ሰሞኑን ሽመልስ አብዲሣና አቢይ አህመድ በአማራ ሕዝቦች ላይ እሽቅንድር ብለዋል፡፡ ማለቴ በአማራ ሕዝብ ላይ፡፡ የዘገምተኛው የአማራ “ፕሬዝደንት” አገኘሁ ተሻገር አነጋገር ተጋብቶብኝ ነውና ይቅርታ፡፡ እነዚህ የአማራ መሪዎች መጨረሻቸው እየታየኝ እንዴት አንጀቴ እንደሚንሰፈሰፍላቸው አትጠይቁኝ፡፡ ሰው የፈለገውን ያህል ሆዳም ቢሆን፤ የፈለገውን ያህል ባይማርና የደንቆሮ ደንቆሮ ቢሆን፣ የፈለገውን ያህል ደደብ ቢሆን … ለይምሰል መሆኑ እየታወቀም እንኳን እወክለዋለሁ የሚለውን ሕዝብ በዚህ ደረጃ ለሰይጣኖች አሳልፎ ይሰጣል ተብሎ አይገመትም፡፡ የጥቁሮችን ከባርነት ነፃ የመውጣት ትግል የተቀላቀሉ ነጮች ሣይቀሩ ለጥቁሮች ነፃነት ከምር ነበር የታገሉት፡፡ እነዚህ ግን ምንም እንኳን አንዳንዶቹ “ክልስ” ቢሆኑም የአማራን ሥነ ልቦናና ቋንቋ ለምደው ሲያበቁ፣ የአማራን ባህልና ወግ ጠንቅቀው በማወቅ በውስጡ ከተመላለሱበት በኋላ አማራን ክደው ለጠላት ማደራቸው ይገርማሉ፡፡ ብአዴኖች ጥቁር ውሻ ይውለዱ!!!
አፄ ኃ/ሥላሤ ለሥራ ጉብኝት ወደ ቻይና አቀኑ አሉ፡፡ ቻይና ደግሞ ያኔም ሆነ አሁን ሀገሯን ለማልማት በሥራ ትወጠር ነበርና አንድም የረባ ባለሥልጣን ሳይቀበላቸው ይቀራል፡፡ማታ በተኙበት ወቅት ታዲያ የወቅቱ መሪ ማኦ ዜዱንግ ሊጎበኛቸው በራቸውን ያንኳኳል፡፡ ያኔ አፄው “ማን ልበል?” ይላሉ፡፡ ማኦም በኩራት “እኔ ማኦ ነኝ!” ይላል፡፡ እሳቸውም ተናደውበት ነበርና “አሁን ከመሸ የምን ሚያው ነው? ቀን የሌለ ድመት አሁን ከመሸ ከየት መጣ?…” በማለት አልከፍትለት ይላሉ፡፡ ንዴታቸውን በዚህ መልሰው እንቅልፋቸውን በሰላም ሲደቁ እንዳደሩ “ታሪክ” ይመሰክራል፡፡
ደግሞ ለጨዋታና ለቀልድ – ሌላም ልጨምርልህ፡፡ አለቃ ገ/ሃና እንዲህ ብለዋል፡፡ አንዲት እንጨት ይሁን ውኃ የተሸከመችን ሴት ከኋላዋ እየተከተሉ ይሄዱ ነበር አሉ – አለቃ፡፡ ሴትዮዋ እንኳንስ አለቃ ገ/ሃናን የመሰለ ነገረኛ ሰው ሌላም ሰው የተከተላት አልመሰላትምና ፈሷን ዘረጥ ታደርግ ነበር፡፡ ጥቂት እንደሄደች ዘወር ስትል አለቃን አየቻቸው፡፡ ያኔ ድንግጥ ትልና “ውይ አለቃ! መቼ መጡ?” ብላ ትጠይቃቸዋለች፡፡ እርሳቸውም “ከመጀመሪያው ደወል ጀምሮ እዚሁ ነበርኩ” ብለው አሳፈሯት፡፡ የለም የለም … ይህኛውን አልነበረም ለማለት የፈለግሁት፡፡ አዎ፤ ትዝ አለኝ፡፡ አንዲት ሴት የአለቃን አጠገቧ መኖር ሳታውቅ ልክ እንደቅድሟ ሴት ትፈሳለች አሉ – ዘወር ስትል ግን አለቃ አሉ፡፡ ያኔ ምንተፍረቷን በአፏ “ጡጥ!” ታደርግና ፈሷን በጡጥታ ልታስመስል ትሞክራለች፡፡ አያ አለቃ ግን “ነቄ” ብለዋልና “ያቺ ሌላ ይቺ ሌላ” በማለት እውነቱን ከውሸቱ መለየታቸውን ገለጹላት አሉ፡፡ አቢይና ሽመልስ ሰሞኑን አማራን ለማታለል የማይፈነቅሉት ድንጋይ አጥተዋል፡፡ በአማራ ምድር የሚመረቅ ነገር ቢጠፋ በሃያና ሰላሣ ሽህ ብር የተገነባ የውኃ ቦይ መመረቅ ይዘዋል – በኦሮምያ ፋብሪካ ሲመረቅ በአማራ መስኖ ይመረቃል፣ ምንነቱና ሥራው የማይታወቅ የመሠረት ድንጋይም ይጣላል፡፡ ሰው ለሥልጣን ሲል እስከዚህ መውረዱ በውነቱ ሥራ አጥነት እስከምን ደረጃ ሊያቀል እንደሚችል በበኩሌ ተረድቻለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ነፃነት በሚመጣበት ወቅት በቅድሚያ ማድረግ የሚኖርብን ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ መጣር ነው፡፡ አለበለዚያ ሥራ ፈቱና ሥራ አጡ ሁሉ ወደፓለቲካው እየገባ ሀገራችንን ልክ እንዳሁኑ ሲያምሳት መኖሩ ነው፡፡
በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የአማራ ክልል መሪ እየመሰለኝ የመጣው ሽመልስ አብዲሣም ሆነ አቢይ አህመድ አማራን ለማነሁለል በብአዴን በኩል እያደረጉት ያለው ጥረት ሁሉ ቢሳካላቸው ደስ ባለኝ፤ ኦሮሙማን ከግብ ለማድረስ እየሄዱበት ያለው የተንኮልና የማስመሰል እንዲሁም የሤራ ፖለቲካ ግልብ አካሄድ እንደሰው እንዳዝንላቸው እየገፋፋኝ ነው – በልጅነት የሚገኝ ሥልጣን እንደሚያሳብድ ከነሱ መገንዘብ አያቅትም፡፡ አንድ ሰው በሥልጣን ሱስና በግል ፍላጎቶች ስኬት እንዲህ ካበደ ለተወሰነ ጊዜ ድል ቢቀዳጅና የሚሆነውን ማየት ቢቻል ብዙም ክፋት የለውም፡፡
ግን ጥረታቸው ሁሉ ከንቱ ነው – ለነሱ ዕኩይ ዓላማ ስኬት የማዘኔ ምሥጢርም ይሄው ነው፡፡ አማራ ሁሉ ተታሎ ምርጫውን እነዚህ ውሾች እንዲያሸንፉ ዕድሉን ቢሰጥ እንኳን እነዚያ የታረዱት አማሮች ደማቸው በጽርሃ አርያም ይጮሃልና የሚሆነው ሁሉ ከመሆን አይዘልም – ልፉ ቢላቸው ነው እንዲህ የሚቅነዘነዙት፡፡ በነሱ ቤት ብልጥ ሆነው ሞተዋል፡፡ ሰውን ማታለል ይቻላል፤ ቀላልም ነው፡፡ እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔርን ግን በፍጹም ማታለል አይቻልም፡፡ ለነገሩ ምርጫውም የተበላ ዕቁብ ነው፤ ከአንበሣ ጉሮሮ ማንም ቢሆን ሥጋ ሊቀማ አይችልም፤ እነእንቶኔም አጃቢ ናቸው፡፡
አቢይ አህመድ እጅግ ብዙ ቢሊዮን ብር ለኦሮሙማ ልማት ከንግድ ባንክ እንዲወጣ ካደረገ በኋላ ዕዳው እንዲሰረዝ ማድረጉን እየሰማን ነው፡፡ በዚህም መቃብሩን አርቆ እየቆፈረ ነው፡፡ ጥቂት ወራትን እንታገስ፡፡ መጥፊያ(ቸ)ው ደርሷል፡፡ ትንቢት ምናምን አይደለም፤ የሚታይ ገሃድ እውነት ስለሆነ እንጂ፡፡
እውነት እውነት እልሃለሁ – የሚጠየፉትንና በእግራቸው የሚረግጡትን የሚያስረግጡትንም የኢትዮጵያ ባንዲራ – አማራን በማስደሰት ያታለሉት መስሏቸው – ልብሳቸው ላይ ማስጠለፍ ቀርቶ ሰውነታቸው ላይ ቢያስነቅሱትም ከእንግዲህ ሽመልስና አቢይ በኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያ ልብ ይገባሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ በዕውቀት ከነሱ ዕጥፍ ድርብ የምትበልጠዋ ሴተኛ አዳሪ እንኳን “አጭበርባሪ አይተኛኝም” ስትል እነሱን መሰል ገሪባዎችን ልክ ልካቸውን ነግራቸዋለች፡፡ ሕዝብን ንቀታቸው ግን ከድድብናቸውም በላይ ነው የሆነብኝ፡፡ ለነገሩ ሲያንሱን ነው! በቁማችን ሞተናል’ኮ፡፡ ቢበቃኝስ ጃል?
ማሳሰቢያ – አምባቸው ደጀኔ የነበርኩት ሰውዬ ከዛሬ ጀምሮ የአባቴን ስም ወደ ዓለሙ መለወጤን የምገልጽላችሁ ከከፍተኛ ይቅርታ ጋር ነው፡፡ ዱሮውንም ይህንን ስያሜ መጠቀም የፈለግሁት የአውራጃየ አስተዳዳሪ የነበረውን አምባቸው ዓለሙን ለማስታወስ ነበር፡፡ ግን “ካረጁ አይበጁ” እንዲሉ ሆነና በስህተት በሌላ ሰው አባት ስጠራ ሰነበትኩ፡፡ ከዛሬ ነገ አስተካክላለሁ ስል ብዙ ቆየሁ፡፡ አምባቸው ዓለሙ ቆፍጣና የየጁ አውራጃ አስተዳዳሪ ነበር፡፡ ሳይሞት የቀረ አይመስለኝምና ነፍሱን በገነት ያኑርልኝ፡፡