መግቢያ
ሃሳቦች አወዛጋቢ የሚሆኑት ሰዎች ማሥተዋለ ቢሥ ሥለሆኑ ብቻ ነው ። ማሥተዋል ደደብነትን በዕውቀት ክምችት በማጥፋት የሚገኝ ጥበብ ነው ።ደደብነት ተፈጥሯዊ ነው ። ሰው ለምን ደደብ ሆነ አይባልም ። ደደብ ሆኖ ከቀረ ግን “ለምን ደደብ ሆኖ ቀረ ? “ተብሎ መጠየቅ አለበት ።አንተ ሰው ፤ ለማወቅ በተጋህ ቁጥር ደደብነት ከውሥጥህ ብን ብሎ ይጠፋል ። እናም ያን ጊዜ የኒቼም ሆነ የኦሾ ሃሳብ ለአንተ ብርቅ አይሆንብህም ።
( መሻወጊ 13/01/14 )
ለጠቅላላ ዕውቀት የሚረዳችሁን የሁለት ፈላሥፎችን ሃሳብ ለዛሬ ይዤላችሁ መጥቻለሁ ። አንዳንዴም ወጣ ባለ ሃሳብ ዓለምን መቃኘት አሥፈላጊ እና ጠቃሚ ነው ብዬ አሥባለሁ ። በፌሬድሪክ ዊልሂ
ም ኒቼ ልጀምር ።
1 . ፌሬድሪክ ወልሂልም ኒቼ
ፈሬድሪክ ኒቼ ጥቅምት 15/1894 ዓ/ም ነው የተወለደው። ኒቼ ፈላሥፋ ከመሆኑ በፊት የቋንቋዎች ተመራመሪ ና ሊቅ ነበረ ። ( philologist ) በዚህ የጠለቀ ዕውቀቱ ገና በ22 ዓመቱ በጀርመኑ የል ዩኒቨርሥቲ ያሥተምር ነበር ። በ25 ዓመቱ በጤና መታወክ ምክንያት ማሥተማሩን አቋረጠ። ወደፍልሥፍና አዘነበለ። እስከ 44 ዓመቱ በጀርመን የታወቀ ፈላሥፋ ሆነ ።ከ44 ዓመት በኋላ ሙሉ ለሙሉ ህሊናውን አጣ ። አበደ ፡፡ ነሐሴ 25/1900 ዓ/ም በ56 ዓመቱ ይኽቺን ዓለም ከመሰናበቱ በፊት ፣በፈላስፋነቱ ፤ በየሙዚቃ አቀናባሪነቱ ፤ በገጣሚ ና ፀሐፊነቱ ይታወቅ ነበር ። የሞቱም መንሥኤ ኒሞንያ ነው ፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ በሚያሰቃየው ግማሽ ጭንቅላትን ከፍሎ ክፉኛ በሚያም ከባድ ራሥ ምታት የተነሳ የአእምሮ በሽተኛ በመሆኑ ሰበብ የአልጋ ቁራኛ ነበር ፡፡ ለጭቅላት ህመምና ለአልጋ ቁራኛነት በመዳረጉ ሰበብም በተኛበት የሣንባ ምች ( pneumonia ) ለተባለ በሽታ ተዳርጎ ለመሞት በቃ ፡፡ ኒቼ በሣንባ ምች ህመም ተፈጥሯዊ ሞት ነው ፤ የሞተው እንጂ አንዳንድ ፀሐፍት እንደሚሉት ራሱን ሰቅሎ አልሞተም ።
” የኒቼ የእግዚአብሔር ሟቷል ። ” አባባል የእሱ ብቻ እንደሆነ እና ሄግል ይህንን ሃሳብ ከእርሱ በፊት ማቀንቀኑንን የሚያወሳ የለም ፡፡ በዚህ ቁንፅል አባባል የተነሳ ኒቼ ህሊናው ሊቋቋመው የማይችል አያሌ ወግዘት ደረሶበታል ። እስከዛሬም የእግዛብሔር ሟቷል ፍልሥፍናው በቁንፅል ሲተረክ ይደመጣል ።
የኒቼ እውነተኛ አባባል ግን በዝርዝር ” ሰቆቃው ዘራቱሥቱራ ” ላይ ( Thus spoke zarathustra ) የሰፈረ ነው ። እንደምታውቁት ክርስቶስ እንዲሰቀል ፣ ወንበዴው በርባን እንዲፈታ በመንጋ ያመፁት የአይሁድ ቄሶች ና ቄሳር የሚያሥተዳድረው ህዝብ በሙሉ ነበር ። እናም ይህንን የእኛን ፤የሰዎችን የክርስቶስ ኢየሱስን ገዳይነት የሚያብራራ እውነት ለመግለፅ እና ሰው የራሴ የሚለውን ጣዖት ለማምለክ እንጂ የወል የሆነ ዓምላክ ለማምለክ እንዴት እንደሚቸግረው ለማሳየት ከዚህ በታች ያለውን ዘላለማዊ ሃሳብ በመፀሐፉ ላይ አሥፍሯል ። እናም ኒቼ የከሰሰው የዛን ዘመኑን ፤ በርባን እንዲፈታ የጮኸውን ፣ ሰው መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል ። ግልፅ ና ያልተቆነፀለው የኒቼ ሃሰብ ከዚህ በታች የሰፈረው ነው ፡፡
God is dead. God remains dead. And we have killed him. How shall we comfort ourselves, the murderers of all murderers? What was holiest and mightiest of all that the world has yet owned has bled to death under our knives: who will wipe this blood off us? What water is there for us to clean ourselves? What festivals of atonement, what sacred games shall we have to invent? Is not the greatness of this deed too great for us? Must we ourselves not become gods simply to appear worthy of it?
ኒቼ በእብደቱ ሰበብ በህሊናው የታጨቀውን እውነት ለመፃፍ አልቻለም ። እስከ 1897 ዓ/ም እናቱ እስከ 1900 ዓ/ም ደግሞ እህቱ ነበር በአልጋ ቁራኝነቱ ሲከባከቡት የኖሩት ።
2 . ባግዋን ሸሪ ራጅነሽ ( ኦሾ )
ኦሾ ከፈላስፋነቱ ጋር የመጣ ሥሙ ነው ። በፍልስፍናም የማስትሬት ዲግሪ አለው ፡፡ እኛም እሥቲ ኦሾ እያልን እንዝለቅ ።
ኦሾ እንደ ጣኦት የሚታይበትን የራጅናሽ እንቅሥቃሴን ( rajneesh movement ) በህንድ አገር የመሠረተ ነው ። የተወለደው ህንድ በእንግሊዝ ቅኝ በነበረችበት ዘመን በ 1931 ሲሆን ይኽቺን ዓለም የተሰናበተው በ1990 ዓ/ም ነው ። በ58 ዓመቱ ።
ኦሾ ደግሞ በፈጣሪ መኖር የሚያምን ሲሆን በኃይማኖቶች አያምንም ነበር ። እንደውም በዚህ ዓለም የበዛ ኃይማኖት በመፈጠሩ የተነሳ ሰዎች የሚገባቸውን ህይወት ለመኖር አልቻሉም በማለት በፍልስፍናዊ አሥተምህሮው ሁሌም ይናገር ነበር ።
በዚህ ምድር ኃይማኖት ፤ዳር ደንበር እና የተሸነሸኑ አገራት አያሥፈልጉም የሚል ፍልሥፍናንን በዋናነት የሚያጠነጥነው ኦሾ ፤ በግለሰብ ገደብ አልባ ነፃነት በእጅጉ ያምናል ። ሰዎች በሥርዓት ይኖሩ ዘንድ ግን አንድ የዓለም መንግሥት በቂ ነው ባይ ነው ።
” የዚህ ዓለም የችግር እና የሰቆቃ መንስኤ የመንግሥታት መብዛት ና የእርስ በእርስ ሹክቻ ነው ። በአለም ላይ በተዝናኖት ለመኖር የማይቻለው አንዱ አንዱን ለማጥፋት ስለማይቦዝን ነው ፡፡ መንግስታት በመብዛታቸው እና ሁሉም በመግደል በማመናቸው የተነሳ በዓለም ሰላም የለም ፡፡የእያንዳንዱ አገር መንግስት የእኔነት ና የስግብግብነት ፍላጎትና የግብዝነት ሥሜት እጅግ በማየሉ ሁሉም አንጣ እንጂ እንካን አያውቅም ። ይኽንን የገዘፈ ስግብግብነትን ለማሶገድ ከተፈለገ ፣ የዓለም መንግሥታት ሁሉ መፍረስ አለባቸው ፡፡ሁሉም ፈ ፈርሰው ሁሉም በመረጡት አንድ መንግስት እንዲመሩ መደረግ አለበት ፡፡ የኽም መንግስት የተባበሩት መንግስታት የሚባል ሳይሆን ” የዓለም መንግስት ” መባል አለበት ። የዛን ጊዜ የዓለም ሀብት ሁሉ እኩል ሥለሚሰራጭ ድህነት በዓለም አይኖርም ። ችግር ና ችጋርም ይወገዳሉ ።ከሁሉም በላይ የሚገዳደሉ መንግሥታትም አይኖሩም ። እናም የጦር መሣሪያና ጦር ሠራዊትም አያሥፈልግም ። ዓለም በፀጥታ ና በህግ አሥከባሪ ፖሊሶች ብቻ መተዳደር ትችላለች ። ወዘተ ። ” ይለናል ኦሾ ። ”
አንድ ሁለት ሐሳቦቹን ልወርውርላችሁ ና ፅሑፊን ልቋጭ ። አንባቢ ሆይ የሁለቱንም አወዛጋቢ ፈላሥፎች የህይወት ታሪክ ያገኘሁት ከዊኪፒዲያ መሆኑንን እወቁልኝ ።
* በአሁኑ ወቅት ሲዖልን በቃላት መግለፅ አሥፈላጊ አይደለም ። በምትኖሩበት አካባቢ ና በምድሪቱ ላይ ዘወትር የሚደረገውን ብታሥተውሉ ሲዖልን በተግባር ታዩታላችሁ ።
* እያንዳንዱ ሰው ልዩ ነው ። ልዩነታችሁን ዘንግታችሁ አንድ አይነት ነን ካላችሁ ፤ መንጋ ትሆናላችሁ ። ግላዊነታችሁ ይወሰድባችኋል ። ራሳችሁን መሆን ያከትምለትና ማሽን ውስጥ ያለ ተመሣሣይ ጥርሥ ትሆናላችሁ ።
* ሰው ሁሉ ልዩ ነው ። ተመሣሣይ የሆነ አእምሯዊ ህሳቤ የለውም ። ተመሣሣይ የእጅ አሻራ የለውም ። ሰው በወል መጠሪያው ሰው ቢሆንም ሁሉም እኩል ና ያው አይደለም ። በአእምሮ ደረጃ ። መጥፎ ና መልካሙን አመዛዝኖ ቶሎ ውሳኔ ከመሥጠት አንፃር ። ወዘተ።ወዘተ።ልዩነት አለው ።
* እያንዳንዱ ሰው ልክ እንደ ሉአላዊ ግዛት ታይቶ መከበር አለበት ። አንዱ የአንዱ የበላይ ሆኖ በእርሱ ግላዊ ጉዳይ በሰውነቱ ያገባኛል ማለት የለበትም ። ማንም ሰው በሰውነት ደረጃ የማንም ሰው የበላይም የበታችም አይደለም ።
* ለዚህ ዓለም የሚያሥፈልገው አንድ መንግሥት ብቻ ነው ። አንድ መንግሥት ብቻ በዓለም ላይ ቢኖር እኮ ጦርነት ባልኖረ ነበር ። እናም የተመጣጠነ በጀት ሥለሚኖር ድህነት እና ርሃብን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች በዓለም ላይ አይኖሩም ነበር ።
ዓለም በአንድ መንግሥት ብትተዳደር ጦርነት የሚባል አይኖርም ። እናም ፖሊሥ እንጂ ጦር ሠራዊት አያሥፈልግም ነበር ። ኒኩለርን ጨምሮ የተለያዩ ገዳይ መሣሪያዎችም አይመረቱም ነበር ።
እናም በዓለም ላይ አንድ መንግሥት ካለ ዓለም የተረጋጋች እና በራሷ ገነት ትሆን ነበር ።
* ሰው ሲባል የራሱን ጭካኔ ለማፅደቅ የሚሯሯጥ ፍጡር ነው ። እንሥሣትን በምኑም ፣ በምኑም እያመካኘ ሲያርድ ና ሲበላ ፣ የፅድቅ ሥራ አድርጎ ይቆጥረዋል ። ድርጊቱንም ማንም ቁብ አይለውም ። አንድ ሰው ያሳደገው በሬ ወግቶ ቢገለው ወይም እንደ መኪና የምታገለግለው በቅሎ ረግጣ ብትገድለው ግን እንደ ጉድ ይወራል ። ታላቅ ዜናም ይሆናል ።