት በይፋ አደጋ ላይ የወደቀበት እና የተዶለተበት የት.ህ.ነ.ግ የጥፋት እና ሞት መመሪያ ምክነያት የኢትዮጵያዉያን በተለይም በይፋ ሞት ያወጁበት ዓማራ ህዝብ የነጻነት እና ህልዉና ትግል ዘመን ያን ጊዜ ተጀምሯል፡፡
ይህንም የጠላት የጥፋት እና ሞት እወጃ ስምምነት (መኒፌስቶ) መነሻ መዝገብ ለመጥቀስ ያህል ፡–
መቅድም ፡ የትግራይ ህዝብ ማለት በትግራይ መሬት ዉስጥ የሚኖሩት እና በተለያየ ምክነያት ከትግራይ መሬት ዉጭ ለሚኖሩ ህዝቦች በመላ ያጠቃልላል ይላል ፡፡ ይህም የትግሉ መነሻ እና መድረሻ ትግራይን እና ትግሬዎችን ማቀፍ ነበር ይህም ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን የማይመለከት መሆኑን መረዳት ለፈለገ እና ለቻለ የህልዉና እና ነጻነት በደል እና ትግል አብረዉ መወለዳቸዉን ነዉ ፣
የመሬት ወይም የግዛት አስተዳደር በሚመለከት የትግራይ መሬት በደቡብ አሏኃ፤በሰሜን መረብ ወንዝ….ይል እና በምስራቅም ሆነ በምዕራብ ምልክት አልባ እና ወሰን ክፍት አድርጓል፣ ለምን ? ያለ ነበር ፤አለ ለዚህ ነዉ የህልዉና ነፃነት ትግል ያኔ የጥፋት ገለባዉ ሲከመር የትግል ዕሳት ተቀጣጥሏል፡፡
ይቀጥል እና እንዲሁ የትግራይ መሬት ወልቃይት እና ጠለምትን ያጠቃልላል ይልኃል፡፡ በሌሎች የትግራይ አቅጣጫ ለምን አልተገለፀም ……..ለምን ቢሉ ልቅ አድርግ ዝለቅ፣ ዘባርቅ …ነበር ምኞቱ ፡፡
ከዚህም በላይ የህልዉና አደጋ አረም እና እሾክ የተተከለዉ እንደ ት.ህ.ነ.ግ. ትግል መመሪያ ከ1968 ዓ.ም. ቀድሞ የ፹ ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረ እና ይህም ሲደመር (80+17+27) 124 ዓመት ሲሆን ይህም የህልዉና እና ነፃነት ይፋዊ ክህደት እና ጥፋት ዕድሜ እንደነበር መረዳት ይቻላል፡፡ ይህም የ፻ መቶ ፳ ዓመት የት.ህ.ነ.ግ. ጥላቻ ፅንሰት እና ዉልደት እና መሰረት ዓማራ ማለቱ ዛሬ ሳይሆን ያን ጊዜ የተስማማበት መሆኑን በት.ህ.ነ.ግ የሴራ ስምምነት መመሪያ የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ትግል ዓላማ ፀረ– ዓማራ መሆኑን ከማሳየት በላይ ምን ይጠበቃል ፡፡
ይህም በዚህ የጥፋት እና ሞት ዕወጃ የት.ህ.ነ.ግ መመሪያ ክፍል II (ሀ) የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ትግል ፀረ – ዓማራ ብሄራዊ ጭቆና እና ፀረ ኢምፔራሊዝም በማድረግ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ማቋቋም ይሆናል ከሚል በላይ የብሄራዊ ህልዉና እና ነፃነት አደጋ ምልክት እና ማስረጃ ከየት እና ከማን እንዲመጣ እንጠብቃለን ፡፡
ለዚህ ነዉ ዕዉነት እና ሽሽት ቢያንስ የአንድ መቶ ኃያ ዓመት ጊዜ ሲኖረዉ ዕዉነቱን ከመቀበል እና በዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊነት ስሜት እና ብሄራዊ አንድነት ከመስራት ይልቅ በሰሞነኛ እና በጠባቂነት አስተሳሰብ የህልዉና እና ነፃነት ተጋድሎዉን ጊዜ በማራዘም የአገሪቷን ሉዓላዊነት እና የህዝቧን ነፃነት ማሳጣት እና ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ መጥቷል፤ ደርሷል፡፡
ከ1983 ዓ.ም. ዓም ወዲህ እንኳ ከኢህዴግ ሽግግር ምስረታ ጊዜ ጀምሮ የትግራይን ዲሞክራቲክ ሪፐፕሊክ ለማቋቋም የኢትዮጵያን አንድነት እና ሉዓላዊነት የመናድ እና የማናጋት ጅምር በኢትዮጵያዊነት ጠንከር ያለ ማንነት ያለዉን እና በግንባር ቀደም ጠላትነት የፈረጁትን ዓማራ የማክሰም እና የማዳከም ስልት በማፈናቀል፣ በማግለል፣ በመደለል፣ በመግደል እና በማስገደል የተጀመረዉ የጥፋት እና ሞት ሀሁ… ዘር ፐፑ…ደርሷል ፡፡
እናም ኢትዮጵያዊዉ ነኝ የምንል ሁሉ የህልዉና እና ነጻነት ጉዳይ በተለይም የዓማራ ህዝብ በግፍ እና በገፍ ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ክፍል ከሰማንያ ሶስት አስከ ዛሬ ሰልስት የለም፡፡
የህልዉና እና ነጻነት ትግል በኢትዮጵያዊነቱ እና በማንነቱ ምክነያት ለ ፩ መቶ ዓመታት እየደረሰበት ላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ የሚያጠቃልል መሆን አለበት ፡፡
የህልዉና እና ነጻነት ትግል ያሳስበናል ይመለከተናል የሚል ሁሉ የህልዉና እና ነጻነት አደጋ ትኩሳት የሚሰማዉ በሰሜን ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከዓማራ ክልል ዉጭ ባሉ የኢትዮጵያ ግዛቶች ከትናንት አስከ ዛሬ በግል እና በጀምላ ለሚደረግ ፍጂት ፣ ሞት እና ስደት ሊተኮርበት ይገባል ፡፡
በስል እና ጥሬ በማድረግ ዘላቂ እና አስተማማኝ የህልዉና እና ነፃነት ብሎ ትግል ሳይሆን ከንቱ መግተልተል እንዳይሆን ሊታሰብበት ይገባል ፡፡
ስለ ህልዉና እና ነጻነት የሚደረገዉ ትግል እና ገድል በመላዉ ኢትዮጵያ የዉስጥ ፣የዉጭ እና ጎረቤት የሚስተዋሉ የዜጎች ነፃነት፣ ፍትኅ እና እንዲሁም ከሱዳን ጋር ያለዉ የድንበር ፤ወሰን ጉዳይ ከልዑላዊነት እና ህልዉና አኳያ አብሮ ሊታይ ይገባል
ከዕዉነት በሆነ ባልሆነ መደለል ከራስ ፣ከአገር ፣ ከጠላት እና ወዳጂ፣ ከወሳኝ ቦታ እና ሁኔታ……እንዳሉት ፤እንደተባለዉ ብሎ መሸሽ ….የትም እንደማያደርሰን አዉቀን ከዕዉነት ሽሽት እና ከመወሻሸት ማቆም አለብን፡፡
ከነበረበት ቦታ የሚለቅ ቦታ እንጂ ከእዉነት እና ከራስ መራቅ ጭንቅ ማትረፍ እንጂ ዕርቅ አይሆንም ፡፡ ይልቅ አርሱ ለዓመታት ከዕዉነት ሲሸሽ የነበር ኡንም ከራሱ የሚሸሽ የትም አይደርስም ፡፡
“የዓማራ ህዝባዊ ህብረት እና አንድነት ለብሄራዊ አንድነት እና ደህንነት አልፋ እና ኦሜጋ ነዉ ፡፡”
ማላጂ
“አንድነት ኃይል ነዉ ”