ብድር እና ዕርዳታ ከጥገኝነት እና ተስፈኝነት ዉጭ የሚገኝ ነፃነት እና ዕድገት አይኖርም ናቸዉ ! – ማላጂ

ለዘመናት በዓለም ላይ ዕርዳታ ሰጪ እና ለጋሽ አገራት ለርካሽ ፖለቲካ ጥቅም ትርፍ ለማግኘት በሠባዊ እና የልማት ዕገዛ ስም በማንኪያ ሰጥቶ በአከፋ የመዝረፍ ምኞት የረጂም ዘመናት የዝርፊያ እና እጂ አዙር ቅኝ ግዛት የ21ኛ ክ/ዘመን ስልት ነበር ፤ ነዉ ፡፡

በተስፋፊዎች እና መዝባሪዎች ምዕራባዉያን ፍርፋሪ እና ብጣሪ ቦርጩ እና ጉንጩ እስኪወጠር አይመርጤ አግብሰብስ እና ክብረ ቢስ ታማኝ አገልጋይ አፍሪካዉያን የአሜሪካ ዲሞክራሲ ተቀባይ እና አሳላፊ ተሰላፊዎች ፣ቤተሰቦች እና ተከታዮቻቸዉ ካልሆነ ለአፍሪካ ህዝብም ሆነ ለአገራት የዘመናት ባርነት ለማትረፍ ጠብ ያለ ነገር የለም ፡፡

በዓለማችን በብድር ፣ ዕርዳታ እና ምፅወታ የዕርዳታ ሰጪ አገሮችን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ህዝባቸዉን እና አገራቸዉን ለባርነት እና ዉርደት አሳልፈዉ የሰጡ አገሮች መንግስታት እና ስግብግብ መሪዎች ህዝባቸዉን ለዘመናት ባርነት እና ተስፈኝነት ፤አገራቸዉን ለረቂቅ ግዞት እና ዉርደት ሲሰጡ ከማየት ዉጭ አገራት እና ህዝቦች ሊለወጡ ቀርቶ ጊዜዉ ሲደርስ እና የአገልግሎት ጊዜያቸዉ ሲገባደድ እንደ አራሙቻ ተነቅለዉ ይጣላሉ ፤ ይቃጠላሉ ፡፡

በዓለማችን ከስዉር ጠላት አገራት ከሚገኝ ዕርዳታ ዕዉነተኛ ማንነትን እና ነጻነትን ከማጣት ዉጭ ዘላቂ እና አስተማማኝ ዕድገት ማግኘት ቀርቶ የዕለት ጉርስ ፤የዓመት ልብስ ማግኘት የማይቻልበት መሆኑን ከኢትዮጵያዉያን እና አፍሪካዉያን በላይ የሚመሰክር አይኖርም ፡፡

የትኛዉም ዕድገት በራስ እንጂ ዕድገት እና ነፃነት ለባርነት እና ግዞት ከሚመኝ የዉጭ አካል ፣አገር እና ዓለም መጠበቅ ከጭንጫ (ዓለት) ከተበተነ ዘር ቡቃያ እንደመሻት ነዉ ፡፡

በራሳቸዉ ከራሳቸዉ ችግር በመነሳት ለራሳቸዉ ችግር በራስ መፍትሄ በፅናት ለተነሱ ፣ለቆሙ እና ለተራመዱ አገራት እና ህዝቦች ዕዉነተኛ ማንነት ፣ነጻነት እና ዕድገት ይታይባቸዋል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጦርነቱ ሁኔታ ዘገባ: የወያኔ ፍጻሜ መጀመሪያ ማሳያ - ግርማ ካሳ

ለዚህም ከአዉሮፓ እና ኤሽያ አህጉር ራሽያ፣ ኪዩባ፣ ቻይና፣ እስራኤል …..እንዲሁም ራሳቸዉን በመሆን በቅኝ ግዛት የጉለበት እና ተፈጥሮ ሀብት ቅርምት ላይ ቢሳተፉም አዉሮፓዉያን ያደጉት በራሳቸዉ እንጂ የዛሬዋ የዓለም ገዥ እና አዛዥ ነኝ ባይ አሜሪካ አልነበረም ፡፡ እንዲያዉም ከዘመናት የእንግሊዝ ቅዥ ግዛት የባርነት ቀንበር ለመዉጣት ተረጂ ነበረች እንጂ ረጂ አልነበረችም ፡፡

ወደ ራስ ምድር እና አገር ስንመለስ ኢትዮጵያም ሆነ ህዝቧ ከድንቁርና ፣ ርሃብ ፣ የኢኮኖሚ ባርነት /ጥገኝነት እና ከሁለንተናዉ ጠባቂነት ሊወጡ የሚችሉት በራሳቸዉ ኃይል እና ማስተዋል ብቻ ነዉ ፡፡

የሁላችንም ጠላት ድንቁርና እና አለመተባበር ብቻ ናቸዉ ፡፡ በድንቁርናችን የራሳችንን እና ዓምላክ አብዝቶ የቸረንን ፀጋ ማየት እና መጠቀም አቅቶን ሁሉን ከዉጭ እና ከሩቅ እንጠብቃለን ፡፡

ይህም በፈቃደኝነት መደንቆራችንን አምነን በመቀበላችን ከዉጭ የመጣ መርዝ ፍቱን መድኃኒት ፤ ዕሬት እንደ ወተት የመቁጠር አባዜ በአድር ባይነት እና በይሉኝታ ተለዉሶ ብሶ ብሶ ከራስ ጥል እና የመለየት ህመም ቁራኛ መሆናችን ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ፤ ዜጎች ክብር እና ነጻነታቸዉን በባርነት እንዲያጡ ከሚሰሩት የዉጭ ጠላቶች ጋር በዕርዳታ እና ስጦታ ስም የሚመለከቱ ቢኖሩ የራሳቸዉን የግል እና ቡድን ጥቅም የማስጠበቅ እንጂ ለአገር እና ህዝብ ከዕዳ ክምችት እና ከትዉልድ ባርነት ማትረፍ ሌላ የሚያስከትለዉ ነገር አይኖርም ፡፡

ለሁላችንም ሆነ ለአገር የሚበጀን በተባበረ ክንድ የዉስጥ ጠላት የሆኑትን ድንቁርና እና መለያየትን ከላያችንም ሆነ መካከላችን ማስቀንጠር እና መመንጠር ነዉ ፡፡

የድንቁርና እና መለያት የክፋት እና ጥፋት ጌኛዎችን ማሸነፍ እና አስከወዲያኛዉ ከምንጭ አስከ ስር ለማንጠፍ በዕዉቀት ፣ በህብረት ፣ አንድነት ዕና በተባበረ ክንድ ለጋራ ዓላማ ፀንተን በመቆም ነፃነታችንን እና የእኛነታችንን ልክ በስራ እና በተግባር በመግለጥ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰንደቅ ጋዜጣ ገጽ ሶስት፣ የአዲስ ዘመን ገጽ ሶስት መንትያ

እኛም ሆነ አገራችን ወደ ታላቅነት የስልጣኔ እና ዕድገት ማማ እና ሠገነት የምንወጣዉ ከጠላት ከሚሰጥ መሰላል በመገፋት አይደለም ፡፡

ነፃነታችንን እና ማንነታችንን ከማይቀበል አካል ዕርዳታ እና ብድር መጠበቅ ለዜጎች ባርነት እና ለመጪ ትዉልድ ማብዛት እና ማቆየት ነዉ ፡፡ አሻግሮ የማየት እና ከሌሎች ጠባቂነት በመላቀቅ በራሳችን ሰርቶ የመኖር እና የመከበር ልምድ እና ባህል ማስፋፋት ፣ የራስን ምርት የማሳደግ ፣ የመጠቀም ግዴታ መኖር አለበት ፡፡

በአገራችን እና በራሳችን የምንተማመን ዜጎች ከሆን በአገራችን ምርት እና ዉጤት መኩራት እና ከዉጭ የሚመጣን መተካት ይኖርብናል ፡፡ ይህ ሲሆን ዘላቂ እና አስተማማኝ ዕድገት እና ነጻነት ዕዉን ይሆናል፡፡

አደንዘዥ፣ አስካሪ፣ ቅንጦት እና ዉበት ማደናገሪያ (cosmetics)…. ከዉጭ መግባት መቆም ወይም ከፍተኛ ቀረጥ ሊጫንባቸዉ እና ሊወገዱ ይገባል ፡፡

የአገር ዉስጥ ምርት ማሳደግ እና መጠቀም ዉዴታ ሳይሆን ግዴታ መሆን አለበት ያኔ ኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆኑ ገንዘባቸዉ ( ብር) በዓለም ላይ ቁጥር ፩ ግንባር ቀደም ተፈላጊ መገበያያ “Abyssinia Birr ” ይሆናል ፡፡

ይህም የሚቻል ሆኖ የሚጠራጠር ቢኖር የባዕድ ነፋቂ እና የድንቁርና አሳባቂ ብቻ ነዉ ፡፡ የአሜሪካ ፣ የአዉሮፓ እና አንግሊዝ ገንዘቦች ዶላር፣ፓዉንድ እና ዩሮ…. ዕኮ ቁሶች እና በሰዎች ጠንካራ ህብረት እና አንድነት ጥምረት በዓለም ላይ በኃይል( በህብረት) የመስራት ፣የማምረት እና የማስገደድ እንጂ የተለየ ሚስጢር እና ታምር ስላላቸዉ አይደለም ፡፡

ያለ ነፃነት ህልዉና ፤ ያለህልዉና ነፃነት አይኖርም ፡፡”

ከሁሉም በፊት ብሄራዊ ነፃነት እና አንድነት ፡፡ ”

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዜብ መስፍንና የቼኮሌቱ ታሪከ

ማላጂ

አንድነት ኃይል ነዉ”

ነፃነት እና ህልዉናን ከኃይል አማራጭ ዉጭ ማሰብ ጉም የመዝገን ምኞት ነዉ ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share