የንጋት ጊዜ ተቃርቧል ! ጮራው በቅርቡ ይፈነጥቃል ! – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

NAIROBI, Kenya (AP) — Ethiopia’s leaders in closed-door talks with a European Union special envoy earlier this year said “they are going to wipe out the Tigrayans for 100 years,” the envoy said this week, warning that such an aim “looks for us like ethnic cleansing.”

( Pekka Haavisto, Finlands foreign minister )

የተከበሩት ሐቪስቶ ለአፍሪካዊው ሰው ክብር ቢኖራቸው ኖሮ ይህንን ቅጥፈት በድፍረት በአደባባይ አይናገሩም ነበር ፡፡

የግለሰብ ሥብሥብ ህዝብ ነው ። ግለሰብ ደግሞ ሰው ነው ። ሌላ ምንም አይደለም ።ሐቪስቶም ሰው ነው ። እንደማናችንም ። ባዮሎጂካል ፍጥረቱ ከቶም ከእኛ የተለየ አይደለም ። ከእኛ የሚለየው ከላይ ባነበባችሁት ሂትለራዊ   የውሸት ፕሮፖጋንዳው ብቻ ነው ። (” በመቶ ዓመታት ውስጥ ፣ የትግራይን ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት እቅድ አውጥተው  የሚንቀሳቀሱ መሪዎች ኢትዮጵያ አሏት ፡፡ ” ብሎ በድፍረት ቅጥፈት የተናገረው ፡፡ )

የተከበሩ ፒኬካ ሐቪሰቶ ሆይ !

ሰው + ሰው + ሰው.. =ህዝብ

ሰው + ሰው = ባልና ሚስት  ይመሰርታል። ሰው+ሰው + ሰው …በጋብቻ ዝምድና ይፈጥራል ።ሰው + ሰው + ሰው ይወልዳልና ዘሩን ይደባልቃል። እንዲህ ፣እንዲያ እያለ ዓለምን ይሞላል ። እኛም ኢትዮጵያዊያን እንዲህ ፣እንዲያ እያልን የበዛን ነን ፡፡

” ሰው በህይወት ቆይታው የተደላደለ ኑሮ ለመኖር ሲል ተስማምቶ ወይም ሳይሥማማ ከሰው ጋር ይኖራል ። ከተስማማው ጋር ይዘልቃል። ያልተሥማማውን ተሰናብቶ ወይም ሳይሰናበት ተለይቶ ደግመኛ ላያገኘው ይሰናበተዋል። እህል ውሃው ከፈቀደለት ጋር ባደረሰው ከተማና ገጠር ኑሮን” ሀ ” ብሎ ይጀምራል። እሥከ “ፐ”ም ይዘልቃል። ወይም ” ሁ ” ሳይል “እልፍ ካላሉ እልፍ አይገኝም ። ” በቃኝ ብሎ ” እግሩ ወደ ወሰደው ይነጉዳል ። እንዲሂ እየተከራተተ…ከአገር ፣ አገር እየዞረ ሣለ ፣ ወገቡን ለማሳረፍ ጋደም ባለበት  እሥከወዲያኘው ሊያንቀላፋ ይችላል ። ” ይህ አንዱ የህይወት ገፀታ ነው ፡፡

ሰው + ሰው + ሰው = ህዝብ የተባለው፣  በዛሬው ዓለም በማህበራዊ ኑሮ ውሥጥ ፣በኢኮኖሚ ና በፖለቲካ ጉዳዮች ወሰጥ በትብብር የሚሰራ ከመሆኑም በላይ ፣ ከአብሮነቱ ተነጥሎ መድመቅ የማይችል ነው።  ይህ ቢታወቅም የበለፀጉት አገራት መሪዎች የተገነዘቡትን የጠንካራ መንግሥት መኖር አሥፈላጊነትን ያልበለፀጉት አገራት ሥላልተገነዘቡ ፣ወይም እንዳይገነዘቡ በበለፀጉት አገሮች የተለያየ ጫና እና ሤራ ሥለሚደረግባቸው ፤ ጥቂት ቡድኖች ፣ በህዝብ ሥም ሥልጣን ሲይዙ ፣ በህዝብ ሥም ለመበዝበዝ እና በግል  ለመበልፀግ ይጥራሉ እንጂ  ፣ አገር ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ፣ ጠንካራ የህግ አሥከባሪ ፖሊስ ፣ ጠንካራ የፍትህ ተቋማት ፣ ጠንካራ የሲቪክ ድርጅቶች ና ነፃ ፕሬስ እንዲኖራ በቅንነት  ተገተው አይሰሩም ።  …

ተጨማሪ ያንብቡ:  በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ

እነዚህ ተቋማት በድህነታችን ሰበብ  በወጉ እንዳይደራጁና እንዳይደረጁ ይደረጋል ፡፡  ብዙዎቹ ፣ የአፍሪካ መንግሥታት የአውሮፖ ና የአሜሪካ መንግሥታት ጥገኛ መሆናቸው ይታወቃል ። ጥቂቶች ደግሞ ለመልማት እና ለመበልፀግ ከሁሉም ባለፀጋ አገራት ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁነታቸውን እያሳዩ ነው ።  ኢትዮጵያ በተለይ ፣   በተግባር ከሚያለሟት ባለፀጋ መንግሥታት ጋራ  አብራ እየሰራች ነው ። ጎላ ባለ መልኩ ደግሞ ከቻይና መንግሥት ጋር ።  ከቻይና መንግሥትና ህዝብ ጋር ያላት የልማት ግንኙነት እጅግ ከፍ ያለ እና ተጨባጭ የልማት  ውጤትን ያሥገኘ ነው ።

ይህ የልማት ግንኙነታችን ብዝበዛን ለለመዱ ለአንዳንድ ዘረኛ ከበርቴ ነጮች  የሚያሥቆጭና የሚያናድድ ነው። ብዝበዛቸውም ሥለሚቋረጥ ፣ ኢትዮጵያ እንድትበለፅግ ከቶም አይፈልጉም። ። የኢትዮጵያን ሀብት ዘርፈው በእነሱ ቱጃሮች ባንክ ያሥቀመጡትን ሌቦች  በትግራይ ህዝብ ሥም ሲደግፉና አሸባሪውን ወያኔ  በሂትለራዊ ፕሮፖጋንዳ ሲደግፉ ይስተዋላል ።

ዛሬም ይህ አውዳሚ ሂትለራዊ ፕሮፖጋንዳ በፈጣጣ ወጥቷል። ያውም በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ልኡክ በሆኑት በፊላንዱ የውጪ ጉዳይ ሚኒሥቴር በፒኬካ ሃቪስቶ ተለቆብናል ። ፕሮፖጋንዳውም ፣

” በ100 ዓመት ውስጥ የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት እንደሚሰሩ ፣ ይፋ ባልሆነ ውይይት ወቅት የኢትዮጵያ መሪዎች ነግረውኛል  ፡፡ ” የሚል ቅጥፈትን ያዘለ እጅግ አደገኛና አሳፋሪ ፕሮፖጋንዳ ነው ፡፡ የአውሮፓ ህብርት ልዩ ልዑኩ በአደባባይ ምላሳቸውን ሳያዳልጣቸው የተናገሩት ፡፡ እንጊሊዘኛው ከላይ አለላችሁ ፡፡

ለመሆኑ ማነው የትግራይን ህዝብ የሚያጠፋው ? እንዴት ና መቼ ነው ጄኖሳይድ የሚፈፅመው ? እንዴት ነው እኔ በጋብቻ የተዛመድኩትን ፤ ቤተሰብ ያፈራሁበትን ከሰባት ትውልድ የዘለለ  ዝምድና ያለኝን ሰው በትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪነቱ ብቻ አምሳያዬን  ላጠፋው የምነሰው ? ኢትዮጵያዊ እንዲህ ዓይነት የወረደ ምግባር አለው ብሎ ማሰብ በራሱ ያናድዳል ። ( የኢነተር ሃምዊ እቅድ በነማን ነው የወጣው ? ማን ነው በወንድማማቾች መካከል ፀብን እየዘራ ያለው ? “ሥንተዋወቅ አንተናነቅ ”

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ ያለው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ነውን?  ክፍል አንድ፣  - ይገረም አለሙ

ማንም ኢትዮጵያዊ ይህንን የወራዶች ተግባር አይፈፅምም ። ፈጣሪን የካዱት በተግባር አሸባሪነታቸውን ያሳዩ ጥቂት የህወሓት ዓባላት… የዳቢሎስ ልጅነታቸውን የራሳቸውን ጓደኞች አንገት በመቁረጥ አሳይተውናል። በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አሥከሬን ላይም መኪና መንዳታቸውን ፤  ዩኒፎርማቸውን ገፈው ራቁታቸውን  ሜዳ ላይ አሥጥተዋል ፡፡ ከቅጣት ላያመልጡ ነገር ፣ ፈርጥጠው በረሃ መግባታቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው ።

ትላንትም ሆነ ዛሬ እያደረጉት ያለው እኩይ ድርጊት የትግራይን ህዝብ ከድህነት ፣ ከችግርና ከችጋር የሚያላቅቅ ከቶም አይደለም ። የትግራይ ህዝብ ዛሬም በፍርሃት ቆፈን ውሥጥ ነው ያለው ። ” እነዚህ ዲያብሎስች ዳግመኛ ለሥልጣን ከበቁ በተለመደው አንድ ለአምሥት ጥርነፋቸው ተጠቅመው ፣ እነሱን መቃወሜን ከሰሙ እዛው ህዝብ ፊት ይረሽኑኛል። ” ብሎ በማሰብ ዝምታ ወርቅ ነው ብሏል ። እናም ከፍርሃት የተነሳ ዝምታን መርጧል ።

ይህ ዝምታው ግን አንድ ቀን ይሰበራል ። ” ከመላው ኢትዮጵያዊ ወንድሜ ጋር በጋራ ልበልፅግ ። በዜግነቴ ያሻኝ የኢትዮጵያ ክልል ሄጄ እንድሰራ የሚያሥችል መንግሥት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ ። ዘረኝነት ይውደም ! ” የሚልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ።…

የንጋት ጊዜ ተቃርቧል ። ጭለማው መበርታቱ ንጋትን ያመላክታል ። ጮራው በቅርቡ ይፈነጥቃል ። የትርምስ ና የሤራ ጊዜም ያልፋል ።  ፈረንጅም ከእኛ በተዘረፈው ዶላር ተገዝቶ ፣ በገንጣዩ ህወሃት ባንዲራ አፉን መሸበቡ በታሪክ እንደ ትዝብት ይወሳል  ።

ሐቪስቶም በውሸቱ እሥከሰባት ትውልዱ ያፍራል ። በግልፅ በአደባባይ የተናገረው  ሂትለራዊው  ፕሮፖጋንዳው  ከሞተም በኋላ በታሪክ አይረሳም ።    ሰውየው  የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ታላቅነት ለመቀበል የማይፈልግ ዘረኛ መሆኑ የቅጥፈት ንግግሩ ያሳብቃል ፡፡   ይህንን አውዳሚ ሂትለራዊ ፕሮፖጋንዳ  ምላሱን ሳያደናቅፈው በድፍረት የተናገረው ዘረኛ በመሆኑ ነው  ። በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የሚገኝ  አንድ የተከበረ የመንግሥት ሹመኛ በእንዲህ ዓይነት መልኩ ሲዋሽ አደገኝነቱን ከቶም ሳይገነዘብ ቀርቶ አይመስለኝም ።   ይዋሻል ተብሎ ከማይጠበቅ አንድ የአውሮፖ ህብረት ባለሥልጣን አንደበት ይሄ አሥደንጋጭ ቅጥፈት  መውጣቱ በራሱ እጅግ አደገኛ ነው  ። ይህ ባለሥልጣን የትግራይ ክልል ተወላጆች በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ መሆናቸውን ያላስተዋለ ከመሆኑም በላይ ፣ የትግራይ ህዝብ በራሱ ድብልቅ እና ከአማራ ና ከደቡብ ጋራ የተጋመደ ዝምድና እንዳለው ታሪክን አንብቦ ያልተረዳ ና የሰውን ወንድማማችነት ና እህትአማማችነት የማይቀበል ” በብዢታ የተሞላ ህሊና ያለው ነው  ። ” (በትሁት ቃል ።) …

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጦርነቱ አለቀ የሚባለው መቼና የት ላይ ሲደርስ ነው? - ነፃነት ዘለቀ

የተከበረው ሐቪሥቶ በዚህ በብዢታ  በተሞላ ህሊናው፣ ” ባልበላውም እበትነዋለሁ ” በሚል አሰተሳሰብ ተነሳስቶ ፤ ” የኢትዮጵያን መንግሥት መልካም ሥም ለማጠልሸት በሂትለራዊ ፕሮፖጋንዳ ፣ የትግራይ ህዝብ በመቶ ዓመት ይጠፋል ። ” መንግሥት ብሏል ። በማለት አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት የመቶ ዓመት እቅድ አውጪ አድርጎ መቁጠሩ በራሱ የሚያሥተዛዝብ ነው ። ውሸቱም እዚህ ላይ ነው የሚጋለጠው ። አንድ መንግሥት ሥራዬ ብሎ ሰውን ለማጥፋት እቅድ አያወጣም ።

ምናልባት የኢትዮጵያ መንግስት  ለሐቪሥቶ ሊነግረው ይችላል ብዬ የማስበው ፤” የዛሬ መቶ ዓመት ፊላንዶች ና መላው አውሮፓ ፣ በሥደተኝነት ወደ ኢትዮጵያ ገብታችሁ የመኖሪያ ፍቃድ እንዲሰጣችሁ ትለምናላችሁ። ” የሚለውን አናዳጅ ቃል ነው ፡፡ መቼም አንዳንድ ዘረኛ ነጭ ፣ ጥቁር እድሜ ልኩን ተበዝባዥ ሆኖ እንዲኖር የማይፈነቅለው ዲንጋይ የለምና ” የዚህን የሤራ ዲንጋይ አይረቤነት በብልጽግናችን እናረጋግጥልህአለን ፡፡ ” በማለት መንግስት ለአውሮፓ ተገቢ ያልሆነ ጫና አልንበረከክም ማለቱ የተከበረውን የአውሮፓ መልእከተኛ ሳያስኮርፈው የቀረ አይመስለኝም ፡፡

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.