“እውነትም ከእናታችን ሆድ ውሀ ሆነን በቀረን” ላለማለት ምን ይጠበቅብናል? * ቹቹ አለባቸው

《ጠላት ጦርነቱን አማራ ክልል ለማድረግ የፈለገበት ዋና ምክንያት ዓላማው አማራን መግደል፣ ማደኸየት፣ ማዋረድ ስለሆነ ነው።》
~ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ
*

ለፅሁፌ ርዕስ የተጠቀምኩት፣ በትዕምርተ ጥቅስ የተቀመጠው የሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌን ንግግር ነው። ከላይ የተጠቀሰውን ሀሳብ ጀኔራሉ በትላንትናው ዕለት በ EBC “ቀይ መስመርየተሰኘ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ከተናገሩት የተወሰደ ነው።

ጀኔራሉ ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ዝርዝር ግፍ ካስቀመጡ በኋላ የአማራ ህዝብ ይሄንን ግፍ መበቀል አለበት፤ ጊዜው አሁን ነው። ይሄንን የማያደርግ አማራ ካለ ሳይወለድ ከእናቱ ሆድ ውሀ ሆኖ ቢቀር ይሻለዋልሲሉ በንዴት ተናግረዋል።

ኦፍፍፍፍ…. በጣም ትልቅ ዕዳ! ያውም ታላቅ የታሪክ ዕዳ። ይህን የምለው ጀኔራሉ ስለተናገሩት ብቻ አይደለም፤ በእኛ በኩል ይህን ሕዝባዊ ጠባሳ በዘላቂ ድል ማከም ካልቻልን የታሪክ ተጠያቂ ስለምንሆን ነው የታሪክ ዕዳያልኩት። መዘንጋት የሌለበት ነገር አንድ የጦር ጀኔራል ኢትዮጵያዊነቱ አላስችለው ስላለ፥ በአማራ ላይ የደረሰው ግፍ እንዲህ አስቆጭቶት መናገሩ ነው። ይህ ከሆነ ዘንድ፦ እኛ የአማራ ተወላጆች ይሄንን የጀኔራሉን ንግግር ስንሰማ ምን ይሰማን ይሆን !?

ወያኔ በሕዝባችን ላይ ያደረሰውን ግፍና በደል በቅርበት የምንመለከተው፣ ከህልውና ጦርነቱ ጋር በተያያዘ ሚና ይዘን የተሰለፍን ሰዎች ህመማችን እንዲህ በአደባባይ ሲነገር ስንሰማ ቁጭቱ የእግር እሳት ሆኖብን እንቅልፍ አያስተኛም።

መቸም ዘንድሮ የአማራ ህዝብ በተለይም ወጣቱና ጎልማሳው በታሪክ ውስጥ ለፈተና ወድቀናል። ከመንግሥት ሚዲያዎች መስማትና መመልከት እንደተቻለው፣ በግንባርም እንደሚስተዋለው የትግራይ ወራሪ ኃይል አማራን በብዙ መልኩ አዋርዷል። የጥፋት ሰይፉን የመዘዘው ሕዝቡ ላይ ነው። 100 ዓመት በድህነት ወደኋላ ለመመለስ አቅዶ በከፈተው የጦር ወረራ በ 4 ዞኖች ሙሉ በሙሉ፤ በ3 ዞኖች ደግሞ በከፊል የሕዝብና መንግሥት ንብረት ዘርፏል፣ ማጓጓዝ ያልቻለውን ደግሞ አውድሟል። ዘረፋው ከሊጥ እስከ ግዙፍ ፋብሪካዎች፤ ከቁልፍ ማህበራዊ ተቋማት እስከ ከተማ ንዑስ አምራቾችና የአርሶ አደሩን ጥሪት፣ አጥንትና ጉልጥምቱን የማድቀቅ ውድመት ነው ያደረሰብን። እንኳንስ የዛሬው የመጪው ትውልድ ሲቆጭበት የሚኖር፣ በሐሰት ትርክት የቆመ የበቀል በትሩን አሳርፎብናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም! ይነጋል በላቸው

ህዝባችን በዘመኑ ያፈራውን ሀብትና ንብረት ከመውሰዱምና ከማውደሙም በላይ አልሚ ጉልበት የመሆን አቅም ያለውን የህብተሰባችን ክፍል ጨፍጭፏል። እናት፣ እህት፣ ሚስት ዕድሜ ባልገደበው ሁኔታ ሴቶች በወራሪው መንጋ በቡድን ተደፍረዋል፤ ያውም የተከበረው የአማራ ሕዝብ ስም እየተነሳ በእንስሳዊ ማንነት ስም እየተገለፀ፣ ጠላት አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚገባ ስድብ እየተሳደበ ነው የተደፈሩት።

እናት ከባሏና ልጆቿ ፊት፣ እህት ከወንድሞቿ ፊት በቡድን ተደፍራለች። የካኽናት ሚስት ሳይቀር በመንጋው ተደፍረዋል። ከአርሶ አደር ቤት ውስጥ አስከሬን በመቅበር አርሶ አደራችን ቀየውን ጥሎ እንዲሰደድ አቅዶ የሰራው ጠላት፣ በተመሳሳይ የኃይማኖት ተቋማቶቻችንን አርክሷል፤ አውድሟል።

በአጠቃላይ ጠላት የአማራ ነው ብሎ በአመነው ሰብዓዊም ይሁን ቁሳዊ ሀብት ላይ ያለምህረት ውድመት አድርሶብናል። ጠላት በወገን ላይ ይህን ሁሉ ግፍና መከራ ያደረሰው አማራ በመሆናችን ብቻ ነው።

የዚህ እኩይ አላማው መነሻ ደግሞ ግልፅ ነው፤ አማራን ማዋረድ፤ ማደህየት፤ ብሎም በአማራ መቃብር ላይ የተመሰረተች ሀገረትግራይን መገንባት ነው። ጀኔራል ባጫ ደበሌ የተናገሩት እውነታ ይህን ነው። ጀኔራሉ የጠላት ፍላጎት አማራን መግደል፣ ማደኸየት፣ ማዋረድ ነውብለዋል። ጀኔራሉ፣ ለፖለቲካ ትክክለኝነት (Political Correctness) ብለው ካልዘለሉት በስተቀር፣ ጠላት በአማራ መቃብር ላይ ትግራይ ሪፐብሊክን መመስረት ህልሙ እንደሆነ እናውቃለን።

አሁን ጥያቄው የአማራ ህዝብ በተለይም ወጣቱና ጎልማሳው የኀብረተሰብ ክፍል ይሄንን ግፍ እንዴት ማስተናገድ አለበት? የሚል ነው። ይህ ለአማራ ህዝብ እንደአጠቃላይ በተለይም ደግሞ ለወጣቱ የቀረበ ወቅታዊና ታሪካዊ ጥያቄ ነው።

የአማራ ወጣት ሆይ! ምላሽህ ምንድን ነው?

ተጨማሪ ያንብቡ:  እያደባ በመስፋፋት ላይ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል (Creeping Genocide) - በዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ

ይህን በእሳተ ጎመራ የሚመሰል የሚያቃጥል ጥቃት እንደዋዛ ታልፈዋለህ ወይንስ ደመኛ ጠላትህን ጀኔራሉ እንዳሉት ትበቀለዋለህ?”

ምንድነው አቋምህነገሩን ትርጉም የለሽ ለሆነው አብሮ ለመኖርስትል በይቅርታ ታልፈዋለህ ወይስ አቶ ዩሃንስ ቧያለው እንዳሉት ጠላት የወሰደውን ሁሉ ማስመለስ ብቻ ሳይሆን የበላውን ታስተፋዋለህ“?

እንግዲህ ውሳኔው የራስህ ነው።

እኔ ግን እንዲህ እላለሁ! የአማራ መዋረድ፣ ንብረቱ መዘረፍ፣ የእናቱና እህቱ መደፈር፣ወዘተ ቆጭቶትና ደሙ ፈልቶ ጠላቱን ለመበቀል የማይነሳ አማራ በተለይም ወጣት ካለ እውነትም ሳይወለድ ከእናቱ ሆድ ውስጥ ውሀ ሆኖ በቀረእላለሁ።

ጎበዝ! እናቱን፣ እህቱን፣ ሚስቱን እና ሀገሩን ከውርደት ያላዳነ ትውልድ በምድር ላይ መኖሩ ጥቅሙ ምንድን ነው? ኳስ ጨዋታ ለማየት? betting ቁማር ለመጫዎት? ፑል ቤት ለመዋል? ወይንስ ከርሱን እየሞላ ለመኖር? ይህን ማህበራዊ መንዘላዘልጠላት የሚፈቅድልህ ይመስልሃል?

የአማራ ወጣት ሆይ!

ጦር ግንባር የሄደ ሁሉ አይሞትም። ጦርነትን ፈርቶ ከቤቱ የዋለ ሁሉም ከሞት አያመልጥም። ሞት በሁሉም ቦታ አለች። የምንሞትበትን ቀን፣ ስዓት፣ ቦታና ምክንያት ደግሞ ወሳኙ ፈጣሪያችን እንጅ እኛው አይደለንም። ለዚህ ነው በአማራ ባህል አሟሟቴን አሳምረውየሚባለው። ይህ አባባል ሞት መቸም እንደማይቀር ግን ደግሞ ስም ያለው ሞት ሰጠኝለማለት ነው። የውሻ ሞት ሳይሆን የክብር መስዋዕትነትን መምረጥ የጥንት አባቶቻችን ባህል ነው።

በእኔ እምነት ካሁን በኋላ የአፄ ቴዎድሮስን፣ ዳግማዊ አፄ ምኒልክን፣ ደጃዝማች በላይ ዘለቀን፣ ንጉሥ ሚካዔልንና መሰል ቀደምት ታሪካዊ መሪዎችን ስም እያነሳ መፎከርና ማስፎከር ያለበት፣ በደጀን ከሱ የሚጠበቀውን ሁሉ እየከወነ ያለ፣ ግንባር የዘመተና ጠላትን ለመበቀል እየተዋደቀ ያለው እንጂ፤ በዚህ የሞት ሽረት ተጋድሎ ሠዓት የዳር ተመልካች የሆነ አማራ መሆን አለበት ብየ አላምንም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጉራፈርዳ የአማራ ተፈናቃዮች ልጆቻቸውን ጉዲፈቻ ለመስጠት እየተማጸኑ ናቸው

በደጀን ከሱ የሚጠበቀውን ድርሻ ሳይወጣ፣ ግንባር ዘምቶ የአማራን ደም ሳይመልስና የትግራይን ወራሪ ኃይል ሳይበቀል ሀገር ከውጭ ወራሪ ጠብቀው ነፃነትን ያወረሱንን ነገሥታትና አርበኞች ስም እያነሳ ሲፎክር እንዲውል መፈቀድ የለበትም። ምክንያቱም እነዚህና መሰል ታሪካዊ መሪዎች አይደለም አማራን ሊያስደፍሩ ቀርቶ ኢትዮጵያንም አሰከብረው የኖሩ ጀግኖች ነበሩና ስል ወንድማዊ ጥሪየን አቀርባለሁ።

ታድያ ዛሬ አማራ ተዋርዶ እና ኢትዮጵያ ተደፍራ እያለ እንዴት የነዚህ ጀግኖች ትንፋሽ ያልነካው ሰው በነዚህ ጀግኖች ስም ሲፎከርና ሲያስፎክር ይውላል? ሞራሉስ ከየት መጣ? አሰቂኙ ነገር ደግሞ ፉከራውንና ማስፎከሩን የሚያበዛው የሳሎን አርበኛውመሆኑ ነው። ፉከራ የአማራ ሕዝብ የጦር ስንቅ ልዩ እሴታችን ነው፤ ቦታው ደግሞ ግሮሰሪ ሳይሆን ጦር ሜዳ ነው።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share