ያመመን ያለዉ የአድርባይነት እና ጥላቻ  ሰንኮፍ ነዉ ! – ማላጂ

ኢትዮጵያ አገራችን በምስራቅ አግሪካ ቀንድ በመልካ ምድር አቀማመጧ፣ባላት የተፈጥሮ መስህብ ፣ የባህል፣ የቋንቋ…እንዲሁም  ቀደምት ዓያቶቻችን ለራሳቸዉ፣ ለአገራቸዉ እና ለመላዉ ዓለም የነበራቸዉ ዕይታ በራስ የመተማመን ላይ የተመሰረተ ስለነበር በሌሎች ጥርስ የመግባት ታሪክ አዲስ አይደለም፡፡

ቀደምት የኢትዮጵያ ነገስታት እና መሪዎች በአገራቸዉ እና በህዝባቸዉ ጉዳይ ላይ ለሚመጣ ሁሉ ቀናዒ እንደነበሩ ዓለም የሚመሰክረዉ ዕዉነታ ነዉ ፡፡

በ18ኛዉ ክ/ዘመን የኢትዮጵያን  አንድነት ለማጠናከር  እና አሁን ስላለችዉ ኢትዮጵያ መሰረት ለመጣል  ዐፄ ቴወድሮስ የሰሩትን ታላቅ ተጋድሎ እና በዚህ በ20ኛዉ ክ/ዘመን ያለ ትዉልድ ሲሶ ሊያስብ ያልቻለዉን ዘመናዊነት የነበራቸዉን የአመራር ቁርጠኝነት እና ብቃት ከማዉሳት እና ለተዉልድ ከማስተላለፍ ይልቅ ወደ ተነሳንበት የበታችነት ስሜት ስለምናጋድል ምሳሌ ለመጥራት ወደ ባዕድ አገር እናማትራለን ፡፡

ዕምየ ሚኒሊክ  ….ሚኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ  ግብሩ አበሻ ነበር እህንጊዜ አበሻ የተባለላቸዉን ብርቱ፣ አርቆ አሳቢ፣ በሩህ፣ቅን፣ ጥበበኛ ለአገራቸዉ እና ህዝባቸዉ ስልጣኔ እና ዕድገት ከፍተኛ ጉጉት የነበራቸዉን  በዓለም ላይ ያሉ ወዳጆችም ፤ጠላቶችም አንቱ ያሏቸዉን  እኛ አንተ ከማለት በላይ ወርደን….ወርደን  የሰሩትን መካድ እና መናድ ከጀመርን ሰነባበትን፡፡

በ18ኛዉ ክ/ዘመን መጨረሻ እና 19ኛዉ ክ/ዘመን መጀመሪያዎች ጥበብን፣ ትምህርትን (ዘመናዊ) ወደ ሩሲያ ወጣቶችን በመላክ)፣ ስልጣኔን፣ መሰረተ ልማትን፣ የመረጃ ስርዓትን፣ የባቡር መጓጓዣ፣ ተሸከርካሪን….. እንዲገባ እና ዜጎች የስልጣኔ ተቋዳሽ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡

በዓለም ላይ ቅኝ ግዛት እና የባሪያ ፍንገላ (ጌታ እና ሎሌ)  ግፈኛ የዓለም ስርዓት በተስፋፋበት እና በተንሰራፋበት የጭለማ ዘመን የሠዉ ልጅ በዓርያ ስላሴ የተፈጠረ ዕኩል እንጅ በቀለም፣ በአኖኗር፣ በሚኖርበት አካባቢ ወይም በሌላ ምክነያት የበላይ እና በታች የለም በማለት አጥብቀዉ ሲያወግዙ እና ሲከላከሉ እንደነበር የሚካድ አይደለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአብይ አህመድ አገዛዝ በአዲስ አበባ የሚያደርሰውን አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣው ዓለም ሊያወግዘው ይገባል!

የአፍሪካ ህዝብ እንደማንኛዉም ሠባዊ ፍጡር ራሱን እና ሠባዊ ነፃነቱን የመከላከል እና የማስቀጠል ተፈጥሯዊ  ማንት እና ብቃት ያለዉ መሆኑን በአፍሪካ የነጻነት ትግል ዓዉድማ “ ዓዳዋ  ” ላይ የኃያልነት ክንዳቸዉን በተስፋፊ እና ወራሪ ጠላት ላይ ያነሱ እና ያቀሙሱ  ዐፄሚኒሊክ መሆናቸዉን ዓለም አስካለ የሚቀጥል ዘላለማዊ ህያዉ ምስክር ነዉ ፡፡

ሁሉም ነግስታት ንግስት ዛዉዲቱ፣ ንጉስ ኃይለስላሴ ፣ ኮ/ል መንግቱ ኃ/ማርያም  ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ የነበራቸዉን ቅን ጥረት፣ፍላጎት እና ምኞት ከስራዎቻቸዉ እኛ እና መጪ ትዉልድ የሚገነዘበዉ ነዉ ፡፡

ነገር ግን በተለይም ከቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስታት ስንጀምር የኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያምን መንግስት ከልጅነት አስካሁን የነበረዉን ክፉ ገፅታ እየተነገረን ማደጋችን ያለፈዉን እና መጪዉን ጊዜ አስተሳስሮ እንደ ሠዉም ሆነ አንደ ትዉልድ በራሳችን ታሪክ እና ማንነት ግልፅነት የሌለዉ ብዥታ ዉስጥ እንደገባን ያለፈዉን መረሳት የመጣዉን ዐሜን ማለት እና እጅ መንሳት ከግለሰብበት ወደ ብሄራዊ አድርባይነት ምዕራፍ መግባታችንን ነዉ ፡፡

ሆኖም የተባለዉን እና የሚነገረንን ሁሉ ዓሜን ብሎ መሸከም ግለሰባዊ እና ማህበረሰባዊ ንቃተ ህሊና ደረጃ የሚወስን ነዉ ፡፡

እኔ ሁሉን ዓሜን የምል ከሆነ ለምን ብሎ የሚሞግት መኖሩን በፀጋ መቀበል ቢሳነኝ እንኳ በጥላቻ እና በአድር ባይነት ልመለከት አይገባኝም ፡፡ የአድር ባይነት እና ጥላቻ ጉዞ አዙሪት እንጅ መዳረሻ እንደሌለዉ ከትናንት ታሪካችን እና ከዛሬ ስንክሳራችን ደጋግምን ልንማር ይገባል ፡፡

የእኛ አገር አድርባይነት ብዙ መገለጫ ቢኖርም በተለይ በፖለቲካም ሆነ በታሪክ ዕይታ የትኛዉም የመንግስት አስተዳደር ከየትኛዉ የላቀ ህዝባዊ እና ብሄራዊ ፋይዳ በህዝብ አስተዳደር፣ በህዝባዊነት/ ዲሞክራሲ፣ በዜጎች መሰረታዊ የመኖር ፍላጎት ማሟላት፣ በነፍስ ወከፍ ገቢ፣ በሰባዊ መብት ጥበቃ፣ በሠላም የመኖር ፣ የአገርን ሉዓላዊነት ፣ዳር ድንበር እና የዜጎችን ዕኩልነት …. ካልን ፍርዱን ለህዝብ እና ለዕዉነት ፈራጂ ዓምላክ ይደር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መጽሐፉን ተወው! እና ሰዉን አጥብቀህ ጠይቅ! (ሥልጣን እንዴት በስልት ይገኛል? አጠናኑ? አካሄዱስ?) - አሳፍ ሃይሉ

ነገር ግን ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን እንጥቀስ ይኸዉም በጎ ስራ ለህዝባቸዉ ፣ለአገራቸዉ እና ለዓለም የሰሩትን የአገራችንን ታላላቅ ሠዎች /መሪዎች በጎ ስራ ዕዉቅና ለመስጠትም ሆነ መታሰቢያ ለማድረግ ከንፉግነት አልፎ ህዝባዊ እና ብሄራዊ ምቀኝነት የተጣባን አስኪመስል ለጠላት ቀዳዳ ከፍተናል ፡፡

ሌላኛዉ ከየትኛዉም የኢትዮጵያ የመንስታት ታሪክ የቀደሙት ኮ/ል መንግስት ጨካኝ እንደነበሩ ለ27 ዓመት በህዝብ ላብ እና ስም በተገኘ የአገር ሀብት እና ንብረት ሁሉ እርሳቸዉን እና መንግስታቸዉን በማጥላላት በተቃራኒዉ ፍፁም ፀረ ህዝብ እና አገር ለነበሩት ከንቱ ዉዳሴ በመከደም ብዙ ወርቃማ ጊዜ አገሪቷም፣ ዜጎችም ሆኑ ኢ.ኃ.ዴ.ግበተለይም ሕ.ወ.ኃ.ት  እንደዋዛ በማባከን አሁን ላለንበት ደርሰናል፡፡

ለመሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ብሄራዊ ጥቅም ማን ሠራ ፤ማን በተቃራኒዉ ነበር ፣ ማን ኢትዮጵያን አዋረደ ፣አሳደደ፣ በዓለም ፊት ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ተወረዱ መቸ እና በማን …..ቢባል ያለጥርጥር ማን  የዚህች አገር ጠላት እና ወዳጅ እንደነበር ማረጋገጥ ይቻላል ፡፡

ዛሬ ቅጥ ያጣ በቅንርት ላይ ጆሮ ደግፍ ድህነት ፣ ድንቁርና ፣ ስደት፣ ሞት ፣ ክፋት ……  ለመፈራረቃቸዉ ተጠያቂ ይኑር ከተባለ ከኢ.ህ.ዴ.ግ. በላይ ማን ሊሆን እንደሚችል ክሊና ላለዉ መገመት የሚያዳግት አይሆንም ፡፡

ግፈኞች በቁማቸዉ የራሳቸዉን የፈጠራ ታሪክ ለማስከተብ ሲሞክሩ፣ በቁማቸዉ ሀዉልት ሲያሰሩ ፣ አገር እና ህዝብ ባጎሳቆሉ እንደመልካም ስራ እና ተጋድሎ ለሰራንዉ ዕዉቅና እና ስጦታ ሲሉ የቀደሙት መንግስታት የሰሯትን አገር  እያንዳንዱን መልካም ስራ ለማፍረስ ሌት ተቀን ሲባዝኑ ሲመሽባቸዉ  አሁንም ጀምረዉ ያልጨረሱትን አገር እና ትዉልድ የመናድ ዕኩይ ስራ  በቁጭት መያዛቸዉ ምንም ዓይነት በጎ ነገር መስራት የሚያስችል ቁመና የሌላቸዉ መሆኑን ያሳያል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከፓርላማዊ ዲሞክራሲ ወደ ፕሬዚደንታዊ ዲሞክራሲ . . . . ለምን? እንዴት? በማን ውሳኔ?

አሁን ላይ ሆነን እንደ አገር የመኖር እና ያለመኖር ምርጫ ዉስጥ ገብተን ባለንበት ብቸኛዉ መፍትሄ አማራጭ በአገር እና በህዝብ ላይ የተሰራዉን እና እየጠሰራ ያለዉን መራር ዕዉነት ዕሬቱን ከወተት የመለየት እና ወደራስ የመመልከት ህዝባዊ ወገንተኝነት ሊሰፍን ይገባል፡፡

በታሪካችን ከዕዉነተኛ ሀዲድ ዉስጥ በህብረት እና በአንድነት መጓዝ እሳካልቻለን ድረስ ወደ ትክክለኛ እና የጋራ ጉዞ ለመዳረስ ያልተገባ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡

በአድር ባይነት መትመም  የሕልም ሩጫ ነዉ ፡፡ ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ በጎ እና ዘመን ተሸጋሪ ተግባር ለፈፀሙ፣ ተጋድሎ ላደረጉት ፣ በግፈኞች ለዘመናት ለተሳደዱት ፣ ለሞቱት እና ለተጎሳቆሉት  ዕዉቅና ፣መታሰቢ (የስማቸዉ መጠሪያ ፣ ሀዉልት…………..) ማድረግን እንድፈር ፤እንጀምር ይህም በዕዉነተኛ ኢትዮጵያነት ላይ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን  በዓለም ፊት ክብር እና ሞገስ በማስገኘት ትዉልድ በራስ ማንነት እና ታሪክ ላይ ለዕድገት እና ብልፅግና እንዲተጋ ያደርገዋል፡፡

ለማስደሰት እና ለማስቀየም በሚል ጊዜ ያለፈበት ዕንቶ ፈንቶ አድር ባይነት አመለካከት ወጥተን መልካም ለሰራ መልካምን ( ምሳሌ ፓና አፍሪካ መካነ ተቋም / የኒቨርስቲ………) ከማለት ሚኒሊክ ፣ የካርል አደባባይ  ከማለት ጣይቱ ብጡል ብንል ማትረፍ እና ለራስ ዋጋ በመስጠት የራስን ዋና ማዉሳት  ነዉና  ከአስተሳሰብ እና ገንዘብ ጥገኝነት ለመዉጣት የሚያስችል ልዕልና ያጎናፅፈናል፡፡  ዕድገት እና ብልፅግና ራስን በመሆን እና በምኞት እና በግዞት አይገኝም ፡፡ ምኞት እና ግዞት/ባርነት የነጻነት እና የድህነት  በር  ናቸዉ ፡፡ ነጻነት እና በራስ የመቆም በሌሉበት ምርታማነት እና ክህሎት ሰለማይታሰቡ ደጋግመን ከራስ ወዳድነት እና አድርባይነት አስር እና ባርነት እንዉጣ ፡፡

የሁላችን ጠላት አድርባይነት እና ጥላቻ  ሰንኮፍ ይርገፍ  !!

ማላጂ

አንድነት ኃይል ነዉ !!

 

1 Comment

  1. ጎበዝ ጦርነቱ መልኩን እየቀየረ ነው።ወያኔ የሰራው ታሪካዊ ስህተት ሁሉን ክልልሎች አስቆጥቷል። የትግራይ ህዝብ ወያኔን በቶሎ ከራሱ ላይ በተደራጀ መልኩ አሽቀንጥሮ እስካልጣለ ድረስ ውጊያው ሰው እስኪያልቅ ቀጣይ ነው። ትላንት በንፋስ የተበተኑ ድቄት የተባሉት ወያኔዎች ዛሬ አፋር ድረስ መሄዳቸው አስገራሚ ጉዳይ ነው። እንደ BBC (online), CNN, My views on the news, and several print and other media outlets are fanning the flame so we can continue to call one another. የሚያሳዝነው የአሜሪካ መንግስት ጨካኝና አረመኔ ከሆነው ወያኔ ጎን መሰለፉ ነው። ዳሩ ግን ረጋ ብሎ የአሜሪካን የውጭ ፓሊሲ ለተመለከተ ቀዳሚ ተግባራቸው ሃገርን ማፍረስ ነው። ለዚህም ነው ከወያኔ ህሳቤ ጋር የሚጣጣሙት። በስመ ሽብርና ዲሞክራሲ ስንት ሃገሮች ተንደው ዛሬ ትራፊው ህዝብ ሃበሳ ቆጣሪ ሆኗል። አንድ ገልቱ የትግራይ ተወላጅ በቢቢሲ ቀርቦ ሲናገር ” ወራሪ ሃይሎች ከምድራችን እስኪወጡ እንዋጋለን” በማለት ሲያላዝን መስማት እንዴት ልብ ይጎዳል። ወራሪው ማን ነው ተወራሪውም የቱ ነው። ይህ ተምሬአለሁ የሚለው ሰው ሙሉጌታ ገ/ህይወት በርሄ ይባላል። ቤተሰቡንና ዘመዶችን በውጭ አስጠልሎ እንዳጋጣሚ ዘመድ ልጠይቅ መጥቼ በዚሁ ትግሉን ተቀላቀልኩ ይልና የ 62 ዓመት አዛውንት እንደሆነ ይናገራል። እናንተ አይደላችሁ የትግራይን ህዝብ እቃ እቃ የምትጫወቱበት? እናውቅልሃለን እያላችሁ። የሌለ ታሪክ እያስተማራችሁ። ወያኔ የእብዶች ጥርቅም ነው የምንለው ለዚህ ነው። ኢትዮጵያን ሲኦል እስክናስገባ ነው የምንታገለው የሚለው ጌታቸው ረዳ ቢታመም እንጂ በጤናው ይሆናል ብሎ ሰው እንዴት ያምናል? ሃገርን ገሃነብ የሚከት አመራር ነው የወያኔ ስብስብ። እኔስ አንድም ሰው ባይሞት ያለንን ተካፍለን ብንኖር ደስ ባለኝ ግን መሻትና ፍላጎት ናልኝ ተብሎ አይገኝ። አሁን ያለው ጉዳይ ግን እጅግ አሳሳቢ ነው። ለመጨራረስ ሁሉም የክተት አዋጅ አውጇል። ማን ሞቶ ማን ይቀራል?
    ወያኔ የሰሜንን ጦር በተኛበት ካረደው በህዋላ የማይወጣበት ማጥ ውስጥ ገብቷል፡፤ አሁን ከአፈርኩ አይመልሰኝ እንጂ ነገሩ አልቋል። የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል። ግን በሚሊዪን በሚቆጠር ካድሬ ታፍኖ የተያዘ ህዝብ ምን ምርጫ አለው? ለዛም ነው ልጆችን ከከተማ እያፈሰ ወደ ጦር ግንባር የሚማግዳቸው። ይህ የማያሳዝነው ሰው ካለ ራሱ ግኡዝ ነው። ወያኔ ያልተረዳው በሃገር ላይ በሚመጣ ማንኛውም ጦርነት የኢትዮጵያ ህዝብ ልዪነቱን አስወግዶ ራሱን አንድ አርጎ እንደሚዋጋ ነው። ብሄር ብሄረሰቦች እያለ 30 ዓመት ያላገጠባቸው አይደል እንዴ ዛሬ ጉሮሮውን ለማነቅ ወደ ስሜን የሚጎርፉት? በስልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሰራው በደልና በመቀሌ ራሱን አስጠግቶ ይሰራ የነበረው አፍራሽ ድርጊት የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። የወያኔ ክፋትና ሴራ ከተነቃበት ቆይቷል; አሁን በወያኔ እህቱ ወንድሙ አባቱ እናቱ የተገደለበት ሁሉ ጥርሱን ነክሶ ለብቀላ ተነስቷል። የወያኔ ድህረ ገጾችና ተከፋይ ድርጅቶች ወያኔ አዲስ አበባ ሊገባ ይህን ያህል ቀረው እያሉ ሲዘግቡ በሰው ህይወት እንደተጫወቱ አይገባቸውም። ወያኔ እንደገና ኢትዮጵያን ይመራል ብሎ ማሰብ ሰማይና ምድር አንድ ሆኑ እንደማለት ነው። ቅዥት ብቻ! ግን አንድ ጦርነት ሌላ ጦርነትን ያመጣል። አንድ ፍርስራሽ ሌላ ፍራሽን ያሳያል። ልብ ላለው ቆም ብሎ መገዳደላችን ይብቃ እኛም ወደ ውጭ ወጥተን እንድንኖር መንገድ ይከፈትልን። በተነድባ፤ በገዳሪፍ፤ በአምራኩባ በሌሎችም የሱዳን ስደተኛ መንደሮች ያሉት ይመለሱ እብደታችን ያብቃ ሃገራችን በአንድነት እንገንባ ቢባል ማለፊያ ነበር። ግን ይህ በወያኔ ስሌት አይታሰብም። እሳት ውስጥ ዘላ እንደምትገባ የእሳት ራት መቅበዝበዝ ብቻ።
    አድርባይነት፤ ወላዋይነት፤ አንድን ገፍትሮ ራስን ወደ ኋላ ማስቀረት የጦርነት ፍትጊያ ውስጥ ከሚታዪ ጥቂት ነገሮችን ናቸው። አንድ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ ከጃፓኖች ጋር ይፋለም የነበረ የአሜሪካ ወታደር የገደላቸውን ወታደሮች ጀሮ እየቆረጠ በከረጢት ይሰበስብ ነበር። አንድ ቀን አዛዡ ምንድነው የያዝከው ሲለው የሰው ጀሮ እንደሆነ ይነግረዋል። ተደናግጦ ዘርግፈው ሲለው የብዙ ሰዎች ጀሮ መሆኑ ይታያል። ለምን እንዲህ አደርክ ሲብል “አላውቅም” ብሎ ሲመልስ በል አሁን ከእነዚህ ጋር ሆነህ ጉድጓድ ቆፍረህ እንዲቀበር ይሁን እንዳለው ታሪክ ያሳያል። ጦርነት የቆመን ያሳብዳል፤ የተቀመጠን በዚያው ያስቀራል። የትግራይ ህዝብ በወያኔ ስም የሚሞትበት አንድም የሆነ ፍትሃዊ ተግባር የለም። ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ነው እያላተሙት ያሉት። ንቃ፤ ተነስ፤ በቃ በል። ያለበለዚያ እልቂቱ ለሁሉም ነው። በቃኝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share