November 12, 2021
20 mins read

ደም ተቀብቶ ዝንብ መፍራት አይሆንም ፤አያዛልቅም ፡፡

የትግራይ ህዝብ ፣ የትግራይ ሠራዊትም ሆነ ትህነግ ጥያቄ አርስዎ እንደሚሉት ነዉን ?

255521509 1101689480603798 4088723045113691793 n

  1. ወልቃይት እና ራያ ከጦርነቱ በፊት በነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ፣
  2. በትግራይ የተደረገውን ምርጫ መንግሥት እውቅና እንዲሰ ፣
  3. በፌደራል መንግሥቱ ተመጣጣኝ የሥልጣን ቦታ እንዲያገኝና በ-2020 በትግራይ የተመረጡት የክልል ተመራጮች በፌደራሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚገቡ ከሆነ ፣
  4. በከፍተኛ የሚኒስቴር ቦታ የሥልጣን መጋራት ከተሰጠን ፣
  5. ለትግራይ ይሰጥ የነበረውን የአስር ቢሊዮን በጀት ከተለቀቀ ፣
  6.  በመከላከያ ሠራዊት ለደረሰብን ኪሳራ መንግሥት ካሳ የሚሰጠንና የትግራይን ህዝብ ይቅርታ የሚጠይቅ ከሆነ ፣
  7. በእሥር ላይ የሚገኙ የትግራይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ሌሎችም ከእስር ከተለቀቁ እንዲሁም ካሳ የሚከፈላቸው ከሆነ ፣
  8. ድርድሩ በትክክል እስኪተገበር ድረስ ዋስትና ሊሆነን ይችል ዘንድ አሁን በያዝነው የአማራ ክልል ለአንድ ዓመት መቆየት የምንችልበት እውቅና ከተሰጠን
  9. የኢትዮጵያ መንግሥት በህወሓት ላይ የተመሠረተው ክስ እንዲቋረጥ እና ለቀጣዩም በህወሓት ባለሥልጣናት ዘንድ ክስ የማያነሳ ከሆነ ፣
  10. በሁመራ የተወሰደብን የሰሊጥ መሬት እንዲመለስልንና የተወሰደብን የሰሊጥ ምርት ካሳ የሚከፈለን ከሆነ ፣
  11. ህወሓት እንደሌላው ክልል ለሠራዊታችን ትጥቅ እንዲፈቀድለት እና አሁን የያዘውንም ትጥቅ እውቅና የሚሰጠን ከሆነና ዓቢይ ሥልጣን የሚለቅ ከሆነ ፣

ክቡር ሸምጋይ ትህነግ ፣ ግብረ አበር እና ሞግዚቶች የትግሬ ወረራ እና ምዝበራ ፊዉታራሪዎች ከትጥቅ ትግል አስከ አሁን ለፈፀሙት ወንጀል በጥቂቱም ቢሆን ማመናቸዉ ዕዉነት ቢሆንም ከጠቅላላ ለግማሽ ምዕተ ዓመት ከተሰራዉ ብሄራዊ የአገር ክህደት፣ ሠባዊ ዉድመት እና ምዝበራ ሲታይ አንድ አምስተኛዉን አምኗል ፡፡

ሆኖም ለዚህ ወደር የለሽ ትዉልድ ይቅር ለማይለዉ እና በታሪክ ጥቁር መዝገብ ሲዘከር ለሚኖረዉ ግፍ እና በደል ኃላፊነቱን ማመላከትም ሆነ ማላከክ ስላልቻለ እና ኃላፊነት ከመዉሰድ እና ተጠያቂ ከመሆን ይልቅ የወንጀል( ጥፋት) ድርጊት ሳይሆን በህዝብ እና አገር ላይ የፀነሰዉ የዘመናት ክህደት በገቢር ማሳየት የወንጌል ጦርነት ቆጥሮ አድርጎ በመቁጠር የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም ለዘመናት በጠላትነት በመፈረጂ ሲገድል ፤ሲያስገድል ፣ሲበድል ፣ ሲያሳድድ የኖረዉን የዓማራ ህዝብ ዕብሪት ለወረራ እና ምዝበራ ይዞ እየገደለ እና እየዘረፈ ያለዉን ህዝብ እና የኢትዮጵያ ግዛት በባርነት እና ግዞት ለማቆየት ዋስትናየ መሆኑ መንግስት እና ዓለም ይወቁልኝ ብሏል ፡፡

ዕዉነት ነዉ ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ እንዲሉ ” በኢትዮጵያ ጥላቻ እና በዜጎች ንቀት የተመረዙት ጠላቶች የአዳከሟትን አገር እና በቁም የገደሉትን ህዝብ ለደረሰባቸዉ ምስቅልቅል በደል ኃላፊነት ሳይወስዱ እና ይቅርታ ሳይሉ ዕዉቅና ላልሰጡት መንግስት ለፈፀሙት የአንድ ዓመት በደል እንዲሰረዝ ጠይቀዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ ነጻ አዉጭ እና ተከታዮች እና ሞግዚቶች ከመንበረ ስልጣን ዘመን 1983 .. ጀምሮ ፡

  1. ለ ፴ ዓመት የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ቆርሶ ለባዕድ የሰጠ፣
  2. ጥንታዊት እና ታሪካዊት የባህር በር ባለቤት አገር አስትንፋሷን የዘጋ ፤ያዘጋ፣

  3. የኢትዮጵያን ህዝባዊ ሠራዊት ( ባህር ሀይል፣ አየር ኃይል፣ ምድርጦር….) አፍርሶ ግለሰብ እና ብሄር አምላኪ ፣ተላላኪ እና አገልጋይ ብሄር አምካኪ ጦር በኢትዮጵያ ህዝብ መስዋዕት ያቋቋመ፣
  4. በአቆቋመዉ የህወኃት / ኢህዴግ ጦር ፳፯ ዓመት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የዜጎችን ደህንነት ከማስከበር ይልቅ ጨቋኝ እና አፋኝ አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም ህዝብ ማስጨነቅ ፤ ማንነትን መንጠቅ እና ዳር ድንበር ማስነጠቅ ነበር ፣
  5. የአንድ አገር መንግስት የአንድን አገር ህዝብ ጠላት እና ወዳጂ ብሎ በመፈረጂ በዓለም ታሪክ የኢህዴግ /ህወኃት መንግስት ነባሩን የኢትዮጵያ ህዝብ “ዓማራ ” በማንቱ እና ኢትዮጵያዊነቱ የነጠላ እና የጂምላ ፍጂት እና ጥፋት ደርሶበታል ፡፡
  6. ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነት መገለጫዎችን ማደብዘዝ፣

  7. የተለያዩ ኢትዮጵያ የግዛት አካላትን በተለይም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ለማናጋት እና የትግራይን አዲስቷ ግዛት ለመመስረት የሚያስችል የተንኮል የክልል አስተዳደር አከላለል መተግበር( ጎጃም ፣ ጎንደር ፣ ወሎ እና ሸዋ …..)

  8. የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሃብት በተለያዩ ስያሜዎች መመዝበር ፣

  9. ትግራይን ለማልማት ኢትዮጵያን በተለይም የትግራይ አጎራባች የኢትዮጵያ የግዛት ወሰኖችን (ወሎ፣ ጎንደር፣ አፋር…) ማሳሳት እና በዚህ መስፋፋት፣

  10. ከራሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ዉጭ ያሉትን እና የነበሩትን ማግለል እና መበደል፣
  11. የኢትዮጵያ ጠላቶች የአገርን ክብር እና ህልዉና ለጠላት እና ጥፋት አሳልፎ በመስጠት እና ህዝብን ለጅምላ ፍጂት መዳረግ ….. ከዋና ዋና ወንጀሎች አንደኞች ናቸዉ ፡፡

ሆኖም ከትህነግ የቅድመ ሁኔታ አኳያ በንፅፅር ሲታይ ፤

  1. ወልቃይት እና ራያ ከጦርነቱ በፊት በነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ፤
  2. ሁለቱም የኢትዮጵያ ግዛቶች የጎንደር እና ወሎ አካሎች በመሆናቸዉ በትግራይ ትግሬዎች የ፴ ዓመታት ወረራ ለደረሰ ሰባዊ እና ቁሳዊ ጥፋት ፣ዉድመት እና ሌብነት ዕዉቀና ፣ ይቅርታ ፤ ካሳ እና የወንጀል ባለቤት እንዲኖር የዓማራ ክልል አስተዳደር፣ ህዝቡ እና ማእከላዊ መንግስት እንዲጠይቅ፣
  3. በትግራይ የተደረገውን ምርጫ መንግሥት እውቅና እንዲሰ ፣
  4. በትግራይ የተደረገዉ ምርጫ የኢትዮጵያን ህዝብ እና በወቅቱየነበረዉን መንግስት ዕዉቅና ያላመላከተ ስለነበር እና ሁለቱም በየፊናቸዉ አንዱ ስለሌላዉ ዕዉቅና በመንፈጉ ሊጠየቅ የሚገባዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ መነግስት ሊሆን አይችልም ፡፡

  5. በፌደራል መንግሥቱ ተመጣጣኝ የሥልጣን ቦታ እንዲያገኝና በ-2020 በትግራይ የተመረጡት የክልል ተመራጮች በፌደራሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚገቡ ከሆነ ፣
  6. የነበረዉን እና ለ፳፯ ዓመት እንደ ግል መሳሪያ ማጥቂያ እና መስፈራሪያ አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረዉን ህገ መንግስት(ትህነግ) አሻፈረኝ ያለ የራሱን ስምምነት የጣሰ በምን አግባብ ሊሆን እንደሚችል ማብራሪያ አለመስጠት ወይም በጉልበት በስልጣን መንበር ለመጎለት ምኞት ስለሚሆን ፣

  7. በከፍተኛ የሚኒስቴር ቦታ የሥልጣን መጋራት ከተሰጠን ፣
  8. የህዝብ ስልጣን ዉክልና በተለመደዉ ህዝባዊ ንቀት ቅርጫ መጠየቅ ፣
  9. ለትግራይ ይሰጥ የነበረውን የአስር ቢሊዮን በጀት ከተለቀቀ ፣
  10. ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለዓማራ ህዝብ ለዘመናት በደረሰ ምዝበራ የሶስት ዓመት በጀት ወደ ዓማራ ክልል ፈሰስ እንዲሆን ፣
  11.  በመከላከያ ሠራዊት ለደረሰብን ኪሳራ መንግሥት ካሳ የሚሰጠንና የትግራይን ህዝብ ይቅርታ የሚጠይቅ ከሆነ ፣
  12. በመከለከያ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ እና በተለይም ለዓመታት የመከራ እና ጭቆና ዶፍ ላደረሱበት በስሙ ፣በክብሩ እናበማንነቱ ለደረሰ ኪሳራ ትህነግ እና የትግራይ ህዝብ ዕዉቅና፣ይቅርታ እና ከሳ ሊከፍሉ ይገባል፤ መጠየቅ አለበት ፡፡

  13. በእሥር ላይ የሚገኙ የትግራይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ሌሎችም ከእስር ከተለቀቁ እንዲሁም ካሳ የሚከፈላቸው ከሆነ ፣
  14. ያልተሳሩ ሆነ የታሰሩት የትግራይ ባለስልጣናት ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የነበሩ መሆናቸዉ ታውቆ በስልጣን ዘመን በአገር አንድነት እና ሉዓላዊነት ክህደት እና ጥፋት እንዲሁም በግለሰብ ፣ቡድን እና ህዝብ ላይ ለደረሰ ዕንግልት፣ሞት ፣ስደት ፣ ሠባዊ ጥፋት፣ ምዝበራ ….. በህግ እንዲጠየቁ ሊደረግ ይገባል፡፡
  15. ድርድሩ በትክክል እስኪተገበር ድረስ ዋስትና ሊሆነን ይችል ዘንድ አሁን በያዝነው የአማራ ክልል ለአንድ ዓመት መቆየት የምንችልበት እውቅና ከተሰጠን፣
  16. ያለምንም ታሪካዊ እና ህጋዊ ድጋፍ የኢትዮጵያን ግዛቶች በጦር በመዉረር የኢትዮጵያን ዳር ድንበር የማመሰቃቀል ፣ ህዝቡን ሠባዊ እና ህጋዊ መብቱን በመንፈግ ፣ በመግደል ፣ በጅምላ ፍጂት ….ወዘተ ትህነግ ሊጠየቅ እና ለዚህም ራሱ ዕዉቅና ስለሠጠ የገንዘብ እና የሞራል ከሳ መጠየቅ አለበት ፡፡

  17. የኢትዮጵያ መንግሥት በህወሓት ላይ የተመሠረተው ክስ እንዲቋረጥ እና ለቀጣዩም በህወሓት ባለሥልጣናት ዘንድ ክስ የማያነሳ ከሆነ ፣
  18. ህወኃት ህልዉናዉ የከሰመ እና አገር ክህደት እና ጅምላ ፍጂት ወንጀል ፴ ዓመት የፈፀመ በመሆኑ ሊጠየቅ ሲገባዉ በሶስት ዓመት ጥፋት ሊቋጭ የማይችል መሆኑና ይህም የሚያስጠይቅ እና ህዘብም ይቅርታ ሊጠየቅ ይገባል፡፡

  19. በሁመራ የተወሰደብን የሰሊጥ መሬት እንዲመለስልንና የተወሰደብን የሰሊጥ ምርት ካሳ የሚከፈለን ከሆነ ፣
  20. የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሃብት በኤፈርት እና በተለያዩ የግል ድርጂቶች ስም ተዘርፎ እና ተከማችቶ የሚገኘዉ ወደ አገር እና ህዝብ ሀብት ቋት እንዲመለስ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡

  21. ህወሓት እንደሌላው ክልል ለሠራዊታችን ትጥቅ እንዲፈቀድለት እና አሁን የያዘውንም ትጥቅ እውቅና የሚሰጠን ከሆነና ዓቢይ ሥልጣን የሚለቅ ከሆነ ፣
  22. በህጋዊ መንገድ የህዝብ ደህንነት እና የአገር ሉዓላዊነት ለማስከበር እንጂ በሴራ የኢትዮጵያን ህዝብ ሀብት (ጦር መሳሪያ) የቀማ እና የታጠቀ ባለመሆኑ እንዲያዉም የህዝብ እና አገር ሀብት ለህዝብ እና አገር መጎሳቆል በማዋል ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል፡፡

እንግዲህ ዉሃን ምን አጮኸዉ ቢሉት ድንጋይ እንዲሉ ደን ተቀብቶ ዝምብ አይፈራም እና ፡

ትህነግ /ህዎኃት እና አገልጋዮች ሆኑ ሞግዚቶች በኢትዮጵያ የዳር ድንበር እና ግዛት ላይ ለዳረሱት ጥፋት ተጠያቂ እና ይቅርታ ጠያቂ እንጂ ተጠያቂ አይደሉም ፤

በዓማራ ህዝብ ላይ በጠላትነት ፈርጆ ለ ፳፯ ዓመት ፍጂት መድረሱን የማይካድ በመሆኑ ይቅርታ ያቅርብ ፣ ከሳ ይጠየቅ እንዲሁም በትህነግ ከትናንት አስከ ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ እና በመነሻ የትህነግ መመሪያ / መተዳደሪያ ላይ ጠላት ያለዉን ዓማራ ላይ ለደረሰዉ ሰቆቃ እናፍጂት “ለሰማዕታት መታሰቢያነት ሀዉልት ” ይቁም ይህም በትህነግ ወጪ መሆን አለበት ፣

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል የደርግ ሳይሆን የህዝብ መሆኑን ትህነግ አምኖ ይቅርታ ይጠይቅ ፡፡

የዓማራ ህዝብ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዉያን በአገር መስረታ ፣ ጥበቃ ፤ልማት እና ዕድገት ምሰሶ እና ማገር እንጂ የማንም ስጋት አለመሆኑን እና ከዚህ በተቃራኒ ትህነግ እና ግብረ አበሮች ለአገር እና ህዝቦች ስጋት መሆናቸዉን ራሳቸዉ በቅድመ ሁኔታ ያረጋገጡ ስለመሆኑ ለዘመናት በዓማራ ህዝብ ላይ ላደረሱት የጥላቻ እና ጥፋት ( አጥፍቶ መጥፋት) በደል ይቅርታ ፣ዕዉቅና እና ከሳ ሊጠየቁ ይገባል፡፡

በጥቅል ያሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል ፤ ሌላ ፈላጊ የራሱን ያጣል……እንዲሉ በራሱ አገር ፣ ህዝብ እና ምድር ፤ ምዝበራ (ሌብነት )፤ ክህደት እና ሞት ላደረሰ ዕዉነት እና ዳኝነት አስካለ ጠላት የመቶ ዓመት ዕድሜ ንስኃ ቢኖረዉ ከጥፋት እና ጥላቻ ዘባዜ የማይላቀቅ የሠባዊነት እና የብሄራዊ አንድነት እና ደህንነት ጠንቅ መሆኑን ከዉልደት አስከ ሞት “ጥላቻ እና ጥፋት አስከ ሞት ” ባህሪዉ በመሆኑ ነዉ ( 1968 .ም አስከ ዛሬ) ፡፡

ህዝብ እና መንግስትም ክር እና ድር ሆኖ የሠላም የመጨረሻ ዓማራጭ ኃይል ነዉና፡

  1. የህወኃት ጥቃት እንዲያቆም መለመን ሳይሆን አሸባሪ ፣ወራሪ እና መዝባሪ የትግራይ ሠራዊት እና ተከታይ ክህደት እና ጥፋት ሴራ በኃይል ደህንነት እና ሠላም በዘላቂነት ማረጋገጥ፣
  2. የዘመናት የዓማራ እና የአፋር ህዝብ ጭቆና ፣ ሞት ፣ስደት እና ዉርደት የሚቆመዉ እና ዘላቂ ነጻነት የሚረጋገጠዉ እና የሚሆነዉ በህዝቦች መራር ተጋድሎ እና እምቡባይነት እንጂ በልመና እና ልቀቁልን የሚገኝ እና የሚቸር ነጻነት እና ማንነት አይኖርም ፣

  3. ለኢትዮጵያ መንግስት ቅቡልነት ዕዉቅና እና ህልዉና ጉዳይ የኢትዮጵያዉን እንጂ አገር እና ህዝብን ክዶ በክንድ እና ግድ የራሱን ዓለም ለመፍጠር ሠባዊ እና ቁሳዊ ግፍ በሚደርስ ዕብሪተኛ ወራሪ ፣ መዝባሪ እና አሸባሪ ከሚባል አካል መተማመኛ መጠየቅ አግባብም ፤ መጣኝም አለመሆኑን ህዝብ እና መንግስት እንደገና አንድ ሊሉት የሚገባ ነዉ ፡፡

 

ማላጂ

አንድነት ኃይል ነዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop