ሀገርን ከውድቀት ሕዝቡን ከልቂት የመታደግ ጥሪ – ሽማግሌው ነኝ ከሁስተን ቴክሳስ

በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አያገኝምና የአገራችን የበሽታ ምንጭ ፍትሐ ነግሥት ነበር። ፍትሐ ነግሥት  በመጀመሪያ ከብሉይና ከአዲስ ኪዳን  ተሰባስቦ፣ ሕዝቡን ይዳኝነት ዘንድ ተዘጋጅቶ ለንጉሥ ቆስጠንጢኖስ የተሰጠ ነበር።ከዚያም ከቤተ ክርስቲያን ሕጎችና እንዲሁም ለማስተማርና ለማስረዳት ዕውቅተ ያላቸው ሰዎች ከጻፉት ድርሳናት ውስጥ በስምምነትና በማስተዋል ተሰብስበው ተካተዉበታል። ፍትሐ ነግሥት “ፍትሕ እና ነገሥት” በሚሉት ሁለት ቃላት የተሰናሰለ ቃል ሲሆን፣ ትርጓሜውም ፍርድ፣ ውሳኔን መስጠት፣ሕግና ሥርዓትን ማስፈን የሚል ነው። የሕጉም አስፈጻሚ ነገሥታቱ ክርስቲያኖች ከመሆናቸው ጋር “ፍትሐ ነግሥት” ተብሎ ተሰይሟል።

በአገራችን ፍትሐ ነገሥት ከዓርብኛ ወደ ግዕዝ የተተረጎመውና በሥራ ላይ የዋለው በንጉሠ ነገሥቱ አፄ ዘርዐያቆብ (ከ1444 እስከ 1468)ዓም ባለው ጊዜ ነበር።ከዚያን ጊዜ አንስቶ፣ ሊቃውንቱ በብራና በእጅ እየጻፉ፣ በጉባዔ እየተረጎሙ ትምህርቱ ከአንዱ ወደ አንዱ በቃል እየተላለፈ በመላ ኢትዮጵያ ተዳርሶ፣እስከ 1948 ዓም ደርስ ሲያገለግል ቆይቷል። በመሆኑም የፍትሐ ነገሥት መጽሐፍ በሀገራችን ሥርወ ሕግ ሁኖ ብዙ ዘመን የተሠራበት ከመሆኑ ጋር አሁንም የሕግ ምንጭነቱን እንደያዘ ይገኛል።

ከዚህ በላይ እንደ ተመለከተው ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት አንድ ነበሩና መንግሥት በጉልበቱ  ወርሮ ከነዋሪው ሕዝብ ከነጠቀው ርስትና ጉልት፣ቤተክርስቲያን በአንድ ሦስተኛው ላይ ባለቤት ነበረች። ስለዚህም   ያንኑ ርስት ክሕዝቡ ለመንጠቅ ነው፣ዛሬም ሕዝቡን አሕዛብ እያለች የምታዋርደውና ከመንግሥት ጋር ለማጋጨት እንቅልፍ በማጣት ላይ የሚትገኘው።

ሁለተኛ  ሕዝባችንን የእርስ በርስ  መተማመን ያሳጡን የነፍጠኛው  ሥርዓት ናፋቂዎች ናቸው።እነርሱም ወደ ቀደመው ሥልጣናቸው ለመመለስ ሲሉ፣  ሕዝቡን ከመንግሥት ጋር ለማጋጨት፣ የስለላ መረብ ዘርግተው  የፕሮፓጋንድ ዘመቻዎችን በመደረግ ላይ ይገኛሉ።ከእነዚህም ዋናው የአጫሉ ግድያና በጁሀር ላይ  የተፈጸሙ የኦርሞ ሕዝቦችን የሚያስቆጡ ተግባሮች ነበር።

በአገራችን ያለውን የብሔር ብሔረሰቦች ቅራኔ ያከረረው፣ መሠረቱ በፍትሐ ነግሥት የተጣለው ቅራኔ በአግባቡ ባለመፈታቱ ነው።    ይህም “ሰዎች ሁሉ በጥንቱ ተፈጥሮ በነጻነት አንድ ናቸውና መጣላትና የፈረሰ ጉልበት እርስ በርሳቸው ይገዛ ዘንድ መገዛትን ታመጣባቸውለች እንጂ፣ የጠብና የማቸነፍ ሕግ ድል የሆኑትን፣ድል ላደርጉት ባሮች (ተገዥዎች)ታደርጋቸዋለችና“የሚለው ነው።

በመቀጠልም “ኦሪትም ከሃይማኖት የወጡትንና ከእነርሱም የተወለዱትን እንዲገዟቸው ታስረዳለች፡፡ እንዲህ የሚል ጽሑፍ በውስጧ አለና።በዙሪያችሁ ካሉ ከአሕዛብና አብረዋችሁ ከሚኖሩ ከስደተኞች የምትወስዷቸው፣ለእናንተ ወንዶች ባሮችና ሴቶች ባሮች ይሁኗችሁ።      ከእነርሱ በአገራችሁ ከተወለዱ ከዘራቸውም ግዙ፣ ለእናንተ፣ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ የምትወርሷቸው ይሁን” ይላል።ፍ ነ፣ አንቀጽ 31ንዑስ ቁጥር 1045፣1046።

ከዚህ አንጻር ከርስቲያን ያልሆነ።ከአጼው ጋር ተዋግቶ የተሸነፈ ሁሉ እንደ ባሪያ ተቆጥሮ ነው፣ ዘር ማንዘሩ ባሪያ ይሁኑላቸሁ ግዟቸው የተባለው።       በመሆኑም  ሕዝባችን ራሱ ባልፈቀደውና ባላጸደቀው፣  አፄ ዘርዐያቆብና የኦርቶዶክስ ቤተ ካህነት በመተባበር ባዘጋጁት ፍትሐ ነግሥት ነበር፣ ከ1444 እስከ 1948 ዓም ድርስ ሲገዛ የኖረው።

አሁንም  ቢሆን ያንኑ የቅኝ አገዛዝን  በሕዝባችን ላይ ለመመለስ ነው የመደመር ፖሊሲ አስቀርጸው በብልጽግና ፓርቲ ጥላ ሥር፣ በሥውር የተደራጁት፡፡ይህ አመለካከትና አስተሳሰብ  ስር በመስደዱ ነው፣ ጭቁን ሕዝቦች፣ተቆጥተው በጸር ብልጽግና ፓርቲ አቋዋም በመደራጀት ላይ የሚገኙት፡፡

የብልጽግና ፓርቲም ራሱ ለአንድ መድብ ጥቅም የቆመ ቢሆን፣ ከመደቡ አባላት ተአማኒነትን በማትረፍ፣ እስትራቴጂያዊ ግቡ ይደገፍ  ነበር። የብልጽግና ፓርቲ የብሔር ድርጅት ቢሆንና የብሔር ብሔረሰቦችን ራስን በራስ የማስተዳደር ዴሞክራሲያዊ መብት ቢያስከብር ኖሮ፣ ከብሔር ብሔረሰቦች ዕውቅናና ድጋፍ ያገኝ ነበር።

አሁን ግን ተግባሩ ሌላ፣ሕገ መንግሥቱ ሌላ፣እስትራቴጂያዊ ግቡ በብዙዎች ዘንድ የማይታወቅ፣ ደብቆ፣ እንዲሁ አምናችሁ ተከተሉኝ የሚል፣ ለብዙዎቹ ግራ አጋቢ፣ለቀደመው ሥርዓት ናፋቂዎች ግን  ሰፊ የዴሞክራሲ  በር የከፈተ፣ ጠላትና ወዳጅን ለመለየት የሚያስቸግር፣ የመደብና የብሔር ቅራኔ አስታራቂ፣ ወደ ግቡ የሚያደርስ ታክቲክ የሌለው መስሎ የሚታይ ነው።

ከዚህም የተነሳ ባለፉት ሦስት አመት ብቻ፣ ቁጥሩ ከመቼውም በላይ የሆነ ሕዝባችን፣እርስ በርሱ፣ በልዩ ኃይል፣በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሠራዊት ተገዳድለዋል። መጠኑ ያልታወቀ ሰው ከመኖሪያ ቄዬው ተፈናቅሏል፣ከፊሉ ታስሯል። ሞትና እስራትን በመፍራት፣የሸፈቱና  ወደ ትጥቅ ትግል የገቡም አሉ።ይህ በዚህ ከቀጠለ “አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል’ ነውና፣ ሁሉም በየጎራው የሰለፋል።አሁንም ጀምሯል።ይህንም በቀላሉ ከኦሮሞ የነፃነት ጦር ፈጣን እድገትና ብዛት አንጻር መመልከት ይቻላል።

ይህ ደግሞ የአማራንም ሆነ የኦሮሞን ሕዝብ የማይጠቅም፣ሕዝቡን እርስ በርስ የሚያፋጅና ፍጻሜውም የኢትዮጵያን ሕዝብ በየነገዱ የሚበታትን አደገኛ በመሆኑ፣የብልጽግና ፓርቲ ወደ እስትራቴጂያዊ ግቡ የሚያደርስ ለወቅቱ ተስማሚ የሆነ ታክቲክ ሊኖረው ይገባል።

ይህም የፌድራል ግንኙነት በመስተካከል ወደ ኮንፌድሬሽን ማሳደግን ይጠይቃል።ሰለዚህም የአማራ ብሔራዊ ክልል፣በጎጃም፣በጎንደር፣በወሎና በምሥራቅ ሸዋ በክልል ሥልጣን ተዋቅሮ ለዞኖች የራስ ገዝ ሥልጣን ቢሰጥ፣ በክልሉ ያለውን አብዛኛውን ቅራኔ የሚፈታ ይሆናል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልልም እንዲሁ የሸዋ ቱለማ፣ ወለጋ፣ (ኢሏባቦር,፣ (አርሲ፣ባሌና ቦረና)፣እና ሐረርጌ፣በክልል ስልጣን ተደራጅተው፣ለዞኖች የራስ ገዝ ሥልጣን ቢሰጥ፣ ከእርስ በርስ ሹኩቻም ሆነ  በሃይማኖተኞች መካከል ያለውን ቅራኔ የሚፈታ፣ ለአስተዳደርም የሚያመች ይሆናል።

የደቡብ ሕዝቦችንም ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት የወለይታ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦችን፣ ወሊይታን፣ኩሎ ኮንታንና፣ለጋሞ ጎፋን በዞን ራስ ገዝ ሥልጣን በመስጠት በአንድ በክልል ሥር ቢሰባሰቡ በቋንቋና ባህላቸው በመጠቀም ራስን በራስ ለማስተዳደር ያስችላቸዋል።

እንዱሁም በደቡብ ሸዋ የሚገኙ፣ለጉራጌ፣ለሐዲያ፤ለከምባትና ለልጤ በዞን ደረጃ የርስ ገዝ ሥልጣን  በመስጠት በአንድ ክልል ሥር በማሰባሰብ ለጥያቄያቸው መልስ በመሥጠት በኅብረተሰቡ መካከል ያለውን የብሔር  ቅራኔ  ለመፍታት ይቻላል።

እንዲሁም በደቡብ ኦሞ፣ማጂና ጌዲኦ ነዋሪ ለሆነው ሕዝብ የዞን ራስ ገዝ  ሥልጣን በመስጠት፣  በአንድ ክልል ማሰባሰብ ይቻላል። ለወረዳዎች  የራስ ገዝ ሥልጣን ቢሰጥ በአካባቢው ያለውን ችግር የሚፈታ ይሆናል።

ሌሎችም ትግራይ፣ ሱማሌ አፋር፣ቤን ሻንጉልና ገምቤላ ለዞኖችና ለወረዳዎች የርስ ገዝ ፣መብት መፍቀድ ይገባል።አዲስ አበባ፣ድሬደዋና ሀረሪ የረስ ገዝ ሥልጣን ኑሮአቸው፣ተጠሪነታቸው ለምክር ቤቶቻቸውና ለሚገኙባቸው ብሔራዊ መስተዳድር ሊሆን ይገባል።

የብሔር ጥያቄ በዚህ መልኩ ለመፍታት ከተቻለ ፣ፓርቲዎች   በሕዝቡ መብት ውስጥ ጣልቃ ሳይገቡ፣ሕገ መንግሥቱን አክብረው በማስከበር፣  በሕዝብ ተወካይች ውሳኔ በሚወጡት አዋጅና ድንጋጌዎች ፖሊሲአቸውን ለማስፈጸም ያስችላቸዋል።ይህ ከሆነ አንዱን ብሔር ከሌላው ብሔር ጋር የሚያጋጨው ነገር አይኖርም። ቢኖርም እንኳን በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚፈታ ይሆናል።

በመሆኑም ከዚህ በላይ ለመፍትሄነት የቀረበውን ጥቆማ ፣ የሕዝብ ተውካዮችና የፌድሬሽን ምክር ቤቶች በጋራ ተመልክተው በማዳበር፣ አቋዋማቸውን  ለፌድራል  መንግሥቱ በማሳወቅ፣የሕዝቡን ችግር ሊፈቱ ይገባል።

ለዚህም የሁለቱም የምክር ቤቱ አባላት፣መነቃቀፍን ትተው፣ ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት፣ አገሪቱን ከውድቀት ሕዝቡን ከእልቂት ለማዳን አስፈላጊ የሆነውን እርምጃ ለመውሰድ እንዲችሉ ፣የኢትዮጵያን አንድነትና የሕዝቡን ነፃነት የሚሻ ሁሉ፣ አመቺ ሆኖ ባገኙት መንገድ ሁሉ፣መሠል ጥያቄ በማንሳት ሊያተጓቸውና  ሊደጋፉአቸውም  ይገባል።

ሽማግሌው ነኝ ከሁስተን ቴክሳስ።

3 Comments

  1. Criticisizing Abiy and his party , bloody idiot team -prosperity party goons, will not free you from the crime you have committed against Tigray , Oromo, Kimant, Agew, Shinasha and others If Amhara got killed you are behind it.

    እንደ ዱቄት አበነንነዉ ደመሰስነዉ የምትሉት ትግራዋይ ቁም ስቕላቹህን እያሳያቹ ነው፥፥ውሸት አያልቅባቹ፥ ለማደናገር እውትን ለማዛባት የምትሸርቡት ሤራ የታለመለት ግቡን አልመታም፥ውጭ ተቀምጠሽ በወገህ ላይ ጦር እየሰበቕ የሕዝብ ገንዘብ በአመፅ ትበላላቹህ፥ህዝባቹ ላይ ብሄር ብሔረሰቡ እንዲነሳሳበት በተቃራኒ እየሰራቹ ነው፥፥እናንተ ተጋሩንና የሌላዉን ብሔር አባላት ለትጨፈጭፉ ዘምታቹ አልሳካ ቢላቹ በሀሰት አማራ ታረደ ትላላቹ፥ሁሌም የናንተ ፕላን ቢ ታረዱክ ተገደልኩ ድረሱልኝ አዉሮፓዉያን አሜርካውያን ብሎ ማለቃስ ነዉ ፥ንፁሃንን መግደል የተሳካ ለታ ግፋ ገስግስ የኔ አማራ እያሉ ማቅራራት ነው፥፥አዉሮፓዉያንና አሜርካውያን በሀገራችን ጉዳይ ላይ ጣልቃ አትግቡ ብሎ መደንፋት ትያያዙታላቹ፥፥በራድ ወይን ትኩስ ስላልሆናቹህ ነፍሰበላነታቹህ እንድትተፉ አድርጓችኋል፥፥ትናትና የሰማሁት የዮሴፍ ይጥና ዩቲዩብ አማራ ገስግስ የሚል ርዕስ ነበረዉ፥አልሳካ ስል ደግሞ አማራ ታረደ ወዘተ እያሉ የትግራዋይን፥ኦሮሞን ሺናሻን አገዉን ና የቅማንትን ዕልቂት ለማለባበስ አማራ ታረደ እያሉ ለማደናገር መሯሯጥ ነዉ የተለመደው የአማራ ልሂቃን የድንቁርና ለቅሶ መልሰዉ መላልሰዉ ሳይታክቱ ሊያሰሙን የወሰኑት፥በጬዉ ባጫ ደበሌ በኩራት በስምንት ወገን የተሰለፈዉን የወያኔ ጭፍራዎችን እንደ ዱቄት በታተናቸዉ፥በማለት ድል የተራቡትንናን ና ቀልባቸዉ የተገፈፉትን ልሂቃንን የሀሰት ስንቅ ያሳቅፋቸዋል፥

  2. ጭንቅላትህ በዝቅተኝነት መንፈስ የቆረቆዘ ሰው ። ህዝብ በማንነቱ እየተመረጠ እየታረደ ዝም አንልም።

  3. ለማ

    እብዱ ለማ ከዳተኛ የአረብ ተላላኪ

    የማን ለምን አትለጥፍ የንተና የመሰሎጭ ጭርንቅላት ተልቷል ገንዘብ ብቻ ነዉ የሚያስበዉ ተኝተንም ቢሆን ወያኔ አያሸንፈንም ያላቹሁት ገና ለመሰናበት ስትቃረቡም ትክዳላቹ የአጋንንት ፈረሶች ሕፃናት መግደል ለጥንቆላ ነዉ የትኛዉ ባሕታዊ ነው የነገራቹ ሀብት ና ሰዉ ለመሰብሰብ ነዉ መሰለኝ ከናንተ ግሞች መልካም ቃላት ንጠብቅም ያልተጠቀምከው የስድብ ይነት ካለህ ጨምር የበታችነጥን ባዶነህን ሊሞላዉ ከቻለ ቀጥልበት የአሁኑ ወር ደሞዝ ተጨምሯል ትንሽ ዉሸት ያልተሰማ ክልበት እበት ኦሮሞንና ጉምዝን ቅማንትና አገዉ እየገደልህና እያቃጠልህ ዉነትን ይዤ አሸንፋለሁ ትላለህ በሰዉ ደም ናህ ዞሯል ሀቅ ና ዉሸት መለየት ስኖሃል ግትቻ ናዉ የዞረ የገማ የቫቢያ ተላላኪ ደንገጡር ለማ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.