July 23, 2021
14 mins read

ሙሥና የብልፅግና ፀር ነውና “ይበቃል ! “ ልንለው ይገባናል   (አባ መላ ዘ አብደናጎ)

የተቀናጀ እና እንደ ህጋዊ አሰራር የሚቆጠር ሌብነት   በፊደራል ና በክልል ገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶች እና በመንግስት የልማት ድርጅቶች  እንደሚሥተዋል ለአዲሱ ለብልፅግና መንግስት የተሰወረ አይደለምና መጪው ጊዜ የህዝቡን  ፤ የመንግሥት በጀትና እና የመንግሥት ፋብሪካዎችን እና የልማት ተቋማትን ሀብት የሚዘርፉትን ገዢው የብልፅግና ፖርቲ አይታገሳቸውም የሚል ፅኑ እምነት የህ ፀሐፊ አለው ።

የፊደራሉም ሆነ የክልል መንግሥታት ፣ ሥራን ያላገናዘበ  ከአገሪቱ አቅም በላይ ፣ ከደሞዝ ውጪ ለጥቅማ ጥቅም የተጋነነ ክፍያ  ፣ እሥከ መምሪያ ኃላፊዎች ድረሥ ይከፍላል ።ይሁን እንጂ  ይሄ ልዩ ጥቅም ተከብረው እንዲኖሩ አላስቻላቸውም ። ( ይህ ፀሐፊ አሳምሮ በሚያውቀው ፋብሪካ   ፣ ቤትም ጭምር በነፃ እያገኙ  ፣ እንደ ቀድሞ የኢህአዴግ ሹመኞች የመሬት ወረራ አዳማ ያለው ለሻሸመኔው ቢሮክራሲ መሬት በመሥጠት ሸጦ እንዲጠቀም እንደሚያደርገው ሁሉ፣ በተለያየ ሰራተኛ ሥም ና በፋብሪካ ሥም  ሲሚቶ ከሙገር ፋብሪካ  እየጠየቁ ፣ በሲሚንቶ ኮንትሮባንድ ኪሳቸው በብር የሞሉ እና ለሙሥና ተባባሪ ሠራተኞቻቸው ረብጣ ብር እንዲያገኙ ያደረጉ  ፣ የመንግሥትን አደራ የበሉ ኃላፊዎች እንዳሉ ያውቃል ። ) ከዚህ እውነት አንፃር ፣  የመንግሥት እንክብካቤ ለእነሱ ቀልድ ነው ፤ ማለት ነው ።

ይኽ ፀሐፊ ፣ በተጨባጭ በሚያውቀው ፣ በመንግሥት የልማት ድርጅቶችም ውሥጥ ፣ ኃላፊነት የተሰጣቸው ባለሥልጣናት ( አሰሪዎች ) ለመንግሥት ሀብት እድገት  በመወገን  ፣በህግ አግባብ ሠራተኛውን  ተቆጣጥረው በማሰራት ፣ ውጤታማ ሆነው   እንዲገኙ አደራ ተጥሎባቸው ሣለ ፤ የመንግሥትን ተልኮ መፈፀም ትተው ሞዝበራን “  በኔት ወርክ “  የመከወን ኩንን ተግባር ላይ ከተሰማሩ የብልፅግና መንግሥት ኪሳራን ሥለማይፈልግ በቸልታ እንደማያያቸው ፅኑ እምነት አለኝ ።

( እነዚህ የመንግሥት አደራ የተጣለባቸው አሰሪዎቹ ( የሥራ ኃላፊዎች ) ፣ የጁንታውን ዓይነት ኔት ወርክ በመፍጠር ፣ ዕውቀት ያለው ጠያቂ የሆነ ኦዲተር በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውሥጥ ዝር እንዳይል ያደርጋሉ ።አንዳንዶቹማ ፣  ራሱን ችሎ ፣ ውሳኔ የሚሰጥ   አሥተዳደር ፣ የሰው ኃብት መምሪያ ( ፔርሶኖል )  የላቸውም  ። ከዚህ የተነሰ አንድ ሰው ከመንግሥት የሥራ ሰዓት ውጪ እንደፈለገው ሰርቶ ትርፍ ሰዓት ቢከፈለው ለምን ብሎ የሚጠይቅ የሚመለከተው የሥራ ቡድን ኃላፊ የለም ።  በእውቀት የካበተ ልምድ ና ከሙሥና የፀዳ የፋይናሥ እና የንግድ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም ኦዲተር  ከውጪ እንዳይቀጠር  በማድረግም ይህንን ገበናቸውን ሸሽገው ጡረታ ይወጣሉ ። ይህ ብቻ አይደለም  ተራ ቅጥር ሠራተኞቹም መብታቸው ሲረገጥ ፣ የእኔንን እግር ጅብ ቢበላው ምን አገባህ ባዮች እንዲሆኑ   ያለብቃታቸው በሙሥና  ይቀጥሯቸዋል ። )

ይህንን መሠል ጁንታዊ የኔት ወርክ ሙሥናዊ አያሌ  ተግባራት በዚች አገር እየተፈፀሙ ያሉት  የኢትዮጵያ መንግሥት በተደቀነበት ፋታ የማይሰጥ አገርን የማዳን ቀዳሚ ተግባር የተነሳ እንደሆነ ይህ ፀሐፊ ይገነዘባል ። የመንግሥት ትኩረት ዋናው ጁንታ ላይ በመሆኑ ፣ የኢኮኖሚ ጁንታዎች ለጊዜው ዘረፋቸውን ቀጥለዋል ። ሌብነትን የሚፀየፈው የብልፅግና መንግሥት  አያየንም ብለው ያለዩሉንታ የአገርን እና የህዝብን ሀብት መዝረፋቸው ግን ነገ ” አይነጋ መሥሎት…።” የሚባለውን ተረት እንደሚያስተርትባቸው ይወቁት ።

ነገ  ከነገ ወዲያ በሰፈሩት ቁና  እንደሚሰፈርላቸው ፈፅሞ ባለመጠርጠር ፣ ጠያቂ ባልሆኑት የጥቅም ተጋሪዎቻቸው የበላይ አካላት ፍፁም  ተመክተው ምንም ብዝበዛቸውን ዛሬ ቢያጦጡፉና ለአገር ብልፅግና ና ለላባደሩ እድገት ደንታ ባይኖራቸውም ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶቹ ባለቤት የሆነው የፊደራል መንግሥት  በጊዜው ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድባቸው ይህ ፀሐፊ ያምናል ።

መንግሥት    አገርን እየበዘበዙ ያሉትን የሚያይበት የራሱ መነፅር እንዳለው ዛሬ ላይ ሆናችሁ ቆም ብላችሁ መረዳት ከነገ ከባድ ውድቀት  ያድናችኋል ብሎም ይመክራል  ። እወቁ ፣ የምትኖሩት ከህዝቡ ጋር ነው ። ህዝቡ ደግሞ አብጠርጥሮ ማንነታችሁን ያውቃልና ከወዲሁ ለንሥሐ ብትዘጋጁ መልካም ይመሥለኛል ። ጥፋት እንደ አውሎ ነፋሥ( እንደ ሱናሚ ) ሳይመጣባችሁ እሥቲ ዛሬ በቃኝን እወቁ ። እሥቲ ዛሬ ለህግ ፣ ለደንብና ለመመርያ ተገዢ ሁኑ ።

ለብዝበዛ የተመቻመቸ ገንዘብ በየፋብሪከው ሥታዩ ፤   ” የፍቅር ቀን  ” ( ቫላንታይን ደይ ) በማለት በኩርማን እንጀራ ና በአንድ ጥፊ ወጥ ሠራተኛውን በመደለል እናንተ በትልልቅ ሆቴል ከበላይ ኃላፊዎቻቸው ጋር በመሆን ፣ በውሥኪ አትራጩ ። …

” ተወው ይሄ ወዛደር እርስ በእርሱ ይንጫጫ ። እኛ በልተገባ ዕድገት ና የደሞዝ ጭማሪ እንዲሁም ፣ ተገቢው ቅጥር እንዳይፈፀም በማድረግ በመቅጠር እንዲሁም ያለህግ ፣ ንብና መመርያ  ፣ የትርፍ ሰዓት እንዲከፈለው ወይም ፊልድ እንዲወጣ በማድረግ ተጠቃሚ  አድርገነዋልና .. ሲሚቶ ከፋብሪካችን ሸጦገዝቶ በውድ ዋጋ ሽጦ ፣ ኪሱን አይቶት በማያቀው ገንዘብ እንዲሞላ ተባብረነዋል እና በቂ የፕሮፖጋንዳ ሃይል አለን ። አትሥጋ ። እዛ ቅንጥብጣቢ ጥለን እዚህ ውሥኪያችንን እናወራርዳለን ። …ማንም ህግን ተደግፈን በሰራነው ሙሥና ተጠያቂ ሊያደርገን አይችልም ። ”  በማለትም አትዘባበቱ ።

(  ወዳጄ በዓመት አንዴ እንደ ፊውዳል ድግሥ  ‘ በእነ ገብሬ ጅራፍ እየተገረፍክ … ‘  በዩልነታ ተሰልፈህ  ሥጋ  በልተህ ከችግርህ አትላቀቅም ።  በሥምህ  አመካኝተው ሊበሉት ያሰቡት ብር ግን   ለአገርህ የዛሬ ችግሯ  ቢውል ፣ ሥምህ በመልካም ይጠራል ። )

ይህ ፀሐፊ  ፣  ይህንን እውነት በአደባባይ ያሰጣው    የብልፅግና መንግሥት  እውነቱን እንዲያውቅና አፋጣኝ እርማት እንዲወሥድ በመፈለጉ ነው ።ኃይለኛ የዘረፋ መረብ በመዘርጋት “ ምን ያመጣል ! “ በማለት  መዘበትና ማሾፍ “ በቃ ! “ እንዲባልም ነው ።

የየአንዳዳችን ንቃተ ህሊና ባልዳበረበትና  ህሊና በእውቀት ጥማት ማመዛዘኑን በተነቀበት አገር ፤ ጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን ለራሳቸው ትርፍ ሲሉ በእውቀት ሰበብ ብልፅግና የራቀውን ህዝብ በተለያየ ሐሰተኛ ትርክት ወደፈለጉበት የጥፋት መንገድ ሊመሩት ይችላሉ። ከሙሥና አንፀርም ሁለት አሥርት ያሥቆጠረው የፌደራል ፀረ ሙሥና እና ሥነምግባር ተቋም የህብረተሰብን ንቃት ከማሳደግ አንፃርን የሚገባውን ሚና አልተጫወተም ።

በሚናው ደካማነት አንፃርም ፣  ሙሥናንን ለመዋጋት በማያሥችል ቁመና ለተደራጀው  ፀረ _ ሙሥና  መታረም የሚገባቸውን  “ የሌብነት ተግባራት “ መጠቆም  ዋጋ ቢሥ እንደሆነ ይህ ፀሐፊ ተገንዝቧል ።

የፊደራል  ፀረ ሙሥና ኮሚሽን ተቋሙ ፣   እጅግ የሸመገለና ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው ። ቢያንሥ ለዚህ ፀሐፊ ።

ጥርሥ አልባነቱም ፤ የበላይ   አካላትን ሙሥና በሥውር መርምሮ እርማትም ሆነ እርምጃ የመውሰድ አቅም በማጣቱ  እናም…  የሙሥና ጉዳዮችን ( ሥልጣንን የአለአግባብብ መጠቀምና በሥልጣን መገልገል ና የማይገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ወይም እንዲያጭበረብሩ ፣ በመንግሥት ማህተም መጠቀም በራሱ ከባድ ሙሥና ነው ።) ወደ ፀረ ሙሥና ተቋሙ ወሥጄ መፍትሄ ለማግኘት ሥለማልችል  ጉዳዩን በቀጥታ ለህዝብ ፣ ለመንግሥትና ለራሱ ለተቋሙ በአደባባይ ይፋ ለማድረግ ተገድጃለሁ ።

በነገራችን ላይ ፣ የሲሚንቶ የሌብነት ኔት ወርክ አንደነበረ እና ዛሬም ኔት ወርኩ እንዳልተበጠሰ  ይታወቃል ። ዛሬም ድረስ የሲሚንቶ መደበቂያ መጋዘኖች በየከተሞቹ ቀበሌዎች አሉ በተለይም በዋና  ዋና ከተሞች ። ኢትዮጵያን እወዳለሁ አገሬ እንድትበለፅግ እፈልጋለሁ ። የሚል ዜጋ ሁሉ ፣ ያለዩልንታ ሌብነትን ና ህግን ተገን አድርጎ ፣ ከደላሎች ጋር በመቀናጀት የሚደረግን ዘረፋ  ለመዋጋት ቆርጦ መነሳት አለበት ። የኢትዮጵያ ደላሎች ዜሮ አምሥት ሳንቲም ግብር  የማይከፍሉ  ሆኖም ግን በሚሊዮን ብር  ጢቢ ጢቢ  የሚጫወቱ በሌብነት የበለፀጉ ቱጃሮች ናቸው ።

በአሁኑ    ሰዓት ፣ ዛሬ ና አሁን ፣ አገርን ለማዳን  የህይወት መሠዋትነት እየተከፈለ ነው ። ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የሚያመጣትን የአባይን የኃይል ማመንጫ ግድብ ለማጠናቀቅ ዜጎች ከመቼውም በላይ የሚጠበቅባቸውን እያደረጉ ነው  ። በተቃራኒው ደግሞ በመንግሥት ጉያ ውሥጥ የተደበቁ ሌቦችና  ደላሎች ፣ እንዲሁም  የጥቅም ተጋራዎቻቸው አሸሸ ገዳሚ  ነጋሪት ሲጎሰም ይሰማል ። ይህ ፀረ እድገት ፣ ፀረ ልማት የሆነ  ነጋሪት ጉሰማ “ በቃ ! “ ሊባል ይገባል ።  የአገር ብልፅግና እንቅፋት ነውና  !!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop