ያንተ በስፋት የተሰራጨ ውሸት እነርሱ በጃቸው ከያዙት እውነት በላይ ተሰሚነት ያገኛል
(እውነቱ ቢሆን)
ወያኔወች፦ አምናም ውሸት፣ ትናንትም ውሸት ፣ዛሬም ውሸት፣ ዘለአለም ውሸት፣ ውሸት ውሸት .. አሁንም ነገም ውሸት ብቻ ናቸው፡፡ ይህንኑ ማንነታችውን በትክክል ለመግለጽ ይረዳ ዘንድ በመረጃ ፎረም ላይ ከአንድ ጸሀፊ ያገኘሁትን ወያኔ ማለት ሙሉውን ውሸት መሆኑን አሳምሮ የሚገልጽ አጭር ጽሁፍ ጽሁፉን እንደወረደ ከስር አቅርቤዋለሁ፡፡
የዲጅታል ወያኔ ማኒፈስቶ፦
ዋሽ፡፡ ነገር ግን በምትዋሽበት ጊዜ ትንሽም ብትሆን እውነትን አትቀላቅል፡፡ በቃ እስከመጨረሻው ድረስ ዋሽ! የእውነታው ድራሹ እስከማይታወቅ ድረስ በውሸትህ ጽና፡፡ ሁሉም ራሱን መጠራጠር እስከሚጀምር ድረስ ውሸትን አቀናብራት፣ ሽፋን እንድታገኝ አድርጋት፣ ሀሰተኛ ዘገባ ዘግብ፡፡ ማንም ባያምንህም በውሸትህ ጽና፦ በሷ ላይ ተመስርተህ ቀጣይ እርምጃህን ፈጽም፡፤እራስህ የፈጠርከውን ሀሰት እራስህ አሰራጨው፡፤ ከዚያም ለእርሱ የሚመጥን እርምጃ ውሰድ፡፤ ያኔ ሁሉም ሰው በግራ መጋባት ውስጥ ሁኖ ጆሮ ይሰጥሀል፡፡በተቻለ መጠን የሀሰት ማስረጃወችን አሰራጭ፡፡ ያሰራጨሀውን ሀሰተኛ መረጃ የሚያጠናክሩ የሀሰት ምስክሮችን ከየአቅጣጫው አዘጋጅተህ አቅርብ፡፡
የሚያዉቁህ በሙሉ አያምኑህም፡፡ አይሰሙህም፡፡ እነርሱን እርሳቸው፡፡ አይናቸው እያየ ጆሯቸው እየሰማ በአደባባይ ሀሰተኛ መረጃን ልቀቅ፡፡ እነርሱ እውነቱን ስለሚያውቁ እነርሱን ለማሳመን አትጃጃል፡፡ ይልቅ በተደራሽነትህ ተጠቅመህ ቅደማቸውና ያንተ ሀሰት የእነርሱን እውነታ እንድሸፍን አድርግ፡፡ያኔ በዙሪያህ ያለው ህዝብ እውነቱን ስለሚያውቅ አንተን እና የሀሰት ፕሮፓጋንዳህን አምርሮ ከመጥላት ውጭ ምንም አያመጣም፡፡ ነገር ግን ያንተ መረጃ በመላው አለም ተቀባይ ይሆናል፡፡ ተቃዋሚወችህ እውነቱን በጃቸው ይዘው ቁመው ይቀራሉ፡፤ የማያውቅህ የሩቅ ሰው ግን አማራጭ አጥቶ ከአንተ ጎን የመሆን እድል ይኖረዋል፡፡
ተቃዋሚወችህ አንተ ደረሰብኝ ያልከውን ሁሉ ባይፈጽሙትም አንተ ራስህ እነርሱን መስለህ ድርጊቱን ተውነው፡፡ ንጹሀን ተገደሉብኝ ካልክ በቃ ንጹሀን እንዲገደሉ አድርግ ወይም ማንነትህን ሰውረህ ንጹሀንን ግደል፡፡ ይህ የትግሉ መንገድ ነው፡፤ ድሉን ለማግኘት ማንኛውንም ነገር መፈጸም ግድ ይልሀል፡፤ ንጹሀን በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉብኝ ብለህ ካሰራጨህ እና ተቃዋሚወችህ ያንን ካልፈጸሙት ይህ ነገር እንድፈጸም የራስህን ድርሻ ተወጣ፡፡ ንጹሀን በሚገኙበት ቦታ ዉጊያ ክፈት፡፡ ንጹሀን አልወጣ ካሉህ ዉጡና ተዋጉ በላቸው፡፡ እምቢ ካሉህ ማንነትህን ሰውረህ የጠላትን ገጽታ ተላብሰህ ጥቃት አድርስባቸው፡፡ ከዛ ሜድያ ላይ ውጣና ድርጊቱን በእጅጉ አውግዝ፡፡ ማውገዝ ብቻም ሳይሆን አጸፋ እወስዳለሁ ብለህ ተናገር፡፡ ዋሽ፡፡ እየዋሸህ ጽና፡፡ የዋሸሀውን ውሸት ሌላው ባያምነው አንተው እመነው እና በዛ ተመስርተህ አጸፋ መልስ ስጥ፡፡ ነገሩ ከቅም በላይ ሲሆንበት ሁሉም ይምታታበትና ያንተ ውሸት ከእነርሱ እውነት በላይ ተሰሚነት ያገኛል፡፡
ይህችን ከመረጃ ፎረም ላይ ያገነኋትን አጭር ነገር ግን የወያኔን ማንነት ቁልጭ አድርጋ የምትገልጽ አጭር ጽሁፍ ልኬያለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር