የቋሳ ምድር …መኮንን ብሩ`

ከሁለቱም ኮረኔሎች ሶስት ሺህ ዓመታት በፊት ነበር ይህች ምድር የቋሳና የደም ምድር ትሆን ዘንድ የተሰራችዉ። በዘመኗ የብዙዎችን ስቃይ አይታለች። የብዙዎችንም የሞት ጣር እና ሴቃ ሰምታለች። በወሃ ጥም ዓመቱን ሙሉ የሚንገላታዉ የደረቀዉ አፈሯና ያገጠጠዉ ኮረብታዎቿ ጥማታቸዉን በሰዉ ልጆች ደም የሚያረጥቡ ይመስል የብዙ መቶ ሺዎችን ደም ጠጥተዋል። አሁንም እየጠጡ አሉ።

ያዋለድኩትን ልጅ ካልበላሁ የሚለዉ ምቀኝነቷና ክፋቷ መቼና ለምን እንደተፈጠረ ብዙ ጥናት ቢያስፈልገዉም ከሶስት ሺህ ዓመታት በላይ በሚዘልቅ ዘመኗ አሁንም መሬቷ ለመድረቁና ኮረብታዎቿ ለማግጠጣቸዉ ምክንያቱ ለዘመናት በዉስጧ የቋጠረችዉ ቋሳ ሰላም እንድታጣ እያደረጋት መሆኑን ከጦርነት ታሪኳ መረዳት ይቻላል።

ዘፈኗ ጭካኔ፣ ባሕሏም ጦርነት፣ ወግና ትርክቷም ቋሳና የሰዉ ደም መሆኑን ከዮዲት ጉዲት እስከ እምበር ተጋዳላይ ወያኔ ድረስ ያለዉን ታሪኳን መቃኘት ይቻላል። ስለዚህም መጥበብና ማነስ እርግማኗ ሆኖ አለ። በአንድ ዘመን ከባሕረ ነጋሽ እስከ አዱሊስ እና በርበራ ድረስ ሰፊ ተፅህኖ የነበራት ምድር ዛሬ በኤርትራና እራሷ ባዋለደቻች ኢትዮጵያ ጭብጥ ዉስጥ ገብታ በርሃብ እና ጥማት የምትንገላታ የቋሳና የደም ምድር ለመሆን መምረጧ የአምላክ ቁጣ እንጂ ምን ሊባል ይችላል።

ትግራይ ዛሬም ወደ ጥልቅ ማነሷና መጥፋቷ መሄዷን ልታቆም የመረጠች አይመስልም። ዛሬም መዉጪያ መግቢያ የሌላት እንዲሁም የደረቀ አፈርና ያገጠጠ ድንጋይ ብቻ የታቀፈች ምድር ብትሆንም ዛሬም የሰዉ ልጆችን በጎዳና አሰልፋ እሳት የሚተፉ አፈሙዝን በመደቀን ዉሃ የተጠማዉ ምድሯን ለአፍታም ልታርስ አቅም እንዳላት እየተናዘዘች አለች። ቀድሞም የቋሳ ምድር ነችና አሁንም ቋሳን ልትዉልድና ይበልጥ መቃብሯን ልትቆፍር ትዉተረተራለች።

የትግራይ ጎበዝ ሆይ … ትናንት የወርቅ ጥርሱን ነቅለህ ከሀገር ያባረርከዉ ኤርትራዊ አልበቃህ ብሎ ዛሬ ደግሞ በአደባባይ ክብሩን በረገጥከዉ ኢትዮጵያዊ መሐል እንደ ቆዳ ለምጥ ተቀምጠህ መሆኑን አለመረዳት የእርግማን ዉጤት ነዉና እናዝናለን::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዜብ እርግጫሽ አልበዛም?

የትግራይ ጎበዝ ሆይ …የሃያ ሰባቱ የሰቆቃ ዓመታት አልበቃ ብሎ አፋሩን፣ ጋምቤላዉን፣ ኮንሶዉን፣ አደሬዉን፣ አማራዉን፣ ኦሮሞዉን፣ ጋሞዉን ሱማሌዉን፣ አድያዉን እና ሌላዉንም ሀገር ሰላም ብሎ በተኛበ የተማረከዉን ያንን ኢትዮጵያዊ ወታደር በቋሳ ምድር መቀሌ ጎዳና አሰልፈህ ስትሳለቅበት በሚመለከት ኢትዮጵያዊ ዉስጥ እየጫርክ ያለኸዉ በቀላሉ ሊጠፋ የማይችል የመጥፊያህን የበቀል እሳት መሆኑ ሊገባህ አለመቻሉ በራሱ እርግማን ነዉና እናዝናለን።

የትግራይ ጎበዝ ሆይ …. ዉሃ የሌለዉ ጪንጫ ምድር ሆናችሁ እስክትቀሩ ዘመናችሁን ሁሉ የአፈሙዝ እና የእርግማን በመሆኑ ሊታዘንላችሁ ቢገባም መጥበባችሁንና ማነሳችሁን ግን መግታት አልተቻለምና እናዝናለን።

ኢትዮጵያ ለምለም ሆና ላለምልማችሁ ባለች ልትበታትኗት ደጋግማችሁ አሴራችሁ። ከሶስት አስርተ ዓመታት በፊት በደርግ ጭካኔ የተዋከበዉን ምስኪን ሕዝብ ይበልጥ አወናብዳችሁና አታላችሁ መንበረ ስልጣኑ ላይ ብትቀመጡም ሀገር ምድሩን አረከሳችሁ። በየከተማዉ ሴቶች በእራቁታቸዉ እስኪደንሱ ሴትነትን አልከሰከሳችሁ፣ ክብር ያለዉን ትምህርትና የትምህርት ማዕረግ አራከሳችሁ፣ ዘመኑን ሙሉ ለሀገሩ ይታገል የነበረን ወታደር በየጎዳናዉ ይለምን ዘንድ አዋረዳችሁ፣ ንፁሐንን በጠራራ ፀሐይ ገድላችሁና ዘርፋችሁ የሁሉ ባለቤት ሆናችሁ። ጄኔራል እናንተ፣ ባለፎቅ እናንተ፣ አምባሳደር እናንተ፣ ሁሉም ትልቅነት የእናንተ አድርጋችሁ ቅድስት በምንላት ሀገራችን ላይ ሳጥናኤላዊ ምግባራችሁን ብቻ ሳይሆን ምልክቱንም በጫንቃችን ላይ አሸከማችሁ።

ያኔ ምናልባት ከእርግማን በፊት አንድ ሺህ ዓመታት በሚዘልቀዉ ታላቅነት አክሱም ከመቀሌ ሳይሆን ከማዛበርን ማዕከሏ አድርጋ በሁሉም አቅጣጫዎች እስከ የመንና ጅቡቲ ድረስ ገናና መሆን ችላ ነበር። ዘመናት ሲያልፉ ግን ከዛግዌ ስርዎ መንግስት ይሁን ከሰሎሞናዊያን ጋር በተፈጠረ ቁርሾ በዉስጧ ልትቋጥር በቻለችዉ ቋሳዋ ዘመኗን ሁሉ ጠልፎ እየጣላት ይህዉ አሁንም ዓለም ስለመራቧ ይተርክ ዘንድ ዕዳዉ ልትሆንበት አንሳለች።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አስተያየት፣ በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” መጽሀፍ ላይ

አክሱም ከዛሬ ሶስት ሺህ ዓመታት ግድም ከሁሉ የቀደመች ነበረች። እሷ ገናና በነበረችበት በዚያ ዘመን ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ አፍሪካ ወዘተ የሚባሉ ሀገሮች ወይም አህጉራት በዉል አይታወቁም። አሁን ግን በቋሳዋ ተጠላልፋና ወድቃ ሁሉም ስለሷ ይጮሃል። ከሁሉም በፊት በስልጣኔ ብቅ ብትልም ይቅር መባባልን ባሕሏ ማድረግ ባለመፍቀዷ ዛሬም እርኩሳትን በመረጡ እምበር ተጋዳዮቿ የማታ ማታ ሰቆቃ የሆነች ምድር መሆኗ ቀጥሏል። ትግራይ።

ዘፈኗ ጭካኔ፣ ባሕሏም ጦርነት፣ ወግና ትርክቷም ቋሳና የሰዉ ደም መሆኑን ከዮዲት ጉዲት እስከ ወያኔ ድረስ ያለዉን ታሪኳን መቃኘት ይቻላል። በአንድ ወቅት ከባሕረ ነጋሽ እስከ አዱሊስ እና በርበራ ድረስ ሰፊ ተፅህኖ የነበራት ምድር ዛሬ በኤርትራና እራሷ ባዋለደቻች ኢትዮጵያ ጭብጥ ዉስጥ ብትገባም ዛሬም የወታደርን ክብር ማጉደፏ የእርግማን እና የዓጥያት ዉጤት ካልሆነ ከምን ሊባል ይችላል? …..

አንሶ የማሳነስ ዓጥያት፣ …..የእርኩሰት ዓጥያት፣ ….ጳጳስ በጳጳስ ላይ የማንገስ ዓጥያት፣ …..ሀገር ወደብ አልባ የማድረግ ዓጥያት፣ …..የወንድ ብልት ላይ ኮዳ የማንጠልጠል ዓጥያት፣ …..ከሴት አልፎ ወንድን ልጅ የመገናኘት ዓጥያት፣ ……እናትን በልጇ እሬሳ ላይ አስገድዶ የማስቀመጥ ዓጥያት …… አዎን ይህ ሁሉ ኃጥያት አልበቃ ብሎ አሁንም በመቀሌ ጎዳና ላይ ዓጥያት እያንቀለቀላቸዉ አለ። መሰረዩን ግን የሚፈልጉ አይመስልምና ዙሪያዉን ቢከበቡም እምበር ተጋዳላይ ማለቱን አላቆሙም።…. ከሀገር አልፈዉም በሰዉ ሀገር በሴት እርቃን ገላ በኃጢያት መንቦራጨቁን በቃን አላሉም። ስለዚህ እኛም ስለቤታችን ሰላምና ፅድቅ ስንል ከእነሱና ከኃጢያታቸው ፊታችንን ልናዞር ግድ ይላል ….

ኢትዮጵያ ትቅደም

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለዋሊያዎች አጭር መልእክት አለኝ - ይድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን!

/ር መኮንን ብሩ።

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share