ከመጨነቅ የመፍትሄ አካል መሆን – ሽመልስ ወርቅነህ

በኢትዮ ሶማሌ ጦርነት ሃረር ነበርኩ የዚያድ ባሬ ወታደሮችና ሰርጎ ገቦች አብዛኛውን የሃረርጌን  ክፍለሃገር ተቆጣጥረው እስከ አዋሽ የመጡበትን ሁኔታ አስታውሳለሁ፡ ድሬደዋም እስከ ለገሃሬ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ደርሰው እንደነበር ይታወሳል፡ ማታ ማታ ሃረር ከተማ መሃል ሰርገው እየገቡ ከተማውን በተኩስ ያናውጡት ነበር፥፥ ታዲያ እውነት ለመናገር ህዝቡ ምንም የከፋ ጭንቀት አላየሁበትም፤ ሲነጋጋ አልፎ አልፎ በቱቦዎች መካከል ማታ የተገደሉ የሰርጎ ገብ አስከሬን ይነሳል ፤ የውጭ ጠላት በመሆኑ አንድነታችንን የሚያናጋ ምንም  ስነልቡናዊ ተፅእኖ  አልነበረውም፡፤  በዘመኔ ኢትዮጵያውያን እንደአሁኑ  በሃገራቸው ጉዳይ እንዲህ ጭንቀት ውስጥ ሲገቡ አላየሁም ፡ ለምን በየቀኑ በሚዲያ ስለምንሰማ ይሆን ፥ አይደለም ፡ ጭንቀቱ ከውጭ የመጣ ወራሪ ሃይል ሳይሆን በጥቂት  ሃገር በቀል እብሪተኞች ስግብግቦች ፥ በአለም ፖለቲካ ውስጥ ለስልጣን ከተደረጉ ግብግቦች ያልተለመደና  ሕጻናትን ሳይቀር ለእልቂት የሚያስልፍ  ጨካኝ ሃገር በቀል የወንበዴ ቡድን በሃገራችን በመከሰቱ ነው፡ ለምን ይህ ሁሉ የህይወት መስዋእትነት? ለነፃነት ? ምን አይነት ነፃነት ? ለእኩልነት ምን አይነት እኩልነት ? ለፍትህ ምን አይነት ፍትህ ነው ? በጣት የሚቆጠሩ የዘረፉ የበደሉ ህዝብ ያሰቃዩ የትግራይ ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ጭምር በችግር ሲጠብሱ የኖሩ ፍትህ ያሳጡ ለነሱ መንደላቀቅ  በትግሬነት  ስነልቡናውን በመስለብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር እንዲቃቃርና ዛሬ ለምናየው የአንድ እናት ልጆች እልቂት የዳረጉትን ክፉዎችን ጦርነት ለምን ፥ በአንድ ጉድጉዋድ ከ20 አመት በላይ አብረውት የኖሩትንና ሲጠብቃቸው የነበረውን መከላከያ ሃይል በአስቃቂ ሁኔታ  የሚያርዱ ጨካኞችን መደገፍ ለምን ፥

በአሁኑ ወቅት በምንም መመዘኛ ቢሆን እትዮጵያውያን ሳይወዱ ተገደው የገቡበትን ጦርነት ለማሽነፍ ብቃት ስልሚያንሳቸው አይደለም ስጋትና ጭንቀት ውስጥ የገቡት፤  እውነት ለመናገር ጦርነት ጦርነት ነው ብለው እየተዋጉም አይደለም ያሉት፡፤ በጁንታው አስከፊ ጭካኔ እየተማገዱ ያሉት የትግራይ ህጻናት አሮጊትና አዛውንቶችን ላለመግደል ሲባል እይተከፈለ ያለው መስዋእትነት ቀላል አይደለም፡፤ የጁንታው የፈስቡክ አርበኞች እንድሚያወሩትም መከላከያ ሰራአዊታችን ቦታዎችን እየለቀቀ የህሄደው አቅም ጉልበት አጥቶ አይደለም፡፤ በርግጥ  በአንድ ነገር ተሽንፎአል፡፤ የተሸነፈውም የቆመለትን የሃገርና የህዝብ ምንነት ጠንቅቆ በመረዳቱ ሃገር ያለ ህዝብ ህዝብ ያለ ሃገር ትርጉም እንደሌለው ስልሚገነዘብም ነው፡ ያ ባይሆን ኖሮ  ጦርነቱ ለመሬት ቢሆን ኖሮ በጥቂት ቀናት ሊፈጸም እንደሚችል የወታደራዊ ሳይንስ አዋቂ መሆን አይፈልግም ። የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ያለውን ስሜት ይዞ ከተነሳ ጦርነቱ ከቀናት በላይ የሚሄድ አይሆንም።

ታዲያ ስጋቱ ለምንድነው ፥ ለመሆኑ የጦርነቱ ውጠቶች ምን ሊሆን ይችላል  የሚሉትን ሲናሪዮዎች በማብሰልሰል ነው፡

1፥ አንዳንድ አፈ ቀላጠዎቻቸው እንደሚያወሩት ትግራይ ልትገነጠል ትችላለችን ?

2፤ የትግራይ መገንጠልን ተከትሎ በኢትዮጵያችን ለመበታተን የሚያስችሉ ሁነታዎች ይፈጠራሉን?

3፤ የጁንታው መወገድና ትግራይ እንደቀድሞው በፌደራል መንግስቱ ጥላ ስር የምትተዳደር ክልል ሆና መቀጠል፥ ይህ ደግሞ ቀደም ሲል በሃይል የትግራይ ክልል እንዲሆኑ የተደረጉ አካባቢዎችን የወደፊት እጣ የሚወስን በመሆኑ ችግሩ እንዴት ሊፈታ  ይችላል?

4፥ ጁንታው አሽንፎ እንደገና ወደ ስልጣን መመለስና የማያባራ የርስ በርስ እልቂት ይቀጥላልን?

5፥ የውጭ ሃይሎች  እንደነ ግብጽ ሱዳን ያሉት የጀመርነውን የአባይ ግድብ እጣ ፋንታ ወሳኝ ሊሆኑ የሚችሉበት ሁኔታ ይፈጠራልን?

6/ በውጭ ሃይሎች በተለይም በነአሜሪካ ጣልቃ ገብነት የዶክተር አቢይን መንግስት በሃይል አስወግዶ የመዋጮ መንግስት ይፈጠራልን  ወይም እንደሚሉት የሽግግር መንግስት እንደኔ የሽግግር ሳይሆን የችግር መንግስት ይፈጠራልን ?

ከሁሉም በላይ ትግራይ ተገንጥላ ሃገርም ብትሆን አሁን እየታየ ያለውን የስነልቡና ቅራኔ እንዴት ማስወገድ ይቻላል ? ተገንጥሎ በሰላም የኖረ ሃገርና ህዝብ አልታየምና ፡ ቢኖርም የረዥም አመታት ውድቀትን ማየት አስከትሎአልና ፡

በአለም ላይ በርካታ ጦርነቶች ተካሂደዋል   በኛ ኢትዮጵያውያን እንኩዋን የቅርቡን ብናይ ከኤርትራ ወንድሞቻችን ጋር የተደረጉትን ሁለት ጦርነቶች  ከትግራይ ወንድሞቻችን ጋር የተደርገው ጦርነት በተለያዩ ጊዘያት በሃገራችን በነጻ አውጭ ስም ከተደራጁ ሃይሎች ጋር የተደረገው ጦርነት የቀጠፈው ህይወት የወደመው ንብረት ከሁሉም በላይ የሞት የስደት ስነልቦና ሃገራችንን ምን ያህል ወደሁዋላ እንዳስቀራት የማይገነዘብ ዜጋ ይኖር ይሆን?

ዛሬ በአለም ላይ እንደኛው የጦርነት ሰለባ ውስጥ ያሉ ኢራቅ የመን አፍጋኒስታን ሲሪያ ሜክሲኮ ቱርክ ሶማሊያ የሳህል ሃገሮች ሊቢያ ከመሳሰሉት ምን ተማርን ?

በነዚህ ሃገሮች ውስጥ ለሚካሀደው ጦርነት የውጭ ሃይሎች በተለይም አሜሪካ የምትጫወተውን የጥቅም ፖለቲካ ለመረዳት ሚን ያህል አእምሮዋችንን ከፍተናል፥

እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎች ቢያስጨንቁንና ግራ ቢያጋቡን ሊደንቅ አይገባም ፡ ከሲናርሪዎቹ ሁሉ በኔ ምኞትና ፍላጎት ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ህዝብ አርቆ አሳቢነት ሲናሪዮ ቁጥር 3 አማራጭ የሌለው ሲሆን ችግሩ እንዴት ሊፈታ ይችላል ለሚለው መልሱ በኢትዮጲያ ህዝብ ሙሉ ተሳትፎ መፍትሄ ያገኛል ብየ አስባለሁ፡ታዲያ ለዚህ መሳካት ዛሬ ከየአቅጣጫው ፉከራና ቀረርቶውን ቀነስ በማድረግ ጁንታው ተነጥሎ የሚመታበትን የፖለቲካ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ  ስልትና ዘዴዎችን ሃሳብ ማፍለቅ በ ጦር ግንባር የሃገሩን አንድነትና ክብር ለማስጠበቅ ጥቂት ከሃዲዎች በፈጠሩት ሴራ ሃገርን ለማፍረስ ከተነሱ ወንበዴዎች ጋር  ሳይወድ በግድ ጦርነት ላይ የሚገኘውን መከላከያ ሰራዊታችንና የህዝብ ሃይል በማቴሪያልና ሞራል መደገፍ አማራጭ የሌለው ተግባራዊ ተሳትፎ ማጠናከር : በሃሰት ፕሮፓጋንዳ የተካኑትን የጁንታው አፈቀላጠዎችን አጥብቆ መታገል  በዚህም የኢትዮጵያን  አሽናፊነት ማረጋገጥ አማራጭ የሌለው ተግባራዊ ተሳትፎአችን ሊሆን ይገባል ፡፤ ስለዚህ ስጋታችን እንዳለ ሆኖ የመፍትሄ አካል እንጂ  የጭንቀት ጎተራ ከመሆን እንውጣ !!!

Shimelis Workneh (aka gishay Gisha)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.