November 4, 2017
6 mins read

የማዳኛው ክኒን ኢትዮጵያዊነት ነው

ገብርኤል ብዙነህ

የእኛን መኖር ማሳወቂያውና የማዳኛው ክኒን ኢትዮጵያዊነትነው።እንደ ሰው ለተፈጠረ ህሊና ላለው ፍጡር። በዚህ የአንድነት ቡቃያዎች የፍቅር መርከብ ሁሉም መሳፈር ይኖርበታል። የአማራና ኦሮሞ ህዝብ አንድነት ለኢትዮጵያ አንድነት ነው። ሆኖም ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ናት። የአፍር የትግራይ፣ የደቡብ፣ የቤኒሻንጉል ፣የጋምቤላና ወ.ዛ.ተ ህዝብ ከኢትዮጵያ ሌላ እናት የለውም። እናም የኦሞና የአማራ ወጣቶች ባሳዩት ፍቅር በተለይ የትግራይ ህዝብ የሚነቃበት ጊዜ አሁን መሆን አለበት።

በእኔ እምነት የትግራይ ህዝብ ወንድምና እህቶቹን የሚጠላ አይደለም።ነገር ግን የወያኔ ነገር” አማራና ኦሮሞ አብረው መቆም ከጀመሩ ያኔ ድርጅቴ ህውሀት ማቅ ትለብሳለች፣ የትግራይ ህዝብ ህልውና በአመሰራውና በኦሮሞው ፍቺ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ለአፍታም መዘንጋት የለበትም፣ መልሰው ጋብቻ የሚፈጥሩበት platform ካገኙ ህውሀት በይፋ ያከትምለሰታል ” መለስ ዜናዊ ከ16 አመት በፊት በትግርኛ ቋንቋ ከተናገረው።“ቅዠት” ባልጠበቀው በወያኔ ፀረአንድነት መንገድ አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ ተደረገ እንጂ ስለዚህ ያለፍላጎቱ የተፈጠረበትን የአንድነት ክፍተት የሚሞላበትን ስልት ለመፈለግ ከዚህ በላይ አጋጣሚ ሊኖር አይችልም።የ100 ሚሊዮን ህዝብ ልብ ሸፍትዋል። አያት ቅድመ አያቶቸው ደማቸውን ያፈሰሱበት፤ አጥነታቸውን የከሰከሰቡት አገር የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የፍቅር ልብ ለሁሉም ክፍት ነው። አማራና ኦሮሞ ዜጎች የከፈቱት የፍቅር አዳራሽ ለማንም አይጠብም።

ኢትዮጵያውያን አስተዋይ የኦሮሞና የአማራ ወጣቶች ባቀጣጠሉት የፍቅር መብራት እየተመሩ የደበዘዘ የአንድነት ታሪካቸውን ዳግመኛ ሊያደምቁት ይገባል። የኦሮሞ ወጣቶች የጀመሩት የታሪክ እርማት ስርዝ ድልዝ ባለበት ገፅ ሁሉ ለኢትዮጵያ የህልውና ተጋድሎ ወጣታዊ ተጋድሎ ሊቀጥል ይገባል የኢትዮጵያ ጉዳይ እረመጥ ነው ። እናንተ የኦሮሞና የአማራ የኢትዮጵያ ወጣቶች፣ ባስተዋይ ምግባራችሁ ሁላችንም ኮርተናል፤ ኢትዮጵያም ለዘላለም ትኮራባችኋለች።አሁን ላለው ወጣት ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤ ለጎልማሳው ትውልድም ልዩ የክብር ስጦታ ነው፤ ኢትዮጵያዊነት የትናንቱን ታሪክ የሚያስቡበት ብቻ ሳይኾን ዛሬ የሚኖሩበት ነገም ተስፋ የሚያደርጉበት ሕይወት ነውና፡፡ የኦሮሞና የአማራ ወጣቶች ላቀጣጠሉት የፍቅር መብራት ለህልማቸው፤ ለተስፋቸው፤ ለራዕያቸው፤ ለተፈጥሯቸው፤ ለመክሊታቸው ልዩ የሆነ ተጨማሪ ጥበባዊ አትኩሮትና እንክብካቤ በእጅጉ ያስፈልጋቸዋል።

በእውነት ነው ምላችሁ እኔ መንግሥት እንደተቀየረ ያህል ነው የተስማኝ !!!! ኢትዮጵያዊነት የአንድነት መሠረታዊ የኢትዮጵያውያን የመንፈስ ጥንካሬ ውሳኔ መሥፈርት ሚስጢር ነው። የእኛን መኖር ለኢትዮጵያ ማሳወቂያውና የማዳኛው ክኒን ኢትዮጵያዊነት ነው። ለአገራችን ኢትዮጵያ ለሕዝቦቿ ተወደድም ተጠላም በአገሪቱ እየነደደ፣ እየተንቀለቀለ ባለው የብሶት እሳት ሠቆቃ ጋር ይኸው 26ዓመት የፓለቲካ ጨዋታ ይብቃ እንደ የኦሮሞና የአማራ ወጣቶች በኢትዮጵያ ምድር ሆኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ነው የሚፈለገው ! በብኩን ቀትረ ቀላል የፖለቲካ የትግል ጉዞ ልንኖር አንችልም የታሪክ እስረኞች አይደለምና….ለኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነትና ነጻነት የታገለና የሞተ ሕዝብ ከራሱ ሊገነጠል አይችልም መብቶች መከበራቸውና ዲሞክራሳዊ ስርዓት መፈጠሩ አይቀርም።አብሮና ተባብሮ አገርን የማዳን፤ ሕዝብን ከከፋ እልቂት የመታደግ ብሄራዊና ሕዝባዊ ትግል ነው። ኢትዮጵያን ከመፈራረስ፤ ሕዝቧን ከከፋ እልቂት ለመታደግ የሚችለው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ብቻ ነው።

“ኢትዮጵያ አገሬ፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነው”
የእኛን መኖር ማሳወቂያውና የማዳኛው ክኒን ኢትዮጵያዊነትነው።
እንደመሸ አይቀርም ይነጋል አትፍራ! ጠበቃህ እግዚአብሄር ነው!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

Ethnic Federalism
Previous Story

ከዘውግ ወዯ ስሌጣን ፖለቲካ እዴገት ወይስ መጫጨት (ቀጣዩን ጊዜ በማን እጅ )???

Next Story

“የህወሓትን ሕዝባዊ ጭፍጨፋና ከፋፋይነት እንኮንናለን፣” – በኮሎኝና አካባቢዋ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ/ኮሚኒቲ ኮሎኝ/ጀርመን

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop