በራሳችን ወርቅ እንድመቅ – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ኢትዮጵያ ፣ በአስተማማኝ  ሠላም ውሥጥ ሆና ዜጎቿ በአሻቸው የአገሪቱ ክልል እየተንቀሳቀሱ ሰርተው ብልፅግናንን እውን ለማድረግ የሚችሉት ፤ ያልወገነ ፣ ሁለንተናዊ  ጥንካሬ ያለው እና በወታደራዊ ዝግጅቱ በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ ፣ የአገር መከላከያ ኃይል ና ለህግ  እና ለህሊናው ብቻ ተገዢ  የሆነ ፣ ፍትህ ና ሠላም በመላው አገራችን እንዲነግስ የሚያደርግ  ሙያውን አክባሪ ፣  ህግ አሥፈፃሚ ተቋም   እና አንድ የጋራ መግባብያ ቋንቋ ሲኖር  ምሑራን ያምናሉ ። ያለ እነዚህ በፍፁም ሰላም እንደማይመጣ  የበለፀጉትን አገራት  የትላንትና  የዛሬን  ታሪክ  መለሥ  ብሎ  መመልከት  አሥፈላጊ  ነው ። ሲሉም ይመክራሉ ፡፡

ቻይና ፣ አሜሪካ ፣ ሩሲያ ፣ ጀርመን ፣ እንጊሊዝ ፣ ፈረንሣይ ፣ ጣሊያን ፣ ስፔን ፣ ፖርቹጋል ፣ ወዘተ ።  በአገራቸው  ሠላም ሰፍኖ ብልፅግና የመጣው ሁሉም ዜጋ የሚመካበት የህግ ሥርዓት ፣ መከላከያ ሠራዊት  ና አንድ ገዝፎ የሚታይ ሁሉም የሚናገረው ብሔራዊ  ቋንቋ ሥላለቸው  ነው ።

ዛሬ  አገራችን  ተከታታይነት  ያለው  ወከባ ፣  ትርምስ ና ሰቆቃ  ውሥጥ  እንድትዳክር  ያደረጋት ፣  የእነዚህ  ሦሥቱ  በወጉ ያለመኖር  እንደሆነ እሙን ነው ።

በአገራችን 80% የሚነገረውን አማርኛን ፤  ብሔራዊ ቋንቋ ለማደረግ ባለመቻላችን እና የባቢሎንን ግንበኞች መንገድ በመከተላችን የተነሳ የአገራችን ህዝቦች ሠላም ክፉኛ እንደተናጋ ይታወቃል  ። የህዝቡን ሰላም ያናጉትም  የፖለቲካ ሊሂቃኑ ናቸው ። እነዚህ ሊሂቃኖች ፣ በምክር ቤት ና በክልል ምክር ቤት በአማርኛ ይናገራሉ :: ወደ ሚያስተዳድሩት ህዝብ ሲመለሱ ፣ “አማርኛ አናውቅም ፡፡ ” ይላሉ  ።  አማርኛ የአማራ ቋንቋ እንዲሆን ከፈጣሪ የተሰጠ እሥኪመሥለን ድረስ አማርኛን ይጠየፋሉ ። ጥላቻንም ይዘራሉ ፡፡

እነዚህ የፖለቲካ ነጋዴዎች ፣” ሁሉም ሰው የፈጣሪ  ሸክላ ነው ብለው አያምኑም ።ፈጣሪም ለሰው ፊት አያደላም ፡፡ ሥለ ነገድ ፤ ጎሣና ቋንቋ ግድ አየሰጠውም ፡፡ የሱ አጀንዳ ፍቅር ነው ፡፡ የዘርና የቋንቋ ሹክቻ አይደለም ፡፡  ሁሉም  ቋንቋ  እኩል  እና ሰውን ከሰው ጋር አቀራራቢ አግባቢ እና አፋቃሪ  እንጂ አጣይ አይደለም ። ማንም ሰው ለማንም ሃሳቡን በአንደበቱ አልያም  በምልክት ቋንቋ ሳይናገር ሊዋደድ ና ሊፋቀር አይችልም ። እንኳን ለፍቅር ለጥላቻም ቋንቋ ያሥፈልጋል ።  ” በማለት ህሊናቸውን ለህብረት ኑሮ አያስገዙም ፡፤

ቋንቋ የመግባቢያ እንጂ  የመጨቆኛ ና የፖለቲካ መሣሪያ አለመሆኑ  ቢታወቅም ፣ በእኛ አገር ወደ ሥልጣን መወጣጫ እርካቡ ቋንቋ  ከሆነ እንሆ 30 ዓመት ሞልቶታልና እነሱ ሁሌም በቋንቋ እያመካኙ ለመበዝበዝ ነው ፍላጎታቸው ። ከ 30 ዓመት በኋላ ፤ ግንቦት 28 / 2013 ዓ/ም አገራዊው  ምርጫ ተካሂዶ ” የቋንቋ ንግሥ ና ያበቃል ። ” የሚል ተሥፋ ይህ ፀሐፊ አለው ።  (…)

ጥቂት የማይባሉ ምሁራን ግን ፣ ዛሬና አሁን ሥር ነቀል ለውጥ ይፈልጋሉ ፡፡ ለምን ተብለው ሲጠየቁ ፣ ” ከምርጫ በፊት ፣ ሌቦችንና የህዝብን ማጅረት የሚመቱ አስመሳይ ፖለቲከኞችን የለውጥ ኃይሉ  አስቀድሞ ከጫወታ ውጪ  ካላደረገ በስተቀር ፣  በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ በሚደረጉ አሻጥሮች አገሪቱ ሰላሟን ታጣለች ብለን እንፈራለን ፡፡ ” ይላሉ ፡፡  ይህ እምነታቸው ባይናቅም ፤” የአገሪቱን  የፀጥታ ኃይሎች በሙሉ በአንድ ዕዝ እንዲመሩ ማድረግ ፤ የአገሪቱን ና የህዝቧን ሰላም ለማስጠበቅ ዝግጁ በማድረግ፡  ይህንን ስጋታቸውን ማቃለል ይቻላል ፡፡” በማለት የመፍትሄ ሃሳብ የሚያዋጡ አሉ ፡፡  የእንባ ጠባቂ ተቋሙ ይህንን ሃሳብ ማዋጣቱን አትዘንጉ ፡፡ ሃሳቡን ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍ ፣ ዋጋ እንደሚያስከፍል ፣ መንግስት የሚገነዘብ ይመስለኛል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃላፊነትና ተጠያቂነት - ጠገናው ጎሹ

ይህንን ሁሉ ሥጋት የደቀነብን ፤ ከ80 በላይ ቋንቋ ያላቸው ጎሣዎች ባሉባት አገር ፣ ሰው ያልፈጠረውን የአንድ ሉአላዊ  መንግሥት ና ህዝብ መሬት በየክልሉ ሸንሽኖ ፤ ለአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ብቻ በመስጠት  ፣ ዜጎች በዜግነታቸው ኮርተው ፣ በአገራቸው ምድር ፣ ሰርተው እንዳይበሉ የሚያደርግ  የአንድ ጎሣ ቋንቋ ንግሥና ነው ፡፡ ይህ አይነቱ ርዕየት አብዮታዊ ዴሞክራሲም በለት መለሲዝም  ፣ ዜጎችን የሚያናቁርና እሥከዘላለሙ  የማያቀባብር  የልዩነት ግንብ ነው ፡፡  ይህንን ሃቅ የለውጡ ወይም አሻጋሪው መንግስት የሚያጣው አይመስለኝም  ። በአውሮፖ ና አሜሪካ ይቅር ና በጎረቤቶቻችን አገሮች የእኛን መሰል የማያቀባብር የቋንቋ አጥር በዜጎች መካከል  እንዳልታጠረም የየክልሎቹ ፕሬዝዳንቶች የሚገነዘቡት ይመስለኛል  ።

እርግጥ ነው የቋንቋ አጥሩ ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር”  የመለስ ዜናዊ አዲስ ፍልሥፍና  መሆኑ እና ለሙከራ ወደተግባር እንዳመጣው ለምራብውያኑ ግልጽ ነው ። “ይህ ሱሪ በአንገት የማውለቅ ያህል የተደናበረና የሚደናብር ፍልስፍና    በዓለም አገራት  የለም ። ህዝብ   በየቋንቋው  አጥር ውስጥ ሆኖ      ( በዜናዊዝም  ፍልስፍና  እንዲተዳደር )  ለ 30 ዓመት ተደርጓል ፡፡ በየትም የሀገሪቱ ክፍል ፤ በቋንቋው እየተለየ ፣ የማይመለመል ወታደርና ፖሊሥ ይህቺ አገር  ቢስፈልጋትም ይህ ለ30 ዓመታት አልነበረም ፡፡  በዚች አገር ውስጥ በቋንቋ ያቋቋምነውን የየክልሉን ኃይል  ወደ ፌደራል  በማምጣት ፣ ለሦሥት ወር በማሰልጠን እና በፊደራል ሥር በማድረግ ፣  ከሁሉም ብሔረሰቦች ጋር በመበወዝ ኢትይጵያዊ  የሆነ ፣ ፖሊስና ወታደር መፍጠር  ካልቻልን በስተቀር አበሳችን ይቀጥላል ።

ይህ መሆን የሚችለው  ከምርጫው በኋላ  ህገ መንግሥቱ ላይ ያሉ አሳሪ አንቀፆችን ፣ በተለይም ቋንቋን ፣ የክልል መንግሥታት ና የፊደራል መንግሥትን ሥልጣን  በተመለከተ አዳዲስ ህጎችን በማውጣት   ፤ የምርጫ ህጉን እና ለሥልጣን የመወዳደሪያ መንገዱ የሚቀየርበትን መንገድ በመቀየስ  እንደሆነ ቢታመንም ጥቂት የማይባል ዜጋ ፣  የዛሬን እንዴት አድሬ እያለ ነው ።ይህ እንደ ሥጋዊው ምሳሌ በቀላሉ ወደጎን የምንገፋው የሰው ሥጋት  አይደለም ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ80 በላይ ቋንቋዎች እየተነገሩ ፣ በ11 ክልላዊ  መንግሥታትት ቋንቋዊ ሥልጣን ለጥቂቶች በመሥጠት  አገርን መምራት ነገ ፣ እንደ ትግራይ ክልል ዓይነት አደጋ እንደሚያስከትል ከወዲሁ መገንዘብ የሥጋቱን እውነትነት ያረጋግጥልናል ፡፡ እናም ፣ በሁሉም ክልል ከ85 % በላይ ተናጋሪ ያለው የአማርኛ ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን ህገ መንግሥታዊ  እውቅና እንዲሰጠው ማድረግ ፣ ከምርጫ በኋላ የመንግሥት ሥልጣን የሚይዘው መንግሥት ኃላፊነት መሆኑን ዛሬ ላይ ሆኜ ማሳሰብ እፈልጋለሁ ።

     ይህን  ሥል  ለሱማሊኛ  ተናጋሪው  ሱማሊኛ  የማይችል  አሥተዳዳሪ  ይሾምለት  ማለቴ  እንዳልሆነ ይታወቅለኝ በኢትዮጵያ  የሚኖሩ  ሱማሊኛ  ተናጋሪ  ሰዎች  በምሥራቁ  የኢትዮጵያ  ፍለ አገር ይኖራሉ ። ( በአገሪቱ በሙሉ ይኖራሉ ፡፡ )  አብዛኛዎቹ   በተለይም  በከተማ  የሚኖሩ  አማርኛ ይነገራሉ አማርኛ  ሁለተኛ የሥራ  ቋንቋቸው  ቢሆን ኢትዮጵያዊነትን  ያጠናክራል   ነው   እያልኩ ያለሁት

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰማያዊ ፓርቲ ተስፋ

በነገራችን ላይ ከጎረቤት ኬኒያ ጀምራችሁ ፣  የአብዛኞቹን የአፍሪካ  መንግሥታትትን  የሥራ ቋንቋ ና ብሔራዊ  ቋንቋቸውን (official and national languages )የቅኝ ገዢዎቻቸው መሆኑንን መገንዘብ ጠቃሚ ነው ። የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ግን አማርኛ ነው ። ( official languages) ጥያቄዬ አማርኛ ቋንቋ ለምን ብሔራዊ ቋንቋ አይሆንም ነው ? ሁሉም የመንግስት ባለስልጣን በቋንቋው እየተራቀቀበት አይደለምን ? የትኛው የክልል ባለስልጣን ነው የአማርኛ ቋንቋ ሲደናገረው ያየነው ? በራሰችን ወርቅ ባንቀልድና እራሳችንን ባናኮስስ መልካም የመስለኛል ፡፡

የጥቂቶቹን የአፍሪካ አገራት  ብሔራዊ  ና  የሥራ  ቋንቋ  በመጥቀስ  የፅሑፊን ጭብጥ በማጠናከር ፅሑፊን እቋጫለሁ ፡፡  ።

አገር                                                            የሥራ ብሔራዊ ቋንቋ

አንጎላ                                                               ፖርቹጋልኛ

ቤኒን                                                                 ፈረንሣይኛ

ቦትስዋና                                                           በከተማ እንጊሊዘኛ  በገጠር  ሳትስዋና

ቡርኪናፋሶ                                                       ፈረንሣይኛ

ብሩንዲ                                                           ፈረንሣይኛ ና ክሩንዲኛ

ካሜሮን                                                         እንግሊዘኛ ና ፈረንሣይኛ

ኬፕቨርዲ                                                       ፖርቹጋልኛ

ቻድ                                                              ፈረንሣይኛ ና አረብኛ

ኮሞሮስ                                                         አረብኛ ና ፈረንሣይኛ

ዴ/ሪ/ ኮንጎ                                                   ፈረንሣይኛ

ጂቡቲ                                                           ፈረንሣይኛ ና አረብኛ

ኢኮተሪያል ጊኒ                                             ስፖንሽና ፈረንሣይ

ኤርትራ                                                      ትግሪኛ ፣ አረብኛ ፣ እንግሊዝኛ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊያን ቆም ብለን የምናስብበት ወቅት ዛሬ ነው - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ጋቦን                                                         ፈረንሣይኛ

ጋምቢያ                                                    እንጊሊዝኛ

ጋና                                                          እንጊሊዘኛ

ጊኒ                                                          ፈረንሣይኛ

ጊኒ ቢሳው                                              ፖርቹጋል

ኬኒያ                                                     እንጊሊዘኛ ና ኪስኋሊ

ላይቤሪያ                                             እንጊሊዝኛ ና 20 የጎሳ ቋንቋዎች

ማሊ                                                  ፈረንሳይ

ሞሪሸስ                                            እንጊሊዘኛ ና ፈረንሣይኛ

ኒጀር                                                 ፈረንሣይኛ

ሩዋንዳ                                             ፈረንሣይኛ ና እንጊሊዝኛ

ሴኔጋል                                                ፈረንሣይኛ

ደቡብ አፍሪካ

ዛምቢያ                                            እንጊሊዝኛ

ዚምባቡዌ                                      እንጊሊዝኛእንጊሊዘኛ እና የራሷ 11 ቋንቋዎች የመንግሥቷ ና የአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ነው ።

ቶጎ                                                 ፈረንሣይኛ

ዩጋንዳ                                            እንጊሊዝኛ

 

( ምንጪ  Nation online project …one world )

 

1 Comment

  1. የህግ ትምህርት ፣ የፖለቲካ ትምህርት ፣ የኃይማኖት ትምህርት እና የታሪክ ትምህርት ጥራቶች ከመቼውም በላይ በወደቁባት የአሁንዋ ኢትዮጵያ ፤ የምንጠቀመው ቋንቋችን አንድ አይነት ቋንቋ ቢሆንም ተደበላልቅዋል ፤ መግባባት አቅቶናል ተመሳሳይ ቋንቋም እየተነጋገርን። የሚጠቅም ምክር አስመስሎ የሚያጠፋ ምላስ በርክትዋል። ወዳጅ መስሎ ሚስጥር የሚሸጥ በርክትዋል። ስብዕናችንን ለመስረቅ ቋምጠው ለሞት ሊዳርጉን አሰፍስፈዋል።

    ግብዝነት ፣ ቅናት ፣ ምቀኝነት ፣ እኔ ያልኩትን ታዘዙ ፣ ፍራቻ ፣ የገንዘብ/የስልጣን ፍቅር እና አለመተማመን ያስተማረን አብይ ነግሶብን ከገዛ የቤተሰብ አባላቶቻችን ጋር እንኳን በአደግንበት ቋንቋ እንኳን ተነጋግረን መግባባት አቅቶናል ተወውና ከሌላ ኢትዮጵያኖች ጋር እንደ ሀገር መግባባትን፤ ቅን ልቦና ጠፍቶዋል ፤ ዘንድሮ በገዛ ቤተሰቦቹ/ወዳጆቹ ሴራ ያልተጠነሰሰበት ኢትዮጵያዊ ካለ ይገርመኛል ፤ ሁላችንም በሴራ ጠንሳሾች በተላኩ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ተከበናል ፤ ስንወድቅ የሚያነሱን ሳይሆን የበለጠ እየገፈተሩ የሚጥሉ ወገኖች ከበውናል ። ስስ ጎናችንን ለማወቅ ብቻ አዛኝ መስለው በለስላሳ ጥያቄዎቻቸው ደካማ ጎናችንን አጥንተው ከእዛ በደከመ ጎናችን አጥቅተው አስጠቅተው ለመጣል የሚያሰፈስፉ በዝተዋል። አንደኛውኑ ሌላ የማላውቀው ቋንቋ የሚናገሩ ሳይሻሉ አይቀሩም። ከእራሳቸው ህሊና ጋር መስማማት ያቃታቸው ፤ ሌሎቻችንንም ከህሊናችን ለማጣላት ከመቼውም በላይ ቆርጠው ተነስተዋል። ፓትሪያርኩ እንኳን አልተረፉም ፤ ከሴራ ጠንሳሾች የተንኮል ከበባ።

    Language/Dialect will not cure a dysfunctional Family/ a dysfunctional society. Ethiopia is a dysfunctional society, we currently put all our eggs in one basket called GERD. If GERD was not there imagine how we would have acted towards each other if we acted like this blaming our own fault on foreigners , ” GERD this , EGYPT that ..” for all the miscommunications we suffer , how worse would we be at each other if we are these bad to each other even at this time when GERD is being constructed.
    ለአንዳንዶቻችን ገንዘብ አፍቃሪዎች ግድቡ ጣኦት ሳይሆንብን አልቀረም። ወገንነታችን/ወንድማማችነታችን በግድቡ ላይ ብቻ የተመሠረተ ከሆነ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share