November 2, 2021
17 mins read

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ – ጭራቁን ወያኔ እጃችንን አጣጥፈን እንጠብቀው? – አብዱራህማን አህመዲን

ጥቅምት 23 ቀን 2014

አሸባሪነቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እውቅና የተሰጠው ህወሓት መራሹ የትግራይ የሽብርና የዘረፋ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ፣ የአማራን ህዝብ ለማዋረድና መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ለመዝረፍና ለማተራመስ የጫረው ጦርነት እየተጋጋመ ነው፡፡ የሽብር ቡድኑ ወደ መሀል አገር የሚያደርገው ግስጋሴም ቀጥሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ህዝብ እየተጨፈጨፈ ነው፡፡ ከሰላማዊ መኖሪያ ቀየው እየተፈናቀለ ነው፡፡ ሀብት ንብረቱ እየወደመ ነው፡፡

ትናንት መሀል የነበሩት አካባቢዎች ዛሬ ዳር ሆነዋል፡፡ ዛሬ መሀል የሆኑ አካባቢዎች ነገ ዳር መሆን አለመሆናቸው የሚወሰነው ዛሬ በምናደርገው የተግባር እንቅስቃሴ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በመሆኑም የችግሩን መጠንና ስፋት ዛሬ መሀል በሆነው አካባቢ የሚኖረው ህዝብ ተገንዝቦ ይህንን አውዳሚ ወረራ በተባበረ ክንድ መመከት አስፈላጊ መሆኑ ጥርጣሬ ውስጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡

የዛሬ 31 ዓመት ወያኔ ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሰ በነበረበት ወቅት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ “የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለቱንም ጭራቆች በሁለት እጁ መታገል አለበት” ብለው እንደነበር በወጣትነት ልቤ ጽፌዋለሁ፤ እስከ አሁንም አልረሳሁትም፡፡ ኮሎኔሉ 2 ጭራቆች ያሏቸው ወያኔን እና ደርግን ነበር፡፡ ያኔ በደርግ የአፈና አስተዳደር ተማሮ የነበረው ህዝብ ግን አልሰማቸውም ነበር፡፡ ከወያኔ ጋር ሆኖ በአንድ እጁ ደርግን ተዋጋ፣ ደርግን ጣለ፡፡ ሁለተኛው ጭራቅ (ማለትም ጭራቁ ወያኔ) ስልጣን ይዞ ውሎ ሳያድር የጭራቅ ተግባሩን ቀጠለ፡፡ 27 ዓመት አረመኔያዊ ክንዱን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አሳረፈ፡፡ ከ3 ዓመት ዝግጅት በኋላ እነሆ አሁን ሀገሪቱን እያመሰ ይገኛል፡፡ ጭራቁ ወያኔ ዳግም ወደ 4 ኪሎ ለመምጣት ልቡ ሻቅሏል… እና ጭራቁን እጃችንን አጣጥፈን እንጠብቀው?

ውድ ወገኖቼ!

ይህንን ጥያቄ የማቀርበው በየትኛውም ስፍራ ለሚገኘው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ያሉንን የፖለቲካም ይሁን የሌላ ልዩነቶች ለጊዜው እናስቀምጣቸውና አንድ ሆነን ሁላችንንም ሊሰለቅጥ እየመጣ ያለውን ጭራቅ እንቅስቃሴ እንግታ፡፡ ካልሆነ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ሁላችንም በጭራቁ መሰልቀጣችን አይቀሬ ነው፡፡ ዛሬ ደሴና ኮምቦልቻ እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ ነገ በያንዳንዳችን ላይ የሚፈጸም መሆኑን አትጠራጠሩ! እናም የሚከተለውን ወገናዊ ጥሪ በአክብሮት አቀርባለሁ፡፡

በቅድሚያ ለአማራና አፋር ወገኔ!

ውድ የአማራና የአፋር ወገኔ! የወያኔን ጭካኔ ታውቀዋለህ፡፡ የወያኔን አረመኔነት አይተኸዋል፡፡ የወያኔን ግፍ ቀምሰኸዋል፡፡ በምድር ላይ ከዚህ በላይ ግፍ የለም፡፡ ማንን ነው የምትጠብቁት? ምን እስኪፈጠር ነው የምትጠብቁት? ሁላችሁም እስክትታረዱ ነው የምትጠብቁት? ሴቶቻችሁ እስኪደፈሩ፣ ንብረታችሁ እስኪዘረፍ… ነው የምትጠብቁት?

እናም የአማራና የአፋር ወገኖቼ መንግስትንም ይሁን ማንንም ሳትጠብቁ ወደ ትግራይ ገስግሱ፡፡ ከጎንደር ወደ ሽሬ፣ ከሰቆጣ ወደ ተምቤን፣ ከአፋር ወደ መቀሌ ሂዱ፡፡ በመሀል አገርም የሽምቅ ውጊያ ጀምሩ፡፡ የደፈጣ ውጊያ ቀጥሉ፡፡ እንደነሱው መሳሪያም፣ ጉልበትም፣ አቅምም፣ ጀግንነትም አላችሁ፡፡ መቀሌ ድረስ ሂዱና ባለጌ ወሮበላ ማጅራት መቺ ልጁቹ ያደረሱባችሁን በደል ለትግራይ ህዝብ ንገሩት፡፡ ልጆቹ ሰርቀውና ዘርፈው ያመጡለትን ንብረት በጨዋ ደንብ እንዲመልስ አድርጉት፡፡

ለኦሮሚያ ወገኔ!

የተከበርከው የኦሮሚያ ወገኔ! ዛሬ በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ የተፈጸመው ነገ በኦሮሚያ ይፈጸማል፡፡ ደም የጠማው፣ የኦሮሞ ልጆችን በእስር ቤት አጉሮ ሲያሰቃይ የኖረው፣ አውሬው ወያኔ “ጅብ እስኪነክስ ያነክስ” እንዲሉ ካልሆነ በስተቀር የኦሮሚያን ህዝብ አይምረውም፡፡ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ ተዘጋጅተን ካልጠበቅነው ነገ ከነገ ወዲያ አረመኔው፣ ይሉኝታቢሱ፣ ዘራፊው ወያኔ ጓዳችን ገብቶ ዓይናችን እያየ ይጨፈጭፈናል፣ ያርደናል፣ አርዶ ቆዳችንን ይገፈናል፡፡ ሴቶቻችንን ዓይናችን እያየ ይደፍራቸዋል፡፡ ለዘመናት ላባችንን አንጠፍጥፈን ያፈራነውን ሀብት ንብረታችንን ዘርፎ ለማኝ ያደርገናል፡፡

ይህንን በአማራ ህዝብ ላይ አድርጎታል፡፡ ይህንን በአፋር ህዝብ ላይ አድርጎታል፡፡ ነገ ከነገ ወዲያ በእኛ ላይ ሊፈጽመው ወደ መሀል ሀገር እየገሰገሰ ነው፡፡ ጭራቁ ወያኔ ደጅህ ላይ ቆሟል፡፡ አረመኔው ወያኔ በርህን እያንኳኳ ነው… አጭበርባሪውና ማጅራት መቺው ወያኔ የራስህን ልጆች “ሸኔ” የሚል የክርስትና ስም ሰጥቶ እያታለለ ከጎኑ በማሰለፍ የአረመኔነቱና የጭራቅ ተግባሩ አባሪ ተባባሪ እያደረገ ነው፡፡ እና ጭራቁን እጃችንን አጣጥፈን እንጠብቀው?

ለሌሎች ክልሎች ወገኖቼ!

ውድ ወገኖቼ!… በአማራ፣ በአፋርና በኦሮሚያ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው የወያኔ ግፍ በእናንተም ላይ እንደተፈጸመ የሚቆጠር ነው፡፡ ዛሬ እሳቱ እናንተ ጋር ባይደርስ የጎረቤት ቤት ተቃጥሎ የሚነድ ነገር ሲያበቃ ወደ እናንተ ቤት መሸጋገሩ አይቀሬ ነው፡፡ የእሳቱ ወላፈን ከሩቅ እየተጋረፈ መሆኑን ልብ በል!

ዛሬ የአማራ ሴችን የደፈረ አረመኔ፣ ዛሬ የአፋር ህፃናትን የጨፈጨፈ ጭራቅ፤ ዛሬ የወሎን፣ የጎንደርን፣ የአገውን፣ የራያን፣ የባቲን፣ የወልቃይትን፣ የጠገዴን፣ የጋይንትን፣ የደሴን፣ የኮምቦልቻን… ወገንህን ሀብት ንብረት ያውደመና የዘረፈ የሽብርና የዘረፋ ማጅራት መቺ ቡድን ነገ እናንተ ቤት መጥቶ ተመሳሳይ ጥፋት፥ የባሰ ውድመት እንደሚያደርስ አትጠራጠር!

እናም ራሳችሁን አደራጁ፡፡ ቀያችሁን ጠብቁ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጎረቤት ወንድም ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍና መከራ በመመከቱ ሂደት ስንቅም ትጥቅም በማቀበል ወገንህ እየበላ ያለውን ጭራቅ ተዋጋ! በወገንህ ላይ የዘመተን አረመኔ በጉልበትም በብልሃትም ተዋጋ!

በጽናት ሀገርህን ለምትወደው የትግራይ ተወላጅ ወገኔ!

የአክሱም ጽዮን ሀገር፣ የትልልቅ ገዳሞች ሀገር፣ የነጃሺና የእስልምና ስር መሰረት ሀገር… ባለቤት የሆንከው ውድ የትግራይ ወገኔ! በልጆችህ የተቋቋመቺው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ባለፉት 47 ዓመታት ምን አመጣችልህ? ምንስ አስገኘችልህ? ነፃነት አገኘህ? ሰላም አገኘህ? እድገት አገኘህ? ከድህነት ወጣህ?… እኛ እንዳየነው በ47 ዓመታት በ3 ትልልቅ ጦርነት ውስጥ ማገደቺህ፣ ከወገንህ ጋር ደም አቃባችህ እንጂ ህወሓት ለአንተም ቢሆን ያመጣችልህ አንዳች ነገር የለም፡፡ “ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ነው” እያለች በስምህ ምላ እየተገዘተች ተጫወተችብህ እንጂ ለአንተም ያስገኘችልህ ፋይዳ የለም፡፡

ውድ ትግራዋይ ወገኔ!

ይህ የሆነው ለምን ይመስልሃል? ለመሆኑ ህወሓትን ታውቃታለህ? “ዓይን ዓይንን አያይም” እንዲሉ ህወሓትን አታውቃትምና የህወሓትን ማንነት እኛ ከርቀት የምናያት እንንገርህ፡፡ ህወሓት ፓርቲ አይደለቺም፡፡ ፓርቲ ነኝ የምትለው ለሌብነቷ ሽፋን ነው፡፡ ህወሓት የፖለቲካ ድርጅት ባህሪም ዓላማም ስነ-ምግባርም የላትም፡፡

አዎ! ህወሃት የመንግስት ስልጣን ይዞ ሀገርን እየዘረፈ ለመኖር የተቋቋመ የሽብርና የዘረፋ ቡድን ነው፡፡ ህወሓት የትግራይን ህዝብ ባሪያ አድርጎ ለመግዛት የተደራጀ ማጅራት መቺ ድርጅት ነው፡፡ በአጭሩ – ህወሃት የትግራይ ማጅራት መቺዎች የፈጠሯት ማጅራት መቺ ናት! ህወሃት ሀገርና ህዝብን እያስፈራሩ ለመዝረፍ የተቋቋመች የዝርፊያ ድርጅት ናት፡፡

ህወሓትን ከኮሎምቢያ የሐሽሽና የውንብድና ቡድኖች የሚለያት መንግስታዊ ስልጣንና የራሷ ግዛት (መሬት) ያላት፤ የምትምልበትና የምትገዘትበት፣ በስሙ የምትቀልድበት ህዝብ ያላት መሆኑ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በትግራይ ምድር የመሳሪያ መቅበሪያ ጉድጓድ እንጂ የእህል ማስቀመጫ ጉድጓድ የሌለው፡፡ ለዚህም ነው ህወሃት መሳሪያ እንጂ ትራክተር ስትገዛ የማትታየው፡፡ ዓላማዋ አርሶና ነግዶ ሀብት መፍጠር ሳይሆን ዘላለም ስልጣን ይዞ በመሳሪያ እያስፈራሩ እየዘረፉ መኖር ነው፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት የታየው ይህ ነው…

ውድ ትግራዋይ ወገኔ!

ሀገርህን ኢትዮጵያን፣ ከሌላው ወገንህ ጋር መስዋእትነት ከፍለህ የመሰረትካትን አደይ ኢትዮጵያን ልጆችህ የሙቀጫ ልጅ ሆነው እያፈረሷት መሆኑን እያየህ እዛዲያ ምነው ዝም አልክ? ወገንህን አማራን፤ ወንድምህን አፋርን ልጆችህ ወረው፣ እንደ ባእድ ጠላት ሀብት ንብረት እየዘረፉ፣ ፋብሪካ እየነቀሉ፣ ጥርስ ላይ ያለ ወርቅ ሳይቀር ሰርቀው እያመጡልህ፤ እንደ ውሻ በየጓዳው እየገቡ ሹሮና በርበሬ ሳይቀር እየሰረቁ ሲያመጡልህ የሌባ ተቀባ መሆንህ ለምነው?

ልጆችህ በማይኻድራ፣ በጭና፣ በቆቦ አጋምሳ፣ በአፋር፣ በውርጌሳ፣ በውጫሌ፣ በደሴ፣ በኮምቦልቻ፣… በወገንህ ላይ የሰሩትን ጭፍጨፋ እውነት ሳትሰማ ቀርተህ ነው ዝም ያልከው? ሴትን መድፈር፣ አቅመ ደካሞችን መግደል፣ ቤተክርስቲንና መስጊድ ማቃጠል፣ ሹሮና በርበሬ መዝረፍ… ነው የትግራይ ጀግንነት? የትግራይ ጀግንነት የሚገለጠው በስርቆት፣ በዘረፋና በውንብድና ነው? የትግራይ ጀግንነት የሚገለጠው ሀገር በማፍረስ ነው? ይኸ ነገር ያኗኑረናል? የዚህን ሁሉ ግፍ ዋጋ ለመክፈል ትችለዋለህ?

ውድ ትግራዋይ ወገኔ!

እኛም ኢትዮጵያውያን ነን፡፡ በአድዋ ምን እንዳደረግን አሳምረህ ታውቀናለህ! እኛ ሐሺሽ ምገን በወገናችን ላይ አንዘምትም፡፡ አንተ ዘንድ ያለው ጀግንነት እኛም ጋር በእጥፍ አለ፡፡ በፍቅር እንጂ በጉልበት ማንም ሊያንበረክከን አይችልም! ግፈኛ ልጆችህ፣ ሳትቀጣ ያሳደግካቸው አረመኔ ልጆችህ፣ … ላደረሷት እያንዳንዷ ብልግናቸው ዋጋ ይከፍላሉ፡፡ በዚህ ቅር እንዳይልህ! በመጡበት መስመር ይቀጣሉ፣ ይወቀጣሉ፡፡ እኛ ዘንድ የመጡት ለመሞት ስለሆነ እዚሁ እኛው መሬት ላይ እንቀብራቸዋለን – እርምህን አውጣ!

ሀገራችን ፈርሳ፣ ሴቶቻችን ተደፍረው፣ ለዘመናት ላባችንን አንጠፍጥፈን ሰርተን ያፈራነው ሃብታችን ተዘርፎ እያየን እጃችንን አጣጥፈን እንደማንቀመጥ አንተም ታውቃለህ፡፡ ለማንኛውም የተዘረፈው ንብረታችን፣ የተነቀለው ፋብሪካችን፣ የሚነዳው መኪናችን፣… አንተው ዘንድ ስላለ በአደራ አስቀምጥልን፡፡ ሰሞኑን በእንግድነት እቀየህ ድረስ እንመጣለን፡፡ እንደ ልጆችህ ብረት ይዘህ ሳይሆን በባህላችን መሰረት እንደምታስተናግደን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የሚወራረድ ነገር ካለም እዚያው እንነጋገራለን፡፡ እዚያው እንወቃቀሳለን፡፡ ወይ ከልጆችህ ወይ ከሀገርህ፣ ከእኛ ከወገኖችህና ከሀቅ ጋር ትሆናለህ፡፡ ምርጫው ያንተ ነው!

አክባሪ ወገንህ

አብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የኢዴፓ ከፍተኛ አመራርና የፓርላማ አባል

ማስታወሻ፤

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop