“ባለቤት ካልጮኸ ገላጋይ አይደርስም ” – ማላጅ

የህዝቦች የዘመናት ብሶት እና ጩኸት እንደቁራ ጩኸት ተቆትሯል ፤ የመንግስት ዝምታ ለዘመናት በጥፋተኞች ለተፈፀሙ እና እየሆኑ ላሉት የዜጎች ህይዎት መመሰቃቀል፣ መፈናቀል ፣ሞት እና ስደት …የመሳሰሉት ጥፋቶች  በወቅቱ  ባለቤት አለመስጠት እና ተጠያቂ አለማድረግ ዛሬ ግፈኞች  ተገፊ ሆነዉ የተገፉት እና የተጠቁት ኢትዮጵያ ፣ ህዝብ እና መንግስት ገፊ ፣ ተስፋፊ፣ አጥፊ …..ለመባል በፍረደ ገምድሎች ዳር ዳር መባሉን መስማት ያሳዝናል፡፡

ኢትዮጵያ እና ህዝቧ የዚህ ዘመን አስከፊ መከራ እና ግፍ ያስተናገዱበት ዓመታት በሰባዊ መብት ጥሰት ፣ በጅምላ እና ለይቶ ማሳደድ ፣ መጋጫት እና የዘር ፍጅት የተከናወነበት የ፪ አስርተ ዓመታት በላይ ደርጊት በጊዜዉ እና በወቅቱ አልተገለፀም  ይህም ለወንጀለኞች የድል ድል ሆኖ ተቆጥሯል ፤ ተወስዷል፡፡

ወንጀለኞችን ተበዳይ በማድረግ  ከተጠያቂነት  ወደ ጠያቂ እና ተጠቂ  ወደ መሆን ጩኸቴን ቀሙኝ ዓለምን የማደናገር  የቅስቀሳ እና ወቀሳ ዉትወታ (propaganda ) ጊዜያዊ መደላደል  በመፍጠር አገራችንን እና ህዝቧን አይከፍሉት ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል ፡፡

በተለይም መንግስት ለ  ከግማሽ ምዕተ ዓመት  በላይ የኢትዮጵያን አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማዛባት በቅርብ እና በሩቅ ባላንጣዎች የተዘጋጁ ወጥመዶች እና የተቀፈሩ ጉድጓዶች ከመበጣጠስ እና ከመድፈን ይልቅ  ማለባበስ አሁን ለምንገኝበት የዉጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ፈር ቀዷል፡፡

ቢረፍድም  ኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያ አንድ አስከሆኑ ድረስ  የማይወጡት አቀበት እና የማይሸገሩት ችግር አይኖርም ፡፡ 

ስለዚህ አሁንም ፡-

፩) በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ህዝባዊ አንድነት ላይ የተደረገዉን ክህደት ቅድመ እና ድህረ ኢህዴግ በግልፅ ለዓለም ማህበረሰብ ማሳወቅ ፣

፪) በ፳፯ ዓመት ዉስጥ  ብሄራዊ አንድነትን ለማናጋት በግፈኞች እና ጎጠኞች አስተዳደር ለዓመታት የተሰራጨዉ የጠሰሳተ ትርክት ስህተት እና ወንጀል እንደነበር ማጋለጥ፣

፫) በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ የደረሰዉን ክህደት እና ጥቃት የድርጊቱን ባለቤት (ፀረ ኢትዮጵያዉያንን) በግልፅ እና ፈጣን መረጃ ተጠያቂ ማድረግ፣

፬) ትህነግ ከፅንሰት አስከ ዉድቀት  ዋና ማታገያ እና ማተላያ በማድረግ በባላንጣነት የፈረጃቸዉን ኢትዮጵያን ፣ ኢትዮጵዊነትን፣ ቤተ ክርስቲያንን እና ኢትዮጵያዊነት ማንነትን አቀንቃኝ የሚለዉን እና በታሪካዊ ጠላትነት የሚፈርጀዉን ማህበረሰብ “ዓማራ ” ብሎ  በጅምላ ያከናወነዉን ማጥላለት፣ ጥፋት፣ ስደት ፣ ሞት እና ዕንግልት  በዘር ፍጅት የሚጠየቅበትን ስርዓት መመስረት እና ማስፈፀም ፣

፭) በኢትዮጵያ የፈደራል ስርዓት እና የአስተዳደር ወሰን ብዙዉን ህዝብ ባላሰተፈ እና ይሁንታ ባላካተተ የክልል አስተዳደር ነባሩን ባይተዋር በማድረግ በገዛ አገር ላይ መጻተኛ፣ ጥገኛ ፣ምርኮኛ እና ጥፋተኛ ብሎም ሟች እና ስደተኛ በማድረግ የአገሪቷን አንድነት እና የህዝቧን  ተፈጥሯዊ እና ህጋዊ መብት የስልጣን ማስጠበቂያ እና መራዘሚያ ሲያደርግ የነበር ኃይል / ቡድን በመልካም አስተዳደር ዕጦት ወይም የህዝብ ስልጣንን ለቡድን ጥቅም ያዋለ እንዲጠየቅ ማድረግ፣

፮) በሰባዊ መብት አየያዝ እና ረገጣም ቢሆን በትህነግ መንግስትነት በራሱ አገር እና ህዝብ ወደር የለሽ ግፍ የፈፀመ  የየትኛዉም የዓለማችን ክፍል ያልበር እና የሌለ መሆኑ እየታወቀ እንዲሁ መታለፉ  ወንጀለኛ ዳኛ ስለመሆኑ እና ለአገልጋይነት ለስልጣን ላበቁት ምዕራባዉያን ጥብቅና መቆም ምክነያት በመሆኑ  በሠባዊ መብት ጥሰት መጠየቅ፣

፯) በተጨባጭ እና በግልፅ የህዝብ እና የመንግስት( አገር) ሀብት በደም ከሳ( ) እና ወደ ስልጣን ማማ ከወጣበት አስካሁን ድረስ በማን አለብኝነት አንጡራ የህዝብ ሀባት በድርጅቱ እና በተለያዩ የግል ባለሀብት ስም የሚገኙ እና የተዘረፉ የህዝብ ሀብት እና ንብረት ወደ ብሄራዊ ሀብት እንዲመለሱ እና ለዚህም ዘራፊ እና ወኪል በባለሀብትነት ስም ተባባናሪዎች ተጠያቂ የሚሆኑበትን ስርዓት መዘርጋት እና በጊዜ ወደ ተግባር መግባት፣

፰) በምርጫ ስም ዓለምን እና የዛሬዎችን የአዞ  አንቢ ሀሰተኛ ሠባዊ እና ዲሞክራሲያዊ  ሰባኪዎችን በማሳሳት ላለፉት የ፭ ተከታታይ  የይስሙላ ምርጫ የህዝብ ሠባዊ ፤ ብሄራዊ  መረገጫ በማድረግ የሀያ ሰባት ዓመት የስልጣን መፈናጠጫ በማድረግ ዘመናዊ ባርነት የነበረበት መሆኑን ይፋ ማድረግ፣

እና በተለይም ለጥቅም እንጅ ለሠባዊነትም ሆነ ለዕዉነተኛ የሰዉ ልጆች መብት ግድ የማይላት ከጥንት አስከ ዛሬ በዓለም ዘንድ የዓለም መሪ ዘዋሪ እና ተቆርቋሪ ከኔ በላይ ላሳር ለምትለዋ አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንድንጠይቅ የሚጠበቅብን  ፡-

የኢትዮጵያ ወዳጅ ከሆነች ኢትዮጵያ በወራሪዉ ኢጣሊ ጨካኝ መንግስት በተወረረበት ዘመን ወራሪዉን የኢጣሊ  መንግስት ለመኮነን ለምን አመነታች፣

  • ከዘዉድ ስርዓት መወገድ በኋላ በሶመሊያ አገራችን ስትወረር  ወራሪዎችን እና የዉስጥ ቅጥረኞችን ከመደገፍ አልፋ የኢትዮጵያን መንግስት እና ህዝብ በጦር መሳሪያ ክልከላ /ዕቀባ  ራሳቸዉን እና ሉዓላዊት አገራቸዉን እንዳይከላከሉ እንዴት እና ለምን አደረገች፣
  • በዘር ፍጅት ሊያስጠይቅ በሚችል በመንግስት በተካሄደ የዓመታት አንድን ዘር ፣ ዕምነት ፣ ባህል እና ወግ መሠረት ያደረገ መጠነ ሰፊ ጥቃት ሲከናወን ከዚህ በላይ የዘር ፍጅት ፣ ኢሰባዊ እና ኢ- ዲሞክራሲያዊ ወንጀል እንዴት ሆኖ ለ 27 ዓመት አልታያትም አልተሰማትም (ምን አልባት መካከለኛዉ ምስራቅ ላይ ትኩረቷ ስለነበር ይሆን )፣
  • ምርጫን በሚመለከት ለመሆኑ በኢትዮጵያ ጉዳይ እኔ ከሌለሁ ዳቦዉ ሊጥ ይሆናል ስትል ላለፉት ሰያ ሠባት ዓመት በተካሀደ ምርጫ  አሜሪካ ያልነበረችበት የምርጫ  ወይም የስልጣን መወጣጫ እና የኢትዮጵያ መቅጫ( ፍዳ) እንዳልነበር መረሳቷ ከሆነ ለምን የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ዕዉነታ ለዓለም አያፈርጠዉም ፡፡ አንድም ጊዜ በአምስት የምርጫ ዙር በፍጥጫ ፣ በርግጫ እና በጡጫ እንጅ  በህዝብ ድምፅ የተመሰረተ መንግስት እንዳልነበር ከወዳጅ አሜሪካ በላይ የሚያዉቅ አለመኖሩን እኛ ኢትዮጵያዉያን ስናረጋገጥ እርሷ አምጥታ፣ መርታ ፣ ጎትታ እና በስልጣን ከርቻ ጎልታ /አስቀምጣ የሾመችዉን ትህነግ  ካለሷ ፈቃድ ዉጭ  ምንም እንደማይደረግ ታዉቅ ነበር ፤ ሆኗል ፣
  • ምርጫ ማስመሰያ እና ማላገጫ መሆኑን አሳምራ ታወቅ እንደነበርም መዘንጋት ለእኛ ለኢትዮጵያዉያን የሚቻል አይደለም ፡፡

ለዚህም ከምርጫ ዋዜማ  አስካሁን የዜጎች የፈሰሰ ደም ፣ የጠፋ ህይወት እና ያለፉ የመከራ ዘመናት ዋቢ  መረጃዎች ናቸዉ ፡፡

እናም ዛሬ እና እኔ  ባይዋ አሜሪካ የለመደችዉን  አፍሪካ ዲሞክራሲ አልባሽነት ልክ ይዛ ዛሬም ያንን ኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያ  የለበሱትን የመከራ ዘመናት ማቅ ካለበሳችሁ ማለቷ ካልኩት አይጉደል የበደል በደል ለእኛ ካልሆነ  ኢትዮጵያ ትነጣጠል ማለት የለየለየት ብልጠት ነዉ ፡፡

የወዳጃችን ዓለማቀፋዊ ተሞክሮ በሶማሊያ ፣ በፓኪስታን ፣ በኢራቅ ፣ በሶሪያ ፣ በየመን ……ምን እንደመበር እና እንደሆነ መርሳት ካልሆ ለ ኢትዮጵያም ሆኑ ኢትዮጵያዉን የሚሰራ መላ አይደለም ፡፡

ኢትዮጵያ ከዉስጥ እና ከወዳጅ ጠላት እንጅ ከሩቅ ወዳጅም ሆነ ጠላት እንደሌላት የዘመናት ህዝቧ እና አግሪቷ ታሪክ የሚመሰክሩ ናቸዉ ፡፡

እባጫ እና ጉርባጭ ካልፈነዳ ወይም ካልለዘበ( ካልሟሸሸ)  ከራስ አልፎ ለሌላዉ ይተርፋል እና ይህ አደገኛ ዕባጭ  ሁለቱን ወዳጅም ጠላትም ሊሆኑ ከማይችሉ ህዝቦች ተርፎ ሌላ ሳይተርፍ ……. ለምንም ቅድመ ሁኔታ  ዉሻ በቀደደዉ ጅብ ይገባል እና  ኢትዮጵያን እና ህዝቧን እያጥላሉ ለጠላት ያደሩት የዉስጥ  ቅጥረኞች  በግላጭ እና በተጨባጭ  በማጋለጥ በህዝብ ላይ ላደረሱት እና ላደረሱት ግፍ እና ጥፋት ፣ በአገር ክህደት እና አገርን እና ህዝብን ለሩቅ ጠላት አሳልፎ የሰጡት እና እየሰጡ ያሉትን አደብ ማስገዛትም ሆነ ዋጋ ማስከፈል  ይገባል፡፡

ህዝብ ደጋግሞ ያሳሰበ ቢሆንም አስካሁን በመንግስት እና በሚመለከታቸዉ ሁሉ ሰሚ ጆሮ በመነፈጉ ለዓመታት የነበሩት ጥቃት እና ዉርደት ሳያንስ በግፍ ግፍ ለሚሰፍሩለት እና ተደጋጋሚ ክህደት ላደረሱበት በደለኞች  ዝምታ የተመረጠበት አግባብ ዛሬ ከኢትዮጵያ ህዝብ አልፎ ለመንግስት ችግር መሆኑ  ሊቆም ይገባል ፡፡

 ዉሃን ምን ያጮኸዋል ቢሉ ድንጊ እንደተባለዉ ከረጅም ዓመታት አስከ ዕዚች ዕለት የነበረዉ እና የሆነዉ ብሄራዊ ጥቃት ፣ ዉርደት እና መጠነ ሰፊ ጥፋት ባለቤት በመንግስት እና ህዝብ ቢመሽም በደንብ ለዓለም ሊገለጥ ጮኸቴን ቀሙኝ ባይም ጥፋተኛነቱ እና ተጠያቂነቱ ሊሰመርበት እና ሊጠየቅበት ይገባል፡፡

እናም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ለመጮኅ እና ዕዉነቱን ለዓለም ህዝብ ለመግለጥ ብንዘገይም  አሁንም  ጊዜ አለን እና አንድም ነገር ሳንተዉ  ጥፈተኛ እና ወንጀለኞችን ህዝብ እና አገርን በጎዱት ልክ እንዲክሱ እና ዋጋ እንዲጠየቁ ለዕዉነጠኛ ዳኛ እና ሽምግልና አንድ ባንድ ማጋለጥ ጊዜዉ አሁን ነዉ ፡፡ ባለቤት ካልጮኸ ገላጋይ ….አይደርስም …. እና በደላችንን እና ቁስላችንን እያስታመምን የምንብሰለሰልበት ጊዜ መቆም አለበት ፡፡ በቁስላችን ስንጥር፣ በሞታችን ሞት ለሚመኙ በድብስብስ ጥፋታቸዉን ማለባበስ ለእነርሱም በጥፋት ላይ ጥፋት መጨመር ስለሚሆን አይበጅም እና መንግስት እና ህዘብ በአንድነት  የተሸረበባቸዉን የሴራ ወጥመድ ሊበጣጥሱት ይገባል፡፡

“ሀሰት ዛሬን  ቢሽቀዳደም  አይቀድምም ፤አይኖርም  ”!!

“ሀሰት እና ስንቅ እያደር ይቀላል ፤ይጠፋል”

 

ማላጅ

አንድነት ኃይል ነዉ!

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፌዴሬሽኑ ታዋቂ ዲጄ ሳይሆን አዋቂ ዲጄ ያስፈልገዋል

2 Comments

  1. ለ ምንም ይሁን ለ ምን መፍትሄው ጠንካራ ሆኖ መገኘት ብቻ ነው የሚያስከብረው። ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም አማራ፣ ህልውናቸውን ከ ኦሮሞ እና ትግሬ ተስፋፊዎች ሊያድኑ የሚችሉት ሃይል ገንብተው መቋቋም ሲችሉ ብቻ ነው። ከ ህልውና የሚበልጥ ነገር ስለሌለ ባጀታቸውን በሙሉ የ መከላከያ ሃይል ግንባታ ላይ ማዋል አለባቸው። አሁን ስላለፈው በደል ላይ ጊዜ የምናጠፋበት ሳይሆን የሚመጣብንን ጭፍጨፋ ለመቋቋም የምንዘጋጅበት ጊዜ ነው። ይህ አረፍተ ነገር አንክሮ ይሰጠው። በ ሰሜን ሸዋ በ አማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እና ከተሞች ማውደም ጅማሮ ነው እንጂ መጨረሻው አይደለም። በ ደቡብ እና በ ምዕራብ ብሔረ
    ሕዝቦች ላይም የ ኦሮሞ ተስፋፊነት ይስተዋላል።
    ለ ኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት እያንዳንዱ ብሔረሰብ በ መንግሥት ሳይሆን በራሱ ህልውናውን ለማስከበር ተዘጋጅቶ ሲዘጋጅ ብቻ ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.