የጥፋት ኃይሎች ለግማሽ ክ/ዘመን አንዲት እና ሉዓላዊት ኢትዮጵያን ለማዳከም የመጀመሪያዉ እና ዋነኛ ተልዕኮ ኢትዮጵያዊነት እና እና ማንነት ማፈራረስ እንደነበር ከነበሩት ያለፉት ሶስት ዓመታት ሁነቶች መረዳት ይቻላል፡፡
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. የተጀመረዉ አዲስ እና ድብቅ ያደረ ሴራ ዕዉን ከሆነ በኋላ በነበረዉ የመከላከል ዘመቻ ከፍተኛ ሠባዊ እና ቁሳዊ ዋጋ ተከፍሎ ለወራትም ቢሆን አንጻራዊ ለዉጥ መንበሩ የሚታወቅ ነዉ ፡፡
ጠላት ለ ስምንት ወራት ጠፍቷል ፤ የዶግ አመድ ሆኗል ሲሉን እንደብረት ጠንክሮ፤ እንደ አሸዋ በዝቶ በነበረዉ እና በተሰጠዉ አጋጣሚ እና የዕፎይታ ጊዜ ለዳግም መደራጀት እና ወረራ ዕድል ተጠቅሞበታል፡፡
በመጀመሪያዉ ወረራ ከአካባቢዉ አልፎ ጎንደርን እና ወሎን በመዉረር በዕብሪት ለግዛት መስፋፋት ባደረገዉ ወረራ ከፍተኛ ዕልቂት ሲፈፅም በህዝብ እና ቁርጠኛ ህዝባዊ ልጆች ባደረጉት ተጋድሎ እነዚህ አካባቢዎች ነጻ ወጥተዋል፤ ዕፎይታ አግኝተዉ ነበር ፡፡
ሆኖም በክብር እና አጀብ የተሸኘዉ አጥፊዉ የትህነግ ስብስብ ከስምንት ወራት ዕረፍት እና ዕፎይታ በኋላ ከቀድሞዉ በባሰ ሁኔታ በሠዉ ኃይል፣ በመሳሪያ፣ ትጥቅ እና ስንቅ ተደራጅቶ በጥናት እና በድብቅ ሴራ ስለመሆኑ በጥፋት እና መስፋፋት መንፈስ በተለያየ አቅጣጫ ፣ ስልት፣ እና ዉስብስብ ሴራ መሆኑ የወራት ዝግጅት መደረጉን አሁን ላይ ያለዉ ሁኔታ አመላካች ነዉ፡፡
የ፪ኛዉ የጥቅምት ወር ተከታይ ወረራ “አጥፊ እና ተስፋፊ” ጠላት እያደረገ ያለዉ እና ያደረገዉ በራሱ ቁመና ሳይሆን ከዉስጥ እና ዉጭ የጥፋት ተልዕኮ ተባባሪ እና አስተባባሪዎች አማካኝነት ከትናንት አስከዛሬ ሽፋን በማግኘት መሆኑን በመገንዘብ ዛሬ እንደትናንቱ በመሰል ማዘናጊያ መዛግ እና መዘናጋት የለብንም ፡፡
ይህ ከዚህ ቀደም እንደነበረዉ ከአካባቢ እና ምሽግ ከሆነዉ የትግራይ ክልል መግፋት እና ወደነበረበት ቦታ መሸኘት ዳግም ለጠላት ከለላ እና የዕድሜ ቀጥል መላ እንደመስጠት ይሆናል ፡፡
በኢትዮጵያ እና በተለይም ለዓማራ ህዝብ በአስተማማኝነት የመቀጠል አለመቀጠል የሚወሰነዉ ከዚህ በፊት ከነበረዉ አደገኛ ስህተት ከመጣበት(ወሻ፣በረሃ…….) መመለስ የሚለዉ የመለሳለስ ቅስቀሳ ፣ስብከት / ፕሮፖጋንዳ ለማያባራ የተራዘመ መከራ ዳግም እንዳይዳርግ ህዝብ እና መንግስት በተለይም የዓማራ ህዝብ እና መንግስት በጥሞና ሊገነዘበዉ ይገባል፡፡
ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን የሆን ሁሉ ብናምንም ባናምንም የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን አካባቢ ፀጥታ እና ደህንነት እንዲከበር እና እንዲኖር(እንዲቀጥል) ማድረግ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ብሎም የቀጠናዉን ዙሪያ የሠላም እና መረጋጋት ዋስትና ማረጋገጥ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
እናም የዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም እንዲሉ አበዉ አሁን ላይ የሚደረገዉ የመኖር ፤አለመኖር የብሄራዊ ህልዉና ተጋድሎ በመመከት፣በመኘት ፣በመሸሸት፣ በአድር ባይነት የሚታለፍ እንዳይሆን እና ይህም አገሪቷን እና ህዝቧን በተዳፈነ ዕሳት ላይ እንደማስቀመጥ እና እንደማዘናጋት ይሆናል፡፡
ስለዚህም ተስፋፊ እና አጥፊ ዕብሪተኛ ጠላትን ከዚህ በፊት በማወቅ ሆነ ካለማወቅ ከተሰጠዉ የዕንግድነት እና የማንሰራራት ጊዜ (8 ወራት) እና ዕድል ዉጭ ዳግም በመጣበት መመለስ እና ከቤቱ(ዋሻ፣ በረኃ፣ ከተማ፣ገጠር…..) መሸኘት /ማድረስ ኃላፊነት የጎደለዉ የእሳት ላይ ጨዋታ ፤የትዉልድ የሞት ዕዳ እንደማስተላለፍ ስለሚቆጠር እና ጠላት ወዳጅ ላይሆን ፤ካለፈዉ ላይማር መዘናጋት አያስፈልግም ፡፡
ይህን ትዉልድ በስንፍናዉ ባቆሰለዉ ዕንቅፋት ለመጨዉ ትዉልድ ደም ማቆየት እና አገሪቷን እና ህዝቧን ለመታደግ ብርህን እና ጭለማ አንድ ሊሆኑ ስለማይችሉ ብርሃን ከፈለግን ጭለማዉን ማስወገድ እንጅ ማገድ ዘላቂ እና አስተማማኝ አማራጭ ላለመሆኑ ከዓመታት በተለይም ከስምንት ወራት የዝገት ፣ መዘናጋት እና ማንቀላፋት ታሪካችን ልንማር እና “ያቆሰለን ሳይጠፋ አናቀላፋ” መንቃት እና በህብረት መቆም ይገባል፡፡
ምንጊዜም የምንዘጋጀዉ በሠላም ጊዜ ሲሆን በሠላም ጦርነት፤ በፍቅር ጠብ መኖሩን ባለመርሳት ለራስ እና አገር ህልዉና አስተማማኝ ዝግጅት ለማድረግ ዕድል ይሰጣል፡፡
በሠላም ጊዜ የሚደረግ ሠላም የማስጠበቅ ዝግጅት ወዳጅ ጠላት እንዳይሆን መጠበቅ ነዉ ፡፡
ይህንም በቅርብ ምሳሌ ለማስተገጥ ፡ ሡዳን ወዳጅ (ጎረቤት) ነበረች ዛሬ የእኛን መዘናጋት እና የዉስጥ ብቃት ባዶነት ገበና ተከትላ የኢትዮጵያን ግዛት ወርራ፤ መሰረተ ልማት አስከመገንባት ደርሳለች፡፡ ይህም በእኛ ቸልተኝነት በሱዳን ዕብሪት እና የወዳጅ ጠላትነት ነገ የሚጠይቀዉ ዋጋ ስንት እንደሆነ መገመት ካልሆነ ማወቅ አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያዊ በርስቱ በግዛቱ የበይ ተመልካች፣ ሎሌ፣ ወዛደር…..ሆኖ እንደማይቀጥል የሚያጠያይቅ አይሆንም እና ነዉ ፡፡
ለማማንኛዉም ዞትር የወዳጅ ጠላትም ሆነ መደበኛ ጠላት የሚጠቀምናቸዉን መዘናጊያዎች እና ማደንዘዣዎች አስቀድሞ መገመት እና መረዳት የሰዉነት ልክ ነዉ እና የቆዩ እና ነባር የህይወት ዘመን የአገራችንን ብሂል ማወቅ ይበጀናል ፡-
“ጅብ አስኪይዝ ያነክስ ”፣ “ያቆሰልከዉን አዉሬ አትመን ” ፣ የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን የረሳ ዕለት ነዉ ” እነኝህ የአገራችን ብሂሎች ከታሪክ እና ከዕዉነታ የመማር እና ያለመማር የሚኖረዉን ፋይዳ ወይም የሚያስከትለዉን ዕዳ /ፍዳ ምን እንደሚሆን ማሳያ ነዉ ፡፡
እናም ወገን ሆይ ተኩሶ ያቆሰለህ ለሞትህ እና ጥፋትህ ሲተጋ ቁስልህን ይዘህ መብከንከን እና ማንቀላፋት ይቅር ፡፡ ወርዉሮ የሳተህን ወዳጂ ማድረግ በሬ ካራጁን እንዳትሆን “ከቃጣኝ የመታኝ ብለህ” ዳግ ሞትን በትብር እና ህብር አስከመጨረሳ ማክሸም እንጅ ሌላ ምርጫ እና መዉጫ የለም፤ አይኖርም ፡፡
ማላጂ
አንድነት ኃይል ነዉ !