January 4, 2022
10 mins read

 ነፃነት በአድርባይነት እና በችሮታ አይገኝም  

Freedomኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን ከስሩ ለማጥፋት የተለያዩ ደረጃዎች እና ክፍሎች ሲታይ  አሁን ላይ የመጨረሻዉ የአጥፍቶ መጥፋት ትንቅንቅ ተጋድሎ ቀጥሏል ፤ ብሷል  ፡፡

ለዚህም የጥፋት እና ሞት መላ ምት በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ፡-

፩ኛ. ኢትዮጵያዊነት አንድነት እና ህብረት መናድ፣

፪ኛ.  ኢትዮጵያዊነት አመላካች ታሪክ መሸርሸር እና ማደናገር /ማዛባት ፣ማሳጣት ፤መቀማት ፤

፪ኛ. ማንነት ተኮር ማጥላላት፣ ማግለል፣ ማፈናቀል፣ ማታለል ፣መግደል ፤

፫ኛ. ኢትዮጵያዊ መሰረትን እና ብሄራዊ ኩራትን ማናጋት፣

፬ኛ. የራስን የጥፋት እና የዉድቀት አስተሳሰብ እና ድርጊት በመደበቅ  አሁን የምንዋደቅበት አገር በደም እና አጥንት ያቆዩዓትን  አገር በበጎ ምግባር እና ተግባር ባለቤት የሆኑትን የአገር ባለዉለታዎች ስም እና ስራ ማጉደፍ ፤

፭ኛ. ኢትዮጵያዉያን በትዉልድ አገር ምድር እና አፈር ባይተዋር በማድረግ የሚኖሩባት አገር ማሳጣት ለአለፉት ፴(ሠላሳ) ዓመት  በዕቅድ የተሰራበት የዉስጥ ጠላቶች የረጅም ጊዜ ምኞት እንደነበር መርሳት ባልተገባ ነበር ፡፡

ይህ ሁሉ በነበረበት የኢትዮጵያ ነባራዊ የዘመናት ተግዳሮት ፫ኛዉ  ብሄራዊ ክህደት ከታወጀበት ጥቅምት ፳፬ ሁለት ሽ  አስራ ሶስት ዓ.ም. ጀምሮ የሚታዩ እና የሚሰሙ  ለዕዉነተኛ ነጻነት ማብቃታቸዉ ሲበዛ የሚያጠራጥር ስለመሆናቸዉ  የሚያጠያይቅ አይሆንም  ፡፡

ለዚህም ከ ፭ ቱ ፬ቱን ወደ ዉስጥ ከመመልከት ይልቅ ወደ ወጪ ማንጠራራት እንደ ስልት መያዝ  ከመደንዘዝ የማያልፍ ለመዘናጋት እና ዝገት መዳረጋችን ምድር ላይ ያለዉ እና እየደረሰ ያለዉን ማወቅ ተገቢ ነዉ ፡፡

ለዚህም ዕዉነተኛ ስም እና ተግባር በተጨባጭ ማየያዝ አለመቻል ሲሆን  ይህም  ፡-

የጥቅምት ወር ሁለት ሽ አስራ ሶስት የወረራ እና መስፋፋት ህልም “ብሄራዊ ክህደት” ሆኖ ሳለ   “የህግ ማስከበር ” ማለት  ፣

የጥፋት እና ሞት አዋጂ በአማራ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያ ሲታወጂ “ ከሀዲ እና ገዳይ” እንደማለት “ጁንታ” ፣ ማለት ፣

ጦርነት ምሽት ተጀምሮ  ሳይነጋ ድል አድራጊነትን አሜን ብሎ መቀበል እና ማስተጋባት ለጦርነት እና የህዝብ መከራ ማብቃት መባቻ ማራዘም አስከትሏል፡፡  ይህን በሚመለከት ድል ሳታደርግ ድል አታብስር ፣ በጊዜያዊ ድል መዘናጋት ለሞት ነዉ በሚል ታህሳስ 2013 ዓ.ም. ስሙልን ማለታችን በወቅቱ በፅሁፍ ወጥቷል፣

በዚሁ ሶስተኛዉ የዉስጥ ችግር እና ጦርነት መቶ በመቶ መጠናቀቅ እና የጠላት እንደ ጉም መብነን በችኮላ የተበሰረ ድል አይሉት መደለል  የአሳር ጉዞዉን አራዝሞታል፤ ህዝቡን በተለይም ዓማራ የፍዳ ዘመኑን እንዲራዘም አድርጎታል ፣

የትግራይ ህዝብ እንዲሰራ  ፤ ትግራይ እንድትለማ ፤ ኢትዮጵያ እንድትወድም  ፤ ዓማራ እንዲከስም የትግራይ  መንጋ ወራሪ  እና መዝባሪ ዳግም የጥፋት እና ሞት ዝግጂት ለማድረግ ዕድል አግኝቷል፣

ከዚኅም በላይ ትግራይ ስትለማ ኢትዮጵያ ትታመም  ፤ ዓማራ ይክሰም ከማለት የማይለይ የጥፋት እና ሞት ዕድል በር እንዲከፈት መከላከያ ለቆ እንዲወጣ እና ጠላትም የጨረቅ መንገድ ያድርግልህ እንደተባለ ያለምንም ከልካይ ከትግራይ ዋሻ በመነሳት አስከ ጣርማ በር ዘልቆ በመግባት የያዘዉን አንጠልጥሎ ፣ የገደለዉን ገድሎ ፤የተረፈዉን አቃጥሎ እና ነቅሎ የምኞቱን  ዓማራን ማዳከም ኢትዮጵያን የማጥፋት የመጨረሻዉ ግብ “ ከሳጥናኤል ትብብር ጋር አስከ ሲኦል” የሚለዉን ፬ እጁን ምኞቱን አሳክቷል ማለት ይቻላል፣

የቀደሙት መዘናጋት ያስከተሉብን የመከራ ቁስል ሳይሽር ጠላትን ፣ አስተሳሰቡን እና ዕኩይ ድርጊቱን ማሳነስ እና መድበስበስም የጦርነቱን መነሻ እና መድረሻ በዉል ካለመረዳት ወይም ችግርን ወደ ዉስጥ ከመመልከት ወደ ዉጭ የማላከክ ልምድ የለቀቀን አይመስልም ፡፡ ጠላትን ወይምጥፋትን ከማሳነስ ድልን ማሳነስ ለዕዉነተኛ እና ዘላቂ ድል  ይጠቅማል ፡፡  አሁን በምንገኝበት ጦርነት ጠላት አከርካሪዉ ተመቷል  የሚቀረዉ እንደ ቃርሚያ  “መልቀም”  መባሉ በተጠለፍንበት መጠላለፍ እና መደነቃቀፍ እንዳይሆን ዛሬም ቢሆን ከትናንት  ስህተት ልንማር ይገባል፡፡

ማንም ራሱን እና አገሩን ዕወዳለሁ የሚል የኢትዮጵያ ህዝብ እና አንድነት ጠላት የዕርሱ ወዳጂ ሊሆን እንደማይችል የሚቀበል እና ለኢትዮጵያ ትንሳዔ በትጋት ከሚሰሩት እና ከሚኖሩት ጋር አሁን ህብረት እና አንድነት ሊመሰርት ይገባል፡፡

ኢትዮጵያዊ እየሞተ እና እየተገፋ በሚኖርባት አገር ዕዉነተኛ ዕድገት እና ብሄራዊ አንድነት የሚመጣዉ ዕዉነተኛ ነፃነት እና ሠባዊ መብት ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ ፡፡

ነፃነ ወይም ሞት ከሚል ሚዛናዊ እና ወቅታዊ አማራጭ ዉጭ በአድርባይነት በችሮታ የሚገኝ ባርነት እና ሆድ አደርነት ነዉ ፡፡

ብሄራዊ የኢትዮጵያን አንድነት እና የህዝቧን ጥቅም ፣ መብት እና ደህንነት ስጋት ከሚሆኑ ኃይሎች ጋር ከሆነ ተጋድሏችን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያን ጠላት ጋር አጋርነት ያላቸዉን ሁሉ ከምንጫቸዉ ለማደረቅ ከኢትዮጵያዉያን ጋር በህብረት እና አንድነት መቆም እና ከፊት መገኘት ይኖርብናል፡፡

በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ሀብት በተገኘ መሳሪያ አገራቸዉን እና ህዝባቸዉን የሚያጠቁ እና ያለበሱ እና ያገረሱ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለሚነክሱ ከኃዲ ጠላቶች አደብ ለማስገዛት ብቸኛዉ መንገድ መዘጋጀት ፣ መንቃት እና በህብረት በኃል  አስከመጨረሻዉ  ማክሰም ነዉ ፡፡

ማናችንም ቢሆን ዛሬ የምንኖርባትን አገር ማጣት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ዓለም ስንለይ የምናርፍበትን አፈር ለማሳጣት ሌት ከቀን ለሚሰራ የዉስጥ እና መሃል ሰፋሪ ጠላት ከ፭ ቱ ፬ቱን እጂ በመስጠት እና ወደ ዉስጥ ችግር እና የችግር ምንጭ ማተኮር የሚገባን ጊዜ አሁን ነዉ ፡፡

“ጠላትን ያስታጠቀ ራሱን እና ወገኑን ማስታጠቅ የሚሳነዉ ህዝብ አይኖርም  ፡፡ ”

አበዉ“ ዕሾክን በሾክ” እንዲሉ  “ዕዉነተኛ እና የሚያስተኛ ዘላቂ ሠላም የሚረጋገጠዉ …ከጦርነት ድል በኋላ ከሚገኝ ኃይል ነዉ” ፡፡

“ዕዉነተኛ ብሄራዊ ፍቅር የሚገለጠዉ ለማይቀር ትግል እና ድል ዞትር ራስን ማመዘጋጀት እና ማብቃት ነዉ ፡፡ ”

“የኢትዮጵያዉያንን አንድነት እና ህብረት የሚፈራ  ከትንሳዔዋ ሞቷን የሚመኝ ነዉ” ፡፡

የጠላት የመጨረሻዉ ምኞት እና ፍላጎት እንደሚባለዉ ዓማራን አንገት  ከማስደፋት(ዉርደት) ባሻገር ፪ቱንም ( ዓማራ / ኢትዮጵያ) በቅደም ተከተል ማክሰም ነዉ ፡፡

ማላጂ

 

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop