August 10, 2021
4 mins read

ለመንግስት (በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ደረጃ)፣ ለባህል ሚንስቴር፣ . .. ለሚመለከተው ሁሉ! – ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

ሻለቃ ደራርቱና ዶ/ር አሸብር ወደ ቶኪዮ የወሰዷት ኢትዮጵያ! የትኛዋ ሀገርን ታክላለች፤ እኛን ትመስላለች?(በድሉ ዋቅጅራ)
ግላዊ ምስል . . .
ደራርቱን ስለሀገር ፍቅሯ አላማትም፡፡ ገና ሳውቃት . . . . ባርሴሎና ላይ አረንጓዴና ቀይ ለብሳ ስትሮጥ ጀምሮ. . . እግሯ ላይ፣ ፊቷ ላይ የተግተረተሩ ስሮቿ ላይ፣ የሀገሯ ብሄራዊ መዝሙር ሲዘመር ያጠለቀችው ወርቅ ላይ እንባ እያዘነቡ ከሰንደቋ ጋር ሽቅብ የተሰቀሉ አይኗቿ ላይ አይቸዋለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሀገር ምልክት ትመስለኛለች፡፡

.

234774249 1741875436019417 412792612501150391 n

በአንጻሩ ዶ/ር አሸብርን ያወቅኩት የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኖ ነው፡፡ ያ ዘመን እግር ኳሳችን በችግር የታመሰበት፣ ፌዴሬሽኑ በቡድን ተከፋፍሎ የተሸበረበት ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰውዬው በሄደበት ስሙን እየመሰለ፣ ይኸው ኦሎምፒ ላይ ደረሰ፡፡ እና እሷ ሀገርን እሱ ስሙን ይመስሉኛል፡፡
.
ለሚመለከተው ሁሉ!
የኦሎምፒክ ጉዳይ የሀገር ጉዳይ ነው፡፡ ይህን የሚያውቅ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ በጥቂት የስፖር አይነቶች የሚወዳደሩ ጥቂት ስፖርተኞችን ይዞ፣ (ያውም በሶስት ጊዜ ተካፋፍለው እየሄዱ) 5 የኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራሮች፣ 10 የኦሎምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚዎች (3ቱ የታገዱ)፣ 7 የመንግስት አመራሮች፣ በከፍተኛ ውሎ አበል ይዞ አይጓዝም፡፡ እነዚህ ሰዎች ከመክፈቻው በፊት ቶኪዮ እንደመግባታቸው፣ በመክፈቻው ላይ ሀገራቸውን ወክለው ቢሆን፣ ትልቅ ውለታና ክብር ነበር፡፡ ግን አላደረጉም ለእነሱ ኦሎምፒክ ገበያ እንጂ ሀገር አልሆነም፡፡
.
አትሌት ገዛኸን አበራን የተናገረውን በቴሌቪዥን ተመልክቻለሁ፤ ሰንደቅ ይዞ የተሰለፈውን የውሀ ዋና ተወዳዳሪ በስልክ አነጋግሬያለሁ፡፡ የውሀ ዋና ተወዳዳሪውና በስፍራው የነበረች የኦሎምፒክ ኮሚቴው “የሂሳብ ሰራተኛ” ባንዲራውን ይዘው ገብተዋል፡፡
.
በኦሎምፒክ ኮሚቴውና በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መካከል የነበረው አለመግባባት የተቋጨው ቶኪዮ ሜዳ ላይ ቢሆንም፣ የሰነበተ ነው፡፡ …. ግለሰቦች በሀገር ስም በሚያገኙት ስልጣን የግል ፍላጎታቸውን ማርካት በፖለቲካችንና በመንግስት ሹመኞች ያማረረን ሳያንስ፣ ያለንን አዎንታዊ የሀገር መልክ ሲመርዘው ዝም ብለን መመልከት የለብንም፡፡
.
የባህል ሚንስቴር፣ መንግስት (በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ደረጃ)፣ . . . ሌሎችን የሚመለከታቸው አካላት ጉዳዩን መርምረው የእርምት እርምጃ መውሰድና ውሳኔውን ለህዝብ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ በዚህ ኦሎምፒክ በተነሳው ውዝግብ መመረጥ ሲገባቸው ያልተመረጡ፣ ተመርጠው ያልተወዳደሩ አትሌቶቻችን፣ በሚቀጥለው ኦሎምፒክ እንደ ‹‹የባህሬኗ›› ቃልኪዳን በሌላ ሰንደቅ አላማ ስር እንደምናያቸው መጠራጠር የለብንም፡፡ . . . ይህ እንዳይሆን እርምጃ መወሰድ ያለበት ዛሬ ነው!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop