ባዶ ድምር እያስከተለ ያለዉ መዘዝ(ባድ -መዘዝ) ! – ማላጂ

shimeles
shimeles

የአዞ ዕንባ ከሚያነቡት አደናጋሪዎች  በየጊዜዉ ከሚሰነዘሩ የማዘናጊያ ቃላት ጋጋታ ከአለፈዉ አለመማር ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል የባዶነት ድምር ማሳያ መሆኑን በመረዳት ካአለፉት ስህተተቶች የምንማርበት ጊዜ አሁን ነዉ ፡፡

ለዘመናት የኢትዮጵያን አንድነት እና የህዝቧን ከብረት የጠነከረ ህብረ ብሄራዊ ህብረት  እንዲዝል በማድረግ ሲሰሩ እና ሲተባበሩ ከነበሩት ካለፈ ድርጊት መማር ካልተፈለገ መስዋዕትነት ራስን፣ ህዝብን እና አገርን መታደግ የሚያስችል ነዉ ፡፡

በተደጋጋሚ በህዝብ እና አገር ላይ ከተደጋጋሚ ጥቃት እና ሞት ለዓመታት ሲዳርጉ የነበሩት ከሀዲዎች እና አጥፍቶ ጠፊዎች ለፈፀሙት ግፍ  ተጠያቂ አለመሆን የግፍ ግፍ ሁለንተናዊ ጥቃት በአዲስ እና በስፋት ተያይዞታል ፡፡

ለአንድ ክ/ዘመን የአገሪቷን ታሪካዊ ፣ቅርስ እና ዉርስ እንዳልነበር ለማድረግ ሲደረግ የነበረዉን የዉስጥ እና የዉጭ ሴራ በግልፅ እና በማያዳግም ሁኔታ ለማስወግድ አለመፈለግ የባዶ ድምር መዘዝ ሰለባ ከመሆን ልንማር ይገባል ፡፡

ኢትዮጵያን ለማክሰም በኢትዮጵያዊነት ምሰሶዎች ማለትም ኢትዮጵያዊነት ፣ ዓማራነት ፣ ኃይማኖት እና ሌሎች ማንነት ላይ ለደረሰዉ ዘር ፍጅት ፣ ስደት ፣ ሰቆቃ፣ ማሳደድ እና የመሳሰሉት ኢሰባዊ  ወንጀሎች አዲስ እና  ድንገተኛ ዕንደ ደራሽ ዉኃ አለመሆኑን ከቀደመ ታሪክ እና ችግር መነሳት እና ህብረት መፍጠር አሁን ምርጫ የሌለዉ ብቸኛ አማራጭ መሆኑን መረዳት አለብን  ፡፡

ይህ የማይታመነዉን ለማመን መፈለግ ከአለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ  ክፍሎች  የዘር ፍጅት ተካሂዷል እየተካሄደ ነዉ ፡፡

ለአብነት በቅርብ አመታት በኢትዮጵያ የሆነዉ ሁሉ የሆነዉ ሁሉ የተካሄደዉ ጥፋት ፣ዕልቂት እና ሞት ነግሷል፣ የዘር ፍጅት ከዓመታት ከመከናወኑ በላይ  ጥንታዊ እና ትላልቅ ከተሞች ( ዝዋይ፣ ሻሸመኔ፣ ሰሜን ሸዋ…..) እንዳልነበሩ ሲወድሙ  የነበረዉ እና ያለዉ  ህግ ፣ መንግስት እና መዋቅር  ነበር ፤አለ ነገር ግን ከማይጠበቅ መጠበቅን ማቆም ይኖርብናል   ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የተከሰተዉ ብሄራዊ አደጋ  በይዘት ካልሆነ በቀር በዓይነቱ  በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል….ክልል ለዓመታት የሆነዉን ፍጅት እና ጥፋት አሁንም ስለመኖሩ እና ሊገታ አለመቻሉ የአቅም ጉዳይ ሳይሆን በፖለቲካ ሴራ ስለመሆኑ ለሚያይ ምን ያህል የንቃተ ህሊና ችግር እንዳለ  የሚያሳይ ነዉ ፡፡

ስለዚህ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያን ለማዳከም ጠላት ለአንድ ክ/ዘመን  አቅዶ እና አልሞ በግንባር ቀደም ጠላትነት እና ይገዳደረኛል ለሚለዉ ኢትዮጵያዊ በተለይም ዓማራን ለማጥፋት የተደረገዉን እና እየተደረገ ያለዉን ሴራ በአንድነት እና በህብረት መቆም ያስፈልጋል ፡፡

ራስን እና አገርን ለመከላከል በዕዉቀት እና በአስተዉሎት በመደማመጥ እና በዓላማ መደራጀት ያስፈልጋል ፡፡

ከዚህ ዉጭ በባዶ ድምር እና ከማይታመን ከንቱ ህልም መዘናጋት መቆም አለበት ፡፡  ለዓመታት የሆነዉን የጠላት መጠነ ሰፊ ጥፋት መርሳት እና አለማዉሳት  የድክመት ድክመት ነዉ ፡፡

አበዉ ያቀሰልከዉን አዉሬ አትመነዉ  እንዲሉ  እኛም ያቆሰለንን መርሳት ወይም መዘናጋት የሚያዋጣ ስለማይሆን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ  ህዝብ በተለይም የዓመታት የግፍ ፤ግፍ ሲያስተናግድ እና እያስተናገደ የሚገኘዉ የዓማራዉ ህዝብ በልማት፣ በብቃት እና በዓላማ ቁርጠኝነት በበቁ አመራሮች የመደራጀት እና ጠላትን አስከመጨረሻ ለማጥፋት ለራስ ዘብ መቆም ያስፈልጋል ፡፡ ይህ ባልሆነበት ዞትር ስለጠላት ማዉራት የቆየዉን ወርቃማ  የአገራችንን አበባል  “ ሞኝን እባብ ሁለት ጊዜ በላዉ አንዴ ሳያይ ሁለተኛ ሲያሳይ  “ በማስታወስ  የቆምንበት ቦታም ሆነ የምንገኝበት ጊዜ የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን አሁንም ዳግም ለእኛ እኛ ዘብ እንቁም ፡፡

 

 “አንድነት ኃይል ነዉ  ”

 

ማላጂ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.