ሰሞኑን አዳነች አቤቤ ወያኔዎች ከፈለጉ ራሳቸው የጻፉት ሕገ–መንግስት አለ ያንን ተከትለው መገንጠል ይችላሉ አለች ተብሎ ከፍተኛ ግርግርና የጸረ–አዳነች ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ እየሰማሁ ነው፡፡ እኔ የሰዎችን ማንነት የማይበት የራሴ የሆነ ምልከታና መስፈርቶች አሉኝ፡፡ ይህች የአዳነች አበቤ የ ንግግር ሐረግ የተመዘዘችወ አደናች ከተናገረቻቸው ብዙ የቁጭትና አልህ ንግግሮች ሁሉ በጥንቃቄ ተጣርታ ነው፡፡ የአዳነች ሙሉ የንግግር መንፈስ ግን የሚነግረን ግን የሴትዮዋን ቆራጥነት፣ እልህና ቁጭት የሞላበት ጀግንነቷን ነው፡፡
አዳነችን ከዚህ በፊት በሰራቻቸው አንዳንድ ነገሮች የምነቅፍባት አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በእነእስክንድር ላይ በአቃቤ ሕግነት ያሴረቸው ወይም ከሴረኞች ጋር የተባበረቸው ከምንም በላይ ከሀዲነትን ሕሊና ቢስነት ነው፡፡ ከዛ በፊት እንዲሁ በገቢዎች ብዙ ስትባል ነበር፡፡ እነዚህ ነውረኛ ድርጊቶች ግን ከአዳነች አቤቤ ከራሷ የውስጥ ማንነት የሚመነጩ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ ከወያኔና ከወያኔ ፈረሶች ጋር ስትሰራ ይልቁንም ደግሞ በኦሮሞ ኦነጋውያ ውስጥ ስትሰራ በእንደነዚህ ያሉ ነውረኛ አሰራሮች መሳተፍ ግድ የሚልበት ጊዜ አለ፡፡ በእኔ እይታ ግን አዳነች አቤቤ ተፈጥሯዊ የሆነ ወይም በልምምድ የራሷ ያረገችው እንዲህ ያለ ነውረኝነት አለ የሚል እምነት የለኝም፡፡ አዳነች ዛሬ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆነችበትን ሂደትም እኔ የምደግፈው አደለም፡፡ በእርግጥም የዲስ አበባ ከንቲባ የሆነችው እንደ ኦሮሞነት እንጂ እንደ ኢትዮጵያዊነት ብቃቷ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሆኖም ግን አዳነች ከንቲባ የሆነችበት ሂደት በኦሮሞነት መንገድ መሆኑ ከፋ እንጂ ከንቲባነቱን በብቃት ለመወጣት ችግር ያለባት አይመስለኝም፡፡ በእርግጥም አዳነች ከንቲባ ከሆነች በኋላ በከተማዋ የምናያቸው አሰራሮች ይበል የሚያሰኙ ናቸው፡፡
ሰሞኑን ደግሞ አዳነች ከአዲስ አበባ ከንቲባነት ዘለግ ባለ ሁኔታ በቁርጠኝነት የተነሳችበት የጸረ–ወያኔ የአዳነች እልህና ቁጭት የተሞላበት ወኔ ለእኔ እንደውም ግርምት ሁሉ አጭሮብጫል ፡፡ ይህች ሰው ዛሬ ኢትዮጵያ መሪ ባጣችበት ወቅት በሙሉ ሥልጣን የመሪነቱን ቦታ ብትይዝ ኢትዮጵያ በእርግጥም ኢትዮጵያን ትመስል ይሆን ነበር፡፡ ዛሬ ከወያኔ ጋር ከቀን አንድ ጀምረው አብረው የነበሩትን እየታዘብን ነው፡፡ አዳነች ዛሬ እየተንቀሳቀሰች የለችበትን አልህና ወኔ የተሞላበት እንቅስቃሴ እስኪ የትኛው ወይም የትኛዋ ባለስልጣን ሲያደርጉት ታያላችሁ?
በእኔ እይታ አዳነች ዛሬ እየሰራች ያለችውን ይህል እያንዳንዳቸው ግማሹን ያህል እንኳን አስተዋጾ ቢያደርጉ ወያኔ አሁን የደረሰችበት የወረራ መስፋፋት ይቅርና ዶቄት ተብላ ከተነገረላት ትቢያም ባልተነሳች ነበር፡፡ እንግዲህ ይህች ሰው ሰሞኑን ወያኔን እንደሚለው ከፈለጉ ትግራይን ራሳቸው በጻፉት ሕገ–መንግስት መሠረት መገንጠል ይችላሉ ስላለች ብዙዎች በአዳነች ላይ አፏጭተዋል፡፡ እውነታው ግን የምናያየው የአዳነች ንግግር እነሱ የጻፉትን ሕገመንግስት የሚባል ተፈጻሚ እንዲሆን ከመፈለግ ሳይሆን ይልቁንም የሴትዮዋን በወያኔ ላይ ያላት ጥርት ያለ አቋምና የወያኔ አሸባሪ ኃይል ፍላጎቱ መገንጠል ሳይሆን በኢትዮጵያ ላይ በወሮበላነት የመቀጠል መብቴን ተነጥቄያለሁ ብሎ እየተዋጋ እንደሆነ ለማሳየት የተናገረችው ነው፡፡
አዳነች ከወያኔ ሕገ–መንግስት ጋር ዝምድናም ያላት አልመሰለኝም፡፡ በባሕሪዋም በድርጊቷም፡፡ አዳነች ይሄ ሕገ–መንግስት የተባለ ነገር ሲሰራ አልነበረችም፡፡ አዳነች በቅርብ ጊዜ ወደ ላይ የመጣች ሰው ነች፡፡ አመጠጧም ደግሞ ቁርጠኝነት በተሞላበት የተግባር ስኬት እንጂ በፖለቲካዊ ውስልትና አልመሰለኝም፡፡ እንደሚገባኝ አዳነች ትኩረት እያገኘች የመጣችው በለማ መገርሳ ጊዜ ነው፡፡ በብልጠትና በአድር ባይነት አይመስለኝም፡፡ እንዲህ ያሉ ባህሪያት በሴትዮዋ ተፈጥሯዊ ማንነት ላይ አይነበቡም፡፡
የሆነ ሆኖ ዛሬ ወያኔን በቁርጠኝነት እየተዋጋ ያለ ባለሥልጣን አለ ከተባለ እኔ ማየት የቻልኩት አዳነች አቤቤን ብቻ ነው፡፡ አስተውሉ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከንቲባ እንጂ የባህርዳር፣ የሚሌ ወይም በአገር ደረጃ ያለ ግዛት አደለም፡፡ ዛሬ ከወንዱም ከሴቱም አንደም ባለስልጣን በጠፋበት ወቅት አዳነች እየተንቀሳቀሰች ያለችው እንደ አዲስ አበባ ከንቲባ ብቻ ሳይሆን እንደ ጦር መሪ፣ የደህንነት ሹምና የአገርን ክብር የማስጠበቅ ታላቅ ሥራ ላይ ነው፡፡
አሁንም አላለሁ አዳነች በኦሮሞነት የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆነችበትን ሂደት አጥብቄ እኮንናለሁ፡፡ አዳነች ግን በኢትዮጵያዊነት የአዲስ አበባ ከንቲባ ከመሆን በላይ ማንነት ያላት ሰው እንደሆነች አስባለሁ፡፡ ከብዙዎች ጋር የማንግባባበት ነገር ቢኖር እኔ ስለወደድኩትና የእኔ ብሔር ስለሆነ ብቻ ሥልጣን ላይ ስላለ የምደግፍ የእኔ ያልሆነው ከሆነ ደግሞ የመነቅፍ አደለሁም፡፡ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያኖች እንድትመራ ሕልሜ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያኖች በሁሉም ብሔር ተብለው በተሸነሸኑት አሉ፡፡ ኢትዮጵያነት በወሬ አደለም፡፡ በወያኔ ሕገ–መንግስት፣ በወያኔ ሰንደቅ፣ በወያኔ ሥርዓትና አሰራር እዲሆሁም አስተሳሰብ እየመሩ ወያኔን በአፋቸው እያወገዙ የሚቆምሩበን ቁማርተኞች እየታዩን አይመስለኝም፡፡ እንደነ አዳነች አቤቤ ያሉ ደፋሮችና እልኸና ቆራጦች ግን መሬት ላይ ያለውን እውነት እንዲህ ደፍረው ሲናገሩት በደቦ ለማውገዝ ቀዳሚ ነን፡፡ በዚህ መልኩ ነጻነት የሚመጣ አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጵያኖች ሆይ እባካችሁ እናስተውል፡፡ የአዳነች አቤቤ ተቺዎች ኢትዮጵያዊ ከሆናችሁ በደንብ አስተውሉ፡፡ የወያኔና አጋሮቹ ሴራ ተባባሪ ከሆናችሁ ግን አስተውሉ አልላችሁም፡፡
አመሰግናለሁ፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
አሜን!