October 11, 2021
11 mins read

ወደር የለሹ የወያኔ ቅዠትና የምቀኝነት ጥግ (ድንቁ ሞላ)

tplfስለወያኔ ቅዠት፦

የወያኔ ርዝራዦች ሳያቋርጡ እንደሚለፈልፉት ቢሆን ኖሮ የእነርሱ የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ ብቻ ትክክለኛ፣ ትህነግ ብቻ ጀግና፣ አማራ ብቻ የሚሞት፣ የትግራይ ወታደር በጥይት የማይመታ …ወዘተ ነው የሚሉት ቀደዳ መሬት ላይ እውነት ሆኖ በተገኘ ነበር፡፡ይህ በደማቸው ውስጥ ስር የሰደደው የውሸትና የሀስት ቀደዳ ከዱሮ ጀምሮ የተጠናወታቸውና አብሯቸው እድሜ ልክ የኖረ በሽታቸው ነው፡፡ በአጭሩ ትዝብትን የማያውቁ የከንቱ ከንቱዎች ናችው፡፡ የሚገርመውም ጭፍን ለጭፍን እርስበርሳቸው በውሸቱ ላይ ተማምለው ሲመመሰጋገኑና ሲደጋገፉ ማየቱ ነው፡፡ያፈጠጠና ገሐድ የወጣ ውሸትን ሽምጥጥ አድርገው ክደው ጉልበታም እውነት ለማስመሰል በድርቅና ክችች ሲሉ ቅንጣት የማያፍሩ ናቸው፡፡ወያኔዎች ከነርዝራዦቻቸው በደደቢት ፍልስፍና ተመርዘው ባሉበት ተቸክለው ቀርተዋል፡፡ በዚህ ላይ እንደ ታምራት ላይኔና ልደቱ አያሌው አይነቶቹን ሆድ አደሮችና በድፍን አማራው ዘንድ የተተፉትን ልክስክሶች ለምስክርነት ይጠቅሳሉ፡፡ ይህ የሆድሞቹ ምስክርነት ከወያኔ የ27 አመታት እጅግ የቆሸሸ ታሪካቸው ማለትም ከሌብነታቸውና ከውሸታምነታቸው ጋር ሲደመር ወደር ለሌለው እጅግ የወረደ የወያኔ ማንነት ማረጋገጫና በቂ ማሳያ ነው፡፡

ማንም ሊክደው የማይችለውና ነግር ግን ማንም ደፍሮ ሊናገረው የማይፈልገው አንድ እውነት አለ፡፤ይሄውም የሰሜን እዝን በዘር እየለዩ በምሽት የተካሄደን ዘግናኝ ጭፍጨፋን ጨምሮ አሁን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ወያኔ አቅዶ የጀመረበት ዋናው ምክንያት ለም የሆኑትን የራያና ወልቃይት የአማራ መሬቶችን በትግራይ ስር አድርጎ ከኢትዮጵያ በመገንጠል ታላቋ ትግራይን በአገርነት ለመመስረት ባለመው ቅዠቱ መሰረት ነው፡፡ በአፈሯ መሸርሸርና በድርቀት ዑደት ውስጥ የምትኖረው ወጣ ገባዋ ትግራይ ወያኔ በጉልበት ወስዷቸው ከነበሩት የራያና ወልቃይት ለም መሬቶች ውጭ በራሷ ራሷን ችላ እንደአገር መቆም እንደማትችል ወያኔወች ጠንቅቃችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ስለሆነም ላይመለስ የከሸፈው ቅዠታችሁ የአማራ ለም መሬቶችን ሰርቆ ወይንም በጉልበት ከአማራው ነጥቆ መገንጠል ነበር፡፡ይህ ግን ሊሆን አልቻለም፡፤ወደፊትም ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ለአመታት አያሌ ሰቅጣጭ ወንጀሎችና ከባድ የዘር ማጥፋት የተሰራበት የአማራ ጀግና ህዝብ የግፍ ጽዋው ሞልቶ የወያኔን የጦርነት እብሪት ገና በጧቱ ስላስተነፈሰው ነው፡፡ ስለሆነም ወያኔወች ሆይ፦ተወጣም ተወረደም ለታላቋ ትግራይ የቋመጣችሁለት የራያና የወልቃይት ለም የአማራ መሬትቶች ቅዠት ብቻ ሆኖባችሁ ለዘለአለም ሲያቃዣችሁ ይኖራል እንጅ ከእንግዲህ አታገኙትም፡፡ እርም ይሁንባችሁ፡፡መሬቶቹ ለህጋዊና ታሪካዊ ባለቤቶቻቸው ለአማራ ህዝብ በደም ዋጋ ተመልሰዋል፡፡ ከእንግድህ በኋላም በውጭ አገራት አደባባዮች በመንከባለልም፣ በማለቃቀስም፣ለውጭ አገራት ባለስልጣኖች ክስን በማቅረብም ፣ ከኢትዮጵያ ድሀ ህዝብ የተዘረፈ ዶላርን በመንዛትም… ወዘተ የሚመጣ ቅንጣት ለውጥ የለም፡፡ አማራው በተረኛው ኦሮሙማ ሴራ የአርበኝነት ተጋድሎው ለጊዜው ክፉኛ እየተሰናከለበት ቢሆንም ያን ሁሉ ችሎ፣ አስተንትኖ፣ በስሌት በመጓዝና በረዥሙ በማቀድ ጀግንነቱን ካልካዳችሁ በስተቀር ጠንቅቃችሁ በምታውቁት ነፍጠኛነቱ እስከመጨረሻውና አስተማማኝ ድል ማድረጉ ድረስ ገና ይገርፋችኋል፡፡ ድርድርም በሉት የኢኮኖሚ ማእቀብና ሌላ ሌላም ማስፈራሪያና ሰበብ እንደዚሁም ማንም ሀይል በምንም መንገድ እነዚህን መሬቶች ከአማራው ይዞታነት ወደ ትግራይ ሊያስመልሳችሁ ፈጽሞ አይችልም፡፡የዘለአለም ቅዠት ሆኖባችሁ ይቀራል፡፡
ስለወያኔ ምቀኝነት፦

እዚህ ላይ ማለት የሚቻለው አጭር ነገርን ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ምቀኝነት እንደቅዠት በሀሳብ ሳይሆን በተግባር ይገለጣልና፡፡ ወያኔ የወልቃይትና የራያ ለም የአማራ መሬቶች ተቀባይነት ከሌላቸው ትርኪ ምርኪ የተደረቱ ትረካወቹና ልብወለዶቹ ሌላ የትግራይ ናቸው ብሎ ለመከራከሪያነት የሚጠቅሰው የቦታወቹን ስሞችን ነው፡፤ ምሳሌ፦አማራ ማይጸብሪን ማይጠብሪ ብሎ ሰየመ፣ ጸገደን ጠገደ ብሎ ስሙን ቀየረ፣ ጸለምትን ጠለምት ብሎ ታሪካዊ የትግርኛ ስሙን ቀይሯል ነው የሚሉት፡፡ እነርሱስ የእነዚህን ቦታወች የአማርኛ ስማቸውን ወደትግርኛ ቀይረዉት ከሆነስ??

በኦሮሙማ የተረኝነት ሴራና የፖለቲካ ቁማር አማካይነት ስሌቱ ለጊዜው ተሳክቶና ወያኔወች በለስ ቀንቷቸው በአማራው ላይ ወደርየለሽ ጥቃትና ወረራ እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ በወረሯቸው አያሌ የአማራ ቦታወች ላይ ሰው ጫካ ገብቶ ሲያጡት ከብቱን ‘ፍጇቸው! የአማራ ከብቶች ናቸው’ እያሉ በመርዝና በጥይት የሚገድሉት ወያኔወች ከዚህ እንሰሳዊ ድርጊታቸው ውጭም በአማራ ላይ ወደርየለሽ ምቀኝነታቸውን የሚያሳይ ሌላ ጉደኛ ማሳያም አለ፡፡

እነርሱ እንደሚሉት ከሆነ አማራ በደሙ ዋዥቶና በቁጥጥሩ ውስጥ አድርጎ አሁን የሚያስተዳድራቸውን ወያኔ የኔ ናቸው የሚላቸውን ቦታወች ስም ማለትም የወልቃይት፣ ራያ፣ ሁማራ፣ ዳንሻ፣ ኮረም፣ አለማጣ፣ ቆቦ ወዘተ ቦታወችን ስም አማራው ከየትኛው የትግርኛ ስም ወደአማርኛ ቀየራቸው?? ምናልባትም እነዚህ ቦታወች የትግርኛ ስማቸው ይህ ይሆን ነበርን?? ወልቃይት – ወልቃይትጺ፣ ሁመራ – ሁመራጺ፣ ዳንሻ – ዳንሻጺ፣ ኮረም ኮረምጺ፣ አለማጣ – አለማጣጺ፣ ቆቦ ቆቦጺ ወዘተ ወይንም እናንተው አስተካክላችሁ ጨምሩበት፡፡ ታሪክም ሆነ የየቦታዎቹ ኗሪዎች(አማራውም ትግራዋዩም) እነዚህን ቦታወች የሚያውቋቸውና የሚጠሯቸው በየትኛው ስማቸው እንደሆነ ማንም ሳይሆን በቦታው ለሽህ አመታት የኖረው ህዝብ ቋሚ ምስክር ነው፡፡አይ ቅሌት!!! ሌላውን ሁሉ ተውት፡፡ እነዚህ ቦታወች በአማራ ስር ሲተዳደሩ የነበሩ ለመሆናቸው የዱሮው የትግራይ ገዥ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ”እኔ ልጅ ሆኜ ሳድግም ሆነ በኋላ ትግራይን ሳስተዳድር ወልቃይት በትግራይ ስር አልነበረም’’ሲሉ እኤአ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓም በነጻ ህሊናቸው ለአሜሪካ ድምጽ ራዴዮ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ በወያኔ ጫና ከ13 ወሮች በኋላ ማለትም ታህሳስ 5 ቀን 2018 በድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥን እንዲቀርቡ ተደርጎ ቃላቸውን እንዲያጥፉ የተገደዱ ቢሆንም ይህንኑ ሚዛን አስገብቶ ማዳማጡ ይጠቅማል፡፡ እንደገናም “የትውልድ አደራ” በሚለው ልዑሉ ራሳቸው ቀድመው በጻፉት መጽሀፋቸው ገጽ 130 ላይ ያሰፈሩትን የጽሁፍ ምስክርነት ማንበቡ በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡

ለነገሩኮ ውርደት መገለጫቸው የሆነው ወያኔዎች ራስ ዳሽን ተራራን ወደ ትግራይ ክልል አካልለው ለትግራይ ት/ቤቶች መማሪያ መጽሀፍ ላይ አሳትመውት ነበር፡፤ ጣና ሀይቅስ የእነርሱ ይሆንን?? እነርሱን ወራዳውች ማለቱ ብቻ አይገልጻቸውምና የፈለጋችሁትን ስም እናንተው ስጧቸው፡፡ በእኔ በኩል እንዳለችው እንሰሳ “ምቀኞች” ብያቸዋለሁ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop