የአዲስ አባባ ምርጫ ለምን በአንድ ሳምንት ተራዘመ? – ፊልጶስ

በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጭም በጠላቶቿ ተቀስፍ በተያዘችበት ሰዓትምርጫለማካሄድ መሞክር ኃላፊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን  ለተጨማሪ ችግር አገርንና ህዝብን ማጋለጥ ነው። መቼም ቢሆን አሁን ባለው የጎሳ ህግመንግስት እየተመራን ዲሞክራሲን አመጣለሁ ማለትላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማእንደመሄድ ይቆጠራል። ግን ገዥዎቻችንምረጡንካሉ ምን አማራጭ አለን፤ ከአገርም ከህዝብም የነሱ ስልጣን ይበልጣልና።

ወደ  ተነሳውበት ጉዳይ ሳመራ

የምርጫ ቦርድ ለምን የአዲስ አበባ እና የድሬደዋን  የምክር ቤት ምርጫ ፣ ከአገር አቀፋ በአንድ ሳምንት እንዳራዘመው የሰጠው ምክንያት ወይም ማብራሪያ የለም።  እኛ ግን  በእናንተው ቋንቋ ቁማሩን  እንገራችሁ፤ በ’ርግጥ ምክንያቱ ከቁማርም ያያነስ፤ ዘርኝነት፣ ተረኝነት፣ ዓይን ዓውጣነት፣ ማን አለብኝነት፣ ድንቁርና፣ ህዝብ መናቅና አገርን የማፍረስ ሴራ ነው። ማን ነበር ፤

በአገርኢትዮጵያ  ቱጃርና ገዥ ለመሆን ከፈለክ ደደብና ደፋር ሁን::ያለው?

የኦነግ/ ኦዴፓ ብልጽግ የድንቁርና ቁማር የሚጀምረው  ‘ልዩ ጥቅም‘  የምትለዋ ከህገ-አራዊት ተነጥላ ወጥታ ”የአዲስ አባባ  ባለቤት እኛ ብቻ ነን ወደ  እሚል የግብዝነት የተረኝነት ፊሽካ ተነፋ። ህገ-አራዊቱ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናዝሪት ናት። የሚለውን እና እስከ 1997 ድረስ ሲተገብሩት የነበረውን ዘነጉት። በዚህም ቁማሩን በላን አሉ።

ቀጣዩ ህገ-አራዊቱ እንኳን የማይፈቅደውን በህግ-ወጥ መንገድ በአዲስ አበባ ላይ ህገ-ወጥ ከንቲባ ተጫነባት። ተግባሩም

1/      የከተማዋን ዲሞግራፊ መቀየር::

2/     በተቻለ መጠን ከአዲስ አበባ ውጭ የኦሮሞ ጎሳ ለሆኑት መታወቂያ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትኩረቱ ወደ ጀግናዉ አጼ ዮሐንስ ከተማ - መቀሌ !

ማደል::( እዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለበት ወያኔ የትግራይን ህዝብ እንደማይወክል ሁሉ ኦነግ/ ኦዴፓ ብልጽግናም የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም። በስሙ ግን ይቆምሩበታል፤ ይህ እምነታችን የሁሉንም ጎሳ ድርጅቶችና ፓርቲዎችን የጨምራል።)

3/     የኮንድሚኒየም ቤት ለኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ማደል::

4/     ክፍት ቦታ ወይም ለመዘናኛ የተከለለን ቦታ ለኦነግ/ኦዴፓ ብልጽግና ማደል፣ መዝርፍና የከተማዋን  ቅርሶች እያፈረሱ ለራሳቸው ደጋፊዋች በስማቼው ማዞር:;

5/     በመዲነዋ የሚገኙትን የመንግስት መስራ ቤቶችን በኦነግ/ ኦዴፓ ብልጽግና

ደጋፊዎችና አባሎች  ማስያዝ::

6/     በየመስራቤቱ ኦሮሞኛ የማይናገሩትን የተለያየ ምክንያት በመፍጠር

ማባብረርና በራሳቸው ሰዎች መተካት::

7/     የመንግስት ግዥውችን ያለ ጨረታ ለኦነግ/ኦዴፓ ሰዎች መስጠት::

8/     የአዲስ አበባን ማንነትና ህብረ-ኢትዮጵያዊነት ለማጥፋት  ለኦሮማማ

የጀግኖች ሃውልት፣ ፍርድቤት፣  የመሳሰሉትን በህዝብ ገንዘብ በቢሊዮን የሚቆጠር   አውጥቶ መገንባት፣ የስራ ኮንትራቱኑ ኦነግ/ ኦዴፓዊያን ብቻ እንዲሰሩና እንዲቀጠሩ ማደረግ:;

በአጥቃላይ በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ያልተነገር እንጅ ያልተፈጸመ ወንጀል የለም። ታዲያ ይህ ሁሉ ግፍ ተፈጽሞ ወደ ምርጫ ቢሄዱ ምንም ድምጽ እንደማያገኙ ሲረዱ ፤ ተስፋ በተጣለበት በምርጫ ቦርድ በኩል መጡ፤ የቁማሩ ትዕይንት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳንም በላ ::

“…..ሰርቄ በልቼ ሳልታጠብ እጀን

አሁን ከምንግዜው ጩኽት ሞላው ደጀን::” አለ ዘፋኝ::

” የአዲስ አበባና የድሬደዋ ምርጫ ከዋና ምርጫ በአንድ ሳምንት ተራዝሟል’ ተባልን። ይህን የሚለን ብዙ የተነገረለት  ገለልተኛ የተባለው የምርጫ ቦርድ ነው። እንግዲህ ”ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት” ማለት እዚህ ላይ ነው።

ለምርጫ ቦርድ በተለይም ለወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ማስተላለፍ የምንፈልገው ምርጫ በአንድ ሳምንት የተራዘመበት  ”ቁማር’’፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  መከላኪያ የህዝብ ወይስ የህወሓት?

-1-

ኦነግ/ኦዴፓ ብልጽግና  ከአዲስ እበባ ከተማ ውጭ  ኗሪ ለሆኑ እስከ ናዝሪት ድረስ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኦሮሞ ጎሳዎች  የአዲስ አበባን መታዎቂያ በገፍና በህገወጥ መንገድ አድሏላ። መቼም ይኽን ለማሰትባበል ከመሞከርግመልን በመርፌ ቀዳዳ ማሳለፍ ይቀላል።እንዚህ  የአዲስ አበባ መታወቂያ የታደላቼው በአገርዊ ምርጫ ከመረጡ ከአንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ለኦነግ / ኦዴፓ ብልጽግና በመዲነዋ የመመርጫ ወረዳዎች ተገኝተው ግዳጃቼውን ይወጣሉ።

ታዲያ  በዚህ ዓይነቱ ተራ ሸፍጥ ዜጋን ወይም አዲስ አበባን ህዝብ ለማታለል መሞከሩ  ተረኛ ገዥዎቻችን ምን ያህል ከወያኔ ያነሱና የወረዱ መንደርተኞች መሆናቸውን ይመሰከራል። እንደ ጡት አባታቼው ኮረጆ ቢገለብጡ ይመረጥ ነበር።  ይኽም ሆኖ  የአዲስ አበባ ህዝብ ለታላቋን ኢትዮጵያ ቅድሚያ  በመስጠት ትግሉን ያካሄዳል እንጅ  እናነት እንደምትመኙት ብጥብጥ ውስጥ ገብቶ አገር አያፈርስም። የህዝቡን ማንነትና የቆመበትና ማማ ደግሞ የአደዋ 125ኛ  የድል በዓል ሲከበር አሳይቷችኋል።

በ’ርግጥ አሁንም ቢሆን  አዲስ አበባን ለአዲስ አበቤ ተውለት፤ ተረኝንተ የትም አያደርሳችሁም፤  ከትላንቱ ወያኔ ተማሩ እንላለን። አዲስ አበባ የሁላችንም መዲና ብቻ ሳትሆን የኢትዮጵያዊነት ማሰሪያ ውል ናት።

————————–//————–ፊልጶስ

E-mail: philiposmw@gmail.com

2 Comments

  1. -Addis Ababa residents are not open to being manipulated by any city or federal government leaders, they tend to stand up for what they believe in if they find out some inappropriate actions are being taken by the leaders of Ethiopia, that is why the leaders like to keep them unaware of what is going on as much as possible, also the Addis Ababa residents are very well inter connected to ethnicities from all over Ethiopia.

    – Addis Ababa residents tend to criticize their country leaders rigorously whenever they feel the leaders of Ethiopia are doing something wrong ,regardless the actions the leaders of Ethiopia took directly affects Addis Ababa residents or not.

    -Our current leader of Ethiopia who got to power to advance so many hidden agendas very well knew he needed to in anyway possible keep those Addis Ababa residents weaker and distracted, so he can swiftly exert his hidden agendas allover Ethiopia. That is exactly why he do those awfull things he do against people of Addis Ababa by continuing the legacy of his former bosses who paved the way for him by illegally forging consituations to make Addis Ababa the EPRDFites playground with the residents having no rights at all , no right to the extent to even know how many people are actually considered registered officially by the government as residents in their own home they live in.

  2. We support Takele Uma , Abiy Ahmed and Adanech Abebe in any way possible if they right away make Finfine officially part of the Oromia region. Oromia can not be free until Finfine is officially declared to be part of the Oromia region.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share