October 24, 2021
17 mins read

አሸባሪው ትህነግ አጥቂ ወይም ጠብ አጫሪ መንጋን ለእኩይ አላማው እይተጠቀመ ነው

አሸባሪው ትህነግ አጥቂ ወይም ጠብ አጫሪ መንጋን ለእኩይ አላማው እይተጠቀመ ነው ፡፡ Aggressive mob

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

tplf
tplf

There is limited research into the types of crowd and crowd membership and there is no consensus as to the classification of types of crowds. Two recent scholars, Momboisse (1967) and Berlonghi (1995)  focused upon purpose of existence to differentiate among crowds. Momboisse developed a system of four types: casual, conventional, expressive, and aggressive. Berlonghi classified crowds as spectator, demonstrator, or escaping, to correlate to the purpose for gathering.

Another approach to classifying crowds is sociologist Herbert Blumer’s system of emotional intensity. He distinguishes four types of crowds: casual, conventional, expressive, and acting. His system is dynamic in nature. That is, a crowd changes its level of emotional intensity over time, and therefore, can be classed in any one of the four types.

Generally, researchers in crowd psychology have focused on the negative aspects of crowds,[7] but not all crowds are volatile or negative in nature. For example, in the beginning of the socialist movement crowds were asked to put on their Sunday dress and march silently down the street. A more-modern example involves the sit-ins during the Civil Rights Movement . Crowds can reflect and challenge the held ideologies of their sociocultural environment. They can also serve integrative social functions, creating temporary communities.

Crowds can be active (mobs) or passive (audiences). Active crowds can be further divided into aggressive, escapist, acquisitive, or expressive mobs.[2] Aggressive mobs are often violent and outwardly focused. Examples are football riots and the los angels riots 1992. Escapist mobs are characterized by a large number of panicked people trying to get out of a dangerous situation. Acquisitive mobs occur when large numbers of people are fighting for limited resources. An expressive mob is any other large group of people gathering for an active purpose. Civil disobedience, rock concerts, and religious revivals all fall under this category .

FROM WIKIPEDIA

የመንጋ አስተሳሰብ ( Mob mentality ) እልፍ ሰው ፣ በግላሰብ /ዎች/ አመለካከትና ሃሰብ ( ጠቃሚ ወይም ጎጂ ሊሆን ይችላል ) የተጠረነፈበት ፣ አቤት እንዴትና ወዴት ብቻ የሚፈቀድበት ፤ አንዳችም ተቃውሞ የማይቀርብበት ፤ በአንድ ግለሰብ ወይም ቡድን ትዕዛዝ ሺዎች በጥቂቶች ላይ ከምላስ ጀምሮ ገጀራ የሚያነሱበት ፤ አካሄድ ያለው ነው ፡፡ በአጥቂ ወይም በጠብ አጫሪ መንጋ መድበን የምንመለከተው ፡፡ ( Aggressive mob ) ፡፡ የዚህ ፅሑፍ ጭብጥ ነው ፡፡ የመንጋ እንቅስቃሴ ለአብዮቶች መዋሉ የታወቀ ነውና በስሜት ተገፋፍቶ ለበጎ ነገር ያለገጀራ የወጣን ህዝብ እንደ ሰላማዊ ሰልፈኛ ቁጠሩት ፡፡ ትንታኔውንም ከዊኪፒዲ ላይ ተመልከቱልኝ ፡፡ …

በመንጋ የሚከሰት ህዝባዊ ንቅናቄ ሁሉ ፤ የተጠረነፈ የህዝብ እልፍ አእላፍ ፣ያለ ጥያቄ የቡድኑ አውራ ያለውን ተቀብሎ የሚተገብር ፤ የመቀበል ( Heard ) አስተሳሰብ ብቻ የሰረፀበት መሆኑንም አትዘንጉ ፡፤ አንዴ በመንጋ ከተፈረጅህ የራስህ ጭንቅላት እንደሌለህ ተረዳ ፡፡

የመንጋ ህሳቤ ያላቸው ሰዎች ፣ በአንድ ቀፎ ውስጥ እንደሚኖሩ ንቦችም ይመሰላሉ ፡፡ የቀፎ ንብ አስተሳሰብ ያላቸው ፡፡ (hive mentality) ንቦቹ ፣ መላ ህይወታቸውን ሙሉ የሚለፉት ለንግስትዋ አገልግሎት እንጂ ለራሳቸው እንዳልሆነ ይታወቃል ፡፡ የሰው መንጋዎችም ለአንድ ግለሰብ ” ድኩም አላማ ” ብለው ህይወታቸውን እሰከመሰዋት ይደርሳሉ ፡፡ የመንጋውን መሪ ብቻ የሚሰማ ና ትዕዛዙን የሚተገብር ህሊና ያላቸው አሳዛኝ ፍጥረቶችም ይሆናሉ ፡፡ እስከ ደም ጠብታ የቀፎዋን ንግስት ንብ የማገልገል ዐይነት ተግባር ተመሳሳይ ወይም መንጋዊ ህሊና ( mob mentality ) ባላቸው ሰዎች ሲከወን ስታዩ ቀፎው የተነካበት ንብ ምህረተ ቢስ ወረራ ትዝ ይላችኋል፡፡ …

ከላይ የሰፈረው የካት ብሩሸ ( Kate Brush ) ፅሐፍም የሚያረጋግጥላችሁ ይህንኑ እውነት ነው ፡፡ የጋርዮሽ ወይም የስማ በለው የጭፍን ጉዞ አስተሳሰብ ፤ግለሰቦች በተፈጥሮ የታደሉትን ህሊና እና በራሳቸው ላይ ራሳቸው የመወሰን ስልጣንን ፤ በስሜት ተገፋፍተው ፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለመንጋው ሃሰብና አመለካከት እንዲገዛ አሳልፈው ሲሰጡ የሚስተዋልበት ነው ፤ መንጋነት ፡፡ ሰዎች አንዴ ወደመንጋነት ከተቀየሩ በኋላ የተቀላቀሉትን ቡድን አላማ ከማራመድና ትዕዛዙን ከመፈጸም ውጪ ምንም ክፍት አማራጭ የላቸውም ፡፡ የመንጋው አባላት በጠቆለፈ ሳጥን ውስጥ የተቀመጡ አሳዛኝ ፍጥረታት ናቸው ፡፡ ከሳጥኑ እንዲወጡ የሚፈቀድላቸውም ለጥፋት ዓላማ ብቻ ነው ፡፡ ልክ ቀፎ ውሰጥ እንደ አደፈጠ የንብ መንጋ ማመዛዘን እና ጠላትን ከወዳጅ ለይተው አያጠቁም ፡፡ ህሊናቸውን የመንጋው ያደረጉ ሰዎች ሁሉ ፤ ፣ አንዱ በቀፎው ዳር የሚሄድን መንገደኛ ለመንደፍ ሲቀሳቀስ ፣ ያንን ሰላማዊ መንገደኛ ለመንደፍ አብረው እንደ ሚንቀሳቀሱ ንቦች ዓይነት ባህሪ ነው ያላቸው ፡፡ ወይም የንቦቹን ቀፎ ፤ አንድ ተንኮለኛ ሰው ቢመታው ፣ በምቱ ተደናግጠው ከቀፈው የሚወጡት ንቦች ፣ ያንን ተንኮለኛ ሰው ለይተው አያጠቁትም ፡፡ ጥቃታቸው የጭፍን እና የመንጋ ጥቃት ነው የሚሆነው ፡፡ በመንጋ በመንቀሳቀስ ፣ በዙሪያቸው ያገኙትን ማንኛውንም ፍጡር ፤ ሰው ና እንስሳ ሁሉ በመንደፍ ፤ አካባቢውን በማሸበር ፣ በትብብር አጠቃላይ ውድመት ነው የሚያስከትሉት ፡፡

ለዚህ ነው ” መንጋነት እጅግ አደገኛ ነው ፡፡ ” የሚባለው ፡፡ አደገኛ የሚሆነው በመንጋነት የተሰባሰቡት ሰዎች በየግላቸው የሚየስቡበት ህሊና ወይም ማሰብያ አእምሮ ስለሌላቸው ነው ፡፡ መንገኞችን በመንጋ ለጥፋት የሚሰባስባቸው አንድ ከእነሱ በንቃት የተሻለ ንቃት ያለው ፤ ሥልጣን ለማግኘት ተሥፋ ያለው ና እኩይ አላማውን በችግረና ሰዎች ላይ ለማስረፅ የሚስችል በቂ ገንዘብ ያለው ሰው ነው ። ወይም ሥልጣንና ገንዘብ በጣምራ ያለው ሰው ፣ ከኋላው እልፍ አእላአፍ ጭፍን ደጋፊ ፣ አደርግ የሚለውን ያለጥያቄ የሚፈፅም መንጋ ለማፍራት ይችላል ( የጃዋርን ኪሰ አይነጥፌነት ና በእርሱ mentality ለጥፋት የተሰማሩትን መጥቀስ ይቻላል ፡፡ ) ። ከእነዚህ ለየት ባለ መልኩ ደግሞ የሚኖርበትን ህዝብ ሥነ _ ልቡና በውል የተረዳ ግለሰብም ፣ ያለውን እውቀትና ተሰሚነት ተጠቅሞ ሺዎችን ለመጥፎ ድርጊት በቀቢጸ ተስፋ አላማ በመንጋነት ማሠለፍ ይችላል ፡፡

ለጥፋት አላማ ሺዎች ከተሰለፉ ደግሞ ፣ ህዝብ ነው የሚባሉት ፡፡ ማሰብ የተሰነው ጭንቅላት አልቦ ህዝብ ፡፡ አሥቀድሞ ነገር በመንጋ የሚጓዝ ህዝብ ፣ በገዛ አእምሮው ማሰብ ያቆመ ፣ በጥቅሉ ትዕዛዝ ተቀባይ ጆሮ ብቻ ያለው ህዝብ መሆኑ የተረጋገጠ ነው ። ህሊናው በመንጋው መሪ ፕሮፖጋንዳ ተሰልቧልና ላይፈረድበት ይችላል ። ሆኖም ግን ይኽ መንጋ አንጎለ ቢስ ነው ።

ይሄ ግልጽ የሆነ እና የልተሸፈነ እውነት ነው ፡፡ ቢያንስ ፣ ቢያንስ መንጋ ህዝብ ፣ ከአንድ ሰው ፣ ወይም ከአንድ ቡድን ጀርባ ለተሰለፈበት ጉዳይ አንጎል አልባ ነው ። ( ጭንቅላታቸው ተቆርጦ ሆኖም ገጀራ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ፣ ፊት አልባ ሆኖም አለዓይን እንደ ልብ የሚራመዱና በቡድን ሆነው ሰላማዊውን ባለፊት ፣በለአይንና ባለ አንጎል የሚያጠቁ ሰዎችን ጭካኔ የሚያሳይ የፊልም እስክሪፕረተ በመጻፍ አንድ ድንቅ አስተማሪ ፊልም ወደፊት ይሰራል ብዬ በመገመት ሃሰቡን እንካችሁ ብያለሁ ፡፡ )

መንጋዊ ህሊና ያለው ፣የራሱ ህሊና የተወሰደበት ጭንቅላት አልቦ ሰው ፤ በቀቢፀ ተሥፋ ና በህልም ምኞት እንደ ደራሽ ወንዝ ወይም እንደ ቅሥፈታዊ አውዳሚ መአበል “ ሱናሚ “ የሚሆነውም አንጓል አልባ በመሆኑ ነው ። መንጋው ፈፅም ለተባለው ጉዳይማሰብ ፣ እንዴት ? ማን ?ለምን ?መቼና የት ? ብሎ የሚጠይቅ አንጎል የለውም ፡፡ መንጋው ያለጭንቅላት ነው የሚጓዘው ፡፡ ለማንኛውም ጥፋት በአንድ ወይም በጣት በሚቆጠሩ ተንኮለኞች ነው ፤ የሚመራው ፤ የሚንቀሳቀሰው ፡፡ ያለአንዳች ማሰብ ነው ፤ የሚተመው ፡፡ የጥቂቶችን ሃሰብም ያለማወላወል የሚተገብረው ፡፡ ” ለምን ? በምን ምክንያት ? መቼ ? የት ? ማን አይቷል ? ማስረጃ አለህ ወይ ? ወይስ በመረጃ ብቻ ነው ? ይህንን አድረጉ ብለህ የምታዘን ” ” ብሎ ከመንጋው መሀል ማንም አይጠይቅም ፡፡

የመንጋው አባል ሁሉ ፣ አንገቱ ላይ ጭንቅላቱ መቀመጡ እውነት ቢሆንም ፤ በተግበራዊ ስራው ላይ ግን የለም ፡፡ ጭንቅላታቸው ዞር ብሎ እስከሚያየው አንገታቸው በተፈጥሮ በተሰጠው አገልግሎቱ ላይ ተሰማርቶ አታገኙትም ፡፡ መንጋዎች ፣ ” አንገት እና ጭንቅላት አለን ፡፡ ” ብለው ያስባሉ ፡፡ ይበሉ እንጂ በአስተሳሰብ ደረጃ ፣ ጭንቅላትም ሆነ አንገት የላቸውም ፡፡

የመንጋዊ አስተሳሰብ ድርጊት ፤ ማስተዋል ላለው ና ለመብላት ብቻ ለማይኖረው ሰው እጅግ አስገራሚና አሳዛኝ ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡ አሳዛኝ ፍጥረት ያደረጋቸውም ጭቅላታቸውን በጥቅማ ጥቅም ፤ በቀቢፀ ተስፋ ና በማይረባ ገንዘብ ማስቆረጣቸው ነው ፡፡ ልክ እንደ አሳዛኙ ” ተገዶ እንጂ ፈቅዶ እነደማይዋገው ” የትህነግ የመንጋ ጦር ፡፡

እናም በሉ የተባሉትን ፤ አድርጉ ና ፈጽሙ የተባሉትን ማንኛውንም ሤጣናዊ ተግባር ሳያቅማሙ ተገደው ፣ ሲላመዱት ደግሞ ወደው ይፈፅማሉ ፡፡

ነገም ፣ ለኢትዮጵያውያን ክብር ፣ ሠላም ፣ ፀጥታ ፣ ፍትህ ፤ የተሞላ ሰላም ፤ ደህንነት እና የጋራ ብልፅግና የሚቆረቆር ህግ አስከባሪ በመላው አገራችን ፣ በተቋም ደረጃ እስከሌለ ግዜ ድረስ፣ እዚህ ግባ በማይባል ጥቅማ ለሚደለል ና ጭንቅላትን በመቁረጥ ለሚያስፈራራ ፀረ አገርና ፀረ ህዝብ ኃይል ሁሉ ተገዢ የሚሆን መንጋ መፈጠሩ አይቀርም ፡፡ ያልተልከሰከሰ ፣ ልጨኛ ና ለፍትህ ሟች ህግ አስፈፃሚ አካል ፤ ዜጎች በሚፈልጉት ደረጃ ፣ አዲሱ መንግስት በአዲስ አስተሳሰብ ፣ ተቋማቱን አጠናክሮ ፤ አንገት ቆራጭና ህሊና ቢስ አድራጊ እጀ እረዢም ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎችን ሴራ ካላከሸፈ በስተቀር ፤ መሰል የጥላቻ ተግበራት ነገም ሆነ ከነገ በስትያ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለመገመት ነብይ መሆን አይጠበቅብንም ፡፡

እንግዲህ ነብይ ባንሆንም ፣ የፕሬስ አባላት ራሳችንነን እንደ አራተኛው የመንግስት አካል እንቆጥራለን እና ” መንጋነትን የሚያስፋፉ እነማን ናቸው ? ” በማለት በህዝብ ምርጫ ለስልጣን የበቀው የብልጽግና መንግስት ማለትም ፤ የህግ አውጨው ፣ የህግ ተርጓሚው እና የህግ አስፈፃሚው አካል ፣ ቆም ብሎ እንዲጠይቅ እናሳስባለን ፡፡ አፋጣኝ መፍትሄም በመሰነድ ይህንን የዘመናት አጀንዳ ሊዘጋው ይገባል የሚል ሃሰብ እናቀርባለን ፡፡

በነገራችን ላይ ፤ ዘላለም አለማችንን በእሳት እንድንጫወት ማነው የሚፈልገው ? ( የአበራሽን ትልቅ የእሳት ጠባሳ እያየን ፤ እሳት ማቃጠሉን መማር እንዴት ያቅተናል ? ) እውን ፤ ከባይደን ፤ ከአልሲሲ ፤ ከቅጥረኞቹ ትህነግ ና ከኦነግ ሸኔ ውጪ ? ማን ነው ይኽንን ሞኝነታችንን የሚፈልገው ?

አውን እኛ በከተማ የምንኖር ሰዎች ከየትኛውም ብሔረሰብ ና ብሄር ( ነገድ ፣ ጎሳ ፤ ዘውግ ) ጋር በጋብቻ የተዛመድን አይደለንምን ? ከተሞችን የአንድ ቋንቋ ብቻ መኖርያ ማድረግ ይቻላልን ? ጭንቅላት የሌለው መንጋ ካልሆነ በስተቀር ሰውን በተራ ቃላት ” በጠባብ ና በነፍጠኛ ፤ በዚህ ቋንቋ ና በዛ ቋንቋ … ” መከፋፈልና ማራረቅ ይችላልን ? ከቶስ የመፈቃቀርና የመጋባት ጉዳይ የሁለት ግለሰቦች የግል ጉዳይና መብት አይደለንምን ? ሰው ልጅ በተፈጥሮ በተሰጠው በራሱ አእምሮ ፍላጎት የተፈጥሮ ስጦተውን ይመራል እንጂ በሌላው አእምሮ ፍላጎት እንዴት ሰውነቱን ለማኖር ይችላል ? የምንበላውን ምግብ እንዴት ሌላ ሰው አላምጦ ይውጥልናል ? ያ የሚመራን ሰው ጭንቅላታችንን ቆረጦ ካልወሰደብን በስተቀር !?… ፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop