“ውሸት ቁጥር የለውም” እና “አያ ጅቦ – ኦሮሙማ መጣብህ” !!

በአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ሰፋፊ መሬቶች ላይ የኦሮሞ አርሶ አደር ታላላቅ ሞልና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንዲገነቡ ተፈቀደ                                     አዳነች አበቤ

ገንዘብ መውሰድና ሙስና ቁጥር አለው፡፡  ውሸት ግን ቁጥር የለውም ፡፡ ማጭበርበር ቁጥር የለውም ስለሆነምእባካችሁ …..

        አትሌት ደራርቱ ቱሉ

የአዲስ አበባ አርሶ አደሮች በከተማዋ ክልል ውስጥ ሰፋፊ መሬቶች ላይ ትልልቅና ዘመናዊ የሆኑ የገበያና የህክምና ማእከላትን እንዲገነቡ ቀጥተኛ ትእዛዝ የሰጠችው ጉድና ጡር አይፈሬዋና በተረኝው የኦሮሙማ የተመደበችው ከንቲባ ተብየዋ አዳነች አበቤ ስትሆን “ውሸትና ማጭበርበር ቁጥር የለውም” የሚለውን  ዘለአለም የማይሞት ትክክለኛና ሀቀኛ ንግግር የተናገረችው ጀግናዋ ተወዳጅዋና ፍልቅልቋ አትሌት ደራርቱ ናት፡፡ ይህንኑም ታሪካዊ ንግግር ስታደርግ ጀብደኛው ሽመልስ አብዲሳ ፊቷ ቆሞ ሀቅ እያነቀውና እየተኮሳተረ ሲያዳምጥ የተስተዋለበትን ድራማ ከዚህ ቪድዮ እንድታዩት እመክራለን፡፡  

አንባቢወች ሆይ፦ የአትሌት ደራርቱን ”ውሸትና ማጭበርበር ቁጥር የለውምና … ስለሆነም እባካችሁ… “ ወዘተ ንግግር በሚመለከት ራሱ አባባሏ ምንም ማብራሪያ ሳይፈልገው ሀቁን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ስለሆነ ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡ ስለሆነም ወደገራሚው የጊዜያችን  እውነታ “አያ ጅቦ ኦሮሙማ መጣብህ” ወደሚለው እሳቤ  እንመለስ፡፡ የጽሁፉን ርእስ “አያ ጅቦ ኦሮሙማ መጣብህ” ያልኩበት ዋና ምክንያት ጅቡን ሊበላው እየመጣ ያለው ኦሮሙማ ስለሆነ ነው፡፡ ዋና እሳቤው ጅብ ብለን የምንጠራውን የዱር እንሰሳውን ከእርሱ የበለጠው “ኦሮሙማ” የተሰኘው ጅብ (SUPER ጅብ) ሊበላው እየመጣ መሆኑን ለማሳያ ነው፡፡ ዱሮ ልጆች ሆነን ጅቡ መጣብህ ተብሎ ሲነገር አናስተውሳለን፡፡ አሁን በእውን መጣብህ እየተባለ ያለው የጫካው ጅብ ሳይሆን የሰው ጅብ፡ የቀን ጅብና የስርአት ጅብ የሆነው ኦሮሙማ ነው፡፡ ኦሮሙማ ሰው ይበላል፡ አገር ይበላል፡ ገንዘብ ይበላል፡መሬት ይበላል፡ ህንጻ ይበላል፡ ሀቅንና እውነትን ይበላል፡፡ ሁሉም የኔ ነው የሚለው የኦሮሙማ የኬኛ መንጋ  በቀን፡ በጠራራ ጸሀይ፡ አይኑን ብልጥጥ አድርጎ ይዘርፋል፡፤ኦርሙማ በተረኝነት ሁሉን የእኔ ማድረግን እንጅ ነግ በኔን አያውቅም፡፡ ኦሮሙማ ወንጀል ምሱ፡ ዘረፋ ቁርሱ፡ ክህደት መንፈሱና  ዘረኝነት እስትንፋሱ የሆነና በአገራችን ላይ በሟቹ ወያኔ ተተክሎ የበቀለ አደገኛ መርዝ ነው፡፡አጀንዳው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን በየተራ እያደባ ማጥቃት ብቻ ሳይሆን ማንነታችንን ፡የጋራ አገራችንንና ታሪካችንን ለማጥፋት በረቀቀ ዘዴ ተግቶ እየሰራ በመሆኑ መርዝነቱ ወደነቀርሳነት ከመሸጋገሩ በፊት ታግለን በቶሎ ከስሩ ነቅለን መጣል አለብን፡፡

የኦሮሙማ  አሳፋሪ ስራዎቹ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመሩ በመሄዳቸው በአገር ደረጃ አደጋው በጣም አሳሣቢ እየሆነ መምጣቱን የሚያረጋግጡ አያሌ ማሳያወች አሉ፡፡ ኦሮሙማ እስካሁን ባሳለፋቸው የሶስት አመታት አጭር ቆይታው ውስጥ ወያኔ በ27 አመት ረዥም ቆይታው የሰራቸውን የሚልቁና የሚያስንቁ  እጅግ አሳዛኝና ዘግናኝ ወንጀሎችን ፈጽሟል፡፡ ከሰራቸውና አሁንም እየሰራቸው ካሉት ዘግናኝ የወንጀልና የዝርፊያ አይነቶች ውስጥ የተሟላ መረጃ ያላቸውን በጣም ጥቂቶቹን ብቻ ለይተን እንደሚከተለው እንመልከት፡፡

የህዝቡ አለኝታና መመኪያ ከሆኑት እድሜ ጠገብ ብሄራዊ ድርጅቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ቴለኮሙኒኬሽን ባላስልጣን፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድና፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠቃሾች ናቸው፡፡  ከነዚህ ሶስት ድርጅቶች ውስጥ የአገሪቱ ታላቁ የገንዘብ አንቀሳቃሽ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወያኔ ክፉ ጊዜ እንኳን ባልተፈጸመ መልኩ አሁን በኦሮሙማ ጊዜ ታላቅ አደጋ ውስጥ ወድቋል፡፡ ባንኩ በኦሮሙማ ሴራ ተጠልፎ በመውደቁ  በፋይናንስ ክስረት ውስጥ ይገናል፡፡ አሳፋሪ በሆነ አሰራር ከላይ እስከታች የነበሩትን የየቁልፍ መምሪያወች፡ ዳይሬክቶሬቶችና የስራ ሀላፊወች በማባረር ቦታወቹን ኦሮሞወች በወረራ ተመርጠው ያለችሎታቸው እንዲመደቡበት ተደርጓል፡፤ ከቀጥታ ዘረፋው ሌላ ያለችሎታቸው የተመደቡት የምርጥ መንጋ ኦሮሞ ሀላፊ ተብየወቹ ባንኩን በታሪኩ ታይቶ የማይታወቅ ኪሳራ እንዲደርስበትና በአፍጢሙ እንዲደፋ አድርገውታል፡፡ በኢትዮጵያ ቴለኮሙኒኬሽን በኩል ያለውንም ሁኔታ ማንም በግልጽ ያውቀዋል፡፤ ከላይ እስከታች የምርጥ ኦሮሞወች ዋና መሰግሰጊያ ዋሻ ሆኗል፡፡የአገሪቱን ዋና የምስጢር ቋትና የመረጃ ቧንቧ የሆነውን ይህንን ድርጅት ለአገሪቱ የሚሰጠውን ጥቅምና ምትክየለሽነት ምዘና  ሳያዝገቡ ወይንም በግደለሽነት ሊዘርፉት ላሰቡት የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይ ብቻ በማተኮር ይዞታውን ለውጭ  ለመስጠት/ለመሸጥ ዝግጁቱን ቀጥለውበታል፡፡ እነዚህ ሁለት የመንግስት ድርጅቶች ብቻ የኦሮሙማው ቀንደኛ ቁንጮ አብይ አህመድ ተጠያቂ አይደለሁም ብሎ ለሚያካሂደው የገበታ ለሸገር ፕሮጀክቱ በድምሩ 1.6 ቢሊዮን ብር የህዝብን ገንዘብ መስጠታቸው ይታወቃል፡፡ አገሪቱ በረሀብ፡ በመፈናቀልና ጦርነቱ በፈጠራቸው ውጥረቶች ተውጣ በጣርና በረሀብ ላይ ባለችበት ወቅት ፍጹም ቅድሚያ ሊሰጠው ለማይገባው ለዚህ ተቆጣጣሪ አልባ  ፕሮጀክት ይህንን ያህል ቢሊዮን ብር  የህዝብ ገንዘብ አውጥቶ መስጠት ሰጪውንም ተቀባዩንም በወንጀል ማስጠየቁ አይቀርም፡፤ እንደነዚህ ሁለት ድርጅቶች ሁሉ በሌላው የአገራችን መኩሪያ በሆነው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚፈጸመው ሌብነት፡ እጅግ አሳዛኝና፡ አሳፋሪ ስለሆነ  በዚህና በሌሎች መሰል ድርጅቶች  ውስጥ ያሉትን የኦሮሙማ የዘረኝነትና የሌብነት ድራማዎች ሰፊ ስለሆኑ ለጊዜው በአጭሩ  “እጅግ አሳዛኝ”  በሚለው እንለፋቸውና  ወደፊት በሚገባ ተጠናቅረውና ተሰድረው ከተያዙት በቂ የመረጃና የማስረጃወቹ ጋር እንመለስባቸዋለን፡፡

በአዲስ አበባ በአስሩም ክፍለ ከተሞች፡ በ116 ወረዳወችና በ817 ቀጠናወች በረቀቀ የኦሮሙማ ሰንሰለት መሬትና ቤት ይዘረፋል፡ ቅርስ ይፈርሳል፡፡ ኦሮሞነት ይስፋፋል ኢትዮጵያዊነት እንዲጠፋ በዘመንጋው ወደ ዳር ይገፋል፡፡ ህዝቡም በረሀብ፡ በችግር፡ በስራ አጥነትና በዋጋ ውድነት ያልቃል ፡፤ ኦሮሙማ አዲስ አበባን ሊሰለቅጥ በቅርብ ርቀት ሆኖ ይቋምጣል፡፤ በከተማው ውስጥ የሚታዩትን የስርአቱን ዘረኝነትና ሌብነት የሚያሳዩ አያሌ ድርጊቶችን ህዝቡ መዝግቦ ይዟቸዋል፡፡ ለጊዜው ህዝቡ ልብ ያላላቸውን በጣም በቅርብ ቀናቶች ውስጥ በይፋና በድብቅ የተከናወኑ መሰሪ የኦሮሙማ አሰራሮች ቀንጭበን እንመልከት፡፡  በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ  ከማዘጋጃ ቤቷ አድራጊ ፈጣሪ አዳነች አበቤ ጋር በተዘረጋ የኦሮሙማ ሰንሰለት በብዙ መቶ ሽህ የሚገመቱ ቤቶችን በየአመቱ እየሰራ ንግዱን በብዙ መት ሚሊዮኖች እንድቸበችብ ኦቦ አልማው ጋሪ የተባለ የኦሮሙማ “ባለሀብት” ያለምንም ውድድርና፡ አሰራር የሌብነት ፕሮጀክቱ ተፈጥሮለት ወደተግባር ገብቷል፡፡ አሰራሩ ውድድርም፡ማስታወቂያም ጨረታም ያልተካሄደበት ነው፡፡ሌላው ደግሞ  በከተማውም ሆነ በፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ያሉ ሰራተኞችን ከምርጫ ማሸነፍ ጋር በተናበበ አሰራር “የሙያ ግምገማ” በሚል የዳቦ ስም የተጀመረው ማንነትን አስተሳሰብንና ዘርን መሰረት ያደረገው ህገ ወጥ የምንጠራና የተከላ ስራ  አስተዛዛቢ ብቻ ሳይሆን ክሰብእና በታች የዘቀጠ አሳፋሪ ተግባር ሆኗል፡፡ ይህም ኦሮሙማን በአዲስ አበባ ምርጫ እንዲያሽንፍ ለማድረግ ታስቦ በብልጽግና ከተነደፉት ሰፊና ሰቅጣጭ የአፈናና የማጭበርበር በሰነድ የተደገፉ አሳፋሪ  የውርደት ዘመቻወች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

በተረኝነትና በዘረኝነት፡ አገሪቱን የእልቂት፡የፍጅት፡ የመፈናቀልና የጦር አውድማ ያደረጋት ኦሮሙማ ጅብ ሆኖ መጣብህ መሰኘቱና በጅቡ መጣብህ ማስፈራሪያነት መመሰሉ ሲያንሰው ነው፡፡ የኦሮሙማ የ3 አመታት ግፍ ከወያኔ የ27 አመታት ግፍ በብዙ እጅ በልጦ ሞልቶ ፈሷል፡፡ ይህ ሀቅ እንዳለ ሆኖ ለእኛ መፍትሄው ይህ የጅብ መንጋ እንዳይበላን መፍራት ሳይሆን ተጋፍጠነው ጅቡን ማጥፋት ብቻ ነው፡፡ ጅቡን ተቋቁመን ብሎም አሸንፈነውና ጥለነው በምትኩ የጋራ የሆነ ለአገራችንና ለማንነታችን ዋስትና የሚበጅ ስርአትን እውን ለማድረግ ለጸረ ኦሮሙማው ትግል ሁላችንም አሁኑኑ እንነሳ፡፡ ይህ ግምት፡ ቀልድ ወይንም መጥፎ ምኞት ሳይሆን እየሆነ ያለና እየባሰበት የመጣ እውነታ ስለሆነ ከማለቃችን በፊት በጋራ ጅቡን እንቋቋመውና ህልውናችንን እናስከብር፡፡ አገራችንንም እንታደጋት፡፤ ይህ ከሆነ በኋላ ብቻ ነው ለሁላችንም ሊጠቅም የሚችል የጋራ ስርአት በጋራ ልንፈጥር የምንችለው፡፡በአጭሩ ጅቡ ኦሮሙማ በልቶ ሳይጨርሰን እንብላው!!! ተረቱስ ጅብ በልተህ ተቀደስ አይደል የሚለው??

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.