March 1, 2022
7 mins read

አድዋን ከሚኒልክ የመለየት አባዜ የኦነጋውያን ቅዥት – ጥሩነህ

274996382 10219608950166763 7178637155815224312 nአፍሪካውያን የሚኮሩበትን የነጻነት ፈና ወጊ የኦሮሞ ጽንፈኖች ያፍሩበታል፤ ይጠሉታል። በነሱው ልክ ሊያወርዱት የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ይጠቀማሉ። በትናንትናው የውሽት ትርክት ላይ እንደቆሙ ዛሬን መኖር ተስኗቸው ነገም እንደጨለመ ያዩታል።

አድዋ ያለሚኒሊክ ለመዘከር መሞከር ልጅን የለናት ተወልደሃል እንደማለት ነው። በአሉ ከሚኒሊክ አደባባይ ወጥቶ አድዋ ድልድይ ላይ ይከበር ማለት ታሪክን ከመሸርሸር የመነጨ የበታችኝነት ስሜት የወለደው መድሃኒት የለሽ በሽታ ነው። የአድዋ ድልድይ ትንሽ መንገድ ላይ  ናት፤ ምኒልክንና ታሪካችንን እንዲሁ ለማሳነስ የተወጠነ የኦነጋውያን ቀቢጸ ተስፋ ነው። ይህን የወሰነው የጫካው ኦነግ አይደለም በመንግስት ውስጥ የተንሰራፋው ባልጊዜው ኦነግ እንጂ። ሽኔ ኦነግ ነው ኦነግም በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ ሃገር ለማፍረስ ከውያኔ ጋር የሚሰራ አካል ነው።

275022965 2265814380241707 58718123955670004 n
የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነጻነት ምልክት አድዋን ድልድይ ስር እንዲከበር ሲታትር የነበረው ኦነጉ ቀጀላ መርዳሳ???? ….ለማንኛውም ነገ መንገዶች ሁሉ ወደ እምዬ ምንይልክ አደባባይ ያመራሉ

እኒህ የታሪክ ስንኩላን ዛሬ ከሚኒልክ አደባባይ ውጭ ይከበር ሲሉ ነገ ምናላባት ስንዳፋ ያደርሱታል ቀጥለውም የምን አድዋ ሊሉን እየተዘጋጁ እንደሆነ እንረዳለን። ታሪክን እያለዘቡ እየሽረሸሩ ማፍረስ ማለት ይህ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በማያዳግም መልኩ እምቢታውን የሚያሳየው ሁልጊዜም ወደሚከበርበት አደባባይ በእቢተኝነት ሄዶ ሲያከብር ነው። ኦነጋውያን በተለያየ መልክ ታሪክን ለማጥፋት የራሳቸውን የውሸት ትርክት ለመትከል ጥረት ማድረጋቸው ይቀጥላል። መልሳችን ግን ወይ ፍንክች ነው።

የኦዴፓ ቀንደኛ ብልጽግናዎች ልባቸውን አሁንም ለኢትዮጵያ እንዳልሰጡ ብዙ ማሳያወች አሉ። ይህ አንዱ ነው። መገንጠሉ ቢቀር አሁንም የበላይነቱን በጥብቅ የሚቆሙለት እንደሚሉትም ከሆነ የሚሞቱለት አላማቸው ነው። በህዝብ እኩልነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያ ህልማቸው አይደለችም። ዛሬ ግብግቡ በአድዋ አደባባይ ነገ መስቀል አደባብይ ከዚያም ፊንፊኔ ኬኛ ይቀጥላል።
ለዚህ ነው ስለ እኩልነትና ስለሰወች መገፋት ሲወራ የሚያንቀጠቅጣቸው። የታሪክ አንካሳወች የሚሆኑት።  ሃሳብን በወጉ ከማቅረብ ይልቅ በድብቅ ተንኮል ላይ ተኝተው በበታችነት ስሜት የሚዋኙት። የበላይነትና የማጠቃለል ስሜታቸውን የጠበቁ እየመሰላቸው ታሪክን ሲገዳደሩና ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካዊ ድንቅ ስም ያላቸውን ዝቅ ለማደርግ የተለመድ ለቅሶ የሚያሰሙት።

ወያኔ በመከፋፈል የገዛውን፣ የበዘበዘውን ኦነጋውያን የቁጥር የበላይነት አለን ብለው ስለሚያምኑ በመጨፍለቅ እውን ሊያደርጉት እየባከኑ ነው።እንደአስተማሪወቻቸው ታሪክን ፤ዘርን ለማጥፋት የሚባዝኑትም ለዚሁ ነው።  ብዙሃን የሞቱለት የእኩልነት፤ የነጻነት ትግልና ታሪክ  ለኦነጋውያን የሚዋጥ አይደለም።
የኢትዮጵያ ህዝብ  ይህን አድሃሪና ሁሉ ኬኛን ስግብግብነት በመተባበር ማምከን አለበት። ዛሬ የአድዋ በአል ይሁን እንጂ የታሪክ ሽሚያውና ትርክቱ እግር እየሰደደ ነው። ዝም ከተባሉ የዛሬዋ አዲስ አበባን ነገ ላይ አናገኛትም። ይህ ደግሞ የሁሉም ትግል ነው።

ትግሉ የጋራ ነው። እምቢተኝነቱ የውል ነው። በተናጠል የሚገኝ ድል የለም በእብሪተኞች መዋጥ እንጂ። ኦነጋውያን ተስፋ የሚያደርጉት ወያኔ በቀደደላቸው በዘር የተከፋፈል ህዝብ ምንም አያደርግም ነው። አድዋ ዘር የለውም ከኢትዮጵያ አልፎ ለሁሉም ጥቁር ህዝቦች የድል ኩራት ነው።

አንዳንዶች የትስ ቢከበር ምን ችግር አለው ይሉናል። ታሪክን ቀስ በቀስ መሽረሽርና ብሎም ማፍረስ ችግር የለውም ካሉን እነሱ ኦነጋውያን ናችው። ዛሬ አንድ ጫማ ከሰጧቸው ነገ በሜትር ይወስዱታል። ማስቆም አሁኑኑ ነው።

የአድዋ በዓላችንን  በምኒልክ አደባባይ እንዘክራለን

 

Minilik

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop