ሰላምን የሚያወርድ፣ – ጆቢር ሔይኢ ከሁስተን ቴክሳስ

10/19/2021

የእግዚአብሔር ቃል፣”ይቅር የሚል ይቅርታን ያገኛል፣ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና።ምሕረትን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፣ምሕረትን ያገኛሉና” ይላል። በአንፃሩም” ሰውን የገደለ ሁሉ ስለሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፣ የሟቹንሰውደምከገዳዩ፣ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ ። የሰውን ደም የሚያፈስ ሁሉ ደሙ በሰው እጅ ይፈሳል፤እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ሰርቶታልና” ይላል።ከዚህ የፈጣሪያችን ቃል እንጻር እያንዳንዳችን ተግባራችንን ብንፈትሽ ፣ እያጨድን ያለነው ያንኑ የዘርነውን ሆኖ እናገኘዋለን።

በዚህም ረገድ ፍቅርን ዘርተን ቢሆን ሠላምን ባጨድን ነበር።የዘራነው ጥላቻን በመሆኑ ሞትን በማጨድ ላይ እንገኛለን። ለዚህ ያበቃን ደግሞሁላችንም በሌላው ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍተመልካቾች በመሆናችን ነው። በራሳችን ዓይን ውስጥ ስለ አለው ግንድ ግን ማየትም መስማትም አንሻም። ስለ አገር ጉዳይ ሲነሳም፣ቄሱም ሆነ ሼኪው ሁላችንምከብሔራችን፣ ከቋንቋችን፣ ከእምነታችን፣ከባህላችን፣ከታሪካችን፣ ክጥቅምና ሥልጣናችን ተነስተንነው፣ ትንታኔና ድምዳሜ የምንሰጠው።ሕገ መንግሥቱን የምንገመግመው፣ የመክላከያ ሠራዊቱን ለማሠማራት የምንሸው፣በመንግሥት በጄት ለመጠቅም የምንፈልገው። የሌላው ወገን ጥቅም ይቅርና በሕይወት የመኖር መብት እንኳን፣ ያለው አይመሰለንም።የማርያም ጠላት በማለት ተረባርበን ነው፣ከምድር ገፅ የምናጠፋው።

እንግዲህ ይህ ትናንት የነበረ፣ ዛሬም ያለ የጋራ ችግራችን ነው። ይህን ድክመታችንን ተገንዝበን፣በጋራ አገራችን ፣እንደ የአንድ አባት ልጆች፣የሁሉንም መብትና ጥቅም በእኩልነት በመክበር፣ በፍቅር መኖር ይገባናል።ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ጊዜና ወቅቱ የፈቀደለት ወገን በማን አለብኝነት ተነሳስቶ ያሸውን የሚያደርግ ከሆነ፣መብትና ጥቅሙ የተሸራረፈበት ወገንም፣ ወቅቱን ጠብቆ መበቀሉ አይቀሬ ነው።ይህንም ከወታደራዊ ደርግም ሆነ፣ከኢሕአዴግም መማር ይገባናል።

በዚህ ላይ ክፉው አለ። ደካማ ጎናችንን ያውቃል። በሥልጣን፣ በዘር፣ በክብር ደልሎ፣ አርስ በርስ አጋጭቶ ደም በማፋሰስ፣ የጥፋት ግብረ አበሮቹ በማድርግ፣ ከፈጣሪ አምላካችን ፈቃድና ፍቅር ሊለየን፣ዓይኑን አፍጦ ይከተለናል።

አምላካችን ደግሞ ልጆቹ በመሆናችን፣ ከክፉ ሥራችን ታቅበን፣ በንስሓ ታድሰን፣ፈቃዱን ፈጽመን፣ በመታዘዝ በፍቅሩ በመኖር እንድንባረክ ይሻል።ይህ እውነት ገብቶን፣ፊታችንንወደ ፈጣሪ አምላካችን መልሰን፣ እጃችንን ወደ እርሱ ከዘረጋን፣ይቅር ይለናል።እንደ ፈቃዱምየሚጠሉንን ከወደድን ፈጣሪ አምላካችንምይወደናል ይባርከና።ድርቅና ተምችን፣ ጦርነትና፣በሽታን ከአገራችን አስወግዶሠላምን ይሰጠናል።

በዚህ ረገድ የአገራችንና የሕዝባችን ነባራዊ ሁኔት ሲታይ፣በመጀመሪያ አንድ የጋራ አገር ነው ያለን እንጂ አንድ የጋራ እምነት የለንም። እኛ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በብሔር፣በቋንቋ፣በባኅል የተለያየን ነን። እያንዳንዱ ብሔር ደግሞ የራሱ የሆነ ቋንቋ፣ ባህል፣በጂኦግራፊ ተለይቶ የሚታወቅ የመኖሪያ አካባቢ አለው።

እያንዳንዱም ብሔር፣ በቋንቋው በመጠቀም ባህሉን ባማበልጸግ ታሪኩን በማዳበር ራሱና በራሱ ለማስተዳደር ይሻል።ይህም ተፈጥሮአዊ ውበታችንበመሆኑ ሊከበርለት ይገባል።የችግራችን ምንጩ ይህን የሰው ልጆችን ተፈጥሮአዊ መብት አለመከበር ነው። እንደሚታወሰው አገራችን የቅኝ ገዥዎችን የባህልና የእምነት ወረራ በመፍራት፣የባሕር በሯንዘግታ፣ ከዓለም ሥልጣኔ ተገልላ ነበር የኖረችው። የሌሎች የአፍሪካ አገሮችን ኢኮኖሚ ከኋላ ቀርነት ያላቀቀው፣ የቅኝ ገዥዎች ዕውቀትና ቴክኞሎጂ ነበር።ይህ ግን ጉዳትም ጥቅምም ያለው በመሆኑ ወደ አገራችን አልደረሰምናልይነቶቻችንን ማስተዋል ይገባናል። ስለሆነምበአገራችን የማምረቻ መሣሪያዎቻችን ሳይሻሻሉ ባሉበት ቁመው በመቅረታቸው፣ ገዥው የጉልተኛው መደብም፣ ወደ ብሔራዊ ከበርቴነት አልተሸጋገረም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መላዉ ኢትዮጵያ ከግፍ እስር እና ፍትህ ዕጦት ነፃ አስኪሆን መሰራት አለበት

መሳፍንታዊውን የዘውድ አገዛዝ የገረሰሰውወታደራዊ መንግሥትም አምባገነን ስለነበር በኋላ ቀር የግብርና ኢኮኖሚ የሶሻሊዝምን ሥርዓት እገነባለሁ በማለት በምኞት ተነሳ። የማምርቻና የማከፋፍያ ድርጅቶችን በመውርስ በማቆጥቆጥ ላይ የነበረውን የካፒታሊዝም ኢኮኖሚ አቆረቆዘ። የብሔር ብሔረሰብ ጥያቄንም አልመልሰም፣ስብዓዊ መብት አላስከበራም። ኢሕአዴግም ቢሆን በስም እንጂ በግብር የብሔር ብሔረሰቦች መብት ጨፍላቂ ነበር።

ከዚህ የተነሳየአገራችን የአሁኑ ሁኔታ ሲታይ፣ብሔር ብሔረስቦች አስተባባር አጥተው፣ የፌድራል መንግሥቱ በክልሎች ሥልጣን፣ ክልሎች ደግሞ በፌድራል መንግሥት ሥልጣን ውስጥ ጠልቃ በመግባት፣በጎበዝ አለቃ ተደራጅተው፣የግዛት ማስፋፋት ወረራ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። ይህ በአንድ አገር ሕዝቦች መካከል እየተካሄደ ያለው አሳፋሪ ጦርነት፣መንግሥት ሊገታው ባለመቻሉ፣ ወደ ፋሺሽታዊ የርስ በርስ ጭፍጭፋበመግባት ላይ ይገኛል።

ከዚህም አንጻር ሕዝባችንበሦስት ጎራ ተሰልፎ ይገኛል።ከጎራዎቹም የመጀመሪያው የብሔር ብሔረሰቦችን መብት በማጥላላት፣ሕገ መንግሥቱንና የፌድርል ግንኙነትን ለማፈራረስ፣ በኢትዮጵያ አንድነት ስም ተደራጅቶ፣ የብልጽግና ፓርቲን ተጠግቶ የሚገኙ፣ የዴሞክራሲመብት ጨፍላቂ ነው።

ይህበጉልተኛ ሥርዓት ተስፈኛ ምሁራንና በከአክራሪ የብሔር ትምክህተኞች ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ፣የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን በመቆጣጠር፣ጥቃቅን ቅራኔዎችን እያራገበ በማክረር፣ብሔር ብሔረሰቦችን እርስ በርስ በማጋጨት፣ አገሪቱን ለጦርነት ማግዶ ፣ ሠላምና እርቅን በማጥላላት፣አገሪቱን ከኃያላን አገሮች ጋር በማጋጨት፣ከፋፍሎና አዳክሞ፣የመግሥት ሥልጣንን ለመንጠቅያሰፈሰፈና፣ ከሁሉም ይልቅ የነቃና የተደራጀ ጎራ ነው።

ሁለተኛው፣የሕገ መንግሥት ደጋፊና፣ የአሐዳዊ መንግሥት ተቃዋሚ የሆነ፣ለብሔር ብሔረሰቦች ዲሞክራሲያዊ መብት መከበርናለኢኮኖሚ ነፃነት የሚታገል ጎራ ነው። ይህ ጎራሕገ መንግሥታዊ ድጋፍ ያለው በመሆኑ፣የመደመርን ፖሊሲ ተቀብሎ፣ የመንግሥት ሥልጣን ከያዘው ከብልጽግና ፓርቲና ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመጣበቅ፣የመሪ ድርጅት ችግሩን መቅረፍ ሲገባው፣በአመራር ጉድለት፣በአሐዳዊያን ትንኮሳ በርግጎ፣ከብልጽግና ጋር በመላተም ሠላማዊ የትግል በሩን በራሱ ላይ የዘጋ ነው።ይህ ጎራ ከዚህ ስህተቱ በመማር የአቋም ለውጥ ካደረገ፣የብሔር ጭቆና ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያስተባብር፣ መደቦችንም እንኳ የሚያስታርቅ፣በሂደትም ተቀናቃኞቹን እየዋጠ ፣ በፍጥነት እየበዛ የሚሄድዲሞክራሲያዊ ጎራ በመሆኑ፣ ሠላማዊ የዕድገት ጎዳና ከተመቻቸለት ማንም ሊገድበው አይችልም።

ሦስተኛው ፣ የመከላከያና የድኅንነት ኃይልን በበላይነት በመቆጣጠር በመንግሥት ሥልጣንና በኢኮኖሚው በማዘዝ ፣የከረረውን የብሔር ጥያቄ በኃይል በማርገብ።በመደመር ፖሊሲ አገራችንን ከድህነት የማላቀቅ ምኞት ያለው የብልጽግና ጎራ ነው።የዚህ ጎራ ዒላማው መልካም ቢሆንም፣ ውስጠ ደርጅቱ፣ በቅራኔዎች የተመላ፣ የወል ርዕዮተዓለም የሌለው፣ቅራኔን አለዝቦ መፍታት የማይችል፣ጠላትና ወዳጁን የማይለይ፣ አገሪቱን በእርስ በርስ ጦርነት በመማገድ፣የወታደራዊ ደርግን ውድቀት በመድገምላይ የሚገኝነው።

በመሆኑም ይህ ጎራ ያልሆነውን የሆነ መስሎት፣ በምኞት መመጻደቁን ትቶ፣ነባርዊ እውነታን በጥልቅ በመፈተሽ ፣የአደረጃጀት ችግሩን በመቅረፍ ፣ ከተቃዋሚዎሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የገባውን ቅራኔ አለዝቦ፣ ከምዕራቡም ሆነ ከምሥራቁ ጋር በመተባበር፣በሕገ መንግሥቱ መሠርት ቢመራ፣አገሪቱን በሠላም ወደ ብልጽግና በማሸጋግር ረገድ ከሁሉም የተሻለ ሥልጣንና አቅም ያለውጎራ ነው።

በዚህም ረግድከሕዝቦችን መካከል ቅራኔዎችን በማስወገድ ፍቅር፣ ስላምና ኅብረት ለማስፈን ከፈቀድን፣ መፍትሔው ከራስ ወዳድነት በመላቀቅ፣ የቅራኔ አያያዝ ሳይንሳዊ መርሆን በመከታል፣ የጭቆና ፈርጆችን ሁሉ በጋራ መታገል ይገባናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአብይ አህመድ ውሸቶች (2018-2020) ክፈል 1 - ሊባኖስ ዮሃንስ

ለዚህ ደግሞ፣ ከሁሉም በፊት፣ በሕዝባችን መካከል የተቀጣጠለውንየጦርነት እሳት ለማጥፋት ሀ / ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም ልዑክ ጋር በመተባበር፣ ጦርነቱንበማቆም፣ ስፍራውን ለአፍሪካ የሰላም ልዑክ ማስረከብ ያስፈልጋል።

ለ / በክልሎቹ መካክከል የተነሳውን የወሰን ግጭት በሰላም ለመፍታት፣የመከላከያ ሠራዊትን ከሲቪሉ ሕዝብ መካከልበማውጣት፣ በወሰንጥበቃ ሥራው ላይ ማሠማራት ይገባል።

ሐ / በአማራና በትግራይ መካከል የይዞታ ይገባኝ ጥያቄ በተነሳባቸው አካባቢዎች የሚገኙ፣ የትግራይም ሆነ የአማራ ታጣቂዎችንየቡድንትጥቃቸውን በማፍታት ለአፍሪካ የሠላም ልዑክ በማስረከብ ፣ወደ ሠላማዊቀጠና እንዲመለሱ ማስተባበር ይገባል።

መ / በጦርነቱ ለተፈናቀሉትና ለችግር ለተዳረጉት ሰብአዊ እርዳታ በፍጥነት እንዲደርሳቸው ለማድረግ ወንድም የሆነውን የኤርትራ ሕዝብና መንግሥት ትብብር በመጠየቅ፣ የምፅዋና የአሰብ ወደቦችና መንገዶችን በተጨማርነት በመጠቀም፣ የነፍስ አድኑን እርዳታ በፍጥነትለሁሉም ማድረስ ይገባል።

ሠ /ጦርነቱ የተካሔደው በአንደ አገር በወንድማማች ሕዝቦች መካከል በመሆኑ፣ጥፋቱም ሆነ ተጠያቂነቱ የጋራ ነው።በጦርነቱ የተሸነፈችውም ሆነ የማቀቅችው፣ ኢትዮጵያ እናት አገራችን ናት። ስለዚህም በአንድ እናት አገር ልጆች መካከል የተፈጠረው የጥላቻ ፋይል በነፃ በመዝጋት፣በቀልን ለፈጣሪ በመተው፣ሠላማዊ የኅብረት ጎዳናን በይቅርታ መጀመር ይገባል።

ረ / ከዚህም አንፃር በጦርነቱ ወቅት የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ሁሉ ሊፈቱ፣ የጦር ምርኮኞች ሊለቀቁና በወንጀል የተከሰሱና በፖሊስ የሚፈለጉክሱ ሊነሳላቸው ይገባል። ሰ/ ለዚህም የሠላም ተግባር መሳካት አገራችን በበኩሏ፣ አንድተደራዳሪየሰላም ልዑክ መርጣ በመሾም፣ ለአፍሪካ ኅብረት ማሳወቅ ይገባታል።

ሸ /ሕገ መንግሥትን በሚመለከት፣

1 / እየንዳነዱ በሔራዊ ክልል የራስን ሕገ መንግሥት አሻሽሎና አዳብሮ በመቅረጽ በሕዝበ ውሳኔ ሊያጸድቀውና ሊመራበት ይገባዋል።

2 / የፌደራል ሕገ መንግሥትምበፌድራል ተግባርና ሥልጣን ላይ የሚያተኩር ሁኖ የክልሎችንምሕገ መንግሥት የሚያስከብር መሆንይኖርበታል።

3 / የመንግሥትና የፓርቲ ሥልጣንና ተግባር በግልጽ የሚለይ፣የሕግ የበላይነትን የሚደነግግ፣ ከማንኛውም አካል ቁጥጥር ነጻ የሆነ፣የፍትሕ አካል ለማደራጀት የሚያግዝ፣ከሁሉም ይልቅ የመንግሥት ሥልጣንን ለሕዝብ የሚመልስ፣ፕሬዚዳንታዊ ቅርጸ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል ሊሆን ይገባዋል።ይህ ከሆነ፣መንግሥት የመራጩን ሕዝብ መብት ለማክበር ይገደዳል።

እስከ አሁን ባለው ሁኔታ፣ ወገናዊነት ከመጠን አልፎ፣ የግለ ስብን ሰርቶ የመኖር መብትና የእምነት ነፃነትን ከሚገፊፍ ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑ፣ ፍርድ ቤቶች፣ሕግና ሥርዓትንበማስከበር ረገድ ህብረተሰቡን በእኩልነት ሊያገለግሉ አልቻሉም፣ስለዚህም የሕግ የበላይነትን በማስከበር ረገድ በየደረጃው የሚገኙ፣ የመንግሥት ሥልጣን አካላት ሁሉ ሊተባበሩ ይገባል።

ቀ /የትምህርትና የሥራ ቋንቋን በሚመለከት፤

በሕገ መንግሥት የፌድራል የሥራ ቋንቋ ሆኖ የተመረጠው አማርኛ ነው።አማርኛ ደግሞ የአንድ ብሔር የአፍ መፍቻ ቋንቋና የአንድ እምነት ድርጅት የመግባቢያ ቋንቋ ነው።ሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ደግሞ የየራሳቸው የአፍ መፍቻና የእምነት ቋንቋ አሉዋቸው።በመሆኑም የአንድን ብሔርና እምነት መብት አክብሮ፣ የሌላውንብሔርና እምነት መብት ማዋረድ ተገቢ አይደለም።በመሆኑም የፌድራል የሥራ ቋንቋችን እንግሊዘኛ ሊሆን ይገባዋል።

ለምን ቢባል1/ ከቋንቋዎች ሁሉይልቅ እንግሊዘኛ ፤በሳይንስና በቴክኖሎጂ ቃላት በጣም የበለጸገ፤ የጥበብ ማሰራጫ፤ የዓለም ሕዝብንም እርስ በርስ የሚያግባባ ቋንቋ ነው። 2 / የዓለም ሕዝብ እየተማረ ያለው አንደበቱን በፈታበት ቋንቋ ነው። ትምሕርት በጀመረውም ቋንቋ እስከ መጨረሻው ይማራል።ከእኛበስተቀር ቋንቋ በመቀያየር፣የትምህርት ጥራትን በመፈታተን፣በትውልዱ ላይ ችግር የሚፈጥር አገር የለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሁለት መነጽሮች ወግ - አስቻለው ከበደ አበበ ሜትሮ ቫንኩቨር ካናዳ

3 / አብዛኛው የዓለማችን ሕዝብ እየተግባባ ያለውበእንግሊዘኛቋንቋነው፤ የአፍሪካ አገሮችም እንዲሁ። በአገራችንምቢሆን ቀድሞ የትምህርት ቋንቋችንከአራተኛ ክፍል ጀምሮ እንግሊዘኛ ነበር። ዛሬም ቢሆን ሃብታሞችና ባለሥልጣኖች ከአጸደ ሕፃናት ጀምረው ልጆቻቸውን በእንግሊዘኛ እያስተማሩ ናቸው። በቋንቋዎች መቀያየር ተጠላልፈው እየወደቁ ያሉት የገበሬዎችና የድሃ ልጆችናቸው።

4 / እስከ አሁንያለው የቋንቋ በየፌርማታው መቀያየርና የተምህርት ጭነት አለመመጣጠንአገራችንንና ሕዝባችንን እጅግ እየጎዳ ነው፤ አንደበታቸውን በአማርኛ የፈቱ የከተማ ልጆች፤ እንግሊዝኛን ብቻ ነው አዲስ ቋንቋየሚማሩት፤ በሌሎች ቋንቋዎች አንደበታቸውን የፈቱ ተማሪዎች ደግሞሁለት አዲስ ቋንቋ፤ ማለትም አማርኛና እንግሊዘኛ የመማር ግዴታ አለባቸው። ከዚህ የትምሕርት ጫና ልዩነት የተነሳ ብዙዎቹ በፈተና ይወድቃሉ፤ ፈተናውን ያለፉትም ቢሆን ነጥባቸው አነስ ስለሚል ከፍተኛ ትምሕርት የመከታተል ዕድላቸው የመነመነ ነው። ሌላው ቀርቶ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው እንኳን፤ በእንግሊዘኛ ከተማሩትጋርበመወዳደር ሥራ ማግኘት ስላልቻሉ፤ብዙዎቹ ሥራ አጥ ሁነዋል።በትምህርት ጥራት ውድድርና በፈተና ውጤት ምዘና ረገድም፣ሁል ጊዜ አዲስ አበባና የአማራ ክልል ልቀው የሚገኙት፣የእነርሱ ተማሪዎችየትምህርት ጭነት፣ከሌሎችተማሪዎች የትምህርት ጭነት የቀለለናበአንድ የትምህርት አይነትያነሰ በመሆኑ ነው።ስለሆነም ምዘናው ራሱ ፍትሐዊ ያልሆነ፣ ሆን ተብሎ ወደአንድ ወገን ያጋደለ ነበር።

5 / ስለሆነም ካለፈው ስህተታችን በመማር፣የብሔር ብሔረሰቦችን የቋንቋ ጭቆናን በማስወገድ፣ ከመጠቀው ካዓለም ሥልጣኔጋር እኩል ለመራመድ፤የመደበኛ ትምሕርትና የፌድራል የሥራ ቋንቋ እንግሊዘኛ ሆኖ፣አረቢኛ፣አማርኛናአፋን ኦሮሞእንደ መግባቢያ ቋንቋ እንዲያገለጉ መፍቀድ ይገባል።ይህ ከሆነማንኛውም ሰው የትም ሂዶ፤ ያለ ስጋትበተማረው ቋንቋ ለማገልገልም ሆነ፣ ከጎሮቤቶቻችን ጋር በይበልጥ በመግባባት፣ለመረዳዳት ያስችለናል።

በ / ከዚህ በለይ የተመለክቱትን ችግሮችን ለመፍታት፣የብልጽግና ፓርቲከኢትዮጵያ ሕዝብ በተጣለበትሃላፊነት መሠረት1ኛ / በፌድራል ሕገ መንግሥቱባለፉት ሃያ ዘጠኝአመትየታዩ ጉድለቶችን ሁሉ ራሱ ሊያስተካክለው ይገበዋል።

2ኛ /የፌድራል መንግሥቱን ሥልጣንና ተግባር ከብሔራዊ መስተዳድሮችና ክልሎች ጋር እንዳይጣረዝ ማድረግ ይጠበቅበታል።

3ኛ / ድብልቅ የኢኮኖሚ ሥርዓት፣ማዕከላዊ መንግሥትንይበልጥ የሚያበለጽግ፣ ሠርቶ አደርን ሕዝብ ይበልጥ የሚያደሃይ፣ሕዝቡን የመንግሥት ጥገኛና፣ ሥራ አጥ የሚያደርግ በመሆኑ፣የዕድገት አቅጣጫችን፣ የነፃ ገቢያ ኢኮኖሚን እንዲከታል ቢያደርግ።

በዚህ መልኩ የሕዝባችን ጥያቄዎች ከተመለሱ፤ ከሕዝባችን መካከል ጥላቻ ይወጋዳል።መፈነቃቀሉ ያከትማል። መንግሥትም በሕዝቡ ላይ ፈላጭ ቈራጭ መሆኑ ያከትማል።ምዕራባዊያን ኢንቬስተሮችን ከአቢዮታዊ ዲሞክራሲ ፍራቻና ሥጋት ስለሚያላቅቅ፣የውጭ መዋዕለ ነዋይ በመሳብ፤አገራችንም ተጨማሪ እርዳታና ብድር እንድታገኝበማድረግ፣ ሕዝባችንን ከሥራ አጥነት በማዳን፤የአፍሪካ አንድነትንና የምሥርቅ አፍሪካን ውኽደት የሚያፋጥን ይሆናል።

ይህምበአገራችንያለውን የሴራ ፖለቲክ በመቅረፍ፣ ዴሞክራስያዊ ሥርዓትን በማዘመን፣ የግለ ሰብና የብሔር ብሔረሰብን እኩልነትን በማስፍን፣ በሠላምናበፍቅር ተባብረን በአንድነት የምንኖርበትን አገር ለማበልጸግየሚረዳን በመሆኑ፣ ትልቁም ሆነ ትንሹ ያለፈውን ጥላቻና ቅሬታን ስለ ፈጣሪ አምላኩሲል በይቅርታ በመተው፣ በንጹህ ልብ ሊቀባበል ይገባዋል።

ስለዚህም ቸሩ ፈጣሪአምላካችን፣ ከእርስ በርስ ጥላቻና ክሴራ ፖለቲካ አላቆ፤ በመተማመን ከወንድሞቻችን ጋር ተስማምተንና ተባብረን በሰላም አብረን የምንኖርበትን፣አጋቤ ፍቅሩንይስጠን።አሜን !

ጆቢር ሔይኢ ከሁስተን ቴክሳስ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share