ከዚህ በታች የማሰፈረው ሃሳብ እንደመነሻ ነው። ስለዚህም በሃስቡ የሚያምን እንዲደግፈው፣ የማያምን ደግሞ እንዲተችበት ወይም አማራጭ የመፍትሄ ሃሳብ እንዲሰጥ፤ በአጠቃላይ ለአገራችን በተለይም ለአማራ ብልጽግና መፍትሄ የሚሆንና ገንቢ ሃሳብ ለማሸራሸር መሆኑ በቅድሚያ ማስገንዘብ እወዳለሁ።
በኔ እምነት ይህ ስልጣንን ለህዝብ አሳልፋ የመስጠት ምክረ-ሃሳብ ለአማራ-ብልጽግና ብቻ ሳይሆን ለማዓከላዊ አገዛዝ ለብልጽግናዎች ብሎም ለመላው አገሪቱ የሚበጅ ነው ብየ አምናለሁ። ነገር ግን ወያኔም ወያኔ ነው። ተረኞቹ ኦሮሙማዋችም ‘”ኢትዮጵያን ተቆጥጥረናል፣ የማይነቃነቅ ልዩ ኃይልም ገንብተናል፤ ነፍጠኛንም ከግራ-ከቀኝ እያጠቃናቸው ግራ -እያጋባናቸው ነው።”’ ስላሉና ፤ ወያኔ ራሱ ጠፍጥፎ የሰራቸው ኦሮሞን እንወካላለን የሚሉትንና ለአማራ እንታገላላን የሚሉትን በተላላኪነት እያባላ ሃያ ሰባት ዓመት እንደገዛ ሁሉ ፣ ተረኞችም በተራቸው አማራንና ወያኔን እያባላን እስከቻልን ደረስ እንገዛለን፡ ካለያ ” ማርና ወተት የሚፈስባትን ኦሮሚያን እንገነባለን። ብለው ከብዙሃኑና ከሰላም ወዳዱ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትና ዓላማ ውጭ ፤ በስሙ የሚምሊና ይሚገዘቱ በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን፤ ከዚህ በፊትም ለቁጥር የሚያስቸግር አገራዊ ምክር ቀርቦላቸው ያለተቀበሉና በአገራዊ ምክክር ስም እድሚያቸውን እያውናበዱ፤ የፓልቲካውን ቁማር በልትነዋል ብለው ያመኑ በመሆናቸው ነው።
ቅንነት፣ ህዝብንና አገርን ማስቀድም ቢኖርማ የአሁኖቹ ተረኞች ከጡት አባታቸው ከወያኔ አወዳደቅ በተማሩ ነበር። ሃቁማ ማንም በጎሳ ተደራጅቶና በጎሳ ተከልሎ ፤ አንዱን የበታች፣ ሌላውን የበላይ አድርጎ የዘር ማጥፋት ወንጅል እየፈጸሙ የሚጸና አገዛዝ የለም፤ የግዜ ጉዳይ እንጅ እንደተለመደው አገርን እና ህዝብን ለመከራ ዳርጎ መሸኘት አይቀርም፤ ያውም ከውርደትና ከሃፍረት ጋር።
የሄደው ሲመጣ፣ የመጣው ሲሄድ
መውጫና መውረጃው ሆኖ ያአገር መንገድ፤
ብዘራው አይበቅል፣ ቢበቅል አያፈራ
መጠላለፍ ብቻ ሆነ የ´ኛ ሥራ።
በተለይም በአሁኑ ሰዓት የአማራ ብልጽግና የሚባለው ቡድን ፡ የተላላኪነቱን ሥራ እንኳን መስራት ተስኖት፤ ህዝብን ከማስጨረስ አልፋ፣ አገርንም እያጠፋ ነውና “ ከነወንጀልህ ብዙ እድል አግኝተሃል፤ ከአሁን በኃላ ግን በቃህ።” መባል ስላለበት ነው። ህዝብም ለማይቀረው ትግል ራሱን ማዘጋጀት አለበት።
እናም የአማራ ብልጽግና ሆይ፤ ብዙ በልተህ ብዙ ለማበት፤ ብዙ ጠጥተህ ብዙ ለመሽናት ፣በአማራ ህዝብ ላይ ብሎም በኢትዮጵያ ላይ የሰራህው ግፍ አንደብት ሊገልጸው አይችልም፤ መጸሃፍ ሊከተበው ቃላት አያግኝም።
ግን በገሃዱ ዓለም የሚታወቀውንና ኢትዮጵያን ለዚህ ያበቃችኋት ከወያኔም ሆነ ከአሁኖቹ ባለግዜዎችና ተረኞች በበለጠ እናንተ ናችሁ። ምክንያቱም ሌሎቹ ሌላው ቢቀር ኢትዮጵያን የማፍረስና ነፍጠኛን የማጥፋት ዓላማ አላቸው። እናንተ ግን ትላንትም ሆነ ዛሬ በሆዳችሁ እያሰባችሁ፣ ለሆዳችሁ የምትኖሩና ለሆዳችሁ የገዛ አገራችሁንና ወገናችሁን የሸጣችሁ በመሆናችሁ ነው።
እስቲ ይታያችሁ፤ ኦህዲድ እንኳ´ ከተላላኪነት ወጥቶ ዛሬ ተረኛ በመሆን እናንተን ተላላኪ አድርጎ፡ እንደ ወያኔ ሁሉ ኢትዮጵያን ያፈርሳል፡ አማራን ያርዳል። እናንተ ግን መጸሃፍ እንደሚለው ” ህሊናችሁ በጋለ ብረት እንደ ተተኮሰ ሆኖ ደንዝዟልና–” ከሆዳችሁ ውጭ ሌላ ዓለም የላችሁም። ግን አሁንም ቅዱሱ መጸሃፍ ” እንጀራም የተሰራው ለሆድ ነው፤ ሆድም የተሰራው ለእንጀራ ነው፤ ሁሉንም ግን እግዚአቢሄር ያጠፋቸዋል።” ይላል።
የእማራ ብልጽግና ሆይ! እስከ አሁን በእናንተ ተላላኪነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት የፈሰሰው ደምና የጠፋው የሰው ህይወት ከአዕምሮ በላይ ነው። ከዚህ በኋላ የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ እናንተን የሚሸከምበት ጫንቃ የለውምና በስምምነና በሰላማዊ መንገድ የያዛችሁትን የተላላኪነት ኃላፊነት አስረክቡ።
ያለያ ግን የኢትዮጵያም ህዝብ ሆነ በምስለኔነት የምትገዙት በየቀኑ የሚታረደው ህዝብ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል። ለዚህ ጉዳይ ተፈጻሚነት ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለሰው ልጅ መብት ቁመናል የምትሉ ሁሉ፤ የተደራጀ ትግል ማድረግና እንደ አስፈላጊነቱ ሰላማዊ ሰልፍ ከማዘጋጀት ጀምሮ ትግሉ ግቡን እስኪመታ በአብሮነት መታገል የህልውና ጉዳይ መሆኑ መዘንጋት የለበትም።
ምክንያቱም ከአሁን በኋላ ህዝብ የሚቀርበት ነገር ቢኖር እንደ በግ እየተጎተተና እንደ አውሬ እየታደነ መገደል ፤ ብሎም አገር አልባ መሆን ነው። እናንተን በማሰውገድ ግን ራስን ከመከላከል አልፎ፤ አገርን ለመታደግ የሚያስችል ኃይል መፍጠር ይቻላል።
የእማራ ብልጽግናዎች ሆይ! የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታን ጠይቃችሁ፤ የያዛችሁትን ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ ለማሰርከብ ተባበሩ። ይህን ብታደርጉ እናንተም ሆነ አገር ተጠቃሚ ይሆናል። ስለዚህም፤
1/ እናንተን የሚተካ በመላው የአገሪቱ ከምሁራን (አውነተኛ ምሁር)፣ ከተከበሩ የአገር ሽማግሊዋችና ለስጋቸው ሳይሆን ለነፍሳቸው ካደሩ የሃይማኖት አባቶች፤ እንድ የባለአደራ አስተዳደር ጉባኤ (አስተዳደር) ይቋቋም።
2/ የዚህ የባለአዳራ ጉባኤ እባላት ከማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲና የጎሳ ቡድን የሌሉበት፤ እስከ አሁንም ያልተሳተፋ፣ ወደፊትም የማይሳተፋ መሆን አለባቸው።
3/ ይህ የባለአደራ ጉባኤ የአማራ ብልጽግና ተተኪዎችን በተዋረድ ከህዝብ በሚያገኘው ድምጽና ጥቆማ በግልጽና በይፋ ይመርጣል። ተተኪ ተመራጮች ከዚህ በፊትም ሆነ ወደፊት በማንኛውም የፓለቲካም ሆነ የጎሳ ቡደን ያልተሰተፍና የማይሳተፋ መሆን አለባቸው።
4/ ለአማራ ብልጽግና ተተኪዎች ከተመረጡ በኋላ፤ ኃላፊነታቸ ከአማራ ብልጽጋና ይረከባሉ። ለአማራ ብልጽግናዎችም በግለሰብ ደረጃ እስከ አልሆነ ድረስ በባለአደራው ጉባኤ ከህግ – ተጠያቂነት ነጻ መሆናቸን ማረጋገጫ ይሰጣቸዋል።
8/ የአማራን ብልጽግና የተኩት ኃላፊዎች ቀጥታ ተጠሪነታቸው ለባለአደራ ጉባኤ ሲሆን፣ እንደ ከፍተኛው የስልጣን አስተዳደር ሆኖ ያገለግላል። የአማራን ብልጽግና የተኩና ከፍተኛ ኃላፊነት የተሰጣቸው በወደፊት ከሚደረግ ፓልቲካዊ ስልጣን የታገዱ ይሆናሉ።
7/ የባለአደራው ጉባኤ ዘመን በራሱ በአባላቱና ከዓላማው ግብ ጋር በሚፈጽማቸው ተግባራት የሚወሰን ሲሆን፤ ህዝብ በባለአዳራው ጉባኤ አማካኝነት ተደራጅቶ አስተዳደሩን መጠበቅ፣ ህግና ሥረዓትን የማስከበር ኃላፊነት እንዲወስድ ያደርጋል።
7/ የባለአደራው ጉባኤ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር በኢትዮጵያና በህዝቧ አንድናተ፤ እንዲሁም የህዝብን መሰረታዊ መብት በማይነካ መንገድ ፤ ግልጽና ለህዝብ ይፋ የሆነ ውይይት በማካሄድ ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ህግ-መንግሥት በህዝብ እንዲረቀቅና እንዲጽደቅ ያስደርጋል።
8/ በመጨረሻም በአዲሱ በህዝብ በረቀቀውና በጸደቀው ህገ መንግሥት አማካኝነት አገራዊ ምርጫ አካሄዶ፣ ለተመራጮች ወይም ለአሸናፊ ፓርቲዎች ኃላፊነቱን ያስረክባል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!
——–//—-ፊልጶስ
Email: [email protected]