በሃገራችን ኢትዮጲያ የህዝቦች መብት በተለይ የገባሮች ይከበር ዘንድ መስዋእትነት የከፈሉ ብዙ አእላፋት ሲኖሩ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል:: በተመሳሳይ መልኩ ያደረጉት ስ ህተትም ለመጭው ትውልድ ለትምህርት መዘከር ይኖርበታል:: በአሁኑ ወቅት ግን ፖለቲከኞችና አክቲቪስት ነን ባዮች መሪዎች ጭምር በዘር ላይ የተመሰረተ ድጋፍና ትችት ሲያቀርቡ በጣም ያሳዝናል የበለጠ የሃገራችንን ውድቀት ያስከትላል::
ሃገራችን ኢትዮጲያ ከታላላቅ ቀደምት ሃገሮች ተርታ እንደነበርች የጥንት ታሪክ ጸሃፊዎች ሄሮድተስ ሆሜር ቅዱሳት መጽሃፍትም ይገልጻሉ:: ሆኖም ግን በመካከለኛው ዘመን የነገስትት ልጆች በስልጣን ፉክክር በመጠመዳቸው የኦቶማንናን የቱርክ ወራሪ መንግስትትም ህዝባችንን በሃይማኖት በመከፋፈላቸው ሀገራችን ከከፍታ የወረደችበት ሁኔታ ተከስቶ ነበር::
የመስፍንት የባላባት ዘመን ያበቃ ዘንድ ኢትዮጲያ አንድ ትልቅ ሃገር ትሆን ዘንድ መይሳው ካሳ አጼ ቴዎድሮስ ብዙ ዋጋ ቢከፍሉም በጭካኔ የጠቀለሏቸው የሃገራችን ህዝቦች በንጉስቹ መሪነት ለወጭ ጠላት እንግሊዝ መንገድ መርተው ራሳቸውን ባጠፉበት ወቅት በተራ መንደር ብቻ የተወሰነ ግዛት ነበራቸው::
ከአጼቴዎድሮስ በኋላ ስልጣን የያዙት አጼ ዮሃንስም በክፋት ቅጣታቸው ቀጥለው ሙስሊሞቹ በተለይ ከመሃዲስትና ደርቡሾች ጋር ተባብረው ለሞት ሲያበቋቸው ተፎካካሪዎች ነገስታት ምኒሊክና ተክለሃይማኖትም የሚተኙላቸው ኣልነበረም:: ምኒሊክ በዘዴ ስልጣኑን ጠቅልለው ሃገሪቱን በመግዛት በወራሪ ጣልያን ላይ ቀዳሚውን የጥቁር የአፍሪካ ድል አስገኙ:: ሆኖም ግን ሚኒሊክም ተቀናቃኝ የዮህንስ ልጅ መንገሻ ለጦርነት ሲነሱ በራስ መኮንን ጉዲሳ ምልጃ በእርቅ አሰግብተው መልሰው በቁም እስር በማስገባታቸው ራስ መኮንን ተከፍተው ለምነና እንደበቁ ይነገራል;: ከዚያም አጼ ሃይለስላሴ አባ መላ ጮሌ የሚሏቸው ስልጣኑን ተረክበው የሚንሊክን የልጅ ልጅ ኢያሱን በዘዴ አስወግደው ብዙ ዘመናት ሲገዙ ጀግና አርበኞችን ማሰር መግደላቸውን በላይ ዘለቀና ታከለ ወልደሃዋርያት ይጠቀሳሉ::
የበላይ ዘለቀ የሞት ፍርድ ምክንያት እናቴ በላይ ብላኛለች ከዚያ በላይ የአጼውን ሹመት ኣለፈልግም በሚለው የንቀት ንግ ግራችው መሆኑ ብቻ ይወሳል የተቀሩት የሃገራችን የትግል መሪዎች ሞትና ስ ህተት የሚከተለው ነው:-
1ኛ ታከለወልደሃውርያት አርበኛና የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩ የሪፐብሊክ መንግስት ለመመስረት የታገሉ አጼሃይለስላሴን ለመግደል አሸምቀው ሲይዙ ራሳቸውን አጠፉ
2ኛ የነግርማሜ ነዋይ መንግቱ ነዋይ አጼ ሃይለስላሴን አገዛዝለመለወጥ ስልጣን በኩዴታ ለመጣል ሲሞክሩ በጦርሰራዊት ተይዘው ተገደሉ ተሰቀሉ
3ኛ ማሞ መዘመር የኦሮሞ መብት ይጠበቅ ዘንድ የታገለ የአየር ሃይል መኮንን የሲኒማ ኢምፓየርን ለማወደም የፈንጂ ጥቃት በማድረጉ ተይዞ በስቅላት ተቀጣ
4ኛ ዋለልኝ መኮንን ማርታ መብራቱና ባልደረቦቻቸው የኢትዮጲያ ኣውሮፕላንን ለመጥለፍ በመሳሪያ ሃይል ሙከራ ሲያደርጉ በኮማንዶዎች ተገደሉ
5ኛ ዋቆ ጉቱ የባሌ ኦሮሞዎችን ንቅናቄ ያቀናበረ ሲማረክ በንጉሱ ለራሱ የሰጠው ጄነራልነት ተጠብቆ ቪላ ቤት ተሰጥቶት ሲኖር ቆይቶ ሶማሌ ኢትዮጲያን ስትወርር የምአራብ ሶማሌ ጀነራል የሚለውን ተቀብሎ ሃገሩን ከዳ ቆይቶ ታሞ ሞተ;:
6 ኛ ቄስ ጉዲና ቱምሳ ከወንድማቸው ባሮ ቱምሳ የኦነግ መስራች ጋር የኦሮሞ መብት ትግልን ባሮ በባሌ በአክራሪ በልደረቦቹ ሲገደል ትግሉን በቤተክርስትያን መቀጠላቸውን ደርግ ሰምቶ ይተዉ ዘንድ ጀነራሎችን ታዬ ጥላሁንና ሌሎችን የታንዛኒያን መሪ ነሬሬን የኖርዌይ ሚሲዮን ሃላፊ ጭምር ፐኦለቲካውን ይተው ዘንድ ተጠይቀው እምቢ በማለታቸው ለጎጃሜዎች አደሉ ተብለው ከተከሰሱት አቡነ ቴዎፎልስ ጋር በደርግ ተገደሉ;: ቄስ ጉዲና በሚኒሶታ ዛሬ ኢትዮጲያ ትወደም የሚለውን ትውድል ላፈራው የዘረኘነት እርም ያበቁ እንጂ ደጋፊዎቻቸው እንደሚሉትና ዶ/ር አብይ በቅርቡ እንደተናገሩት በሰላማዊ ወይም መንፈሳዊ ትግል የተሰዉ አይደሉም::
7 ኛ የግንቦቱ መፈንቀለ መግጽ ጄነርሎች ኮሎኔል መንግስቱን ለመገልበጥ ሴራ ማድረጋቸውን የመንግስቱ ሰላዮች መረጃ ሰጥተው ሰው ቀርቶ ትንኝ መግደል አልፈልግም የሚሉ ተቃዋሚዎቻቸውን ሲገድሉ ግን ለቁርስ ያሰቡንን ምሳ አደርግናቸው በሚሉት ኮሎኔል መንግስቱ ተሳታፊነት በዘግንኝ ሁኔታ በብረት ተቀጥጥጠው በሳንጃ ተውግተው ተገደሉ::
ስለዚህ የሃገራችን መጻኢ እድል ይሰምር ዘንድ ሚዛናዊ ድጋፍና ትችት ለትግል መሪዎችና የፖለቲካ መሪውች በበመስጠት ሃገራችንን የጤናማ ፖለቲካ መድረክ እናድርጋት::
ዲጎኔ ሞረቴው ከሚድዌስት አሜሪካ የካቲት 2013