December 22, 2021
6 mins read

ወደ ሃቀኛ ብሄራዊ መግባባት! – ገለታው ዘለቀ

በኢትዮጵያ ውስጥ ብሄራዊ መግባባት ወይም ምክክር የምንለው ሃሳብ ከጦርነት አቁም ስምምነት ሁሉ በላይ ነው። ሃገራችን ወደ ለውጥ መሄድ ካለባት አሁን ያለው ጦርነት ባይኖርም ብሄራዊ መግባባት ያስፈልጋል።  ብሄራዊ መግባባት አስፈላጊ ጉዳይ የሆነበት ምክንያት ሃገራችን ኢትዮጵያ የረጋ ቅርፀ መንግስት የሌላትና እንዲሁም በአያሌው ስምምነት ላይ ያልተደረሰበት መተሳሰሪያ መርሆዎችን ታቅፋ የምትኖር ሃገር ስለሆነች ነው። ስለሆነም የሽግግራችን ምክክሮች በአብዛኛው መተሳሰሪያ መርሆዎቻችንን ሁሉ እንደገና እየከለስን በፅሞና እንድናይ በር የሚከፍቱ መሆን አለባቸው።

የመተሳሰሪያ ዋና ዋና መርሆዎቻችንን እያነሳን ስንወያይ ህገ መንግስታዊ ማሻሻያዎችን እንድናደርግ የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ ያስገባናል። ችግሮቻችን ሁሉ ከዋና ዋና መተሳሰሪያ መርሆዎች በታች ቢሆኑ ኑሮ ውይይታችን ሁሉ በህገ መንግስቱ ማእቀፍ ስር ብቻ ይወድቅ ነበር። ነገር ግን ህገ መንግስቱ ላይ ያሉ አንዳንድ ገዢ መርሆዎች ራሳቸው ጥያቄ ውስጥ የወደቁ በመሆናቸው ህገ መንግስቱ ለሃገራዊ ምክክሩ መውጫ ሆኖ አይታይም። ለዚህ ነው ሃገራችን ወደ ተሻለ ምእራፍ እንድትገባ ሁሉን አቀፍ ምክክር ያስፈልጋል የሚያሰኘን። ምክክሩ ፈጭቶ አሳምሮ ያመረተው ሃሳብ ለህገ መንግስት ማሻሻያ ዋልታና ማገር እያቀበልን የጋራ ቤታችንን ጥሩ አድርገን እንድንሰራ ያደርገናል። በመሆኑም ብሄራዊ መግባባቱ ሁሉን አቀፍ ሆኖና ሃቀኛ ሆኖ ፍሬ ካፈራ በውጤቱ በተሻለ መተሳሰሪያ መርሆ በተከሸነና በፀዳ ህገ መንግስት ወደፊት ሊያራምደን ይችላል። ለዚህ ምክክር አጀንዳ ናቸው ያልኳቸውን ሃሳቦች እንደገና ከዚህ ቀጥሎ ላንሳቸው። ጠቃሚ ናቸው።

1. በህብረታችን ወይም በአብሮነታችን ፍፁምነት  ላይ። ህብረታችንና የጋራው ቤታችን በምን ያህል አቅም ወይም በምን ያህል የአብሮነትና የወዳጅነት የቃልኪዳን ልክ ይታተም? የሚለው ዋና የምክክር አጀንዳ ነው። አሁን ያለው መተሳሰሪያ መርሆ የህብረታችንን ልክ በመገንጠል የወሰነው ሲሆን አሁን ይህንን የህብረት ልክ እንዴት እናሳድገው የሚለውን ቁልፍ ጉዳይ ነው :: ለዚህ ነው Towards a More perfect Union እያልኩ የፃፍኩት:: ውይይታችን የጋራውን ቤት ፍፁም ወደ ማድረግ እንዲሆን መወያየት ያስፈልጋል ::
2.  በቅርፀ መንግስት ላይ ምክክር ያስፈልጋል ። ቅርፀ መንግስት በምርጫ መንግስት ሲመጣና ሲሄድ የሚቀየር አይሆንም። በዚህ አንድ ኢትዮጵያን የመሰለ ቅርፀ መንግስት መስፋት አለብን። ይህ ጉዳይ ሀገሪቱ ፓርላመንታሪ ትሁን ወይስ ፕሬዝደንሺያል? የፌደራል ሥርዓቱ ምን መልክ ይያዝ? የመንግስት ቅርፁ ምን ይጨምር ምን ይቀንስ? ለምሳሌ የህገመንግስት ዳኛ ይኑር ወይስ እንዴት እንቀጥል ወዘተን ይመለከታል ::
3. ብሄራዊ ማንነትንና የብሄር ማንነትን እንዴት እንንከባከብ። በምን አይነት ምህዋር ይዙሩ? እንዴት ሳይጠላለፉ ይኑሩ በሚለው ላይ ምክክር ያስፈልጋል።በማንነቱ ፖለቲካ ላይ ውይይት ያስፈልጋል ::
4. ብሄራዊ ምልክቶችን በተመለከተ መመካከር ያስፈልጋል። ባንዲራን መዝሙርን ወዘተ ይመለከታል።
5. የመሬት ላራሹ ጥያቄ ምክክር ውስጥ መግባት አለበት። የፓሊስ ቀጭን ጉዳይ አይደለም ይህ አጀንዳ።
6. ያለፈ መጥፎ ትውስታዎች እንዴት ይታዩ? (Past bad memories) የሚለውን ማንሳት ተገቢ ነው።
7. ቋንቋና ተግባቦትን በሚመለከት ውይይት ያስፈልጋል። ይህ ጉዳይ የአንድ ፓርቲ ፓሊሲ ሳይሆን የቋንቋ አያያዛችን ላይ የጋራ አቋም መያዝ ይቻላል።
እነዚህ ናቸው አጀንዳዎቻችን። በነዚህ ላይ የምናደርገው ስምምነት ህገ መንግስት የሚያሻሽሉ ሃሳቦችን ያመርትልንና ወደ ህገ መንግስት መሻሻል ስራ እንገባለን ስምምነቱ በጋራ ቃል ኪዳን ይፀናል ማለት ነው። ህዝቡም በዚህ ስምምነት ላይ ተሳትፎ ሊኖረው ይገባል። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop