November 19, 2021
13 mins read

የጸረ-ኦርቶዶሱ ብልጽግና ቁማርና ደጋፊ ሚዲያዎቹ – ሰርፀ ደስታ

adanechከትላንት ወዲያ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በቤተክህነት መሣሪያ ተገኘ የሚለውን ወሬ ሰምቼ ምን ተገኝቶ ይሆን ብዬ ነበር፡፡ ጉዳዩን ግን የዛን ያህል ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር፡፡ አንድ ራሱን የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ የሚያደርግ አደባባይ የተባለ ሚዲያም ጉዳዩን አንስቶ ሲያወራ በጨረፍታ ሰምቼ የሆነ ነገር ተገኝቶ ይሆናል ብዬ ያው በወያኔ ዘመን የተቀበረ ሊሆን ይችላል ከሚል ግምት ያለፈ ብዙም ቦታ አልሰጠሁትም፡፡ ትላንትና ነበር የብልጽግና ልሳን የሆነው ኢሳት የአዲስ አበባ ከንቲባዋን ኢንተርቪው የሰማሁት፡፡ የሴትዮዋን ንግግር ላስተዋለ በኦርቶዶክስ ላይ ያላትን ጥላቻ ያሳበቀ እንጂ አንድ በዛ ደረጃ ያለ ባለስልጣን የሆነው ነገር በእርግጥም እንደተባለው ለልዩ ወንጀል የተከማቸ መሳሪያ ቢሆን እንኳን ገና በምርመራ ላይ ያለን ጉዳይ በሚዲያ መናገር በራሱ ሕገ ወጥነት ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ደግሞ ፍተሻ የተባለውን ሒደት ሚስጢራዊነት ሊኖረው ሲገባ በእርግጥም ለልዩ ዓላማ መሳሪያ ያከማቹ ካሉ እንዲያሸሹና እንዲሸሽጉ ከወዲሁ ጥቆማ መስጠት ነው፡፡ ኢሳት የተባለው የብልጽግና ልሳን እንዲህ ከብልጽግና ሹማምንት ጋር ባለው ቅርበት የተነሳ ከፍተኛ የተባሉ የጦር መኮንኖችን ሳይቀር በማንጋገር በወታደራዊ ተቋሙ ብቻ ሥር መሆን ያለባቸውን ጉዳዮች ሳይቀር ለገበያው እየሸቀጣቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ አይተናል፡፡ የዛሬውም አዳነች አቤቤን ያነጋገረበት ሂደት ይሄው ነው፡፡ አዳነች አቤቤ በቤተክርስቲያ ላይ ያላት ውስጠ ወራዊ ጥላቻ በግልጽ ያሳየችበት ምን አልባትም እግረ መንገዷን ሌላ ቦታ የሚጠረጠሩ በእርግጥም ለልዩ ወንጀል መሳሪያ የደበቁ ካሉ ተጠንቀቁ፣ አሽሹ ያለችበት አደገኛ የሆነ ንግግር ነበር፡፡ እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነው ፍተሻው ፍተሻ ሀኖ አዲስ አበባን የሚያድነው? ብሎ መጠየቅ ወሳኝ ነው፡፡

በትላንትናው እለት በቤተክህነት ተገኘ የተባለውን ከተለያየ ሚዲያ ሳይ በግልጽ በወያኔ አድጎ ራሱን ብልጽግና ያለው ቡድን መሪ ነኝ የሚለው አብይ አህመድ የጻፈውን የጸረኦርቶዶክስ የብልጽግና ማኒፌሽቶ እንደገና እነዳስተውለው ግድ ብሎኛል፡፡ ወያኔ በግልጽ የአማራ ጠል ማኒፌስቶ ጽፋ እንደተነሳች ብልጽግናም በግልት የኦርቶዶክስ ጠልነቱን በማኒፌስቶ ጽፎ አንደመጣ አይተናል፡፡ ማንም ግን ስለዚህ በአብይ አህመድ የተጻፈ የብልጽግና ጸረኦርቶዶክስ ማንፌስቶ ትኩረት ሰጥቶ ለምን ብሎ የጠየቀ አላያሁም፡፡ ዛሬ በቤተክህነት መሳሪያ ተገኘ በሚል በግልጽ ቤተክርስቲያኒቱን ለማጠልሸት አዳነች አቤቤ የሄደችበት ርቀት ትልቅ ደወል ሊሆን ሲገባ ይባስ የቤተክርስቲያን ነን የሚሉት እንደነ አደባባይ የመሰሉት ሚዲያዎች ሳይቀር ተቀብለው ሲያራግቡት በአግራሞት ተመልክቻለሁ፡፡ ለመሆኑ ማን ነው ለእውነት የሚታመነው?

በቤተክህነቱ ግምጃ ቤት ተገኘ የተባለው መሳሪያ ሳይሆን 1800 ጥይትና የጥይት ሳጥን እንዲሁም የክላሽንኮቭ ካዝዘና (ማለትም የጥይት ማስቀመጫው ቀፎ) ነው፡፡ እንደው እንኳንስ ፖሊስን የሚያህል ትልልቅ ሚስጢራዊ ወንጀሎችን ያወጣል ተብሎ የሚገመት አካል ይቅርና ለማንም ተራ ሰው 1800 ጥይት በቤተክህነት ግምጃ ቤተ መገኘቱ አዲስ ነገር ይሆንበታል? ጭራሽ እንደ ልዩ የምርመራ ውጤት በእነ አዳነች አበቤና በብልጽግና ሚዲያዎች በስፋት ሲሰራጭ ተመለከትን፡፡ ሊያም እውነት የተገኙት ጥይቶች ለልዩ ሴራ ተደብቅ የተገኙ እንኳን ቢሆን የቤተክርስቲያኒቱን ክብር መጠበቁን ይተውትና በዚህ ወቅት ሚስጢራዊነትቱን መጠበቅ ለቀጣይ ፍተሻ ወሳኝ መሆኑ እየታወቀ፡፡ ተገኙ የተባሉት 1800 ጥይቶች እንግዲህ በአንድ ትልቅ የአገሪቱ ታሪካዊና ተምሳሌታዊ በሆነችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት ግምጃ ቤት ውስጥ ነው፡፡ 1800 ከዛም በላይ ጥይት ለጥባቃ ሥራም ይሁን በተለያዩ ጊዜ በታሪክ ሊሰበሰቡ የሚችሉም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ደግሞም የሆነው ይሄው ነው፡፡ በቤተክርስቲያኑ ግምጃ ቤት ለጥበቃ ሥራ የሚሆኑ ጥይት ብቻ አደለም መሳሪያም ይገኛል፡፡ ለብ በሉ ተገኘ የተባለው 1800 ጥይት ነው፡፡ እንደው አንድ 20 ክላሽንኮቨ ቢያገኙ ምን ሊሉ እንደሚችሉ አስቡት፡፡ በእርግጠኝነት በጠቅላይ ቤትክህነት ብቻ ከ20 በላይ ለጥበቃ ሥራ የሚውል የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ይኖራል፡፡ በጠቅላይ ቤተክህነቱ ግን ለሌሎች ቦታዎችም ሊሆን የሚችል በርከት ያለ መሣሪያም ሊከማች ይችላል፡፡ ሆኖም ያ እንኳን ያለ አልመሰለኝም፡፡ እንዲህ ያለን እውነት በመካድና ሆን ተብሎ ቤተክርስቲያኒቱን ለማጠየም እየተሰራ ያለውን የብልጽግና ቁማር ምዕመኑ እንደ ዋዛ ማለፍ ያለበት አይመስለኝም፡፡

አደባባይ የተባለው በዋናነት የቤተክርስቲያን ነን የሚሉ የሚሰሩበት ሚዲያ ጉዳዩን ከቤተክርስቲያን በቀጥታ በማጠራት ለሕዝብ ግልጽ ማድረግ ሲገባው ጭራሽ በቤተክርሲቲያን ሰዎች ነን በሚል ሽፋን የብልጽግናን ሴራ በሕዝብ ተቀባይነት እንዲያገኝ አንድ ቀን ሳይሆን ሁለት ቀን ሥራዬ ሆይ ብሎ ሲያሰራጭ አይቼ አዝኛለሁ፡፡ አደባባይ የሚባለው ሚዲያ በተደጋጋሚ በኦርቶዶክሳዊነት ሽፋን ለጸረ ኦርቶዶክሱ ብልጽግና የኮንቪንስና ኮንፉውዝ ሥራ ሲሰራ ታዝበናል፡፡ የዛሬውም ዝግጅቱ የዚሁ አንድ አካል እንደሆነ ስናስተውል እጅግ በማዘን ነው፡፡ ባለማወቅ ቢሆን ጥሩ በሆነ፡፡ በተደጋጋሚ ያየንው እውነት ነው፡፡ የዛሬው ደግሞ የለየለት የብልጽግናን ጸረኦርቶዶክሳዊነት በይፋ ደግፉ መርዝ ሲረጭበት ያየንበት ነው፡፡ ይህ በእውነት ያሳዝናል፡፡ ማንን ማመን ይቻልል? ኢሳት በግልጽ የብልጽግና ልሳን ስለሆነ ብዙም አልገረመኝም፡፡እንደምናየውም የአገሪቱ ትልልቅ ሚስጢራዊ ተቋማትን ባለስልጣ ሳይቀር ቃለ መጠይቅ የሚያደርገው ከመንግስትም ሚዲያ በላይ ኢሳት ነወ፡፡ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ነኝ የሚለው አደባባይ ግን በዚህ መልኩ የጸረኦርቶዶክስን መርዝ ሲረጭ ማየት አሳዛኝ ነው፡፡

ለማንኛውም 1800 ጥይት በቤተክህነት ግምጃ ቤት (የቤትክርስቲያኒቱ ትልቁ ግምጃ ቤትም ሊሆን ይችላል) መገኘቱ ስህተት ሳይሆን ከዛም በላይ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከዛ ይልቅ በሺዎችና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጦር መሳሪያዎች በብልጽግና ለኦነግሸኔ እየተላለፉ እንደሆነ ማንም አይናገርም፡፡ ዛሬም ቢሆን በአዲስ አበባ ሳይቀር ሌላውን በፍተሸ በሚል እያሸማቀቁ በጎን ለኦረሞ ብልጽግና ጠባቂዎች ማስታጠቅ እንደተስፋፋ እንታዘባለን፡፡ የብልጽግና ስልት ከወያኔ እንደወረደ የተቀዳ ብቻም ሳይሆን እንደወያኔ እንኳን ጥንቃቄ ባለበት ቀስ እየተባለ ሳይሆን በወረራ ምልክ ነው ነገሮች ሁሉ በኦሮሞ ኦነጋውያን ቁጥጥር ስር እንዲሀገቡ እየተደረገ ያለው፡፡ ግን አዋጣም፡፡ ከምንምና ምንም በላይ ይሄ አደጋው ለኦሮሞ ሕዝብ ለራሱ ነው፡፡ የኦሮሞ ፖቲከኞች የወያኔ መንፈስ የተጠናወታቸው የሚየስቡት እንኳ እንደ ሶፈትዌር ወያኔ በጫንችላቸው አስተሳሰብ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ ማሰብ ቢችሉ 27 ዓመት የተበላበትንና ሕዝብ አንቅሮ የተፋውን የወያኔን ሥልት እንደወረደ ዛሬ በብልጽግና ሥም ባልመለሱት ነበር፡፡ ሁሉም ይጠፉ ዘንድ ግን እየሆነ ያለው ሁሉ እየሆነ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ሀሉ አስተውሉ፡፡ በተለይ ኦርቶዶክሳውያን አስተውሉ፡፡ በአለፉት ሶስትና ከዛ በላይ በሆኑት ዓመታት የሆነውን ሁሉ አስተውሉ፡፡ ሰዎች በወያኔ ጥላቻ ብቻ ስለታወሩ ከወያኔ የከፋውን የኦሮሞ ኦነግ/ብልጽግናን ሴራና አረመኔነት እያስተዋሉት አይመስልም፡፡ በአለፉት ሶስት አመታት የሆነውን ደጋግማችሁ አስተውሉ፡፡ ግን አያዋጣም፡፡ ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም ሆኖ ነው፡፡ ሁሉም በሴራቸው ተጠልፈው የሚጠፉበት ጊዜ ሩቅ አይመስለኝም፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ

አሜን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop