ሃምሌ2 ቀን 2013
1 ዐማራዉ አምላኩን ያምናል፡፡በዚህ እምነቱም ሰዎች ሁሉ ሲወለዱ በተፈጥሮአቸዉ ነጻ እና እኩል መሆናቸዉን፣እኩል ሰባዊ ነጻነት፣ መብት እና ክብር ያላቸዉ መሆኑን ፣በዚም እምነትታቸዉ የዘር፣ የቀለም፣ የጾታ፣ የቋንቋ፣ የሀይማኖት፣ የፖለቲካ አቋም፣ የብሄር የመደብ፣ የንብረት፣ የልደት፣ የማእረግ ምርጫ እና ልዩነት ሳይደረግ ሁሉም የሰዉ ልጆች በምድር ላይ ለሰዉ ልጅ ጠቃሚ ለሆኑት ቁሳዊ እና ህሊናዊ ነገሮች በእኩልነት ባለቤት እና ተጠቃሚ መሆናቸዉን፣ የሰዉ ልጆች እኩልነትን ፣የግለሰብ ነጻነትን ፣ ፍትህን ሌላዉን እንደራስ ማየትን፣ ለእሱ የሚያደርገዉን ለሌላዉ ማድረግን ፣ ሌላዉን እንደራስ መዉደድን እና መፈቃቀርነ አፍቅሮም ለአፈቀረዉ ሁሉ ለሚገጥመዉ ችግር ግንባር ቀደም ተሰልፎ ችግር ፈች መሆኑ፤
2. ዐማራዉ በኢትዮጵያዊነቱ ያምናል፡፡ ኢትዮጵያ ከብዙ ሚሊዮን ዓመታት በፊት የሰዉ ልጅ እራሱ በአካል እና በአእምሮ መሳሪያዎቹ አድጎና ዳብሮ በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተባት ታሪካዊ ሥፍራ እንደሆነች፣በቅድመ ታሪክ የሰዉ ልጆች እና ቋንቋዎቹ መነሻቸዉ ከኢትዮጵያ ምድር መሆናቸዉን፣ በፍልሰት እና በሰፈራ እቅስቃሴ ባህርን ተሸግረዉ በኢስያ እና በአዉሮፓ አህጉራት እንደሰፈሩ፣ የአረኪኦሎጂ፣ የሊንጉስቲክስና የፓሊኦንቶሎጂ መረጃ እና ትምህርት ያምናል፡፡ ማንም ሰዉ በየትኛዉም ሥፍራ እና በምንም ጊዜ በህግ ፊት ሉዐላዊ ክብሩ የመታወቅ መብት ያለዉ መሆኑን፣ በዚህም እምነቱ ሰባዊ እና ዲሞክራሲዊ መብቶች እና የግለሰብ ነነጻነቶች፣ለትዳር የደረሱ ወንዶች እና ሴቶች በጋብቻ ጥያቄ የዘር የዜግነት የሀይማኖት ገደብ ሳይኖርበት በመፈቃቀድ እና በመፈቃቀር የመጋባት መብት መኖሩን፣
ቤተሰብ የህብረተሰብ መሰረት በመሆኑ የመንግሥት ጥበቃ እንደሚያስፈልገዉ፣፣ማንምሰዉ በግል ወይም በጋራ ሥራ ንብረት የማፍራት እና የመያዝ መብት ያለዉ መሆኑን፣ማንም ሰዉ በህገወጥ መንገድ ነብረቱን እንደማያጣ አምኖ ለተግባራዊነቱ ይታገላል፡፡በዚህ እምነቱ የሌላዉን ንብረት ቅንጣት አይፈልግም የራሱንም አምኖና ፈቅዶ ከአልሆነ በስተቀር ከዚህ ዉጭ ባለ መንገድ መዉሰድ ቀርቶ አይታለምም፡፡ ምክንያቱም በዉል ከሄደች በቁሎየ ያለዉን የሄደች ጭብጥ ጥሬየ ትቆረቁረኛለች የሚል የትባህል በአአምሮዉ ተቀርጾአል እና፤ እርግጥ ነዉ የሰዉ ጀግንነቱ ጊዜ፤ቦታ እና ቀን በመሆናቸዉ በጊዜ የሚያጣዉ ነገር አለ፡፡ ይኖራልም፡፡ ለመግኘትም እንደዚሁ በመሆኑ ነቅቶ እና ተደራጅቶ መጠበቅን ይጠይቃል፡፡ ዐማራዉ በዚህ አምኖ እስከ ሞት ሽረት የመታገል ልምዱን የአጥቂነት ባህሉን አዳብሮ ከአገር አጥፊዎች እና ከፋፋይዎች ባንዳ የባንዳ ዝርያዎች በስተቀር ንጹህ ኢትዮጵዊያንን አክብሮ፣ አቅፎ እና አፍቅሮ በመያዝ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያን በወታደራዊነት ከመንግሥት ምስረታ ጀምሮ አግልግሏል፡፡ እየአገለገለም ነዉ፡፡ ወደፊትም ያለመሰልቸት ለማገልገል የእሱን እምነት ለልጅልጅ ያስተላልፋል፡፡
3.ዐማራዉ ክንዱን እና ተግባሩን ያምናል፡፡ በዚህም እምነቱ የመንግሥት ሥልጣን መሰረቱ የህዝብ ፈቃድ መሆኑን፣ ማንም ሰዉ በቀጥታ ወይም በነጻ ምርጫ በተመረጡ ወኪሎች አማከይነት በሀገሩ መንግሥት ጉዳይ የመሳተፍ መብት እንዳለዉ ያምናል፡፡ እኩል እና ነጻ በሆነ የድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግን፣ማንም ሰዉ በሀገሩ፣ በህዝባዊ አገልግሎት በእኩልነት የመሳተፍ መብት እንደ አለዉ፡፡ ማንም ሰዉ የራሱን ስብእና በነጻ እና በተሟላ መንገድ እና ሁኔታ ለሚያድግበት ህብረተሰብ ተገዥ የመሆን ግዴታእንደ አለበት፣ የራሱን መብት እና ነጻነት ተግባራዊ የሚያደርግ ማንም ሰዉ የሌሎችን መብት እና ነጻነት ማክበር እና ለዲሞክራሲያዊ ህብረተሰብ የሚያስፈልጉ የሞራል፣ የህዝባዊ ሰላም እና ደህንነት ጉዳይዎችን እና ግዴታዎችን ማሟላት እንደአለበት አምኖ ይሰራል፡፡በሌላ በኩል የራሱን ህልዉና አስከብሮ ኢትዮጵያን ከባንዳዎች እና አለቆቻቸዉ የጥፋት ዘመቻ በቆራጥነት ይከላከላል፡፡
ዐማራ እራሱን አዉቆ ጠላቶቹንም ያዉቃል በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ እየተከፈላቸዉ ጸረዐማራ ትምህርት እንዲወሰዱ የአደረጉትን እና የወሰዱትን፣ እንደጆን ያንግ የአሉ በሀገር ዉሥጥም ከሀገር ዉጭም ዐማራን በማጥላላት ሥራ የተሰማሩትን የወያኔ ቅጥረኞችን፣ መስከረም 16 ቀን2002 ዓ.ም በታተመዉ የ10ኛ ክፍል የሥነ ዜጋ ትምህርት መጽሀፍ በገጽ 24 ላይ እራስ ዳሽን የትግራይትልቁ ተራራ ነዉ ተብሎ በካርታ ወጥቶ ትግራይ ዉሥጥ በመደበኛ ትምህርት የተሰጠዉን እና የዓለምን ህብረተስብ የአለማመዱበትን ፡፡ጆን ያንግ የተባለዉ የወያኔ ቅጥረኛ ጋዜጠኛ በ1989 ዓ.ም ፒዛንት ሪቮልዩሽን ኢን ኢትዮጵያ ዘትግራይ ፒፕል ሊቨሬሽን ፍሮንት ከ1975 እስከ 1991 ዓ.ም በሚሉ መጽሀፉ ኢትዮጵያ ከሚገኘዉ ኤንዲፒ አገኘሁት የአለዉ ካርታ የተገኘዉ ከወያኔ ካርታ ሥራዎች ድርጅት መሆኑን፣ ዐማራዉ ይህን ካርታ በዉጩ ዓለም እያለማመደበት መሆኑን እና ለተተኪዉ ትሙልድ አስጠንተዉ በዐማራ እና በትግሬ መካከል የማያቋርጥ ጥላቻ እየነዙበት መሆኑን አዉቆ ለልጆቹም አሳዉቆ የተከዜን ወንዝ ደንበርነት በማስከበሩ ያምናል፡፡ ፡፡ይህም ሲባል ከቅሩቅ ዘመድ የቅርብ ጉረቤት በሚል ይትባህል ኢትዮጵያን ለማጥፋት በቅድሚያ የኢትዮጵያ አለኝታ እና መከታ የሆነዉ ዐማራን አጥፍተን ኢትዮጵያን እናጠፋለን ከሚሉት ባንዳዎች እና የባንዳ ዝርያዎቸ በስተቀር ከሌላዉ የትግራይ ህዝብ ጋር በኢትዮጵያዊነታቸዉ ዐመራዉ የሚያገኘዉን አግኝተዉ የሚያጣዉን አጥተዉ በሰላም በፍቅር ሰምእና ወርቅ ሁነዉ መኖር እንደሚችሉ በማመን ነዉ፡፡፡፡
ዐማራዉ ለኢትዮጵያ ጸንቶ መቆም፣ ጋሻእና መከታ መሆን የዉጭ ወራሪዎች ጸሃፊዎች ሳይቀር ሰንደዉ አስቀምጠዋል ከነዚህም ዉስጥ፡-1 ፕሮፌሰር ሰብሰኪ የኢትዮጵያ ታሪክ በፋሽስት ወረራ ወቅት በሚለዉ መጽሀፉ ጣሊያን ዓላማዋን ለማሳካት ለኢትዮጵያ አንድነት ዋና መሰረት ነዉ የአለችዉን የዐማራ ነገድ በሌሎች ነገዶች ማስጠላት እና በጠላት እነት እንዲተያዩ ማድርግ ይህንም እርዳታ በማረግ ማጠናከር
2.የግብጹ ተስፋፊ መሪ የመሀመድ አሊ የልጅለጅ ከዲቭ እስማኤል ከስዊዘርላንድ ተወላጅ ከወርልድ ሙዥንገር የተሰጠዉ ምክር ዐባይን ከምንጩ ለመቆጣጠር እና ግብጽን ለመስፋፋት ከተፈለገ አንድም ኢትዮጵያን መዉረር እና እስልምናን ማስፋፋት፤ ከአልተቻለም እድሜ ልኳን እየተናኮረች እንድትኖር በዐማራዉ ነገድ ላይ የማጥላሊያ ዘመቻ በማካሄድ ከሌሎች ነገዶች ጋር አናክሶ እንዲኖሩ ማድረግ፡፡
3. ሮማን ፐርቻስካ በአዉሮፓዊያን ላይ የሚሰነዘረዉ ጸረ ቅን ግዛት ለመከላከል በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት በተለይም በዐማራዉ ላይ የዐማራዉ ገዥ የሚኒልክ ሥራ የአዉሮፓን ተቋማትን ለማጥፋት የተቃጣ አካሄድ ነዉ፡፡ በመጽሃፉ ገጽ ሶስት ላይ ምእራባዊ ያን ወገኖቸ ስሙኝ በምስራቅ አፍሪካ በምትገኘዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ዐማራ የሚባል ነገድ አለ፡፡ ይህ ነገድ እኛ ምእራባዊያን በአፍሪካ በምናደርገዉ የማስፋፋት ፖሊሲ ትልቅ እንቅፋት ነዉ፡፡ ዐማራ ከተደራጀ እንኳን ለአፍሪካ ለኛም ትልቅ ስጋት ነዉ፡፡ እያንዳንዱ ምእራባዊያን አገሮች የሚከተሉት ፖለሲ ከዚህ አንጻር መቃኘት አለበት ብሎ በጥናት መጽሀፉ ለምእራባዊያን አሰራጨ፡፡
4. ሩደልፍ የተባለ ጸሃፊ ዐማራ ለኢትዮጵያ የቆመ ኃይል ነዉ ፡፡ ዐማረ እንዳይደራጅ ጠብቁት፡፡ ዐማራ የተሸነፈ መስሎ አንገቱን ቢደፋ ቀን ጠብቆ መነሳቱ አይቀርም፡፡የሞተ ዐማራ አይነሳም ብሎ ማመን እንጂ የተዳከመ ዐማራ አይነሳም ብሎ ማመን ቂልነት ነዉ፡፡ ሲል መጻፉ‹፡፡
5. የምእራባዊያንን ዓላማ ለማሳካት ኢትዮጵያን ለማጥፋት በቅድሚያ ዐማራን ማጥፋት በሚል ስሌት ዐማራን ለማጥፋት በመርሀ ግብር ነድፎ እና እቅድ አዉጥቶ በማጥፋት ላይ የነበረዉን እስከአሁንም ሸንኮፉ ያልተነቀለዉ፡፡ዐማራዉ እስከ ልጅለጆቹ የማይረሳዉ የዐማራ ቀንደኛ ጠላት መለስ ዜናዊ ሳይቀር ዐማራዉ የማያወላዉል ኢትዮጵያዊ መ ሆኑን ለተከታየዎቹ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ዐማራ ኢትዮጵያዊነቱ ዘልቆ የተዋሀደዉ እና ከደመነፍሱ ጋር የተሳሰረ ነዉ፡፡ ይህን ከህዝቡ ስነ አእምሮ ነጥሎ ለመጣል በዘር፣በቋንቋ ማደራጀት እና በዚህ ዓላማ የሚመሩ ድርጅቶችን መፍጠር ነዉ አለ፡፡በዚህም ዓላማዉ ካሳንቸስ ከሚገኘዉ ማዳም ጠጅ ቤት ባለመሟሎችን አሰባስቦ ሰኔ 24 ቀን 1983 ዓ.ም 25 ድርጅቶችን መሰረተ የዐማረን የማጥፊያ ሰነድ አዘጋጅቶ ህገመንግሥት ነዉ ብሎ ሰየመ ፡
ዐማራዉ ልብ ሊለዉ የሚገባ ዐማራዉ እንደሌላዉ ለራሱ ብቻ የሚያስብ ባለመሆኑ ኢትዮጵያዊ ለሆነ ህዝብ ከተሰነዘረበት እልቂት ማትረፍ ማለት እዚያዉ በዚያዉ ዐማራን መታደግ መሆኑን፣ ዐማራን እና ኢትዮጵያን ነጣጥሎ፣ ለያይቶ ማየት የማይቻል መሆኑን፣በተቃራኒዉ ለቆሙት ጠላቶቹም ዐማራን ማጥፋት ማለት ኢትዮጵያን በመበታተን እንደፈለጉት ማድረግ ማለት እንደሆነ የተረዳዉ ዐማራ ባለ ሁለት ኃላፊነት ታሪኩ በአንድ በኩል ለራሱ እንደህዝብ መቆም ይታገላል፡፡ በሌለ በኩል ለሀገራዊ አንድነት ሲል ኢትዮጵያዊ የሆኑ ነገዶችን በማሰባሰብ ከሱ ጋር በጋራ እንዲሰለፉ የሚድርግ ትብብር ይፈጥራል ፡፡ እነዚህ ሁለት በአንድ ጊዜ እና በአንድ የትግል ጎዳና ዉስጥ የሚራመዱ ተግባሮች ናቸዉ፡፡ ዛሬ አንዱን ነገ ሌላዉን የምንለዉ አይደለም፡፡ግቡም ለሰዉ ልጅ ነጻነት እና እኩልነት ላይ ያጠነጠነ የነገዶችን አንድነት እዉን ለማድረግ እናት ሀገር ኢትዮጵያን ከወደቀችበት ማንሳት ነዉ፡፡የሁሉም ነገዶች ህዝብ የኛ የሚለዉ ህገመንግስት እና መሪ ኑሮት ከዘረኝነት፣ ከሙስና፣ ከአድልዎ፣ ከስርቆት፣ ከወንጀል፣ወዘተ የጸዳ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሥርርትን መገንባት ነዉ፡፡
ዲመክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የመንግሥት ብቻ አለመሆኑን እና የሀገር ባለቤትም ህዝብ መሆኑን ማወቅ ነዉ፡፡ በባለቤትነቱም ህዝብ መንግሥት የሚያደርገዉን የመከታተል መብቱን አዉቆ መስራት አለበት፡፡በህዝብ የተመረጠ መንግሥትም ለምረጫ ቅስቀሳ የተጠቀመባቸዉን ማንፌስቶ ዓላማ እና ግብ ተከትሎ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ለመንበሩ ያበቃዉ ሕዝብ መሆኑን ያወቀ መንግስት ከመንበሩ የሚያወርደዉም ህዝብ መሆኑን ይዘነጋዋል አይባልም፡፡ይህን የሚዘነጋዉ በጉልበት ወጥቶ በጉልበት መዉረድ የሚፈልግ ብቻ ነዉ፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ በይበልጥም ዐማራዉ ሊያተኩርበት የሚገባዉ ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት ሣይንሳዊ የፖለቲካ አመራር ንድፈ ሃሳብ እና ተግባር ጥምረት መሆኑን ነዉ፡፡የነዚህ የሁለቱ ጥምረት በጉልህ የማይታይ ከሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ሊያነሳ ይገባል፡፡
ዐማራ ሆይ ከዚህ በላይ ከተራቁጥር 1 እስከ 5 የተዘረዘሩት ኢትዮጵያዊ ማንነትህ በጠላቶችህ የተመሰከሩልሀ መሆኑን ነዉ፡፡ የዉጭ ጠላቶችህ በዉሥጥ ባሉ የባንዳ ዘርአዝርት ጠላቶችህ መልካቸዉን እና አቀራረባቸዉን እየቀያየሩ የዝምድና ቋንቋ እየተናገሩ ለሚመጡ ጠላቶችህ ንቁ ሆኖ መጠበቅ ነዉ፡፡ በተለይ የወያኔን የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ለአንድ አፍታም ሳጥዘነጋ ችግርህ ሥር የሰደደ እና ዉስብስብ መሆኑን በአንክሮ ተመልክተህ የማንነትህን እሴቶች፣ የጠፉትን በመፈለግ ፣ የተሰረዙት በማጉላት፣ በሰያሜ የተለወጡትን በነባሩ ስማቸዉ በመጥራት፣ በአጠቃላይ የሄደብህን ንብረት በሄደበት መንገድ ለመመለስ የዐማራዉ መጥፋት የኢትዮጵያ መጥፋት፣የኢትዮጵያ መጥፋትም የዐማራዉ መጥፋት መሆኑ የተረዱ ኢትዮጵያዊያንን አስተባብሮ አጠናክሮ አሁን ወቅቱ የጣለብህን አገር አድን ኃላፊነት በትጋት እና በብቃት እንደምትወጣ በኢትዮጵያዊነትህ ያለማወላወል የሚያምንህ እና የሚያዉቅህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ አደራዉን ጥሎብሀል፡፡ ሙላት በላይ