ተዉ እነ ጅብ አስፈጂ ! –  ማላጂ

ለዓመታት የኢትዮጵያን አንድነት እና ህዝብ አደጋ ዉስጥ ሲገባ አይቶ እንዳላያ በማየት በህዝብ መስዋዕትነት የግል ጥቅም እና ስልጣን ለማስቀጠል በቅዠት የኖሩ እና እየኖሩ የሚገኙት ዛሬም ከኖሩት እና ከሚያዩት መማር አለመቻሉ ነዉ ፡፡

ለኢትዮጵያ ጠላቶች እና አጥፍቶ አጥፊዎች የምትሆን አገር ለሞቱላት እና እየሞቱላት ላሉት ዕዉነተኛ ዜጎች እናት ምድር የምትሆንበት ጊዜ ዛሬም በ፳፩ኛ ክ/ዘመን  መናፈቅ እንጂ መጠየቅ የሚቻል አልሆነም ፡፡

አሁንም በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ግዛት በሚገኙ የአገራችን ህዝቦች እና ክፍሎች የዉስጥ እና የዉጭ  የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ታሪካዊ ጠላቶች አመች ባሉት አጋጣሚ፣ ጊዜ እና ቦታ ሁሉ ሳይታክቱ እየሰሩ ነዉ ፡፡

ርግጥ ነዉ በአገር አቀፍ ደረጃም ሆነ በክልል በንቃተ ህሊና ብቃት ማነስም ሆነ በአድር ባይነት ጥገኛ አመለካከት የተጠፈሩ በየትኛዉም የህዝብ እና አገር አላፊነት ደረጃ ያሉ ሆድ አደር ጅብ አስፈጆች አንድም በአድር ባይነት ሌላም በአቅመ ቢስነት ዛሬ ላይ እየሆነ ላለዉ  ብሄራዊ ቀዉስ ( ሰባዊ እና ቁስ አካላዊ ዉድመት) ለ፳፯ ዓመታት የሚያዉቁት ግን በምንቸገርኝነት እና በማን አለብንነት ያሳለፉትን አሁንም ለማለፍ እየሞከሩ ስለመሆኑ ለሚያይ ሠባዊ ፍጡር  አሳዛኝ ነዉ ፡፡

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል ለዓመታት በማንነት ላይ  በተደራጀ እና በተጠና ሴራ የኢትዮጵያዊነት መሰረት በማናጋት እና  በማዳከም  “ዓማራ ” የሚባል ማህበረሰብ በጠላትነት የፈረጀዉን አዉራ ድርጅት( ት.ህ.ነ.ግ.ን) ሲከድም ለኖረ ከዚያ ቆፈን ለመላቀቅ የስጋ እና ነፍስ ዉጊያ ሊገጥመዉ ይችላል፡፡

ሆኖም በተለይም የሰሜን ምዕራብ ህዝብ እና ግዛት ለዘመናት የዉጭ እና የዉስጥ ቅራኔ በተነሳ ቁጥር ዳፋዉ እንደማያልፈዉ  ህዝቡና የአካባቢዉ መልካዓ ምድር ሳይቀር ምስክሮች ናቸዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል - ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ-ማርያም

ይህ በሆነበት የክልሉ መንግስት  የቀድሞዉ ብአዴን ፣ አዴፓ  …..ብልፅግና…..ህዝብ እና ምድሩ …..ሳር ቅጠሉ ሳይቀር በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች ጭምር ለዓመታት ዓማራ/ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ የሞተ፣ የተሳደደ፣ የተፈናቀለ ፣ ሀብት ፤ንብረቱን ያጣ …. መኖሩን ካለፉት የ ፴ ዓመታት የመከራ ዘመናት ያለመማር ችግር ዛሬም ይስተዋላል ፡፡

አሁንም በዚህ የህልዉና ትግል  ክተት ጥሪ ያስገኘዉን ህዝባዊ ቅቡልነት በመጠቀም በአመራር ዘገምተኝነት፣ ቸልተኝነት እና ኃላፊነት ባለመወጣት በዓማራ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ለደረሰ እና እየደረሰ ላለ  ማንነት ተኮር  አሳር የበዛበት ስቃይ ለመካስ ያለመነቃቃት ወይም ያዝ ለቀቅ የማድረግ ዝንባሌ ይታያል፡፡

ይህ  ዕብሪተኛ ፣ ወራሪ እና መዝባሪ  የትግሬ  ኃይል  ለሚያደርሰዉ  መጠነ ሠፊ ጥፋት ከስያሜ ሳይቀር ጁንታ  እያሉ  ባሉበት መርገጥ  የአካባቢዉ ህዝብ ለዓመታት እያየን በጅብ መበላት በቃን ብሏል ፡፡

ለዚህም መንቃት፣ መደራጀት ፣ ህብረት እና የጋራ ዓላማ ፅናት  ሲል መባጀቱን እና ለዚህም ጆሮ ዳባ ልበስ መባሉ ዛሬም እንደ አለፉት የመከራ ዘመናት ሞት እና ዕልቂት ለማስተናገድ አገሪቷ እና ህዝቧ ተገደዋል፡፡

በመጨረሻም  ዕዉነተኛ የህዝብ እና አገር  የዓመታት   ግፍ ለሚያሳስበዉ ሁሉ  ጅብ አስጂ  ከሆነ አስተሳሰብ እና ድርጊት በመዉጣት ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለዘመናት ከተዘጋጀላቸዉ የጥፋት ወጥመድ ለማዳን የተግባር  እና ህዝባዊ  ጀግኖችን ሠዎችን ወደፊት ከማምጣት ጀምሮ ከበድን አስተሳሰብ ያልወጡትን በድኖችን በቃ ለማለት ጊዜዉ ዛሬ መሆን አለበት ፡፡

የኢትዮጵያ እና ህዝቧ የዘመናት ጠላቶች ግብዓተ መሬት ባልሆነበት ነፃነት ማሰብ  የዘመናት ብሄራዊ የሞት እና ጥፋት ዕንክርዳድ መዝራት ስለሚሆን የተጀመረዉ የህልዉና ትግል  አስከሙሉ ነጻነት በአጭር ጊዜ ሊሆን ይገባል  ፡፡ እነ ጂብ አስፈጂ ከጂቦች የማይለዩ የጅቦች ከዳሚ ስለሆኑ በአስተሳሰብ ሆነ በተግባር ሁሉም በተለይ የኢትዮጵያ እና ዓማራ መኖር  ይመለከተኛል የሚል ሁሉ በቃ ፤ዕምቢ የሚልበት ጊዜ ዛሬ ፤አሁን ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አይጥ ሞቷን ስትሻ..............! ከታምራት ይገዙ

“  ጦርነት   የማራዘም  ሀሳብ ለጠላት ጥቅም ፤ ለአገር እና ህዝብ ደም(ባላንጣ) ከማቆየት አይለይም ፡፡ ”

ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ ፣

የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ፡፡(ዮፍታሄ ንጉሴ )

 

ማላጂ

አንድነት ኃይል ነዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share