ክልል በሕገመንግስታዊ ድሞክራሲ ካልጠፋ በዘረኝነት መንገስት ለሰላም የለም ተስፋ

ለኢትዮጵያችን ብልፅግናና ሰላም ሕገመንግስታዊ ድሞክራሲ ይተግበር፣

የዘረኝነት አባት  ክሊል ይዉደም፣ ስልንም ይገርሰስ።                

ክልል የመለስ  አገር አፍራሸ መርገት ፤ የችግሮቹ ሰንኮፍና በዲሞክራሲመፍትሔዎች

በአካባቢዬ  ካላት አንድ ካህን ጋር ስለ ክልል ስንወያይ እንዲህ አሉ ፡፡  ክልል ማለት መጋረጃ  ሽፋን  ላለመታየት  መከለል ማለት ነው  ሲሉ የማውቀውን ነገሩኝ፡፡ እንዲሁም አንድ ሌላ ሰው ሲናገሩ ክልል ማለት ድንበር፣  ወይም ወስን መካለል ማለት ነው   ከዚህ አትለፍበኝ  አልደርስብህም  በመባባል  ተለያይቶ  ለመኖር  የሚያስችል ውሳኔ ነው ሲሉ ደመደሙልኝ፡፡`

ይህን ከመሳሰሉት በመነሳት ፣ ክልል ማለት አንዱ ከሌላው ተለያይቶ መኖር ያለበት፣ መገናኘትም የሌለበት ማለት ሲሆን ፤ በሌላው ዳግም አንዱ የሌላውን ድንበር ማለፍ የሌለበት ነው፡፡ ያለበለዚያ ግን ፀበኝነት  መጠላላት  መወነጃጀል  ከባሰም በጦርነት መጠፋፋት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በማያከራክር መልኩ ለተማረና ለአወቀው በትክክል የቅኝ ግዛት ስርአት ነው ፡፡ (characteristics of colonial system google አድርጎ ማየት ነው) ፡፡ ይህ ለያይተህ አዳንቁረህ ግዛው የሚለው የቀኝ ግዛት ገፀባህሪ በኢትዮጵያ ላይ በትክክል መተግበሩ ግልፅ ነው ፡፡

የአገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ እንደተባው ይህ የቅኝ ግዛት እና የመጣው የክልል በሽታ በኢትዮጵያ ላይ የተጣለው ኢትዮጵያ ከአብራኳ በተፈጠሩት፣ የጠቡትን ጡት ነካሽ እና የበሉበትን ገል ሰባሪዎች በመሆን አዙረውም ማየት ያልቻሉ ጥቂቶች ልጆቿ መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡  ክልል የህዝብ ችግሮች ሰንኮ፣ ማለት የጥፋቶች መሰረት ስለሆነ ይደምሰስ ፣ ይጥፋ ፣ ይህ ብቻ ቢሆን ነው ከክልል ጋር የመጡት ሀገራዊ ጣጣና ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት፡፡ ክልል ተደምስሶ በምትኩ ዲሞክራሲያዊ ህገመንግስትና ስርአቶች በአገራዊ ፣ በየክፍለሀገራት ፣ በአውራጃዎችና በወረዳዎች ተመስርተው ህዝባዊ አስተዳደር፣ ሰላም አንድነትና እድገት ሊኖር የሚችለው ፡፡ ስለዚ የሚከተሉት አገር አቀፍ ችግሮች ከክልል ጋር ይደምሰሱ ፡፡ መደምሰስም ካለባቸው አስር የክልል ምክንያት ከተፈጠሩት ችግሮች ዋና ዋና የሆኑትን እንገንዘብ ፡፡

ችግሮች                              ምክንያት                                                      መፍትሄ

 

    ዘረኝነት                               በክልል                                            ዲሞክራሲ፣  ከ ሀ አገር ስከ ወረዳ

    መገዳ  ል                             ››                                                                            ››

    ጥላቻ                                        ››                                                                            ››

    መከፋፈል                                   ››                                                                            ››

    ስደት                                         ››                                                                            ››

    ሽብር                                         ››                                                                            ››

    ዝርፍያ                                      ››                                                                           ››

    መፈናቀል                                  ››                                                                            ››

    ስራ እጦት                                  ››                                                                            ››

    አገር መቆራረስ                           ››                                                                            ››

    

    ሌሎችም ሌሎችም                ››                                                                           ››

እንግዲህ   የክልል  ድቀት ፣ መዘዝና ሰቆቃ እነዚህና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ስለዚሂም ኢትዮጵያ ዛሬ ባለችበት የተወሳሰበ፣ በተለይም ባለው የፖለቲካ ያለመረጋጋት፣ ብሔርተኝነትና ዘረኝነት፣ ጥላቻና እልቂት እራስን በራስ ማስተዳደር የሚቻል መስሎ ፈጽሞ የማይታየን ብዙ ልንሆን እንችላለን፡፡ በመለስና ግብረአበሮቹ፣ ዘረኝነትን መሠረት በማድረግ፣ የተዘጋጀው ሕገ መንግሥት ተብዬው ኢትዮጵያን በክልል ለመበታተን ታቅዶ በሥራ ላይ የዋለ ነው፡፡ እነሆ ውጤቱም እየታየ ነው፡፡ ክልል ኢትዮጵያን ለመበታተን የተዘጋጀ መርዝ ነው፡፡ ዛሬ ሁሉም በብዛት ይጠይቃል፤ ምነው ምንነካን፣ ምነው ሰላም አጣን  እየተባለ ሕዝብ ከያለበት ይጠይቃል፡፡ በሐቅ ትክክለኛውን መልስ የሚሰጥ ግን እምብዛም አይታይም፡፡

ኢትዮጵያን የመረዘውና ሰላምን እያጠፋ አገሪቱን የባሰ በክልል ስም ለማፈራረስ የታቀደው ኣላማ በመተግበር ላይ ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለማዳን ምን ይደረግ፣ እንዴትስ ይደረግ የሚለው ጥያቄ መጠየቅና መመለስም የግድ ነው፡፡ በአጭሩ ለችግሮች ሁሉ ምክንያቱ ክልል ከሆነ መፍትሄው ክልልን አስወግዶ በምትኩ ዲሞክራሲ የሚተገበርበትን የፖለቲካ መዋቅር መዘርጋት። ይሀም የሕዝባዊ አስተዳደር ማለትም እራስን በራስ ማስተዳደርን በሥራ ላይ ማዋል የግዜው አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚሂም ይኸ ብቻ ሲሆን  በትክክል ዲሞክራሲ በሥራ ተተርጉሞ በገሀድ የሚታይ ይሆናል፡፡

ለኢትዮጵያ ሰላም ፤ ብልፅግናና እድገት በአስቸኳይ የሚያስፈልጉት የ‹ዲሞክራሲ ተግባራት ናቸው፡፡ ይኸም የሚሆነው በአብዛኛው በአዲስ አበባ ከዚያም በየክልሎቹ የተከመሩትን ስልጣኖች ለሕዝብ እንዲሆኑ በአስቸኳይ ማወራረድ፣ ማለትም የሕዝብን ስልጣን ማክበር ነው፡፡ ቀድሞ በፊውዳል ባህላዊ ሥርዓት፣ ከዚያም በደርግና ዛሬም በኢሐድግ ስልጣንን በመሀል አገር እያከማቹ ለሚፈልጉት ሹመት ለክፍለ አገሮች፣ ለአውራጃዎች ከዚያም ለወረዳዎችና ለም/ወረዳዎች እያደላደሉ፤ ሕዝብን በቤቱና በወንዙ የመበትና የንጻነት ደሃ ሲያደረጉት ኖረዋል፡፡ እንዲያውም በባሰ መልኩ፣ ክልል የተባለ ፀረ ሰላምና የዘረኝነት ሥርአት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላምና መብት እየነፈገ አንድነቷንም እያሰጋ ነው፡፡

ፍትሔዉ፣ ክልልን አስወግዶ ሕዝባዊ ስልጣን ከመሃል አገር እስከ ወረዳዎች በሕገመንግስት ማዋቀር።

የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነቷን ለማስጠበቅ በመሃልአገር እስከየኪፍለአገሮች፣ ከዚያም እስከ አውራጃዎችና ወረዳዎች ሕዝብ እራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር መብቱ በሕገመንግስቱ ተደንግጎ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ በነመለስ ግዜ ግንባታ ሲባል፣ ዛሬ ደግሞ ሽግግር እየተባለ ከመሰብሰብ፣ ከመናገርና ከመጻፍ አልፎ ገና ሕዝባዊ ተግባራዊነቱ  በአስተዳደር መልኩ አልታየም፡፡  በኢትዮጵያ ዲሞክራሲን የማያወድሳት እንጂ በአግባቡ ተሚተገብሯት አልታዩም፡፡ “ዲሞከራሲ ግንባታ” እየተባለ ሃያ ሰባት (27) ዓመታት ሲወደስ ነበር፡፡ ግንባታዉ ግን ስልጣን አጥብቆ ለመያዝ እንጂ ለሕዝብ ሰላምና አንድነት ብሎም ብልፅግና አላመጣም፡፡

የለሕዝብ ሰላምና አንድነት ብሎም ብልፅግና ሊመጣም ሆነ ሊሆን የሚችለው ስልጥን ለሕዝብ ሲሆን ነው። በአብዛኛው የተባበሩት መንግስታት ምክር እንደሚያበስረው፤ ስልጣን ለሕዝብ ወይም “Powe Decentralization” የስልጣን ግርሰሳ ሊባል በሚችለው ወይም ስልጣን ለሕዝብ ሲሆን ነው፡፡ ይኸም ሲባል ስልጣን በተዋረድ ከመሃል አገር ተገርስሶ እስከታች ላለው ሕዝብ ዲሞክራሲ ይተገበራል ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ዲሞክራሲ መተግበር ሲባል ምን ማለት እንደሆነ መጥቀሱ አግባብ ነው፡፡

ዲሞክራሲ የሚተገበረው በአጭሩ ክልል ተወግዳ ሕዝባዊ ስልጣን ከመሃልገር እስከ ክፍለአገር  ከዚአም አዉራጃዎችና  ወረዳዎች ድረስ ለሕዝባዊ አስተዳደር ሥርዓት መመስረት የግዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ ይኸም ሕዝባዊ ሕገ መንግሥት ማዘጋጀትን  ይጠይቃል፡፡ ሕዝባዊ ሕገ መንግስጥ ሲባል ምን ማለት ነው ይኸም እንደሚከተለው መመለስ ያለበት ይመስለኛል፡፡

በመሰረቱ ዝባዊ ሕገ መንግሥት ሲባል  ከሥርአቱ አወቃቀር እና ከሕዝቡ ተሳትፎ አንፃር የሚታይ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ስርአት አወቃቀር ሲባል፣ የፖለቲካም አወቃቀር ሊባል ይችላል፡፡ በመሰረቱ ግን የመንግስታዊ ስራ ወይም ኃላፊነትን የሚያሳይ አወቃቀር ወይም የመንግሥት የሥራ ክፍልፍል ማለት ነው፡  ይኸም በአንድ በኩል ሐገራዊ ወይም መእከላዊ መንግስት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ክፍለ ሀገሮች፣ አውራጃዎችና የወረዳዎች ሕገ መንግስታዊ የስልጣን አወቃቀር ወይም ድርድር ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ዲሞክራቲክ ፈደራሊዝም እንደሚባለው ሁሉ (Beyond the basic rights of freedom of speech, press and assembly, Democracy is everyone’s political and human rights and duty) ዲሞክራሲ የየአንዳንዱ ሰው የፖለቲካና የማነነት መብትና ግደታም ነው።  Whereas Federalism is constitutional power sharing agreement between national or central government on one hand and states (or regionals) plus local governments on the other in the delivery of services to the people.)  

ይሕም ሲባል ሕገመንግስታዊ (Constitutional) የስልጣን አወቃቀር ዋልታዊ (Vertical) እና ማገር (Horizontal) የተባሉ ገጽታዎች (Features) ይኖሯቸዋል፡፡ ለዋልታዊው አወቃቀር ከማዕከል (ሐገራዊ) መንግስት ጀምሮ እስከ ታችኛው ቀበሌዎች አስተዳደር በአንድ ዓይነት ይዋቀራሉ፤ በተቋም ገፅታቸውም . ሕግ አውጪ (Legislative) 2. ሕግ አስፈጻሚ (Executive) እና 3. የፍትሕ (Judiciary) የሚባሉ ገፅታዎች አሏቸው፡፡

ከሶስቱ ዋልታዊ (Vertical) የአስተዳደር አወቃቀር በተለየ መልኩና አወቃቀሩ በበለጠ ትኩረት መታወክ ያለበት ማገራዊ (Horizontale) የአድተዳደር አወቃቀርቸው ነው፡፡ ከሶስት ቋዋሚና መሰረታዊ በሆኑት ዋልታዊ እና እርከናዊ (ማገራዊ) አወቃቀር እንደሀገሩ ፖለቲካ ሁኔታና በተመሰረተ የእርከኖች (የማገሮች) የተለያዩ ይሆናሉ፡፡ የለሎችን ማገራዊ አወቃቀር ወይም እርከኖች  ብናይ ለምሳሌም፣

 )  የአሜሪካ አስተዳደር ሶስት እርከኖች አሉት 

  1.   ማእከላዊ (Central)    2. ስቴቶች (States) እና
  2.  ወረዳዎች (Localities) እና መዘጋጃ ቤቶች (Municipalities) ናቸው፣

)  የፈረንሳይም አስተዳደር አራ እርከኖች አሉት 

  1.   ማእከላዊ (Central)      2. ኪፍለ አገሮችህ (Regionals) 3. ወረዳዎች (Departmental)
  2.    አካባቢዎች (Communities) እና መዘጋጃ ቤቶች (Municipalities) ናቸው፣

 ሐ)  ከዚህ አኳያ ሲታይ ፣ እንደሚትወቀው የኢትዮጲያ አስተዳደር ግን ሰባት እርከኖች አሉት፤

  1.  ማእከላዊ (አገራዊ/የወል) መንግስት    2. ክልል (ፀረ ሰላምና ፀረ ሕዝብ)   3. ክፍለ አገር

        4  አውራጃ  5. ወረዳ   6. ም/ወረዳ    7. ቀበሌዎች  ናቸው።

እዚህ ላይ መነገር ያለበት አስተዳዳርዊ  ሐቅ አለ፡፡ ይኽውም ማገራዊ እርከኖች በተቀነሱ መጠን የመንግስት አስተዳደራዊ ስልጣን እና አገልግሎት ለሚገባችው እታች መንደር ላሉት ብዙሐን ሕዝቦች ይቀርባል።

የአስተዳደር እርከን ቅነሳውም ከላይ ብቻ ሳይሆን ከታችም ም/ወረዳዎች በሙሉ ወደ ወረዳዎች ተቀይረው ቢስፋፉ አገልግሎቱ ለሕዝብ በጣም ይቀርባል። የህም ሲሆን የሰርዶ ዲሞክራሲም (Grassroots Democracy) በግልጽ በስራ ይተረጎማል፣ አስተዳደሩም ህዝባዊ ይሆነል፡፡

እግዚአብሕር ኢትዮጵያንና ሂዝቦችዋን በሰላምና በአንድነት ይጠብቃት። አሜን !!!!!

     አበራ መ

የሕዝባዊ አስተዳደር ሊቀምሁር

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.